Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
የጓደኛዬ ማስታወሻ ልቦለድ በአቡሽ ታሪካየሁ ዓም ይሄን መጽሐፍ ከጸሀፊዉ ፍቃድ ዉጪ ማባዛትና ለተለያዩ አላማዎች መጠቀም በህግ የተከለከለ ነዉፎ አስተያየት ካላችሁ ጓሃርከቪመጀበበኋርዐበገ ስለ መጽሐፉ ይህ መጽሐፍ በማስታወሻ መልክ የቀረበ ልብወለድ ነዉ መልካም ንባብ አቡሽ ታሪካየሁ መግቢያ ብዙ ሰዎች ጣና ላይ መዝናናት የሚመርጡት ጸሀይ ልትጠልቅ አካባቢ ሲሆን የጸሃይ ግባቷን ለማየት ነፋሻማ አየሯን ለመቀበል በጣም ምቹ ሰአት በመሆኑ ነዉ እኔ አብዛኛዉን ጊዜ በአራት እና አምስት ሰአት አካባቢ መሄድ ያስደስተኛል በዝያ ሰአት ያለዉ የጣና ዝምታና ቅዝቃዜዉ በሰዉነቴ ዉስጥ የሚረጨዉ ልዩ ስሜት አለ ጣና በዉስጡ ምንም እንዳልያዘ መስታወት መስሎ የሰማይን ምስልን ያስተጋባል ልዩ የሆነ ዉበት።
በአራት ሰአት አካባቢ በአለተ እሁድ ለሰኞ ፈተና ዝግጅት ነበር ሀንድ አዉት ይዝ ከዶርም የወጣዉት ፖሊ ጊቢን ትቼ እንደወጣዉ መንገዱን ተሻግሬ የጣናን ሀይቅ ዳር በቀኝ በኩል ይፔ መጓዝ ጀመርኩ የጀበና ቡና የሚያፈሉ የሚመጣዉን እንግዳ ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ነዉ ጀልባዎችም አፋቸዉን ከፍተዉ ቱሪስቶችን ይጠባበቃሉ ጣና ሆቴል ጀርባም አስር የሚሆኑ ቱሪስቶች ተሰባስበዉ እያወሩ ካጠገባቸዉ አለፍኩ ከባህሩ መሀል ሁለት አስጋሪዎች በደንገል ታንከዋ ወዲያ ወዲህ እያሉ ዉሃዉን እያሳበሩ ይቀዝፋሉ መንገዱን አንደጨረስኩ ወደ ዉስጥ ገባ አልኩና ዲንጋይ ፈልጌ ዳር ላይ ተቀመጥኩ አስር ደቂቃ ከተመሰጥኩ በኃላ ወደችከላዬ ገባዉ ለግማሽ ሰአት ያከል እያገላበጥኩ እንደቆየሁ ቀና ሰል አንዲት ደንገል ታንኳ ቀስ በቀስ ወደኔ እየቀረበች መጣች የተቀመጥኩበት ቦታ ብዙ ጊዜ መረብ የሚጣልበት አካባቢ ስላልነበረ ቀጥታ መምጣቱ ትንሽ ግራ አጋባኝ አንድ መስመር አንብቤ ቀና ስል አሁንም እየተጠጋ ነዉ አይኔን ሀንዳዉቱ ላይ ተከዬ በጎሪጥ መከታተለል ጀምርኩ በአርግጥ የቀዛፊዉ ትኩረት ወደሌላ አቅጣጫ ስለነበር ትንሽ ተረጋጋዉና ሀንዳዉቱን አስቀምጩ ጣና ጣናን ማየት ገባዉ ቀጥ ብሎ መጣና ያለሁበት ቦታ ላይ አቆመ በጣም ደነገጥኩ ነገር ግን ምንም እንዳልሆንኩ ለማስመሰል ሌላ አካባቢ ማየትና ማማተር ጀመርኩ ወረደና የያዘዉን የተደጎሰ መጽሀፍ ነገር ፊት ለፊቴ አስቀምጦ በሌላ አቅጣጫ ተመልሶ ሄደ አዉነት ለመናገር በጣም ፈርቻለሁ ምንም ሳይናገር ደግሞ የማላዉቀዉ ሰዉ ብዙ ጥያቄዎች መጡብኝ ትቼዉ ለመሄድም እያሰብኩ ነበር ከደቂቃዎች በኺላ የልባዱ ግርጌ ላይ የተጻፉ ቁጥሮችን አየሁና ትንሽ ወደራሴ ተመለስኩ ቁጥሩን ከአንድ ሰዉ ጋር ብቻ ነዉ የምግባባበት የቁጥሩም ትርጉሙም ተሾመ ምትኩ ነዉ ማለት ነዉ እንዴት ኣልኩ መጽሃፉን አነሳዉና ደግሜ አየሁት የእጅ ጽሁፉም በጣም ተመሳሳይ ነዉ ቁጥሩም ተደግሞ ከዉስጥ ገጽ ላይ ተጽፏል በቃ ከአሱ እንደሆነ ገባኝ ሁለተኛ አመት የሜካኒካል ምህንደስና ተማሪ እያለን ነበር የጠፋዉ ከሱ ጋር ብቻ ነበር በዚህ ቁጥር የምንጻጻፈዉ በጣም ገረመኝ አላመንኩም መጽሀፉን ይዢ ወደ ዶርሜ ገባሁ ከተሼ ጋር አንደኛ አመት ሁለተኛ ሴሚስተር ነበር የተዋወቅነዉ የትምህርት ከፍላችንን ከመረጥን በኺላ ብዙ ጊዜ አብረን እናሳልፍ ነበር በነጻነትም ብዙ ነገር አብረን እንጨዋወታለን እሱ ለትምህርት ብዙ ትኩረት ባይሰጥም በጣም ጎበዝ ነበር አብዛኛዉን ግዜ ወደፊት የምንማራቸዉን የትምህርት መጽሐፍቶች እየተዋሰ ያነብ ነበር ያኔ ከኢትዮጵያ ስድስት ቋንቋዎችን ግእዝን ጨምሮ ከዉጪ ደግሞ አምስት ቋንቋዎችን ይችላል እንደዚህም ሆኖ ሌሎች የቋንቋ መጽሃፈቶችን ለማጥናት ይገዛል ከአስራ አንድ ሰአት በኃላ ያለዉን ሰዓት ወደ ቤተከርስትያን እንሄዳለን በተለይ የቅኔ ምሽት ፕሮግራም ካለ የትም ቢሆን አይቀርም ይዞኝ ይሄዳል ያዉ እኔ ብዙም ግእዝ ባልችልም ቅኔ ሲያቀርቡ በስሜታቸዉ እደመም ነበር ሁለተኛ አመት የመጀመርያው ሴሚስተር እንደተጠናቀቀ ቤተሰብ ጋር እንደሚሄድ ነግሮን ተሰናበተን የሚኖርበት ቦታ ስልከ ስለሚያስቸግር አንገናኝም እረፍት አልቆ ትምህርት ጀምረን ብንጠበቀዉ ብንጠበቀዉ አልመጣም ቢያቅተን ቤተሰቦቹ ጋር በቶሎ እንዲመጣ ደብዳቤ ጽፈን በመልእከተኛ ላከን ቤተሰቡ በድንጋጤ ወደ ጊቢዉ መጡ ለእረፍት እንኳን እንዳልመጣ ነበር የነገሩን ታድያ የት ሄዶ ይሆን ፖሊስም መጥቶ ጠየቀን ቤተሰቡም ከጎን ያፋጥጡናል እኛ በእዉነት ምንም የምናወቀዉ ነገር አልነበረም የሚገርመዉ እናትየዉ ገላችሁትም ከሆነ እሬሳዉን ስጡኝ ትል ነበርምን ብለን አንገለዋለን ያኔ ሰዉ መቅረብ እራሱ በጣም ነበር ያስጠላኝ እሱን ማጣታችን ሳያንስ ሌላ ወቀሳ ቤተሰብ አጽናንተን የልጁን ፎቶ በየጊቢዉ ማስታወቅያ ቦርድ ለጥፈን ከተማ ውስጥ አንድ ፖል ሳይቀረን ሁሉም የትምህርት ከክፍላችን ተማሪዎች ወጥተን ስንለጣጥፍ ነበር እንዲሁ ስንባከን በጥርጣሬ ጊቢ ዉስጥ ስንታይ እኛ ይመጣል እያልን ስንጠብቀዉ የዉሃ ሽታ ሆኖ ቀረ አሁን ከሁለት አመት በኃላ መሆኑ ነዉ ከሱ ደብዳቤ የተቀበልኩት የህይወቱን ጉዞ ከኛ ከተለየ በኺላ ያሰፈረበት የማስታወሻ ደብተሩ ነዉ ወደ ማስታወሻዉ ሚያዝያ እዚህ ከመጣሁ ይኸዉ አንድ ወር ሆነኝ ለመጻፍም ብዙም ጊዜ አላገኘሁም ነበር የአያንዳንዷን ቀን ሁኔታ ብከትብልህ ደስ ይለኝ ነበር ይሄን ጽሁፍ ስጽፍ ከፊቴ እንዳለህ እያወራዉህ አንደሆነ አያሰብኩ ነዉ ደግሞም በሕይወት እንዳለሁ ስታዉቅ መደንገጥህ አይቀርም በአካል አንደምንገናኝ ቃል ልገባልህ እፈልጋለሁ አሁን የተፈጠርኩበትን የህይወቴን አላማ እያሳካሁ ነዉ ታስታዉሳለህ ሁለተኛ አመት ልንጨርስ አከባቢ በጊዮርጊስ የተዘጋጀዉን የቅኔ ምሸት መሪጌታዉ እያቀረበ እያለ ከመሀል የዘረፈዉን ሰዉ ያቺ ስንኝ ነበረች የህይወቴ ቁልፍ ቅኔዉ በሚስጢራዊነት አንድ ሰዉ በኢየሱስ ከርስቶስ አምሳል ሆኖ ነዉ የተነገረዉ ይህም ሰዉ የሚጠብቅበት ቀን የቦታዉ መሪ ካርታ ደግም የሚገኝበት መጽሐፍ ይህን ሁሉ የእያንዳንዷን የቅኔዉን ስንኝ ለይቼ ፊደሉን ቆጥሬ ነበር ከአንድ ሳምንት በኸላ ያገኘዉት መጽሀፍዋ ደርናባዋ ጽዮን ዉስጥ ያለች ስትሆን በበዓላት ብቻ ያዉም በአለቱ ካህን የምትነበብ ናት ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰብኩ ያለኝም ጊዜ በጣም ትንሽ ስለነበር ፈተና እንደጨረስኩ በጠዋት ለመዉጣት ወሰንኩ እናንተን ተሰናብቼ እያቆራረጥኩ በወሎ መስመር አድርጌ ኮምቦልቻን አልፌ ሰላድንጋይ ከተማ በመኪና ደረስኩ እዛዉ የጻድቀኔዋን ደብር ተሳልሜ የሚቀረዉን የእግር ጉዞ በበነጋታዉ ለመቀጠል ምሽቱን በከተማዋ አሳለፍኩ ሌሊት ላይ ብርዱ በጣም ከባድ ነበር በጠዋት የካህናቱ ማህሌት ነበር የቀሰቀሰኝ ወድያዉ ተነስቼ አቡነዘበሰማያት አድርሼ ጉዞዬን ቀጠልኩ እየነጋ ሲሄድ ጸሀዩም ስለማያስኬደኝ ብዬ በፍጥነት ነበር የምጓዘዉ ገደሉን መዉረድ ስጀምር ፀሀየዋ መከረር ደመረች አሁንም ቢሆን ከሁለት ሰአት የማያንስ የአግር ጉዞ ይጠብቀኛል ቁልቁለቱን በጥንቃቄ እያፈጠንኩ ሩጫዬን ቀጠልኩ ወደ አራት ሰአት አካባቢ ዋናዉ የቤተክርስቲያኑ መዉረጃ ገደሉ ላይ ደረስኩና ጸሎት አድርጌ ትንሽ እረፍት አረኩገደሉን ያዉ ከዚን በፊት ስለወረድኩት አዲስ አይሆንብኝም እንጂ በጣም የምያስፈራ ነዉ ለመዉጣትም ለመዉረድም ምንም የሚያዝ ገመድ ወይም እንጨት የለዉም እንዲሁ የቆመ ድንጋይ ላይ እንደ ዋልያ ወይም ዝንጀሮ እየቧጠጥከ ካልወረድክ በስተቀር ባላገሮቹ ግን እቃ በጭንቅላታቸዉ ተሸከመዉ አለቱን ደገፍ እያረጉ በቀላሉ ይወርዳሉ ይወጣሉ እኔ በጥንቃቄ የምቆመበትንና የሚይዘዉን አለት እየመረጥኩ ድንጋዩን እየተንፏቀኩ ከሰላሳ ደቂቃ በላይ ፈጅቶብኝ እታች ወረድኩ ከዚያም ፈጣሪን አመስግፔጌ ወደ ማረፍያ ቦታ አመራሁ አንድ ሳምንት እንደተቀመጥኩ በቃ አብዛኛዉን የቤተከርስቲያን ማህበረሰብ ተግባብቼ ነበር ያዉ በከህነቱም ዲያቆን ቢሆንም እራሴን እንደ ካህንቄስ አድርጌ ነበር የምቀርባቸዉ ግዴታ ይሄን አድል ለማግኘት ሁሉንም ሙከራዎች መጠቀም አለብኝ ካህን ብሆን አራሱ እዚህ ከሀያ በላይ ቀሳዉስት ባሉበት እድል ለማግኝት በየቀኑ ማድረግ ያለብኝ ተሳትፎ ወሳኘነት ስላለዉ ከማህበረ ካህናቱና ከቤተከርስቲያን አልጠፋም ነበር በርግጥ በጥርጣሬ የሚያዩኝ አንዳንድ ካህናት ነበሩ እኔም የሆዴን በሆዴ ይዝ አላማዬን ለማሳካት ሁሌ ደፋ ቀና እንዳልኩ ነዉ ሁለተኛ ሳምንቴን እንደጨረስኩ ያላሰብኩት ችግር መጣ የቤተከርስቲያኑ አስተዳዳሪ ለብቻዬን ጠርቶኝ ሁኔታዬ እንዳላማረዉና ከመጣዉ ጀምሮ ሲከታተለኝ እንደነበር ነገረኝ ያዉ ብደነግጥም አላማዬን በልቤ ይዢ የባጥ የቆጡን ቀባጥሬ አሳመንኩትና እንደዉም በይበልጥ ተግባብተን ወደ በአቴ ገባዉ የበአሉ ቀን ሲቀርብ የካህናት ጉባኤ ስላላቸዉ እኔም በእንግድነቴ ሳልገለል ከነሱ ጋር ተቀላቅዬ ስብሰባዉን ተሳተፍኩ በዝያ ቀን ስለሚደረገዉ አገልግሎት ነበር ዉይይቱ እኔ በምፈልገዉ ዋናዉ የቄሱ ቦታ ሁለት ካህናትን አስቀምጠዋል ሌሎቹ የቀሩት በማህሌትና በዝማሬ የሚያገለግሉ ናቸዉ ግዴታ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝና ካልሆነ በከንቱ መመለሴ ነዉ የበዓሉ ዋዜማ የሚደረግ ግብዣ ላይ በሁለቱ ካህናትና ሌሎች አራት ወጣት ካህናት ጠላዉ ዉስጥ ለሁለት ቀን የሚቆይ ሆድን የምረብሽና ተቅማጥ በተቅማጥ የሚያደርግ ብናኝ አረኩባቸዉ በሰላም ከመሶቡ ተመግበን ወደየበአታትን ገባን ሌሊት ላይ አስተዳዳሪዉ በአቴ ድረስ መጥተዉ ቀሰቀሱኝ ጸሎት ላይ ስለነበርኩ ስላወቁ ገርበብ ያለዉን በር ከፈት አረጉና ገብተዉ እስከጨርስ ጠበቁኝ ከአሳቸዉ ጋር ሆፔ ስርአቱን እንድከዉን ነግረዉኝ አሁኑኑ እንድመጣና ወደ መቅደስ እንድገባ አዘዙኝ በጣም ደስ ብሎኝ ለቅዳሴዉ ከዲያቆናት ጋር ተሰናዳን ቅዳሴ ማርያምን ጀመርንና ሰአቱ ሲደርስ አባ መጸሀፉን እንድያነቡት አመጣሁላቸዉ እንደጨረሱት አዞሩትና አስቀመጡት ወስጄ ወደ ማስቀመጫዉ አመራሁ መሪዉ ካርታ ወደሚገኝበት ገጽ ቁጥር ከፈተኩት የለም እያገላበጥኩ መፈለግ ጀመርኩ አላገኘሁትም ካህናቱ በትዝብት ምን እያደረገ ነዉ በሚል አስተያየት ያዩኛል በጣም ነበር የተናደድኩት ጉዞዬ ሁሉ ከንቱ እንደሆነ አሰብኩ በእርግጠኝነት ደግሞ የቅኔዉን ስንኝ አንዳላዛነፈኩ አዉቃለሁ አንድ ሳምንት ነበር ለመፍታት የፈጀብኝ ቅዳሴዉን ጨርሰን ደጀሰላም ገብተን እህል ዉሀዉን ቀምሰን እኔም በራሴ እያዘንኩ ወደ በአቴ ገባዉ በቃ ተስፋ ቆርጩ መደብ ላይ ተኝቼ እያብሰለሰልኩ እያለ በሬ ተንኳኳ አሁንም አስተዳዳሪዉ ነበሩ አገልግሎት ላይ ባሳየሁት ነገር ሊቆጡኝ የመጡ መስሎኝ ነበር ለካ ከመጣሁ ጀምሮ ሁኔታዬን እየታዘቡ ነበር ለምን ካህናቱን እንደዛ እንዳረኳቸዉ ጠየቁኝ በጣም ነበር ያፈርኩት ማንም በማያስተዉልበት ሁኔታ ነበር ያደረኩትና ለመዋሸት ብዙ ጥረት አረኩ እይ የልጅ ነገር እያሉ የተጠቀለለ ወረቀት ከኪሳቸዉ አዉጥተዉ ሰጡኝ ካርታዉ ነበር በአግራቸዉ ላይ ተደፍቼ ይቅርታ ጠየኳቸዉ እሳቸዉም ባርከዉኝ ወደበአታቸዉ ተመለሱ አባ እንደወጡ ካርታዉን ከፈትኩና ማጥናት ጀመርኩ መነሻና መደረሻ በሚያሳዩ አቅጣጫ ምልከቶች የተቀመጠና አካባቢዉ ስዕላዊ መግለጫ ያለዉ ነዉ በተቀመጠዉ ልኬት አንጻር ቢያንስ ከዚህ ጀምሮ የሁለት ቀን ጉዞ የሚሆን መንገድ ያዉም በእግር አለዉ በርግጥ ከሰባ እስከ ሰማንያ ኪሎሜትር ቢሆንም አካባቢዉ ገደላማ ስለሆነ ብዙ ያስኬዳል በጠዋት መነሳት ስላለብኝ አቃዎቼን ሸከፌ አዝያ የተዋወኳቸዉን ካህናትና መነኮሳትን ለመሰናበት ወጣዉ ለሁሉም በነጋታዉ እንደምነሳ እየነገርኳቸዉ አብረን እየተጨዋወትን አመሸንና እኔም ወደ በአቴ ተመለስኩ ወፍ ሳይንጫጫ ጉዞዬን በሌሊት ጀመርኩ የካርታዉን አቅጣጫ ተከትዬ ዳገት ቁልቁለቱን እያሳበርኩ ወንዝ እየተሻገርኩ ያቺን አንዷን ቀን ወድያ ወዲህ ስል በዚያ ሀሩር በሆነ ጸሀይ ተቃጥዬ አሳለፍኩኝ በመሀል ለምሳዬ ብዬ የቋጠርኳትን ቀመስኩና ጉዞዬን ቀጠልኩ ገና ግማሹን ጉዞ ሳላገባድድ በጣም ደከሞኝ ስለነበር ወደ አስር ሰአት አካባቢ ማረፍ እንዳለብኝ ተሰማኝና አንዲት ቤተከርስቲያን እስኪያገኝ አዘገምኩ በዚያ አለት ውስጥ ፈንጠር ብላ የተሰራች በዛፎች ብቻዋን የተከበበች ቤተክርስቲያን አገኘሁ ሰው በዙርያዋ አይታይም ወደ አስራ አንድ ሰአት አካባቢ ይሆናል በወንዶች መግቢያ በኩል ተሳለምኩና ድካሙ ፋታ ስላልሰጠኝ ወደ ዳር ሄጄ አንዲት ድንጋይ ላይ ተቀመጥኩ ሊመሽ አካባቢ አንድ መነኩሴ በጊቢዉ በር አድርገዉ ወደ አንድ በአት ሲያቀኑ አየዉ ተከተልኩና አናገርኳቸዉ ማረፍያ ቦታ ካለ እንዲሰጡኝ ወድያዉ የእግር ዉሃ አመጡና ካላጠብኩህ ብለዉ ግብግብ ገጠምን ያዉ ከገዳሙ ስርአት ማፈንገጥ ስለሌለብኝ ተዉኩና እግሬን አጥበዉ ማረፍያ ቦታዉን አሳዩኝ አስካሁኑ አንዲት ቃል ከአፋቸዉ አልወጣም ከሰላሳ ደቂቃ በኺላ ዳቤ ይዘዉ መጡና ከፊቴ አስቀመጡ እንድበላ በምልክት እየነገሩኝ ዳቤዉን ካስቀመጡልኝ ጠላ ጋር አጣጥሜ በላሁና ሳህኑን አመስገፔ መለስኩላቸዉ እሳቸዉ አሁንም ዝም እንዳሉ ነዉ ወድያ ወዲህ እያሉ የራሳቸዉን ስራ ይሰራሉ አንዲት ደቂቃ እንኳን እረፍት አያደርጉም ጋደም እንዳልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ስነቃ ወፎች እየተንጫጩ ነበር ደነገጥኩና በፍጥነት ተነሳሁ ያለችኝ ቀን ይች ናት ያዉም አስራሁለት ሰአት ብቻ ጸሎት አደረኩና በተኛዉበት ቤት ዉስጥ ዞር ዞር ብዬ ሳይ ማንም የለም በሩን ከፈት አረኩ በቀስታ ወደ ዉጪ ወጣሁ ቤተከርስቲያኑ ዉስጥ ድምጽ ይሰማል የተወሰኑ ሰዎችም ጊቢ ዉስጥ አሉ ያዉ ማህሌት እያደረሱ ስለሚሆን ብዬ በቀስታ ከጊቢዉ ወጥቼ ጉዞዬን በፍጥነት ቀጠልኩ በእልህ ነበር የምራመደዉ ምንም አይነት የድካም ስሜት ለማስተናገድ ፍቃደኛ አይደለሁም እያመመኝ እንኳን እያወኩ በጉልበት ነበር የምጓዝበት ረፋድ ላይ አንዲት ቋጥኝ መውጣት ነበረብኝ እንዳለ ድንጋይ ብቻ ነዉ ያን ዲንጋይ እየቢጠጥኩ መሀል ላይ እንደደረስኩ የረገጥኩት ድንጋይ አዳለጠኝና በእጄ ሌላ ነገር ለመያዝ ስታትር እራሴን ከገደሉ ስር አገኘሁት በቃ መነሳቴን እራሱ እኔ እንጃ ተስፋ ቆረጥኩ ትንሽ አግሮቼን ያዝያዝ አረኳቸዉ እንደተሰበሩ ለማረጋገጥ ትንሽ ተቀጥቅጧል ህመሜን ዋጥ አረኩና ቆምኩ ብዙም አልተሰማኝም ይሄኛዉን አቅጣጫ ትቼ ሴላ መንገድ መፈለግ ጀመርኩ በካርታዉ ላይ ያላስተዋልኩት ምልከት ነበረች ወደዚያዉ አመራሁና መወጣጫዉን ተከትዬ አለፍኩት ቀትር አካባቢ ላይ ስንቄን ፈትቼ ቀመስኩ ምንም እረፍት የሚባል መዉሰድ እንደሌለብኝ አዉቃለሁ ቢያንስ ሶስት ሰአት ስለሚቀረኝ ወዲያዉ መንገዴን ተያያዝኩት አስራ አንድ ሰአት ተኩል