Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
የፍርሀት ስሜት ያስክረዋል ማለት ነው ቀ አርሱም ታላቅ ይሆናል» ቆ ወንድን ከማታውቅ ሴት ያለአባት ተወልዶ ታላቅ የሚሆነው እንዴት ነው። በእኛም ሕይወት የሚሆነው እንዲሁ ነው።
ምዕራፍ ድፍረት «መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ ሉቃ ኢሙት መልአኩ ማርያምን አትፍሪ ያላት እስከ አሁን እየሆነ ስላለው ብቻ ሳይሆን የፈቃዱ ምሥጢር በሕይወቷ ሲገለጥ ስለሆነ መፍራት እንደሌለባት ለማስገንዘብ ነው የእግዚአብሔር ሰላም ደስታ መገኘት በረከትና ሞገስ ሲመጣ ፍርሀትን አስወግዶ ድፍረትን ይተካል እነዚህን የእግዚአብሔር ስጦታዎች የተለማመደ ሰው ሁኔታዎችን አይፈራም የእግዚአብሔር መገኘ ት ከፍርሀት በላይ ያደርገዋል ሞገስ አግኝተሻልና አትፍሪ ነበር ያላት ሞገስ ሲመጣ የፍርሀትን ሰንሰለት ይበጣጥሳል በሞገስ የሚኖር ሰው ዓላማና ዕቅድ ስለሚኖረው የእምነትን ርምጃ መውሰድ አይፈራም የእግዚአብሔር ሞገስ ሲመጣ ሰው የእግዚአብሔርን ራአይ ማየትና ማለም ስለሚጀምር በነጻነት በአምላኩ ፈቃድ ውስጥ በመግባት ዓላማውን ለመፈጸም ወደ ኋላ አይልም ፍርሀት በሰው ሕይወት ውስጥ የሚከሠት የድንጋጤ ስሜት ነው ይህ ስሜት አአምሮን ሲቆጣጠር ሰው በትክክል ማሰብና መሥራት የሚገባውን ማድረግ ወይም መሆን የሚገባውን መሆን ያቅተዋል በአጠቃላይ አነጋገር ሦስት ዓይነት ፍርሀት አለ አንደኛው በተፈጥሮ እግዚአብሔር ለሰው የሚሰጠው ፍርሀት ነው ለምሳሌ አደጋን በመፍራት ዘወር ማለት ከጐዳት ይጠብቃልፁ እሳትን ፈርቶ መሸሸ ከመቃጠል ያድናል መንገድ ስናቋርጥ መኪና እንዳይገጨን የምናደርገው ጥንቃቄ አደጋ እንዳይደርስብን ይረዳናል አደጋን ለማስወገድ የሚያስችለን ትክክለኛው ፍርሀት ባይሰጠን መኖር አንችልም ነበር ይህ እግዚአብሔር አጥር በመሆን እንዲጠብቀን የተሰጠን የተፈጥሮ ፍርሀት ነው ጤነኛና በትክክል የሚያስብ ሰው ይህ ዓይነት ፍርፃት አለው ይህ ዓይነት ፍርፃት ከሌለ ሰው አደጋ ላይ ይወድቃል ለኅብረተሰቡም አደገኛ ይሆናል ይህ ዓይነት ተፈጥሮአዊ ፍርሀት በውስጡ የሌለ ሰው ሌላውንም ከመጐዳት ወደኋላ ስለማይል አደገኛ ነው ሁለተኛ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ይህ ትክክለኛ ከመሆኑም በላይ በጣም አስፈላጊ ነው ይህ እግዚአብሔርን ከማክበር የሚመነጭ ቅዱስ ፍርሀት ነው የእግዚአብሔር ቃል አጥብቆ የሚያዝዘን ከአክብሮት የተነሣ እግዚአብሔርን በመፍራት እንድንኖር ነው እግዚአብሔርን መፍራት እኛን ከኃጢአት አደጋ ከመጠበቁም በላይ የእግዚአብሔርን ክብር ዝቅ እንዳናደርግ ይረዳናል ፈሪሀ እግዚአብሔር ወደ እውነተኛ አምልኮ የሚያደርስ ጎዳና ነው በቅድስናና በትሕትና እየታዘዝን እንድንኖር የሚያስችለንም ይህ ቅዱስ ፍርሀት ነው በተጨማሪም አግዚአብሔርን የመፍራት ጥቅሞች በመንፈሳዊ ሕይወት በጣም ብዙ ናቸው ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል የጥበብና የዕውቀት ሁሉ መሠረት ነው ሰው በትክክለኛ ፅውቀትና ጥበብ ከተሞላ ከዚያ በላይ የከበረ ሀብት የለም «የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው» ምሳሌ እግዚአብሔርን መፍራት ማስተዋልን ይሰጣል በመንፈሳዊም ሆነ በተፈጥሮ አስተዋይ ሰው ይፈለጋል ለነገር ሁሉ ቁልፍ ነው ቁልፍ የተዘጋውን እንደሚከፍት ሁሉ ቅዱስ ፍርሀትም እንዲሁ ነው «የዘመንህም ጸጥታ የመድኃኒት ብዛት ጥበብና ዕውቀት ይሆናል እግዚአብሔርን መፍራት መዝገቡ ነው» ኢሳ እግዚአብሔርን መፍራት የእርሱን ዓይኖች ያባባሉ እርሱ በመልካምነትና በርኅራጌቴ የሚያየው የሚፈራውን ሰው ነው ወደሚፈራው ሰው እንደሚመለከት በቃሉ አረጋግጦልናል «ነገር ግን ወደዚህ ትሑት ወደ ሆነና መንፈሱ ወደ ተሰበረ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመሰከታለሁ» ኢሳ አኢመት ዱ የእግዚአብሔርን መልካምነት ያመጣል እግዚአብሔር ለሚፈሩት መልካም ነገር በማድረግ ደስ ይለዋል ኤር ብ እግዚአብሔርን መፍራት ሕይወትን ይሰጣል «አግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች» ምሳሌ ለትዳር በረከት መሠረት ነው ለባልና ሚስት በትዳር ውስጥ መባረክ ብቻ ሳይሆን ለልጆችም መባረክ መሠረት ነው «እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ በመንገዱም የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው ፌ ሚስትህ በቤትህ እንደሚያፈራ ወይን ናት ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ተክል ናቸው እነሆ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል» መዝ ። በሚሉት ጥያቄዎች ስለሚሞላ ጌታውን ማስደሰት ይሳነዋል እግዚአብሔርን ያለ እምነት ደስ ማሰኘት አይቻልምና ፍርሀት ያስራል አልፎም ሽባ ያደርጋል ሰው በጣም ሲፈራ ነገሮቹ ሁሉ ስለሚታሠሩ መውሰድ የሚገባውን ርምጃ መውሰድ ያቅተዋል መቀበል የሚገባውን መቀበል ይሳነዋል መናገር የሚገባውን መናገር ያዳግተዋል መሥራት የሚገባውን መሥራት ያስቸግረዋል ይህ መንፈሳዊ መታሰር ብቻ ሳይሆን ሽባነትንም ያስከትላል ለዚህ ነው እግዚአብሔር ሰዎችን ለፈቃዱ ሲፈልጋቸው በቃሉ ደጋግሞ «አትፍራ» የሚላቸው የፍርሀት ወጥመድ መወገድና መሰበር ያለበት ለዚህ ነው ካልሆነ ፈቃዱን ለመፈጸም ታላቅ ዕንቅፋት ይሆናል አግዚአብሔር ልጆቹን «አትፍሩ» ሲላቸው የኃይሉን ታላቅነት ብቻ ለመግለጽ ሳይሆን ፈቃዱን የሚከለክል እንደሌለ ለማረጋገጥ ነው ፍርሀታችን ከተወገደ የእርሱን አሳብና ፈቃድ ሊያቆም የሚችል አይኖርም ማርያምን አትፍሪ» ያላት የፈቃዱን ምሥጢር መግለጫ እንድትሆን ስለተመረጠች ነውር መፈለግንም ማድረግንም በልጆቹ የሚያደርግ እርሱ ስለሆነ የእርሱን ዓላማ መረዳት ጥያቄና ጥርጥር ከሚያስከትለው ፍርሀት ይጠብቃል ፍርሀት የመታዘዝ ጠንቅ ስለሆነ ቅጣት አለበት ፍርሀትን ማሸነፍ የነጻነትና የፍቅርን ሕይወት ያበለጽጋል በነጻነት ሕይወት መመላለስ ለአግዚአብሔር ሙሉ ፈቃድ ያዘጋጀናል ለእግዚአብሔር አሳብ የመኖርን ድፍረት ይሰጣልና ስለዚህ ነው ጳውሎስ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ» ፊልጵ በማለት ከፍርሀት ነፃ የሆነ ሕይወት እንዲኖረን የሚያደፋፍረን ፍርሀት ተስፋን