Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
የፖኾ የበላይነት በተለይ በይፋ የተሰበከው በሮሙ ፖፕ በሣልሳዊ ኢኖሴንት የተዘጋጀው አራተኛው የመስቀል ጦርነት ዓላማውን የሳተ የዝርፊያና የጥፋት ጦርነት ነበር ። የመስቀል ጦረኞችን ያዘምቱ ከነበሩት መሪዎች የጥቂቶቹን አስተሳ ሰብ ከንቱነት የሚገልጸው ቀደም ሲል እንደተመለከትነው ከፖፕ ጎርጎርዮስ ሰባተኛ እስከ ፖፕ ቦኔፌስ ስምንተኛ በ ድረስ የሮም ፖፖች በአብያተ ክርስቲያናትና በነገሥታት ዘንድ ተሰሚነትንና የበላይ ነትን አትርፈው ነበር ። ለምሳሌ የእንግሊዝ ንጉሥ ቀዳማዊ ኤድዋርድ ከካህናትና ከቤተ ክርስቲያን ሀብት ከፍተኛ ታክስ ግብር እንዳይሰበስብ ፖኙ ከልክሎት ነበር ። በጣም የከፋው ጠብ ግጭት የተካሄደው ግን የመ መ በፖኙቹና ከፍተኛ የብሔርተኝነትና የሥልጣን ጥም ባደረበት በፈረንሳይ ንጉሥ በፊልጾስ አራተኛ መካከል ነበር ። ረ ፖፖች ከሮም ውጭ አቪኞን ውስጥ ለሰባ ዓመታት ያህል የተቀመጡበት ጊዜ ። ፊልኦስ አራተኛ የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን ሲጋፋና ሀብቷን ሲመዘብር ፖፕ ቀሌምንጦስ አምስተኛ ድርጊቱ ሕገ ወጥ መንገድ ፖፕ አድርገው በመሾማቸው እላይ የተመለከትነው በ ዓም ኢጣልያ በምትገኘው ፌራራ ውስጥ ቀጥሎ ሳለ በካቶሊክና በግሪክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮች ተወካዮች በጉባኤው ላይ ተገኝተው ነበር ። ለጊዜው በአንዳንድ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ገፋፊነት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መለያየትም እስከ ዛሬ ድረስ እንደቀጠለ ነው ።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጴጥሮስ የሮም ቤተ ክርስቲያን መሥራችና የመጀመሪያው ጳጳስ ፖፕ መሆኑን ታስተምራ ለች ። በ ዓም በተደረገችው የኬልቄዶን ጉባኤ ውሳኔ መሠረት የልዮንን ትምህርት የሚከተሉ የካቶሊክና የግሪክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት አሉት ሲሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት መሪና አባት ቅዱስ ዲዮስቆ ሮስ ለኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ባሕርይ አለው በማለቱ አንድ የነበረችቱ ቤተ ክርስቲያን ተወጋግዛ ሁለት ላይ ተከፈለች ። እንዲሁም በኬልቄዶን ጉባኤ በኛው አንቀጽ የመናገሻ ከተማዋ የቀስጥንጥንያ ፓትርያርክና የሮሙ ፖፕ በክብር እኩል ናቸው የሚለውን ድንጋጌ የግሪክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ተቀብለው በተግባር ላይ ሲያውሉት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አልተቀበለችውም ። በተጨማሪም የሮሙ ፖፕ በግሪክ ቤተ ክርስቲያን ላይ የበላይነትን መንፈስ ስላሳየ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንደዚሀ ያለው መንፈስ ሕገ ወጥ ነው ስትል በጥብቅ ተቃውማለች ። ለ ከስምንተኛው መቶ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ እስከ ዐሥራ አንደኛው መቶ ዘመን ድረስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች አስተምረው ከጣዖት አምላኪነት ወደ ክርስትና ከመለሱአቸው ነገሥታት ጋር በመተባበር እንደ ሠሩ ዩፍራንኮችና የፖፖች ተባብሮ መሥራት ። ይህ የፔፒን ስጦታ የካቶሊክን ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ፖፖች ለተከታዮቹ አንድ ሺህ ዓመታት ያህል በሮም ከተማና በመካከለኛው ኢጣልያ ክፍለ ግዛት ላይ የምድራዊ የዓለማዊ ገዥነት መብትን አጐናጽፎ ነጻ መንግሥት እንዲያስተዳድሩ አደረጋቸው ። ፖፔኙ ግን ሃይማኖት ነክ የሆኑ ጉዳዮችን ሁሉ መወሰን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ተግባር መሆኑንና በሁለተኛዋ የኒቅያ ጉባኤ የተወሰነውም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተስማማችበትና ቀድሞም በቤተ ክርስቲያን ሲፈጸም የነበረ ቀጥተኛ እምነት መሆኑን ገልጾ የፍራንክፈርትን ውሳኔ ውድቅ አደረገው ። እንዲሁም ከቻርልስ ዕረፍት በኋላ ፖፖች በነገሥታቱ ላይ የነበራቸው ቤተ ክርስቲያን በቤተ መንግሥት ላይ የነበራት የበላይነት እየተጠናከረ ሄደ ። ሆኖም አንዳንድ ችግሮች ቢከሰቱም ቅሉ ከ በነበሩት ዓመታት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሚስዮናውያንን ወደ ኖርዌ አይስላንድ ግሪንላንድ ቦሔምያ ሀንጋሪ ፖላንድ ወዘተ በመላክ የክርስትናን ትምህርት አስፋፍታለች » ብ ሐ ከ ዓም በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተደረገው ተሐድሶ ለውጥ መሻሻል ከላይ በተጠቀሱት ዓመታት በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተደረገው መሻሻል ተሐድሶ በሚገባ የተካሄደው ፀፖፕ ጎርጎርዮስ ሰባተኛ በሒልዴብራንድ ቢሆንም ቅሉ የተሐድሶው ተግባር የተጀመ ረው ቀደም ሲል በፖፕ ልዮን ዛጠንኛ ነበር። መ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች አነሳሽነት የተካሄ ደው የመስቀል ጦርነት ዳግማዊ ኡርባን የተባለው በ ዓም ፖፕ ሆኖ ሲመረጥ ጎርጎርዮስ የጀመረውን የተሐድሶ ፈር የሚከተልና የፖኙን የበላይነት የሚያጠናክር መሆኑን ገለጸ ። እንዲሁም ይኸው የፈረንሳዩ ተወላጅ ዳግማዊ ኡርባን የተባለው ፖፕ በ ዓም ፈረንሳይ ውስጥ በምትገኝ ክሌርሞንት በተባለች ቦታ በራሱ ሊቀ መንበርነት በተካሄደው ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ወደ ቅድስት ሀገር ለስግደት የሚሄዱ ምእመናን ፍልስጥኤምን ይገዙ በነበሩ ቱርኮች ከሚደርስባቸው ዝርፊያ መጉላላት ግድያ ወዘተ ኢየሩሳሌምን ነጻ በማውጣት ለማዳን የሮሙን ፖፕ ዝና ከፍ ያደረገውን የመጀመሪያውን ከምዕራብ አውሮጳ ሀሇች በተለይ ከፈረንሳይ ከሎሬንና ከደቡብ ኢጣልያ የተውጣጣውን የመስቀል ጦረኛ ሠራዊት አዘመተ ። እላይ እንደተመለከትነው ክርስቲያኑ የኢየሩሳሌም መንግሥት በዙርዱ ተወላጅ በሳላዲን በሚመራው ጦር ድል ከመመታቱ በፊት የቱርክ ጦር አንዳንድ እንደ ኤዴሳ ሲዶን ናዝሬት ወዘተ ያሉ የቅድስት ሀገር ክፍለ ሀገሮችን መያዙ አውሮጳ ውስጥ ስለተሰማ ሣልሳዊ ኤውጌንዮስ የተባለው ፖፕና ቤርናርድ የተባለው ካህን የአውሮጳ ነገሥታትና ሕዝብ ቅድስት ሀገርን ከጥፋት እንዲያድኗት ስለሰበኩና ስለተማጸኑ በፈረንሳይ ንጉሥ በሉዊስ ሰባተኛና በጀርመኑ የተቀደሰው የሮማ ኤምፓየር ንጉሠ ነገሥት በሣልሳዊኮንራድ የተመራው ሁለተኛው የመስቀል ጦር በ ዓም ዘምቶ በመንገዱ የገጠመውን የጠላት ጦር ድል እየነሣ ኢየሩሳሌም ከተማ ደረሰ ። ወዲያውም በተከታታይ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አርባ ዓመት ያህል የፈጀው መለያየት ቀደም ሲል እንደተመለከትነው ከ ዓም ጀምሮ በፈረንሳይ መንግሥት ጥያቄ ትእዛዝ የፈረንሳዩ ተወላጅ ፖፕ ቀሌምንጦስ አምስተኛ ለፖፕነት የሚያስፈልገው የምርጫና የጸሎተ ሚመቱ ሥነ ሥርዓት ሊዮን ውስጥ ከተፈጸመለት በኋላ ሮም ሄዶ በመቀመጥ ፈንታ በፈረንሳይ ንጉሥ ተጽእኖ በ ዓም በደቡብ ። የፖኙን የበላይነት ሥልጣን ክደው ተቃውመው ከመላ አብያተ ክርስቲያናት የተወከሉ ካህናትና ምእመናን ለሚካፈሉበት ጠቅላላ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ተገዥ መሆን አለበት ። ሆኖም ዮሐንስ ሸሽቶ ከተቀመጠበት ቦታ ሆኖ ጉባኤውን ለመበተን በማሰብ አጉል ፕሮፖጋንዳውን ስለቀጠለ የጉባኤው አባላት የአጠቃላዩ ጉባኤ ሥልጣን ከፖፕ በላይ መሆኑን በመግለጽ ለፖፕ ዮሐንስ ይህ አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በሕጋዊ መንገድ የተጀመረ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመወከል በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የሚሠራ ሥልጣንም የተቀበለው በቀጥታ ሽእግዚአብሔር ስለሆነ ማንኛውም ክርስቲያን ፖም ጭምር ይህ ጉባኤ መከፋፈልን አስወግዶ አንድነትንና እምነትን ለማጽናት ለሚያወጣው ሬጄ ጨ እምነት ነክ ውሳኔ ሁሉ ታዛዥ መሆን ይገባዋል በማለት መልስ ሰጡት ። በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ለውጦችን መሻሻሎችን ለማድረግ ታቅዶ በፖፕ ኤውጌኒዮስ አራተኛ በ በ ዓም ከኢጣልያ ውጭ በተከፈተው በባሴል አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ላይ ከተካፈሉት አባቶች መካከል አብዛኞቹ ከፖ የጉባኤው ሥልጣን ስለሚበልጥ ጉባኤውን እኛ እንመራለን በማለት ተነሠ ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የፖኾ ሥልጣን ከአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በለይ መሆኑ ተረጋገጠ ። እላይ የተመለከትነው በ ዓም በኤውጌንዮስ አራተኛ ባሴል ውስጥ የተጀመረው አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በተከታታይ እንደገና በ ዓም ኢጣልያ በምትገኘው ፌራራ ውስጥ ቀጥሎ ሳለ በካቶሊክና በግሪክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንድነት ለመፍጠርና ከቱርክ መንግሥት አደጋ መከላከያ የሚሆን የጦር እርዳታ ለመጠየቅ የቀስጥንጥንያው የቢዛንታይን ንጉሥ ዮሐንስ ፓሌዎሎጐስ አምስተኛ ፓትርያርኩ ዳግማዊ ዮሴፍ ሌሎችም የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮች ተወካዮች በጉባኤው ላይ ተገኝተው ነበር ። ለጊዜው በአንዳንድ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ገፋፊነት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንድነት ተመሥርቶ ነበር ።