አካበቢ ቦታዉ ለይ ደረስኩ ካርታዉ ላይ በተጠቀሰዉ ድንጋይ ላይ ተቀመጩ የሚሆነዉን መጠባበቅ ጀመርኩ ከኔ ራቅ ብሎ ሁለት መነኮሳት የሚመስሉ ፈንጠር ፈንጠር ብለዉ ተቀምጠዋል ደከሞኝ ስለነበር ምንም ማድረግ አልፈለኩኝም ጀምበር ስታዘቀዝቅ በግምት ከአንድ ሰአት ቆይታ በኺላ አንድ ሪዙ ረዥም ቁመቱ ሰማይ የሚደረርስ ቢጫ ነጠላ ለብሶ የሞራል በሚመስል እያጨበጨበ ወደኛ ተጠግቶ በመሀላችን ቆመ በአንዲት ስንኝ ምከንያት እዚህ ጫካ ወውስጥ ተገኛችሁ ሰዋች መምጣት አይደለም ምንም በማይታወቅ ቦታ ያን ሁሉ መከራና ፈተና መመለስ እስከትናፍቁ ድረስ ቢደርስባችሁም በአላማችሁ ጸናችሁ ይሄ ገና የሁሉም ነገር መጀመርያ ነዉሹእያየን ነበር የተናገረዉ እነዚያም እንደኔዉ በተለያየ መንገድ ለአንድ አላማ የተጠራን መሆናችንን ገባኝ ያቺ በጨለማ ዉስጥ ተስፋ ያነገበች ልብ እዉቀትን ያስቀደመች ህይወት ጥበብን ያፈቀረች ነብስ ምንም ነገር በፊቷ ቢቀመጥ እሱን አሻግራ ማየት የምትችል አይን በአላማዉ የጸና መንፈስ ትንሽ ትንፋሽ ወሰደ እኔ አንዴ ወደ ምድር ሌላ ጊዜ ሰዉየን እያየዉ የሚሆነዉን በጥሞና እከታተላለሁ አንተ እንድትኖር ማንም የሚፈልግ የለም ያ ጽናትህ ነዉ አሁንም ድረስ በህይወት ያቆየህ አዉቃለሁ እጅ አትሰጥም ዛሬ ደግሞ በራስህ ህይወት ላይ ወስነህ እዚህ መጥተሀል ህይወትህን ልታስቀጥል መከራን ፊት ለፊት ልትፋለም ይሕን ህዝብ ልታሻግረዉ የህዝቡ ዘብ ልትሆንለት ነገዉን ልትሰራ ማንነቱን ልትገልጽለት ሀላፊነት ልትቀበል ተጠርተሀል አንደበቱ የሰላ ነዉ በቁጭትና በወኔ ነበር የምናገረዉ ከሁለት ሰአት በላይ ነበር ያወራዉ አንዳችን እንኳን ምንም አልተነፈስንም ነበር አንዲት ተወርዋሪ ኮከብ ከአንድሮሜዳ አናት ላይ በርታ እንደጠፋች አማትሮ አየና እየጠቆመን ተከተሉኝ ብሉን ይዞን ሄደ ከተራራዉ አናት ላይ አንዲት ቤተክርስቲያን በመብራት ተንቆጥቁጣ በዚያ ቦታ ላይ እንደ እንቁ ለአካባቢዉም ጭምር ታበራለች ሁለት መነኮሳት ከተራራዉ ግርጌ ማዶለማዶ ቆመዉ ጸሎት የሚያደርጉ ይመስላሉ መሀላቸዉ እንደደረስን ወደ አለቱ ዞረና ለአንድ ደቂቃ ያህል ዝም ብሎ ቆመ ከፊት ለፊት ያለዉ አለት ወድያዉኑ ለሁለት ተከፈለ ደንግጩ አንድ ሁለት አርምጃ ወደ ኺላ ሸሸዉ ዞር ብሎ እንድንከተለዉ በምልከት አያሳየን ተራመደ ሁለቱ መነኮሳት ምንም እንቅስቃሴ አያሳዩም ወደአለቱ ዘልቀን እንደገባን በሩ ተከረቸመ አለቱ በሚያስደንቅ አለም የተሞላ ነዉ የማየዉን ማመን ነዉ ያቃተኝ ከመሬት እስከ ጣርያዉ ያለዉ ርቀት ሀያ ሜትር አካባቢ ይሆናል በቀኝ በኩል ትላልቅ አዳራሾች አሉ ጣል ጣል ብለዉ አንድ ሀያ የሚሆኑ ሰዋች መጽሐፍት ይዘዉ ተቀምጠዋል አንድ ሰማንያ ሜትር የሚሆን የአለቱን ግድግዳ ተጉዘን እንደጨረስን በቀኝ በኩል ታጥፈን በደረጃ ወደ ላይ መዉጣት ጀመርን የደረጃዉ ጫፍ ላይ እንደደረስን በብርሀን የተጥለቀለቀ አንድ ሌላ ትልቅ ግዛት የሚመስል ሌላ አለም ሰዎች ወድያ ወዲህ ይመላለሳሉ በአብዛኛዉ ነጭ የለበሱ ከላይ የደረቡ ናቸዉ በአየሁት ነገር ፈዝፔ ቆምኩ ለካ እነሱ ትተዉኝ ታች ወርደዋል ወድያዉ እየሮጥኩ ተከተልኳቸዉ ደረጃዉን ወርደን በቀኝ በኩል ታጠፍንና ሀያ ሜትር ያህል እንደሄድን በስተግራ ባለዉ በር ገባን በሩ ላይ ሀዲም የሚል ጽሁፍ አለ በሁለት ደረጃና ግራና ቀኝ የተደረደሩ መኝታዎች ቤቱ የተሞላ ነዉ ያመጣን ሰዉ እነዚህ የናንተ ማረፍያዎች ናቸዉ የናንተ ስም የተቀረጸበት ከፍል አለ ከዚህ በኃላ የምትጠሩት በዚህ ስም ነዉ ብሎ ጽሁፍ ያለዉ ሳንቲም እመለሳለሁ ቤቱን ስታገኙ ጫፍ ላይ ባለዉ ፏፏቴ ታጠቡነ ከአንድ ሰአት እርፍት በኃላ መጣሁ ብሎን ሄደ ሶስታችንም የተደረደሩ ቤቶችን ሳንቲሙ ላይ ከተቀረጸዉ ስም አስተያይተን አገኘንና እቃችንን አስቀምጠን ፎጣ አገልድመን ወደ ከፍል አመራን ከተራራዉ አናት ላይ በሚፈሰዉ ፏፏቴ የተሰራ መታጠብያና ከስሩ ደግሞ ሰፋ ያለ ገንዳ አለዉ በዝያ እራሳችንን አቀዝቅዘን ወደየ ከፍላችን ተመለስን ትንሽ እራሴን እንዳሳረፍኩ አለቃችን በየስማችን ጠርቶን ከመኝታ ቤቱ ሰላሳ ሜትር አካባቢ ወደሚርቀዉ የግብር አዳራሸ ይዞን ገባ ይሄ ለኛ ተብሎ የተዘጋጀ ምግብ ነበረ ከነገ ጀምሮ መኝታ ቤታችን ላይ የተቀረጸ መርሀግብር ስላለ ሁሉም ነገር በሱ መሰረት እንደሚሆን ነግሮን ወደየቤታችን አመራን እሱም ተሰናብቶን ወጣ የኔ ማረፍያ ከፍ ያለዉ ላይ ሲሆን ሶስት የመሰላል እርከኖችን ወጥቼ ነዉ የምደርሰዉ በጣም ስለደከመኝ በቶሎ ወጣዉና ገባ አልኩ ወደ ውስጡ ብርሀን ሆነ ከአልጋዉ ራስጌ በኩል የተወሰኑ የተደረደሩ መጽሀፍቶች አሉ ዛሬ ምንም ማድረግ የለብኝም ከነገ ጀምሮ ሁሉንም ነገር እንደ አዲስ ለመጀመር የፕሮግራሞቹን ሰአት ብቻ አይቼ ወደ እንቅልፍ አመራሁ ጭዉ ያለ እንቅልፍ ላይ እያለዉ የሆነ ለስለስ ያለ ድምጽ እንደምያባበል መስሎ ከራስጌ አከባቢ ቀሰቀሰኝ ውድያዉ ሰአቱን ሳይ አስር ሰአት ይላል ተነሳዉና ተጣጥቤ ጸሉት አደረስኩ ለአስራ አንድ የተወሰኑ ደቂቃዎች ሲቀሩት የትናንቱ ሰዉዬ ድምጽ ነዉ በየስማችን ጠራን ሶስታቸንም ከመኝታችን ወርደን በተጠንቀቅ ቆምን እየተጠባበቅን እንደሆነ ያስታዉቃል ዛሬ አንድ መንበሩ ከሚባል ሰዉ ጋር አስተዋወቀንና መርሃ ግብሮችን አንደሚሰራልን ነግሮን ትቶን ሄደ እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ የከፈልነዉን መስዋእትነት አድንቆ ተቀበለን የሳምንቱን መርግብር አብረን ቀረጽን የሶስታቸንም መርሀግብር በተወሰነ መመሳሰልና መለያየቶች አሉት የኔን የተወሰነዉን ላሳይህ ጠዋት ከአስራ አንድ ሰአት አስከ ሁለት ሰአት የተቋሙ ቋሚ ያልሆነ ስራ ላይ መሰማራት ይሄ በየጊዜው ይቀያየራል ከሁለት ሰአት እስከ ሶስት ሰአት የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የተለያዩ ማጎልመሻዎችን የምንሰራበት ጊዜ ነዉ ተራራ መዉጣት ፈረስ መጋለብ መጎተት መሮጥ መከላከልና ማጥቃት ኢላማ ልምምድ በጣም ብዙ ናቸዉ ከሶስት ሰአት እስከ አራት ሰአት የምግብና የአረፍት ጊዜ ነወ ከአራት እስከ ሰባት ሰአት በአንድነተ ትምህርት የምንማርበት ጊዜ ነዉ ከሰባት እስከ አስር ሰአት የተለያዩ የምርምር ስራዎች ላይ እንደ አጋዥ ሆነን የምንሰራበት ነዉ ከዶከተር ኬራየን ጋር እንድሰራ ተመድብያለዉ ምን እንደምንሰራ ሌላ ጊዜ እነግርሀለዉ ከአስር እስከ አስራ ሁለት ሰአት የቋንቋ ሰአት ነዉ አንደየችሎታችን ቋንቋ የምንማርበትና ምናስተምርበት ሰአት ነዉ ከአስራ ሁለት እስከ ሁለት ሰአት ማታ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎችና ዉይይቶች የሚቀርቡበት ነዉ ከሁለት እስከ ሶስት ሰአት ማታ የምግብና የእረፍት ጊዜ ነዉ ቀሪዉ እረፍትና የእንቅልፍ ሰአቴ ነዉ ከዚህ በተጨማሪ እንደየሁኔታዉ አስቸኳይ ሁኔታ ስያጋጥምና ተልዕኮዎች ሲኖሩ የሚቀያየሩ አሉ ብሎም በየሳምንቱ መጨረሻ የመርሀግብሩ አፈጻጸም ይታይና ማስተካከያዎች ካሉ ይሻሻላሉ መርሀግብሩን ቀርጸን ስንጨርስ ሶስት ሰአት አካባቢ ይሆን ነበርና ወደማዕድ ቤት ሄድን እዛ በጣም ብዞ ሰዎችን ተዋወቀን ከምግብ በፒላ ሳቤዝ ከሚባል ሰዉ ጋር አገናኝቶን የተወሰኑ ስራዎችንና ቦታዎችን አሳየን በእያንዳዱ ቦታ ላይ ያሉ የደህንነት ሁኔታና ብዙ ነገሮችን አሳየን ከዚህ በኺላ በሳምንቱ መጨረሻ ለመጻፍ ሞከራለሁ ሚያዝያ ለካ ጊዜ ካልተጠቀሙበት የሰአታት ድምር ብቻ ይሆናል እያንዳንዷ ሰአት ለአንድ ግብ በቁምነገር ስታልፍ ሰውን የመለወጥ አቅሟ የማይተካ ነዉ የመጀመርያዋ ሳምንት የመጣሁበትን መንገድ የታዘብኩበት ያሳለፍኩትን ህይወት የገመገምኩበት የዉስጥ ማንነቴ የተነቃቃበትና አላማ ያነገብኩበት ነበር አሁን ሌላ ሰዉ ነኝ የተቀበረዉን የአባቶቼን ስልጣኔ ማማ ላይ የምሰቅል የሰዉን ልጅ ጉዳት የማልቀበል ለህዝብ ሁሉ የምቆም ህዝቡን ከጥቃት የምከላከል አድሎነትን የማልቀበል ሰዉ ወደማንነቱ እንዲመለስ የማምንና የምሰራ የዕጅ አዙር ባርነትን የምጸየፍ ኢትዮጵያዊ ነኝ አንድ ነገር ልንገርህ አፍሪካ ዉስጥ መንግስንት የለም መንግስት የሚኮነዉ እዚህ ያሉት ጥቃቅን ሀይሎች ከባዕዳን በሚያገኙት ድጋፍ ነዉ እነዚህ የሚሰሩት ለህዝቡ ሳይሆን ድጋፉን ለሚሰጣቸዉ አካል ነዉ ድጋፍ አድራጊዎቹ የሚፈልጉትን ግብአት ቀጥታ ከነዚህ ሀገሮች ያገኛሉ ምርት ተመርቶልን ይምጣ ካሉ ኢንዱስትሪ ተቋቁሞላቸዉ የአገሬዉን ህዝብ አሰማርተዉ ያስፈጉታል የምርት ዉጤቱን ደግሞ ወዳገራቸዉ ለቃቅመዉ ያስጭኑታል ለኛ የሚቀረዉ ለአካባቢ ጸር የሆኑ ተረፈ ምርቶችና አካባቢን የሚበከሉ ንጥረነገሮች ናቸዉመንግስት መስራት የነበረበት ያንተንና የኔን ሕይወት በሚቀይሩ ነገሮች ኢንዱስትሪም ማቋቋም ያለበት እኛ በየቀኑ ልንጠቀማቸዉ ከምንችለዉና ለሚያሰፈልጉን ነገሮች ነበር ለራሳችን ሳንሆን ለሌላ እየሰራን እያጌጠናቸዉ እንኖራለን አስተዳዳሪዎቻችን ሆዳቸዉ ይሙላ ፊታቸዉ ይቅላ እንጂ ህዝቡን ዞር ብለዉ አያዩትም በዚህ ብቻ ቢቀር መልካም ነበር አንገቱን ደፍቶ ባጎረሳቸዉ ያንን ሚስኪን ህዝብ ያጠቃሉ ቀና ለማለት ስትሞክር ይቀጠቅጡሀል በማናየዉም በምናየዉም ይዋጉናል ቆሻሻቸዉንና ጥራታቸዉ የወረዱ ምርቶች ማራገፍያቸዉ ያደርጉናል ወርቅ ልከንላቸዉ መዳብ ይሰጡናል አሳምረናቸዉ እኛ አመድ መስለን እንዞራለን አይ። አይዞን ቀና ብለህ የምትራመድበት ቀን ሩቅ አይሆንም ግንቦት ሰሞኑን እግሬ ተያይዞ ነበር ሰኞ እኛ ካለንበት እስከ ናፍቃን ተራራ የሆነ እቃ ተሸከመን አመጣን በአንድ ሰአት ዉስጥ መጨረስ ስለነበረብን ሰዉነታችን ዉልቅልቅ አለ በየቀኑ የምንሰራቸዉ እንቅስቃሴዎች ከባድ ናቸዉ አሁን እየለመድኩት መጥቼ ነዉ እንጂ መጀመርያ አካባቢ ላይ ትንፋሽ በጣም ያጥረኝ ነበር አሁን እያገዝኩት ያለዉ ዶከተር ኬራየን ጥናቱ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ስለሚኖረዉ ታላቅ ከስተት ነዉ አፍሪካ ለሁለት ትከፈላለች በዚህ ሁኔታ ሊቀየሩ የሚችሉ መስተጋብሮች ስነምህዳሮች የብዝሀ ህይወት ሁኔታዎችን እያየን ነበር የራሽያ ቋንቋን ሰላሳ ለሚሆኑ ሰዎች እያስተማርኩ ነዉ በጎን ደግሞ እኔም ስዋሂሲን እያጠናዉ ነዉ የስዋሂሊ ቋንቋ የሚነገረዉ በምስራቅ አፍሪካ ሲሆን ለያዝነዉ አላማ ትልቅ መሳርያ ይሆናል ሺካሙ ብዬሀለሁ ከባለፈዉ ሳምንታት ትንሽ የፕሮግራም ለዉጦችን አድርግያለዉ ትንሽ ስራ ሊበዛ ስለሚችል ሳልጽፍ ልቆይ እችላለሁ ግንቦት ያሳለፍነዉ ሳምንት በጣም ደስ ይል ነበር እንቅስቃሴና ማጎልመሻ ከአስራሁለት ሰአት እስከ ሶስት ሰአት ሰርቻለሁ አድካሚም ቢሆን ያረካል የማስተምረዉ የራሽያ ትምህርት ከአንድ ረዳት ጋር በጣም እየሄደልኝ ነዉ አብዛኛዎቹ የሚማሩት በቴከኖሎጂ መስከ ላይ የሚያጠኑ ናቸዉ እሮብ አለት ከዶከተር ፖከር ጋር አራት ሆነን ሶስት ሰኣት አካባቢ በግዩድ ወጣን ግዩድ በመሬት ዉስጥ በተሰራ መስመር ነዉ የሚጓዘዉ አስራ ሁለት የሚሆን የተቋሙ ቦታዎችን የሚያገናኝ የመሬት ዉስጥ መስመር በአራቱም አቅጣጫ አለ በሰአት እስከ ኪሜ ድረስ ግዩዱ ይሄዳልአንዱ እስከ ሀያ ሰዉ አካባቢ የሚይዝ ምቹ ቦታ ሲኖረዉ ተጨማሪ ካስፈለገም ከሌላ ግዩድ ጋር ተገናኝቶ መሄድ ይችላል ግዩዱ በሰዉ ቀጥታ መሪነተ ሳይሆን የሚሄደዉ ከዋናዉ ተቋም በተሰጠዉ መረጃ መሰረት ያደርሳል ምንም የሚሄድ አይመስልም ነበር ከሁለት ሰአት በኺላ መድረሻችን ጋር እንደደረሰ አሳወቀችን ተከታትለን ወጣን የቆምንበት በጣም ሰፊ ሆኖ ጭር ያለ ቦታ ነዉ ወደ መውጫው ስንጠጋ በሩ በራሱ ጊዜ ተከፈተ ዉጪዉ በጣም ለምለም አረንጓዴ በጥቅጥቅ ዛፎች የተሞላ ነዉ ለካ ከአንድ ተራራ ስር ነበርን ከአናቱ ላይ የመድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን አለች ትንሽ በእግር እንደሄድን ይዞን የመጣዉ ሰዉ የተዘጋጀልንን መኪና አሳየንና አኔ እየነዳሁ ጉዞ ጀመርን የጉዞአችን መዳረሻ አሬሮ። የምትባል አካባቢ ሲሆን እዛ አካባቢ ያለዉን ዩራኒየም ለማጥናት የሚረዱ ናሙናዎችን ለማምጣት ነዉ የተወሰነ ከሄድን በኺላ አስፓልት መንገድ ላይ ወጣን ከሁለት ሰአት የመኪና ጉዞ በኺላ ነበር ቦታዉ ላይ የደረስነዉ ዶከተር ፖከር በሚያሳየን መሰረት የቦታዉን አቅጣጫ ጠቋሚ መረጃ ካረጋገጥን በኺላ ናሙና መቀበያ መሳርያዉን ተከልነዉ መሳርያዉ ሀያ ሜትር ያህል ወደዉስጥ መግባት ስችል በያንዳንዱ ሜትር ልኬት በራሱ ናሙናዎችን ይወስዳል ሀያዎቹን ናሙናዎችን ካስቀመጥናቸዉ በኺላ ተጨማሪ ናሙናዎችን ለመዉሰድ ተነሳን ሁለተኛዉ ናሙናዉ ቢያንስ ከዚህ ቦታ የአምስት ኪሎሜትር ርቀት በደቡብ አቅጣጫ ሲሆን የተቀሩት ሁለቱ ናሙናዎች ከበፊቶቹ ሁለቱ ናሙናዎች በምስራቅ አቅጣጫ የአምስት ኪሎሜትር ርቀት ያለዉ ነዉ መሬቱ ድንጋያማ ስለነበር በጣም ያስቸግራል በአንድ ሰአት ዉስጥ የአራቱንም ቦታ ናሙናዎች እንደወሰድን በሌላ አቅጣጫ ወደ ተቋማችን ተመለስን ሰኔ በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ በቅርብ አመታት ዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ብዙ ናቸዉ ከላይ ሲታይ መልከአ ምድሩ ምንም ያልተቀየረ ደህና ይመስላል እንጂ ዉስጥ ዉስጡን አምቆ የያዘዉ ሀይል ሊወጣ እያጉተመተመ ነዉ ያለዉ ከዚህ በኺላ ስምጥ ሸለቆዉ አካባቢ በተለይ ደግሞ በአፋር ምድር በዚህ ሀይል ሳብያ ርዕደ መሬት አዳዲስ እሳተገሞራ ፍንዳታዎች ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሊከሰቱ ግድ ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ መልካም ነዉ እነዚህ ሀይሎች የስምጥ ሸለቆዉን መስመር ይዘዉ ምድሪቱን ቀስ በቀስ ለሁለት ይከፍሏታል እነዚህን በቀላሉ ሊሰነጥቁ የሚችሉ ደካማ መስመሮች ከዶከተር ኬራየን ጋር ያዉ እኔ በአጋዥነት እየሰራን ነዉ የስምጥ ሸለቆዉ አሰራርና ዉቅር በጥልቀት በማጥናት የሚከፈልበትን ቦታ በየ አምስት መቶ ሜትር ርቀት ልዩነት እየሰራን ነዉ ብዙ ጊዜ ለዚህ ጥናት የሚጠቅሙ ናሙናዎችን ከየቦታዉ እንሰበስባለን ከምድር በታች እየሆነ ያለዉን ሁኔታም በየጊዜዉ እንከታተላለን በዚህ የምድር መስተጋብር ምከንያት ከተሞች ለሁለት ይከፈላሉ መንደሮች ይለያያሉ ሰዎች ግዴታ ከነዚህ አካባቢ ተነስተዉ ሌላ ቦታ ላይ መስፈር አለባቸዉ የሰራነዉን ስራና ያጠራቀምነዉን ንብረት ሕይወታችንንም ጭምር በአንድ ቀን የሚያሳጣን አደጋ ሊከሰት ይትላል ሁነቱ የመሬት ለሁለት መከፈል ብቻ አይደለም ከባህር ጠለል በታች ያሉ አካባቢዎች ዉቅያኖስ ይወርሳቸዋል አሁን ሰዎች የሚተራመሱበት በዚያን ጊዜ አሳዎች መኖርያቸዉ ያደርጉታል እያንዳንዷ የምንኖርባት ቤት የምንኩራራባት መሬት የምንመካበት ምድር ዉሀ ይዉጠዋል የአዋሽ ወንዝ እንደ አመጸኛ ግዛት አልገብርም ማለቱን ያቆማል መገበር ብቻ አይደለም ሙሉ በሙሉ በኑብያዉ ዉቅያኖስ ተጠቅሎ ይወሰዳል ዛሬ የበረሀዉ አንበሳ የሆኑት አፋሮች አሳ አስጋሪዎችና የባህር ላይ አርበኞች ይሆናሉ ሌላ ተጨማሪ አህጉር ይፈጠራል ኑብያ የምትባል አፍሪካዊ ስነመሰረት ያላት በኑብያ ዉቅያኖስ በግራና በህንድ ዉቅያኖስ በቀኝ የታጠረችና የዉቅያኖስ ማዕከልንሜድትራንያንን እንደቆብ ያጠለቀች ሰኔ አይ የኔ ነገር በጣም ቆየዋ ሥራ በዝቶብኝ ለመጻፍ ጊዜ አላገኘዉም መማሩ ማስተማሩ ስልጠና የጥናት ስራዎች መስከ በቃ ብዙ ፋታ አይሰጡም በአለፈዉ ሳምንት አዲስ የጀመርኩት ስልጠና ብዙዉን ሰአት እሱ ላይ አሳልፋለዉ የከብጥይር ሁለተኛ ረዳት ተቆጣጣሪ ላይ አየሰለጠንኩ ነዉ ከብጥየሯን ለሶስት እንቆጣጠራታለን በርግጥ በተለያዩ አይነት መንገዶች ልትሰራ ትችላለች የመጀመርያዉ ሁሉም መረጃ ተጭናባት በራሷ የተላከችትበት ደርሳ አላማዋን አሳከታ መምጣት ትችላለች ሌላዉ እዛዉ ተቋሙ ላይ ባለዉ መቆጣጠርያ ማሳካት ይቻላል ነገር ግን አብዘኛዉን ጊዜ ሰዉ እንድቆጣጠርና እንደየ አስፈላጊነቱም ሁለቱን በመሀል ማስገባት ይመከረል ከብጥይር ከብ ቅርጽ ሲኖራት የተለያየ መጠን አላት እንደየ ተልዕኮዉ ሁኔታ ይወሰናል በየትኛዉም የአየር ክልል ላይ ያለምንም ገደብ መብረር ትችላለች ብዙ ጊዜ የምንጠቀመዉ በሌላ አሕጉር ተልዕኮ ሲኖረን ነዉ በዚህ ሳምንት አንድ የምርመራ ስራ ላይ ተመድቤ ነበር አሁንም ድረስ በተለያየ ስራ ላይ ረዳት ሆፔ ነዉ የምሰራዉ ከኔ ጋር ሁለት ሰዎች አሉ የሚያስፈልጋቸዉን መረጃ በማቅርብና እንደየ አስፈላጊነቱም በመተርጎም ምርመራዉን ማገዝ ነዉ ሶስት የተለያዩ እንከብሎች በህብረተሰቡ ወስጥ በተለይ ደግሞ በተማሪዎችና በወጣቶች መሀል በከፍተኛ መጠን እየተዘዋወረ ያለ ከተራ መድሀኒት መደብር እንኳን እንከብሱን አንድ ታዳጊ በቀላሉ የሚገዛዉ ወጣቱ በከፍተኛ መጠን እየተጠቀመዉ ያለ ሱስ የሆነበት ያለሱ መዉጣት መግባት ችግር የሆነበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ ሶስቱ እንከብሎች ከምን እንደተሰሩና የት እንደተመረቱ በቂ መረጃ እንኳን ያልተገለጸባቸዉ ሲሆን ቀጥታ ወደ መመርመርያ ከፍል ተልከዉ እንዲጣሩ ተደረገ የመጀመርያዉ እንከብል ቫልየም የተባለ ንጥረ ነገር የተገኘበት ሲሆን በእርግጥ ለተለያዩ የጭንቀትና የድብርት ማስታገሻ ህከምናዎች የሚዉል ነዉ ያለአግባብ የሚጠቀሙት እነዚህ ለጊዜዉ የነጻነትና ደስተኝነት ስሜት ለማግኝት ኑዉ ስሜቱን ለመጨመር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑን አብዝተዉ ይወስዱታል ይህኔ ለከፍተኛ በሸታና አደጋ ያጋልጣቸዋል እስከሞት ድረስም ሊደርሱ ይትላሉ ሌሎች ሁለቱ እንከብሎች የተገኘባቸዉ ንጥረነገር ኮዲን እና አዴራል ሲሆን በአብዛኛዉን ከቫሊየም ጋር ተመሳሳይነት አላቸዉ የህክምና ጥቅማቸዉ የጎላ ቢሆንም አዚህ ደግሞ ለመዝናኛነት አዕምሮን አያደነዘዙ እየተጠቀሙት ነዉ በጣም የሚገርም ነዉ ሀገርን ወገንን ለማገለልገል የገቡትን ቃል ገደል ከተዉ በገንዘብ ፍቅር የሰከሩ ህዝብ ካለዉ ሀብት ላይ ቀንሶ ባስተምራቸዉ ዉለታዉ ትዉልዱን ወደ እብደት መምራት ይሁን ሰስት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በህከምና ሳይንስ ከሰባት አመት በፊት ያጠናቀቁ ዶክተሮች ናቸዉ ህጋዊ የመድሐኒት አስመጪ ንግድ ፈቃድ አዉጥተዉ እንከብሉን ለወጣቱ በገፍ አያከፋፈሉ ያሉት አንዱ አሜሪካን አገር የሚኖር ሲሆን በተለያዩ መንገዶች ግዢዉን ከየሀገራቱ ይፈጽማል ዶከተር አቤል ይባላል ሌሎቹ ሁለቱ ዶከተሮች ዶክተር ዲዲሞስና ዶክተር ናታን የተባሉ ሲሆኑ ከእርሱ ተቀብለዉ በሀገር ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች የሚያከፋፍሉ ናቸዉ ከስራቸዉ የሚሰሩም በጣም ብዙ ሰዎች አሉ በዚያኑ ረቡዕ ቀን ነበረ ከዶከተሮቹ ጋር ግኑኝነት ያለዉ ኪግ የሚመዝን ኮዲን የተሰኘዉን ንጥረነገር ያለዉ እንከብል ከሌሎች እቃዎች ጋር የጫነዉ መርከብ ሜዲተራንያን ባህርን አቋርጦ የጂቡቲ ወደብ ላይ ያራገፈዉ አሰግድ የተባለዉ ባለሙያ ነበር ከተለያዩ በይን መረቦች አማካኝነት አንጥሮ ያወጣዉ ወድያዉ በኬራዉድና ኬፋ መሪነት በዚህ ጉዳይ ላይ ተወያየን እቃዉ ከጂቡቲ ወደብ ተነስቶ ወደዉስጥ ሲገባ በረሀ ላይ እንዲወገድ ተስማማን ለቁጥጥር እንዲመቸን የኛኑ ሰራሪአቅጣጫ ጠቋሚ በረሮ እንዲጠባበቅ ተላከ ሰራሪዉ ሁለት አካላት ስኖሩት ዋናዉ አካልና በራሪዉ አካል ነዉ በራሪዉ አካል ከቦታ ቦታ እንዲሄድ የምያደርገዉ ሲሆን ዋናዉ አካሉ ደጎሞ በተጫነለት መረጃና ከተቋሙ መልዕከት እየተቀበለ አስፈገላጊዉን መረጃም የሚልከ ሲሆን አንዳንድ ተልኮዎችንም ማከናዎን ይችላል ሶስት የመመርመርያ ጣቢያዎች ሲኖሩ እነሱም ኮናድ መኩሪያና አልዋ ናቸዉ ኮናድ ለጂቡቲ ቅርብ በመሆኑ ሰራሪዉ ከዛ እንዲላከ ተደረገ አርብ ረፋድ ላይ ነበር ሰራሪዉ እንቅስቃሴ ያሳየዉ ወድያዉ ሶስት ሆነን ተልዕኮዉን ለመፈጸም ግይዴን አስነስተን ወደ ኮናድ አመራን ከሁለት ሰአት አርባ አምስት ደቂቃ በኺላ ነበር የደረስነዉ የዕቅዱም አላማ ከጅቡቲ ወደብ ስድስት መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ጭዉ ያለ በረሀ ላይ መገኝት ነበር ወዲያዉ ወደ በረሀዉ መኪናችንን አስነስተን ከዋሻዉ ወጣን ከአስራ አምስት ደቂቃ በኃላ ቦታዉ ላይ ደረስን ትንሽ እንደቆየን በግምት አንድ ኪሎሜትር የሚረዝም ካርጎ የጫነ ባቡር ከፊት ለፊታችን ቆመ ይሄ የሆነዉ በሰራሪዉ ሲሆን የተጫነበት መረጃ ባቡሩ በቦታዉ ከመደረሱ አምስት ኪሎሜትር በፊት ሁሉንም ተግባሪዎች እንዲዘጋ ነዉ ኮንቴነሩን ከለየንና ከፊት ለፊት የነበረዉን ካርጎ እንደለየን ለሰራሪዉ እንዲያስነሳና ተልኮዉን ስለጨረሰ ወደ ቦታዉ እንዲመለስ መልከት ላከን ሁለት መቶዉን ሜትር የሚረዝመዉን ወደኺላዉ ትቶ ስምንት መቶዉን ሜትሩን እየጎተተ አለፈ ኮንቴነሩን አዉርደን ዉስጡ ያለዉን ካረጋገጥን በኃላ ነዳጅ አርከፍከፈን እዛዉ ሀዲዱ ጎን ላይ አቃጠልነዉከሰላሳ ደቂቃም በኺላ ከቦታዉ ተሰወርን ሀምሌ የጥንት የኢትዮጵያ ስልጣኔ እስካሁን ድረስ በሂደት ላይ ነዉ ፍሬ ለመስጠት ምቹ ሁኔታን ብቻ ነዉ ምጠብቀዉ በዚህ ሳምንት ከተለያዩ ሰሰዎች ጋር የዕቅድ ዉይይቶችንና ጥናቶችን ስናደርግ ነበረ ገዳማት የኢትዮጵያ የጥንትም የአሁንም ዩኒቨሪስቲዎች ናቸዉ ከዉጪ ሰታዩ ሀይማኖትን ትምህርት ብቻ የሚየስተምሩ ቢመስሉም የተለያዩ ምርምሮችን ዛሬም ድረስ ያከናዉናሉ በሚገርመዉ እነዝህን እንቁ ገዳማት ከዉስጥም ከዉጪም ለማጥፋት የሚታትሩ ብዙ ናቸዉ በጉብኝት ሰበብ ተደርጎ የቅርስ ምዝበራዎች እየተደረጉ ነዉ የተለያዩ የጥናት ዉጤቶች በቅርብም በሩቅም ጊዜ የተሰሩ እየተዘረፉ ነዉ ይሄን ነገር ሁላችንም የምያሳስበንና በተገቢዉ መንገድ ጥንቃቄና ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ የምንታገልለት ነዉ ይሄ ተቋም አላማዉ አባይ ላይ መሰረቱን ያደረገ ጠንካራ ሀገረ መንገግስት መገንባት ነዉየዚህ ረቂቅ እቅድ ከዛሬ ሀምሳ አመት በፊት ወጥ ቅርጹን የያዘ ሲሆን በያመቱ በሚደረጉ ጥናቶችና