ያጨልማል የተከፈተውን በር በመዝጋት ጊዜያችንን በከንቱ እንድናባክን ያደርጋል ሐዋርያት እንኳ ጌታ ኢየሱስ ለሦስት ዓመት ካሠለጠናቸውና ሥልጣንም ከስጣቸው በኋላ በትንሣኤ ቀን በፍርሀት በራቸውን ከዘተጉ በትንሣኤ ቀን ወጥተው ለሁሉም መነሣቱን ማወጅ ነበር የሚገባቸው ፍርሀት ግን እምነትን ስለሚሰርቅ በድፍረት በመውጣት እንደ ተስፋ ቃሉ ትንሣኤውን ማወጅ አልቻሉም በተሰጣቸው ዕድል ላይ በር ስለ ዘጉ ትንሣኤውን አይተው ለመመስከር በመውጣት ፈንታ በፍርሀት ተዋጡ እንግዲህ ፍርሀት ራእይን ያጠብባል በር ያዘጋል ለሌላ ከማሰብ ይበልጥ ለራስ በደኅንነት መኖርን ያስመርጣል ከዚህ የተነሣ ሕልምንና ራእይን ያደክማል በጊዜው የማይገታ ከሆነም ያጠፋል ፍርሀት በቃላችን እንዳንቆም ያደርገናል ሰው በፍርፃት ሲያዝ መናገር የማይገባውን ይናገራል ማሰብ የሌለበትን ያስባል እውነት ነው ብሎ የያዘውን መጠራጠር ይጀምራል በዚህ ምክንያት ታማኝነትን ስለሚያጠፋ ወዳጅንም ያስክዳል ቃላችንን እንድንለውጥ ያደርገናል ሐዋርያው ጴጥሮስ ጌታውን የካደው ለዚህ ነበር አላውቀውም ብሎ ሦስቴ የካደው ስለማያውቀው ወይም ስለ ጠላው ሳይሆን በፍርሀት ስለ ተሸነፈ ነበር የሚፈራ ሰው ዋጋ ከፍሎ መድረስ ወዳለበት መድረስ ወይም ጥሪውን ተጨባጭ ማድረግ አይችልም ስለዚህ ነው ፈሪ ብዙ ጊዜ የጀመረውን የማይጨርሰው ጌታ ወደ ፈቃዱ የጠራቸውንና ለትልቅ ነገር የተጠቀመባቸውን ሁሉ አትፍሩ ይላቸው የነበረው ከዚህ የተነሣ ነው ለማርያምም የመጣው መልእክት ይኸው ነበር ማርያም ለተገለጠው ፈቃዱ በመታዘዝ ይህን ታላቅ ተልእኮ ለመፈጸም የእምነት ርምጃ ከመውሰዷ በፊት ከፍርሀት ነፃ መሆን ነበረባት ለተገለጠው ፈቃዱ በመኖር ደስ የምናሰኘው በእውነትና በፍቅር በመታዘዝ ብቻ ነው ፍርሀት ካለ እውነትም ሆነ ፍቅር አይኖርም ፍርሀት ፍቅርን ስለሚያጠፋ መለኮታዊ ሥራ ለመሥራት ትልቅ ዕንቅፋት ነው ፍርሀት የእግዚአብሔርን ከእኛ ጋር መሆን ሙሉ በሙሉ እንዳንቀበለ ጥርጥር ውስጥ ስለሚከተን የፈቃዱ ምሥጢር በሕይወታችን እንዳይገለጥ ዕንቅፋት ይሆናል ለዚህ ነበር መልአኩ ለማርያም «በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ» ያላት የአግዚአብሔር ህልውና በድፍረት ይሞላል የእግዚአብሔርን ታላቅነት ስንረዳ ትልቅና የማይቻል መስሎ ያስፈራን ነገር ሁሉ ትንሽ ሆኖ በእውነተኛ መልኩ ስለሚታየን በድፍረት እንሞላለን ከዚህም የተነሣ «ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል። በዚህ ሰዓት በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል ቀ አጠቃላዩን ጊዜ ሳይደክሙና ሳይሰለቹ በትዕግሥትና በእምነት መጨረስ ይህ ወቅት የዝግጅት ጊዜ ስለ ሆነ በዕድሉ በመጠቀም መቀየር የሚገባውን መቀየር መታረስ የሚገባውን ማረስና ማለስለስ ቀ መዘራት የሚገባውን በሰዓቱና በወቅቱ መዝራት ቀ የበቀለውን ወይም ማደግ የጀመረውን የተስፋ ዘር ማረም መኮትኮት መጠበቅና በአጠቃላይ አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ ማድረግ ጥቂቶቹ ናቸው ከእርግዝናም አንጻር ብንመለከተው በመዘግየቱ ምክንያት እንደ ሣራ ባለማመን ተስፋ የመሩረጥን