ዉይይቶች እየዳበረ የመጣ ነዉ ያለምንም ጦርነት ካሁንዋ ታንዛንያ ሰሜን እስከ ግብጽደቡብ ድረስ በአንድ መንግስት ለማስተዳደር በጣም ጥቂት አመታት ብቻ ናቸዉ የሚቀሩን ለዚህም ከአስር አመት ወዲህ ከየሀገራቱ የተዉጣጡ ወጣቶች በተለይ በሶስቱ ተቋማት አልዋ ኮናድና መኩሪ ላይ ለአራት አመታት የሚቆይ ትምህርቶችንና ስልጠናዎችን ይወስዳሉ ወደ ሀገራቸዉ ሲመለሱም በምን አይነት መልኩ የአሰተዳደር ተቋሞች ላይ መሳተፍ እንዳለባቸዉ በተለይ ደግሞ የመከላከያ የደህንነትና ቴሌኮም ቦታዎች ላይ ሀላፊነት እንዲቀበሉ የሚያስችል ስልጠና ገፋም ካለ ከፍተኛ የስልጣን እርከኖችን እንዲቆጣጠሩና እንዲመሩ የሚያደርግ የመሪነት ከህሎት ያስታጥቃቸዋል እዚህ ላይ የደቡብና የሰሜን አቅጣጫ መሰረት ያደረገዉ የአባይን ውሀ ተፋሰስ መሰረት አድርጎ ነዉ የአባይ ምንጮች ወይም ከፍታ ላይ ያሉት ሰሜን አቅጣጫ ላይ ሲገኙ ታቸኞቹ ደግሞ በደቡብ ይገኛሉ ሁሉም ግቡ ለዛች ከስሟ በላይ ለገዘፈች ሀገር ነዉበአሁን ሰአት በአልዋ ተቋም ከኬንያ ኢትዮጵያ ሩዋንዳ ዩጋንዳ ታንዛኒያ ግብጽና ሶማልያ የመጡ አምስት መቶ የሚሆኑ ምጡቅ አእምሮ ያላቸዉ ወጣቶች አሉ ነሀሴ ትልቁ ቤተመጻፋችን ኢተያ በኢትዮጵያ ንግስት ስም የተሰየመዉ መግብያ አካባቢ ላይ ያለዉ አሉ የተባሉ መጽሀፍቶችንና በዚያ ብቻ የሚገኝ እጅግ በጣም ብዙ ጥናታዊ ጽሁፎች አሉ የተወሰነ የጥናት ሰአቴን ቢያንስ በቀን ሁለት ሰአት እዚህ እጠቀማለሁ ስለ ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ የተለያዩ አመከንዮዎችን የያዘ ከአንድ ጽሁፍ ያገኘዉትን ልንገርህ ኢትዮጵያ በእግዚአብሄር ዘንድ ያላት ቦታ ተልቅ ነው እግዚአብሔር ያከበረዉን ደግሞ ማንም ሰዉ ሊያዋርድ አይችልም ልናዋርድና ልናኮስስ ብንፈልግ ያ ማድረግ ያሰብነዉ ወደ ራሳችን ይመለሳል ሰይፍን የሚያነሳ በዚያዉ ሰይፍ ይሞታልና እኛ ኢትዮጵያዉያን ለምን ይሄን ከፊት ለፊታችን ያለዉን እዉነት እግዚአብሔር የመሰከረልንን ተረድተን ለራሳችን አንኳን ከብር እንደማንሰጥ አይገባኝም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በመጀመርያ የተጠራችዉ ሀገር ኢትዮጵያ ናት ገነትን ለማጠጣት ምንጭ ያደረገባት ቅድስት ምድር የኢትዮጵያ ሕዝብ በእግዚአብሔር ዘንድ ያለዉ ቦታ ከአስራኤላዉያን በላይ እንደሆነ መጽሐፍ ቀዱስ ያስረዳል ምክንያቱን በሚከተለዉ የእስራኤለዉያን የስደት ታሪከ ዉስጥ መረዳት እንትላለን የአስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ወጥቶ ወደ ከነአን በሚያደርገዉ ጉዞ ያምጽ ነበር እግዚአብሔርን በጣም አሳዝነዉታል ያን ሁሉ ተአምር እያደረገ ከእስራኤላዉያን የሚያገኘዉ መልስ ግን የሚያሳዝን ነበርበድፍረት እግዚአብሄርን ተናግረዉታል ከእግዚአብሄርና ከሙሴ ትዕዛዝ ወጥተዉ ያልተገቡ ብዙ ነገሮችን አድርገዋል እርሱንም ትተዉ ጣኦትን እስከ ማምለከ ደርሰዋል በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን ይሄንን ሕዝብ ላጥፋዉና አንተን ታላቅ ሕዝብ ላይ ልሹምህ ብሎት ነበር በሙሴ ምልጃ አማካኝነት እግዚአብሔር እስራኤላዉያንን ትቷቸዋል እዚህ ጋር እግዚአብሔር ሙሴን ታላቅ ሕዝብ ላይ ልሹምህ ሲለዉ ከእስራኤል ውጪ የትኛዉ ሕዝብ ላይ መቼስ ከእስራኤል በላይ ታላቅ ሕዝብ ቢኖር ነዉ እንጂ ይሄንን ለሙሴ ባላለዉ ነበር በትንቢት ደግሞ እስራኤላዉያንን እግዚአብሔር ሲያጽናና የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን ይላል እንደ የማነጻጸርያ ቃል ናት በግልጽ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ልጆች ከእስራኤል ልጆች አብልጦ እንደሚወድ የገለጸበት ቦታ ነዉ የላይኛወን ታሪከ በዚኛዉ ዐረፍተነገር ሙሉ ስናረገዉ እግዚአብሔር ለሙሴ ቃል የገባለት ሀገር ኢትዮጵያ ናት ማለት ነዉ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን መልከ የገለጸበት መንገድ ደግሞ መቼም ቢሆን የማይቀየርና በዘመናት መካከል ልዩነት እንደሌለዉ ነዉ ከነብር ዥንጉርጉርነት ጋር እያነጻጸረ ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይቀይርም መልከ መገለጫ ነዉ እኛ ኢትዮጵያዉያን በእግዚአብሔር ፊት የምንታወቅበት መልክ ብዙ ናቸዉ እነሱም ለዘላለም ጸንተዉ የሚኖሩ በዘመናት የማይቀያየሩ መልኮች ናቸዉ ጠላት ለመቀየርና ለማጥፋት ቢሞከር የማይቻለዉ መልከ አብርሀም የተገለገለበት የመልከጹዴቅ ከህነት በዮቶር ቤት ዉስጥ ሙሴን የተቀበልንበት መልካችን ጥበብን ሽተን ወርቅና ብር ጭነን አገር አቋርጠን በረሀዉን ሰንጥቀን ባሕር ተሻግረን እየሩሳሌም ያስደረሰን የጥማታችን መልከ ከርስቶስ እራሱ የመሰከረልን እዉቀትን ፈላጊዎችና አንባቢዎች የመሆናችን መልክ የጦረኝነት መልክ የሃይማኖተኝነት መልካችን በእግዚአብሔር ፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ምስከርነት ጎልቶ የምታይ ነዉ እነዚህ መልኮች ሁሌም ሞገስ የሚሆኑንና ቀና ብለን እንድንራመድ የሚያደርጉ ደግሞም ለዘለአለም የማይቀየሩ ናቸዉ ነሀሴ ባለፈዉ ጊዜ ሶስቱም ዶክተሮች ጋር የምያደርጉትን የመልዕክት ልውዉጦች በተለይ በእንክብሎቹ ላይ ያለዉን መረጃ እንዲልኩልን ሰራሪዎችን ወደ ኮምፒዩተራቸዉ ልከንባቸዉ ነበር እነዚህ ዶክተሮች ምንም በማያዉቁበት ሁኔታ ወደ ኮምፒዩተራቸዉ በተለያየ መንገድ ተሰከተዉ እነሱ የሚልኩትንና የሚቀበሉትን መልዕክት አጣርተዉ ወደኛ ይልካሉ በመጀመርያ ለያንዳዳቸዉ ዶከተሮች ግልጽ የሆነ መልዕከት ልከንላቸዋል እየሰሩ ያሉት ስራ ትከክል እንዳልሆነና እንዲታቀቡ ካልሆነ በህይወታቸዉ የሚጸጸቱበትን እርምጃ እንደምኖስድባቸዉ አሜሪካ ያለዉ ዶከተር አቤል ከቁብም አልቆጠረም ነበር በሳምነት ልዩነት ዉስጥ ከህንደ ቀጥታ ቫልየም ለማስጫን የተነጋገራቸዉ አስር የምሆኑ መልዕከቶች ደረሱን በቃ ወድያዉ እርምጃ ተወሰደበት በተኛበት ሰራሪዋ እንድትነድፈዉና እስከመጨረሻዉ ሽባ እንዲሆን ተደረገ መስከረም ሳልጽፍ በጣም ብዙ ጊዜ እንደሆነኝ አስባለሁ ይሄን ስከትብ የሚሰማኝ ስሜት ልክ ጓደኛዬን አግኝቼ እንደማዋራ ነዉ ከወራት በፊት ከዶክተር ታምርና ዶክተር ኪን ጋር ስንሰራ ነበር በያንዳንዱ የጥናትና ምርምር ዉስጥ ስሳተፍ ከማበረከተዉ አሰተዋጽአ ይለቅ የማገኘዉ ብዙ ነዉ በእርግጥ ከሁለቱ ዶከተሮች ጋር በአጋዥነት የምንሰራዉ አምስት ስንሆን የተለያዩ የስራ ድርሻዎች አሉን እኔ ከሁለቱ ጓደኞቼ ጋር ሆነን በዶከተሮቹ መሪት የተለያዩ እቃዎችን መስራትና ሙከራ ማድረግ እንደሚፈልጉት ማዘጋጀት ነዉ ሁለቱም ዶከተሮች በጠፈር ላይ ምርምር የሚያደርጉ ስሆን ዶከተር ታምር የጠፈር ማዕድናት ላይ ሳጠኑ ዶከተር ኪን ደግሞ ለኑሮ አመቺ የሆኑ ፕላኔቶች ላይ ጥናትና ምርምር ያደርጋሉ ጠፈር ላይ ጥግ የለህም ነገር ግን እራስህን አንድ ቦታ ላይ ወስነህ መንቀሳቀስ ይኖርብሀል የሰዉ ልጅ ፍላጎት ደግሞ የራሱ ልምድ ላይ መሰረት ያደረገ ነዉ በጠፈር ከኛ ፍላጎት በላይ ሊያሟሱ የሚችሱና ከዚህ በፊት አይተነዉ የማናዉቀዉን ልምምድ ሲያጎናጽፉን የሚችሉ ሁነቶችና ንጥረ ነገሮች በርካታ ናቸዉ አዕምሮህን በተሻለ ሁኔታ ያለምንም አሉታዊ ተጽኖ መጠቀም የሚያስችሉ ሰዉነታችንን የሚያደድሱና ሁሌም ጠንካና ጤነኛ ሆነን እንድንኖር የሚያደረጉ ምድርንም ትተን ወደ ሌላ አለም እንሂድ ካልን በጣም የሚያስፈልጉን መጠነ ቁሶች ከተለያዩ ነገሮች የሚከላከሉን በከፍተኛ ሁኔታ ሙቀትን ግፊትንና ቃጠሎን ሊቋቋሙ የሚችሉ መጠነ ቁሶች ከፍተኛ የሆነ እፍጋት ያላቸዉ ከሁኔታዎች ጋር እራሰቸዉን የሚቀይሩ ሀይልን ሙቀትንና ብርሀንን በቀላሱ ሊያመነጩ የሚችሉ በጣም ብዙ አይነት ናቸዉ ከዚህ በፊት የመጡ ሁለት ናሙናዎች አሉ አብዛኛዎቹ ዉህድ ናቸዉ እነሱን መለየትና ማጥናት ብዙ ጊዜ የወስዳል ሌሎች የተወሰኑ ንጹህ የሆኑ አሉ ብዙ የአገልግሎት ድርሻ ያላቸዉ በናሙና ደረጃና በብዛት ሲፈለግ የሚመጣበት ሁኔታ ይለያያል በተለይ በዚህ ሰዓት በብዛት አስፈልጎን ያለዉና ለማምጣት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራን ያለንበት ከታንታለም አስር አጥፍ የሚሆን እፍጋት ያለዉ ከኛዉ ጋላከሲ ለማምጣት የመጀመርያ ሙከራ አድርገን አንዳንድ የሚስተካከሉ ነገሮች ስላሉ እየሰራንበት ነዉ ትንሽ ያስቸገረን በጣም ተመሳሳይ የሆኑ ንጥረነገሮች በዚያ አካባቢ ላይ ስለሉ በቀጥታ እኛ የምንፈልገዉን ብቻ የሚለይልንን ማሻሻያ ካደረግን በኺላ አንሞከርና ከተሳካ ወደ ዋናዉ ማዕድኑ ላይ የሚሰሩ ወደ ጠፈር የሚላኩትን መስራት እንጀምራለን ቢያንስ ከስድስት ወር የበለጠ ጊዞ ሊወስድብን እንደሚችል ገምታለሁ ዶከተር ኪን ደግሞ ከኛ ጋላከሲ ዉጪ የሆኑትን ወደ አምስት የሚሆኑ ለሰዉ ልጆች አመቺ የሆኑ ፕላኔቶችን ያጠናል ሀመጸ የተባለዉ ፕላኔት ከመሬት ጋር በጣም ተመሳሳይነት ያለዉ ሲሆን ይቺ መሬት ከሶስት ሚሊየን አመት በፊት የነበራትን ገጽታ አሁን ላይ ይዞ ይገኛል ሕይወት እንደሚኖረዉ የተለያዩ ፍንጮች ያሉ ሲሆን በጣም ከመመሳሰሉሱ የተነሳ ሁለተኛዋ የሰዉ ልጆች መዳረሻ ሊሆን እንደምችል ይገመታል በዚሁ ጋላከሲ ሌሎች ሁለት ፕላኔቶችን የደረስንባቸዉ ሲሆን ከሚፈነጥቁት ብርሀን የተነሳ በዉበታቸዉ ገነት መንግስተሰማይ ሊያስብሉ የሚችሉ ናቸዉ ታህሳስ ባለፈዉ ሳምነት ሀሙስ እለት የሰይጣኒዝም ሀይማኖት መሪ ይመጣል ተብሎ በድብቅ የሚደረገዉ ሽርጉድ ይገርም ነበር ለምንድነዉ ኢትዮጵያ መምጣት ያስፈለገዉ ኢትዮጵያ ሁሌም እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ነዉ ምትዘረጋዉ ዉሀ እያሳሳቀ አይደል የሚወስደዉ በተለያየ መንገድ እንደቀልድ ሳናዉቀዉ የነሱ ደጋፊዎች ሆነናል የነሱን ልብስ አንለብሳለን ምግባቸዉን አንበላለን እነሱን እንከተላለን በተለይ ወጣቱ የዘመነ መስሎት እየተሳበ ነዉ በዚህ ከቀጠለ ነገ ወደማንወጣበት አዘቅት ዉስጥ እንገባለን ሰይጣኒዝም የድሮዉ እምነት ሴይጣንን አምላከ ብሎ የምያምን ሲሆን አሁን ደግሞ መልኩን ቀይሮ በተለይ ከ የሰይጣንዝም መማርያ መጽሐፍ ከታተም በኺላ የመጣዉ እምነት ለራስ ትልቅ ቦታ የሚሰጥና እራስን ከተለያዩ እስራቶች እነሱ እንደሚሉት እምነት ባህል ህግ መርሆች ነጻ ማዉጣትና እራስን በራስላይ መሾም ብሎም ወደ አምላከነት የማሳደግ መንገድ ነዉ ብለዉ ያምናሉ ሁለቱም መንገዶች አንድ ናቸዉ ሰይጣን በመጀመርያ ከከብሩ የተዋረደዉ እያወቀ አምላክከ ሳይሆን አምላክ ነኝ በማለቱ ከሱ በታች ያሉትን በማስገደዱ ነዉ እኛም ልቦናችን እያወቀ ወደዛ ጠጋ ማለታችን ችግር ያለበት ነገር መሆኑን ልንረዳ ይገባል በያንዳንዱ የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ላይ አሁን እያመጣ ያለዉ ተጽኖ ቀላል የሚባል አይደለም ሰይጣኒዝም ነጻነት ስል የራስን አንስሳዊ ባህሪን ማሳደግና ግልብተኛ ትዉልድ የመፍጠር አላማዉ ስለሆነ ነዉ ለዚህ ጉዳይ የሚሰሩ በያንዳንዱ ቦታዎች ላይ የምናገኛቸዉ ተጨባጭ መረጃዎች ጉድ የሚያስብሉ ያገር ያለህ በምትላቸዉ ሰዎች በሰበብ አስባቡ የሚከናወን ነዉ የጾታ ትምህርት ስርአቱ ላይ ቢኖር ጥሩ ነዉ በይበልጥ ተማሪዉ አራሱን እንዲያዉቅና ከአላስፈላጊ ነገሮች እንዲቆጠብ ያደርጋል ነገር ግን በዚህ ሰበብ ተሰግስገዉ ያሉ ትምህርቶችና ልምዶች ልጤኑ ይገባል ለተማሪዎች ከፍለጊዜ ተቀርጾላቸዉ እርስ በርስ ጾታ ሳይመርጡ የሚሳሳሙበትን ሰአት መመደብ አግባብ ነዉ ብዬ አላስብም ይሄን የምያደርጉ ትምህርት ቤቶችና መምህራን ሊታረሙ ይገባል ቤተሰብ ልጆቹን የተለየ ጸባይ ስያሳዩ መከታተልና ማስተካከል አስፈላጊ መሆኑን ሳልገልጽ አላልፍም በተለይ መካከለኛና ዝቅተኛ ትምህርት ደረጃ ላይ አደንዛዥ ንጥረነገርና ኮንዶም የሚያድሉ ትመህርት ቤቶች ሀይ ሊባሉ ይገባል ሚድያዎችም የመረጃ መረቦች የነዚህ ተግባር አቀንቃኞችና አራጋቢዎች ከሆኑ ሰነባብተዋል ልቅ የሆኑ የወሲብ ታሪኮችንና ዘፈኖችን በግዴለሽነት የሚያስተላልፉ እራቁትነትን የሚያበረታቱ ሰዉን በስሜት ፈረስ እያስጋለቡ የሚያሳድሩ ነዉረኞች ሆነዋል አሁንም በነዚህ ሚድያዎች የምጪጧጪሁ መልዕከቶች ወዳልተፈለጉ መስመሮች የሚያስኬዱ ናቸዉ በርግጥ ሰዉ ሲኖር ማጥፋቱ አይቀርም ይሄን ጥፋት ተጠቅሞ ለሌላ አላማ ማዋል ግን ትክከል አይደለም ወንዶች የሴቶች ደብዳቢዎቸ ደፋሪዎች አድርጎ በመወንጀል በተለይ አንዳንዱ ለመስማት የሚቀፉ ነገሮችን በተደጋጋሚ ጆሮ ላይ በማስጮህ ወንዱ አጠፋ አላጠፋም የወንጀለኝነት ስሜት እንድሰማዉ ማድረግ የወንጀለኝነት ስሜት የተሰማዉ አዕምሮ እራሱን እስር ቤት እንደገባ ይቆጥራል በእስር ቤት ያለ ሰዉ ደግሞ በራሱ ላይ እንኳን ምንም መብት የለዉም ይሄ በወንዶችና ሴቶች መሀል ያለዉን ግኑኝነት የመበጠስ ሴራ ነዉ ሴቶች ወንዶችን እንዳያምኑና መቃቃርን ለመትከል ደፋ ቀና እያሉ ነዉ ለዝህ ደግሞ ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማት ብዙ ናቸዉ ለሴቶች መብት የቆሙ መስለዉ ግን አላማቸዉ ሌላ ነዉ ይሄንኑ አላማቸዉን ለማጠናከር በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ላይ ለምሳሌ ኬኒያ የሴቶችን መንደርን የማስፋፋት ስራ ላይ ተጠምደዋል ይሄ ደግሞ ሰዎች ከተፈጥሮአቸዉ ዉጪ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል በመንደሮቹ ላይም የሚሰጡ ትምህርቶች ወደዚህ የሚያመሩ ናቸዉ በጣም የሚገርመኝ ምስኪኑን አርሶአደር አምስት አስር የወለደዉን ሴቱንም ወንዱንም በጎራ ሰብስበዉ ስለወሲብ አደራረግ የሚያስተምሩና ግለወሲብን የሚያበረታቱ የባዕድ ተቋማት እየሄዱ ያሉበትን መንገድ ልንከታተላቸዉ ይገባል ሲሆን አርሶ አደሩ የሚያስፈልገዉን የእርሻ ትምርት ሊሰጡት ሲገባ እርሻዉን ትቶ ሌላ ነገር ሲያጠና ማስዋሉ ተገቢ አይደለም የሰይጣኒዝም እምነት ተከታዮች አላማ ይዘዉ አቅድ አዉጥተዉ ነዉ እየተንቀሳቀሱ ያሉት አሁን ላይ ከዉጪ በተለያዩ ምከንያቶች በተለይ ደግሞ ለድጋፍ የሚገቡ ተቋማት ዋነኛ አጀንዳቸዉ እራሱ ይሄ እምነት ነዉ ይሄንን ደግሞ የሚያስፈጽሙት በሚከተሉት መንገዶች ነዉ አንደኛዉ መንገዳቸዉ አሁን ላይ ያለንን እምነት የሚያጣጥሉ የተለያዩ ትምህርቶችን በፕሮጀከት ደረጃ ተቀርጸዉ ተፈጻሚ አንዲሆኑ ይደረጋል እኛ ይሆናል ብለን በማናስበዉ መንገድ በጊዜ ሂደት ሀሳባቸዉን እያሰረጹና ማንነታችንን እየተዉን እንድንመጣ ያደርጉናል ሁለተኛዉ የሚጠቀሙት መንገድ ማህበረሰቡ የኖረበትን ባህልና እሴት