ሣቅ ብንሥቅና እንደ ማርያም አእንደ ቃልህ ይሁንልኝ» በማለት የእግዚአብሔርን አሳብና ፈቃድ ብንቀበል የእግዚአብሔር ነገር በውስጣችን እንደ እርግዝና ስፍራ ይዞ ማደግ ይጀምራል ተቀብለነው አሳቡ ከእኛ ጋር ሲዋሐድ ወደ ሙላት ያድጋል ማርያምን እነሆ ትፀንሻለሽ ሲላት የእግዚአብሔር ተስፋ የሚፈጸምበት ጊዜ ደርሷልና ከዚህ በኋላ መጠበቅ ሳይሆን መንከባከብ ይኖርብሻል ማለት ነበር ይህን ወቅት ልዩ የሚያደርገው የመጠበቅ ሰዓት አልፎ የመንከባከብ ጊዜ መድረሱን ማስገንዘቡ ነው «አግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሣራን አሰባት የገባውን ተስፋ ፈጸመላት ሣራ ፀነሰች ልክ እግዚአብሔር ባለው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት» ዘፍጥ የእግዚአብሔር ፈቃድ በሕይወታችን መገለጽ ከጀመረ ይህ በጣም ልዩ ጊዜ ስለሆነ የበቀለው እንዳይበላሽ የተረገዘውም እንዳይጨነግፍ በማስተዋል መመላለስ ያስፈልጋል አንዴ ከተረገዘ እስኪወለድ ድረስ ጊዜ ስለሚወስድ በትዕግሥት መጠበቁ በጣም አስፈላጊ ነው እህል በበቀለ ቀን አይታጨድም ልጅም በተረገዘ ቀን አይወለድም የእግዚአብሔር ፈቃድ ምሥጢር እየተገለጠ የሚሄደው በእርሱ ሰዓትና መንገድ ስለሆነ በማስተዋል መመላለስ በጣም ተገቢ ነው ሦስተኛውን የተወደደ ሰዓት ልንለው እንችላለን ይህ ጊዜ የተጀመረው የእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ሙላት የሚደርስበት ጊዜ ነው በሚቀጥለው ምዕራፍ ውስጥ በሚገባ ተብራርቷል እንግዲህ የእግዚአብሔር ቅዱስ ዘላለማዊ አሳብና ፈቃድ በውስጣችን እንደ ፅንስ ስፍራ አግኝቶ እንዲያድግ የሚከተሉትን ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል ቀ የእግዚአብሔርን አሳብና ፈቃድ ተቀብለን ለማስተናገድ ፈቃደኛ መሆን የመጀመሪያው እርምጃ ነው የአግዚአብሔር ፈቃድ በሕይወታችን ውስጥ የሚገለጸው በፈቃደኝነታችን መጠን ነው የእግዚአብሔርን ዘመንና ወቅት ለይቶ በማወቅ ጊዜውን መጠቀም ለዓላማው ያዘጋጀናል ቃሉ እንደሚለው ለሁሉም ጊዜ አለው የማረስ ጊዜ እንዳለ ሁሉ የመዝራትና ለበቀለው እንክብካቤ ማድረጊያ ወራትም አለ እንዲሁም ደግሞ የእርግዝናውን ወራት በተስፋው መሠረት የመጠበቅ ዓመታትም አሉ ተስፋውን የሰጠ የታመነ ነውና የእርግዝና ወራት ከጀመረ ግን ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል በሚል ጥያቄ ከመሞላት «ይልቁንም በእምነቱ በመጽናት ለአግዚአብሔር ክብርን ሰጠ እንጂ የእግዚአብሔርን ተስፋ አልተጠራጠረም እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ እንደሚፈጽም በሙሉ ልብ እርግጠኛ ነበር» ሮሜ ኢመት ተብሎ እንደ ተነገረለት እንደ አብርፃም ማመን ይገባል እግዚአብሔር በውስጣችን የጀመረውን ወደ ሙላቱ እስከሚያደርስ ድረስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረግን በምስጋናና በአምልኮ የመወለጃውን ወራት መጠበቅ የፈቃዱን ምሥጢር በጊዜው በሕይወታችን እንዲገለጥ ያደርገዋል ማርያም የፅንሱን አዋጅ በእምነት ተቀብላ በምስጋናና በአምልኮ መመላለስ ስለ ጀመረች የፈቃዱ ምሥጢር በሕይወቷ ውስጥ ተከሠተ በእኛም ሕይወት ውስጥ እንዲሁ መሆን አለበት ምዕራፍ መውለድ «ማፎርም ሯፎፀ ዕሪላዜለጩጨረራ ያጋድ ም»ነጎ ። » ብሎ የጠየቀው ጠቅላላ የሕይወቱን አቅጣጫ እንደ ፈቃዱ በመለወጥ ለተወሰነለት ጐዳይ ለመኖር ፈልጎ ነበር ቆይቶም ስለዚህ ሲመሰክር እግዚአብሔር ከማኅፀን ለዚህ እንደለየው ጽፎአል በበላ ዱ ይህ መሠረታዊ የሕይወት ጥያቄ ለምን ዓላማ በ ቸት ዬርኑጌ ዯ ዑ እንደ ተፈጠርን የፈቃዱን ምሥጢር ግልጽ ያደርገዋል አንዴ ለምን እንደ ተፈጠርንና እንደ ጠራን ከተረዳን የሚያስከፍለውን ዋጋ ከፍለን ለፈቃዱ ለመኖር ጭንቅ አይሆንብንም አንደ ጳውሎስ እንግዲህ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ ከሰማይ ለታየኝ ራእይ አልታዘዝ አላልሁም» የሐዋ ሥራ ኢሙት እንላለን የሚያስወግር የሚያስንቅና መከራንም የሚያመጣ ቢሆንም እንኳ እንደ ማርያም የሕይወት ጥሪ ነው ወይም ጌታ ለሕይወቴ ያለው ፈቃዱ ነው ብለን በእምነትና በእርሱ በመደገፍ እንቀበላለን ለዚህ ደግሞ መልእክቱ ከየትና በማን በኩል እንዴ መጣ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው ለማርያም የተላከው መልእክት ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ በመግሰጽ ነው ምዕራፉ ወደ ዝርዝር ውስጥ የገባው «ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ» ሉቃ የሚለው ሐረግ በጣም አስፈላጊ ነው የሕይወትን አቅጣጫ የሚያስለውጠው ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣው ፈቃዱ ብቻ መሆን አለበት መልእክት መቀበል የምንወደውን ያህል የመልእክቱ ምንጭ እግዚአብሔር መሆኑን ማረጋገጥና መፈተን መጠራጠር ወይም እግዚአብሔርን አለማመን አይደለም ርግጠኛ መሆን ግን በጣም አስፈላጊ ነው ቃሉም «የመንፈስን እሳት አታዳፍኑ ትንቢትን አትናቁ ሁሉን ነገር ፈትኑ መልካም የሆነውን ያዙ ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ» ዐኛ ተሲሴ ኢመት ይላልና የመንፈስን እሳት ማጥፋት ከእግዚአብሔር የተላኩትን ነቢያትና መልእክታቸው ከአርሱ መሆኑን እያወቅን ያለመቀበል ነው እውነተኛ የሆነውን ፈትኖ አውቆ በመታዘዝ ፈቃዱን መፈጸም ግን የመንፈስን እላት ማጥፋት ሳይሆን አስተዋይ መሆን ነው ለፍሬያማ ሕይወትና አገልግሎት የሚያበቃንን እውነት የሆነውን ፈትነን በማወቅ በዚያ መሠረት መኖር ነው «ፍቅራችሁ በጥልቅ እውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ እጸልያለሁ ይኸውም ከሁሉ የሚሻለውን ለይታችሁ እንድታውቁ እስከ ክርስቶስም ቀን ድረስ ንጽሓንና ነቀፋ የሌለባችሁ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሚገኘ ው የጽድቅ ፍሬ እንድትሞሉ ነው» ፊልጵ ኢመት ተብሎ ተጽፎአልና ሌላው ደግሞ መልእክቱ ብቻ ሳይሆን መልእክቱን ይዞ የመጣውን ሰው ማንነት ማወቅ አስፈላጊ ነው ፈቃዱን ታደርግ ዘንድ ወደ ማርያም የመጣው የእግዚአብሔር መልአክ ቢሆንም የመጣው ከእግዚአብሔር የተላከ መልእክተኛ ነበር እውነት ነው እግዚአብሔር በማንም መጠቀም ይችላል ፈቃዱ ግን በእርሱ መልእክት ላይ ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ በሚቀርቡት ባሪያዎቹ መጠቀም ነው ስለዚህ እግዚአብሔር በአህያም ሆነ በሁኔታ ከተጠቀመ የሕይወትን አቅጣጫ ሳይለውጡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚላከውን መልአክተኛ በጸሎትና በተዘጋጀ ልብ መጠበቅ ጥርጥር ወይም ጊዜ ማባከን አይደለም እግዚአብሔር ከእርሱ የሆነውን ያጸናል የእርሱ ያልሆነውን ግን የትም አያደርስም ብዙ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያልተላከውን መልእክት እየተናገሩ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት የጠበቀ ስላልሆነ ሥጋዊ ነገርን የሚደባልቁበት መልእክተኞች መኖራቸውንም መገንዘብ መልካም ነው እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች ስጦታ አላቸው ነገር ግን የሕይወት ፍሬ ወይም ባሕርይ ይጐድላቸዋል ከዚህ የተነሣ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ «ሰው ሁሉ ማደግህን ያይ ዘንድ በእነዚህ ነገሮች ላይ አትኩር በትጋትም ፈጽማቸው ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ በእነዚህም ጽና ይህን ብታደርግ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና» ያለው በኛ ጢሞ ኢሙት እድገታቸው በሁሉም አቅጣጫ ያልተገለጸ መልእክተኞች ሰውን ወደ ደኅንነት በማምጣት ፈንታ ሊያስቱ ይችላሉ የዚህ አሳብ ዓላማ በዚህ በመጨረሻው ዘመን መልእክትን ከራሳቸው አሳብ ጋር የሚያደባልቁና እንደ ፈሪሳውያን ለራሳቸው ልማድ ሲሉ የእግዚአብሔርን ነገር የሚያጣምሙ ስለሚበዙ የምንሰማውን መልእክት ከመቀበላችን በፊት እንድንፈትሽ ለማስጠንቀቅ ነው በተጨማሪም የተመረጡትን እንኳ ሊያስቱ የሚችሉ ሐሰተኞች ሐዋርያት ነቢያት አስተማሪዎች ወዘተ መነሣት የመጨረሻ ዘመን ምልክት ስለሆነ በማስተዋልና በመለየት ጸጋ መመላለስ ከስሕተት ይጠብቃል ማቴ ማር ሉቃ አንብብ በዚህ ውስጥ ለማርያም ግልጽ የሆነላት ሌላው ጉዳይ መውለዷ ብቻ ሳይሆን የምትወልደው ወንድ ልጅ እንደሆነ ነበር እነሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። ታ ሆይ የሚወለደውን ልጅ እንዴት አድርገን ማሳደግ እንዳለብን እንዲያስተምረን ያ ወደ እኛ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና እንዲመጣ ታደርግ ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ» መሳ እግዚአብሔርም ጸሉቱን በመመለስ ሙሉ ፈቃዱን ገለጸላቸው እግዚአብሔር ፈቃዱን ለሕይወታችን ሲገልጽ የሚያየን በሕይወታችን የሚከናወነው በእርሱ ፈቃድ ውስጥ አስቀድሞ እንዳለ ነው መልአኩ ለማርያም ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ያላት አስቀድሞ በትንቢት የተነገረውን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተጻፈውን ነበር ማርያም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለሕይወቷ የተቀበለችው ልጅ ለመውለድ ነበር በፈቃዱ ምሥጢር ውስጥ ልጅ ከወለድሁ ይበቃል የሚባል ነገር የለም እግዚአብሔር በሕይወታችን የሚያደርገው ነገር መልክና ሥርዓት ስላለው ግልጽ ነው እግዚአብሔር ጾታው ያልታወቀ ነገር አያደርግም በመንፈሳዊ አነጋገርም ቢሆን የእግዚአብሔር ጥሪና ፈቃድ የሚታወቅ ነው እግዚአብሔር ነህ ያለውን ተቀብሎ መኖር ለእርሱ ክብር ለግለሰቡም ርካታን ያመጣል ጌታ ነጋዴ ነህ ካለ ነቢይ ካልሆንሁ ብሎ ከመታገል በሰጠህ ቦታ ስጦታና ንብረት እንዴት እንደምታገለግል ጠይቀው ወንጌላዊ ከሆንክ ለምን መጋቢ ወይም ነቢይ አልሆንሁም ብለህ ፈቃዱ ባልሆነ ሕይወት ውስጥ አትመላለስ እንግዲህ እግዚአብሔር በቃሉ እንደ ተጻፈው የሚናገረውን ለይቶ የሚናገር አምላክ ነው ያን መለየት ብቻ ሳይሆን መቀበሉም ለሕይወት ዕረፍት ነው ለማርያም ምን። ለሚለው ጥያቄ «ወንድ ልጅ» የሚል መልስ ተሰጣት አርሷም ተቀበለችው የተላከው መልአክ የምትወልደውን ልጅ በምን ስም መጥራት እንደሚገባት ሲያበሥራት «ስሙንም ኢየሱስ ትዋለሽ» ብሎ ነገራት የፈቃዱ ምሥጢር ሲገለጥ ሁሉም ነገር በብርፃን ውስጥ እንዳለ ስለሚሆን ድብዝብዝ የሚል አይኖርም ለማርያም የተነገራት ወንድ ልጅ እንደምትወልድ ብቻ ሳይሆን ምን ብላ መጥራት እንዳለባትም ጭምር ነው በማርያም በኩል የሚወሰደውን ልጁን አግዚአብሔር የሚያውቀው «ኢየሱስ» በሚል ስም ስለሆነ ሌላ ስም ልትሰጠው አትችልም በእርሷ በኩል ይወለድ እንጂ የሚፀነሰው በመንፈስ ቅዱስ ነው ከተወለደም በኋላ የእግዚአብሔር ልጅ እንጂ የማርያም ልጅ ተብሎ አይጠራም «የልዑልም ልጅ ይባላል» ተብሎ ተጽፏልና ከእግዚአብሔር ፈቃድ አንጻር ይህ በጣም አስፈላጊ ነጥብ ነው ከአግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በእኛ ውስጥ የሚወለደውን በራሳችን ስም ልንጠራው አንችልም በራሳችን መጥራት ከጀመርን ፈቃዱን የምናደርግ አይደለንም የዚህ መጽሐፍ ርእስ «የፈቃዱ ምሥጢር» የተባለው ለዚህ ነው እግዚአብሔር ፈቃዱን በሰው በኩል ይገልጣል ውጤቱ ግን የሰው ሳይሆን የእርሱ ነው ክብሩም የሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ነው መፈለግንም ማድረግንም በሰው ውስጥ የሚሠራው እርሱ ነውና በሁሉም ነገር ውስጥ ፈቃዱን የሚያደርጉ ባሪያዎቹ በምስጋናና በአምልኮ ሆነው «ሁሉም ከእርሱ በእርሱ ለአርሱ ነውና ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን አሜን» ሮሜ ኢመት ማለትን ማቋረጥ የሌለባቸው ይህ ስለሆነ ነው ይህ ከሆነ በሕይወታችን የሚገለጸው የእግዚአብሔር ፈቃድ በትክክለኛ ጾታና ስም ከመጠራትም በላይ የማን እንደሆነ ተረድተን በሚገባ ማስተናገድ በጣም አስፈላጊ ነው መቼ። ከእግዚአብሔር የተላከው መልአክ ለማርያም ግልጽ ያደረገላት እግዚአብሔር ለሕይወቷ ያለውን ዓላማ ብቻ ሳይሆን ዘመኑንም ጭምር ነበር መቼ የሚለው ጥያቄ ለማርያም በማያጠራጥር ሁኔታ ተመለሰላት እግዚአብሔር ፈቃዱን በሕይወታችን ውስጥ የሚገልጸው ወቅቱን ጠብቆ ነው አለጊዜው የሚሆን ነገር የለም የእግዚአብሔር የዛሬ ፈቃዱ ለሁሉም ክርስቲያን አንድ ዓይነት ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው» ኛ ተሲ ፋ ኢመት በቅድስና መመላለስ እግዚአብሔር በሕይወታችን ሊገለጽ ለሚወደው የፈቃዱ ምሥጢር ዝግጁ ያደርገናል ቀደም ሲል እንዳየነው የማረስ ጊዜ በአጠቃላይ የመጠበቅ እንደ መዝራቱ ወቅት የእምነት ርምጃ የምንወስድበትም ልዩ ጊዜ አለ ሦስተኛውና መብራራት ያለበት የተወደደ ሰዓት ያልነው ይህ ነው የተወደደ ሰዓት ከመጠበቅና ከእርግዝና አልፎ ልጅ የሚወለድበት ወይም የእግዚአብሔር ሙሉ ፈቃድ በፍሬ ተጨባጭ በሆነው ሁኔታ የሚገለጽበት ወቅት ነው ቃሉ «በትክክለኛው ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ኛ ቆሮ ይ ኢመት ይላልና ለማርያም «ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ» የሚለው የተወደደ ሰዓት መድረሱን ነበር ያበሠረላት መቼ ቢባል በዚህ ወቅት ከዘጠኝ ወር በኋላ ዝግጅቱ በኤልሳቤጥ ሕይወት ከተጀመረ ወር ሆኖአል ይህ የተወደደ ጊዜ ልጅ የሚወለድበት ወይም የእግዚአብሔር ተስፋ የሚፈጸምበት ወቅት ስለሆነ ከመጠበቁም ከእርግዝናው ወራትም ይበልጥ ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ሰዓት ነው የሕክምና ዕድል በማይገኝበት ጊዜ ብዙ እናቶች ከልጆቻቸው ጋር የሚሞቱት በወሊድ ችግር ምክንያት ነው ሲወለድ ጥንቃቄ ያልተደረገለት ሕፃን የመሞት ካልሞተም አካለ ስንኩል የመሆን ፅድሉ ከፍተኛ ነው ለዚህ ነው በዚህን ጊዜ ታላቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ከእግዚአብሔር ፈቃድ አንጻር ቢታይም እንዲሁ ነው በዚህ ምክንያት ቃሉ «አንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዝመኑን በሚገባ ዋጁ ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ» ይለናል ኤፌ ዱ ኢሙት ይህ ጊዜ የእግዚአብሔር ፈቃድ በሕይወታችን የሚገለጥበት ሰዓት ስለሆነ የፈቃዱ ምሥጢር እንዲገለጥ በጥንቃቄ በማስተዋል የተረገዘው እንዲወለድ መጠባበቅ አስፈላጊ ነው መልአኩ ለማርያም «ትወልጃለሽ» ሲላት ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሔርም የተወደደ ሰዓት መሆኑን ነበር የገለጸላት ያንን ሰዓት አውቀን በንቃት መጠበቅ ዘላለማዊ ዕቅዱ በሕይወታችን እንዲከናወን ያስችለናል የጌታን ልብ ከሚያሳዝኑት ነገሮች መካከል የእግዚአብሔርን ዘመንና ሰዓት ያለ ማወቅ ወይም ያለማስተዋል አንደኛው ነው በምድራዊ የአገልግሎት ጊዜው ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ያለቀሰው ሁለት ጊዜ ነበር ሁለቱም የተወደደውን ሰዓት ሰዎች ካለማወቃቸው ጋር የተያያዙ ናቸው በመጀመሪያ ያለቀሰው ስለ ኢየሩሳሌም ሲሆን ይኸውም «ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረብ ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት እንዲህም አለ ሰላምሽ የሚሆነውን ምነው አንቺ ዛሬ በተረዳሽ ኖሮ።