ማጥፋትና ከዝያ የራሳቸዉን ባህል ነጻነት በሚሉት ካባ ደርበዉ ያለብሱናል በመጨረሻም ሀፍረት የማይሰማዉ የራሱን ስሜት ብቻ ተከትሎ የሚሄድ ትዉልድ ይፈጥራሉ ሶስተኛዉ እራስ ላይ ብቻ ያተኮረ አስተሳሰብ መፍጠር ነዉ በዚህ አለም ላይ ከራሱ ዉጪ ስለማንም እንደማያገባዉ የራስ ወዳድነት ስሜት ያለበት እኔ ብቻ የሚል በመጨረሻ እራሱን አምላከ አድርጎ የሚያስቀምጥ ትዉልድ መፍጠር ነዉ አላማቸዉ በተለይ ደግሞ ማህበረሰቡ ሰዉ ላይ ያተኮረ እምነት ቢተዉ መልካመም ነዉ ሰዎችን ዛሬ የተናገሩትን ሰምተህ አላማቸዉን ማወቅ አትችልም በቴለቭዢን መሰኮት ስለምትፈልገዉ ሀይማኖት ስላወራ መከተሉ አስፈላጊ ነዉ ብዬ አላምንም ይሄ መሪዬ ነዉ ያልከዉ አንዴ አዕምሮህን ከተቆጣጠረ በኺላ ወዳዘጋጀልህ ድግስ ይመራሀል በርግጥ የሰይጣኒዝሙ መሪ የምመጣበት ሁለት ትላልቅ አላማዎች እንዳሉት አዉቀናል የመጀመርያዉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሴሎች የአፍሪካ ሀገራትን የሚያሰባስብ ትልቅ ወጥ የሆነ ሕብረት ለመፍጠርና የሕብረቱን መሪና ሹመኞች ለማጽደቅ እና ይሄን ሕብረት የሚቀላቀሉትን ትላልቅ መሪዎችን ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎችን የቃል ማሰርያ ስርአት ለማስፈጸም ነዉ ጊዜዉም የአፍሪካ ሕብረት የአመታዊ ስብሰባ የሚደረግበት ነበርና ገና የአዲስ አበባን ምድር ሲረግጥ ዝናብ እየጣለ ነበር በተለያዩ ሹማምንቶች የሀገር መሪዎች አቀባበል ተደረገለት ሙሉ በሙሉ ጥቁር የለበሰ ሲሆን በስተግራ ኪስ በኩል በትንሹ በቀይ ቀለም የተጻፍ ካሙዌ የሚል ጽሁፍ አለ ይሄ ቃል ምናልባት ነገ ሊቀየር ይችላል ብዙን ጊዜ የመግቢያ ቃላቸዉን በዚህ አይነት መልኩ ይለጥፋሉ አንዳንዴ መሪዉ በሚያደርገዉ ኮፍያ አናት ላይ በቀይ ቀለም ሆኖ በጥቁር ጨርቅ ላይ ዋናዉ ፕሮግራም ነገ ስለሆነ የሚከታተላቸዉ በቅርብ ከኛዉ ተቋም የወጣና በአመራር ደረጃ ያለ ሰዉ አለ የተለያዩ መረጃዎችን ያቅብለናል አርብ ጠዋት ከብዙ ዝግጅት በኺላ ወደ ቅርብ መዳረሻችን በግዩድ ነበር የሄድነዉ ተልዕኮዉ ላይ አራት ስንሆን ሁለታችን በቀጥታ በመርሀግብሩ ላይ የምንሳተፍ ስንሆን የቀሩት ሁለቱ በዉጪ ሆነዉ መረጃዎችን የምያጠናከሩና ሁኔታዎችን እያጠኑ የምያቀብሉን ናቸዉ መግብያ ላይ የማትታይ የሚገባዉን ሰዉ ማንነት የምትለየና ምታስቀምጥ መሳርያ አስቀምጠናል እሱን ያጠናከሩታል የቤቱን የተለያዩ መቆጣጠርያዎችን ጥሰዉ ገብተዉ እንደምፈልጉት ያደርጋሉ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ ለመረዳት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰራሪ ተቀምጧል ዉስጥ ያለዉን የዝግጅቱንና የኛንም ሁኔታ ለመከታተል ያመቻቸዋል በምያስፈልግበት ሁኔታ እኛንም ተከተዉ ይሰራሉ በመርሀግብሩ መሰረት መሰብሰብያ ሰአቱ ከሶስት እስከ አራት ሰአት ስለነበር ለአራት አምስት ደቂቃ አካባቢ ሲቀረዉ ቦታዉ ላይ ደረሰን ከደብረዘይት ወጣ ብላ ባህር አጠገብ ሰፋ ያለ ጊቢ ያላት የተንጣለለ የመኖርያ ቤት ስሆን ስንደርስ ጊቢዉ ጭር ብሏል ሰዉ አይደለም ወፍ ዝር ያለበት አይመስልም ጥቁር መኪናችንን አያሸከረከርን ለሁለት ገባን ዉጪ ካሉት ጋር ጆሮ ስር በተቀበረ ምንም በማይታወቅ ማዳመጫ ትዕዛዝና መረጃ እንቀበላለን የተለያዩ ሁነቶችን ለመቅዳት የሚረዱን መሳርያዎች ከፊትና ጀርባ ልብሳችን ጋር ተዋህደዉ የተሰሩ ናቸዉ የተለያዩ ሁኔታዎች ካጋጠሙን መልዕከት በቀላሉ የምናስተላልፍበት መንገድ አለን መኪናዉን ካቆምን በኺላ አንድ ሰዉ ወጣ አለና ወደኛ ቀርቦ ቁልፉን ተቀብሎን መኪናዉን ወደ ጓሮ ይዞት ሄደ ወደ በሩ አንድንሄድ አቅጣጫ እየጠቆመን ምንም አላልነዉም መኪናዉን ለማስቀመጥ ስለነበር ወድያዉ ከዋላችን እየሮጠ መጣና በሩን ከፈተልን የእንግዳ መቀበያ ከፍል ነበር አንዲት ሴት ወደ ማዶ ከጠረጴዛ ጀርበ ቁጭ ብላ አስከሪን ላይ የሚታዩትን የደህንነት ምስሎችን ትመለከታለች ሶስት ወደ ዉስጥ የምያስገቡ ሌሎች በሮች አሉ የግራዉ ቀጥታ መርሀግበሩን የሚታደም ሰዉ ብቻ ነዉ የምገባዉ ግዴታ በዚህ በር መግባት አለብን ቀጥታ ፊትለፊት ላይ የሚታየዉን በር ደግሞ እዛ ዉስጥ የሚያገለግሉና ትንሽ ያጠራጠራትን የምትልክከበት ነዉ በቀኝ በኩል ደግሞ ያለዉ መርሀግብሩን መሳተፍ የሌለባቸዉን ወደመጡበት የምትመልስበት በር ነዉ ወደሷ ሄድንና ቆምን ዞር ብላ እንኳን ለአፍታም አላየችንም ከኛ የሆነ ነገር እየጠበቀች እንደሆነ ገብቶናል ወድያዉ ካሙዌ አልናት ሚስጢራዊዉ የመግብያ ቃል ነበረች ወድያዉ ዞር ብላ ደስ በሚል ፈገግታ አናገረችን ለሁለታችንም ጭንብሉችን ሰጠችንና የግራዉን በር አሳየችን ጭንብላችንን አድርገን ወደ ዉስጥ ስንገባ ምንም ጭንብል ያላደረጉ ወንዶች ወደ ሰገነት መሩን ከዉጪ ያሉት ጓደኞቻችን አንድ ማየት ያለብን ነገር ስላለ አገናኙልን የአይናችን ብሌን ላይ የሚቀመጠወን መመልከቻ አነቃነዉ ወደ አምስት የሚሆኑ ሴቶች ህጻናት እድሜያቸዉ በግምት ከሰባት እስከ ዘጠኝ የሚሆኑ ነጫጭ ልብስ ለብሰዉ ተቀምጠዋል ፊታቸዉ ላይ የፍርሀትና የጭንቀት ምልከት ይታይባቸዋል እነዚህ ልጆች ከተለያየ አካባቢ ተታለዉና ተሰርቀዉ የሚመጡ ለአምልኮ መስዋእት ለመሆን ግዜአቸዉን የሚጠባበቁ ናቸዉ በየቦታዉ ቤተሰብ በጭንቀት የት ገቡ ብሎ ይማስናል እነሱ አዚህ የአሳት እራት ለመሆን ቀርበዋል እነዚህን ህጻናት የሚያመጡት በእዉነት ህሊና የጎደላቸዉ የሰይጣን ባርያ ናቸዉ አጠፋዉትና ወደ ሰገነቱ አመራን ገና መርሀግብሩ አልተጀመረም ነበር ሰገነቱ በሰዎች ጢም ብሏል ሴቶች ጥቁር ካባቸዉን ደርበዉ በዙርያዉ ቆመዋል ዋናዉ መሪ በጣም ለስለስ ባለና በተረጋጋ ድምጽ ፊት ለፊት ተቀምጦ እያወራ ነዉ ስለ ሰዎች አዕምሮን መቆጣጠር ነበር የሚያወራዉ ወደ ተዘጋጀልን ስፍራ እየተመራን ተቀመጥን ከጥቂት ቆይታ በኺላ የሚያስደምም ድምጽ ከመሰረት ወጣ ቀንድ የለበሱ ፊታቸዉ ደም የሚመስል አስር ወንዶች ዋንጫዎችን ይዘዉ እየጮሁ ወጡ ሁላችንም ከተቀመጥንበት ተነሳን የተወሰኑ ንባቦችንና አንዳንድ አንቅስቃሴዎችን ካደረጉ በኺላ አዲስ ሕብረቱን የምቀላቀሉ ሰዎች አንዳሉና የነሱ ሰአት አንደሆነ ተነገረን የተለያዩ ሰዎች ነበሩ የተለያዩ ሀገራት የመንግሰት አመራሮች የሀይማኖት መሪዎቸ በተለይ የራሳቸዉን የቴለቭዥን ጣብያ ያላቸዉ ከዘፋኞች እስከ ተዋናዮች ባለሀብቶችና ታዋቂ ሰዎች የሆኑ ናቸዉ ሁሉም ጣታቸዉን አድምተዉ በያንዳንዱ ዋንጫ ዉስጥ የደም ጠብታቸዉን አኖሩ ይሄ በአስሩም የሰይጣን ህጎች የመገዛታቸዉ ምልክት ነዉ ደሙን ከወር አበባ ደም ጋር ቀላቀሉትና አሰሩም ጽዋዉን የያዙት መሪዎች የተቀላቀለዉን ደም በአምስቱም ጣታቸዉ እየነከሩ የሰዎቹን ግንባር ቀቧቸዉ የወር አበባዉ የሰይጣን ልጅነታቸዉን ማግኘታቸዉን የምያረጋግጡበትና ከራሳቸዉ ደም ጋር መቀላቀሉ የአንድነታቸዉ ማህተም ነዉ ከጥቂት ደቂቃዎች በኺላ የአይን ጭንብል ብቻ ባደረጉ ሴቶች ተከቦ አንድ ሰዉ መጣ ሁለት ደግሞ ሌሎች ቀንድ ያጠለቁ በታላቅ ድምጽ እየጮሁ መጡና ሰዉየዉ ፊት ቆሙ የተለያዩ ቃላቶችን ይላሉ ከሌላ አለም የመጣ ቋንቋ ይመስላል ከፊት ለፈታቸዉ ያለዉን መጽሐፍ እያነበቡ ደም እያጠቀሱ ይረጩበታል ሁሉም ሰዉ በተመስጦ ቆሞ የምሆነዉን ይከታተላል በአፍሪካ የሰይጣንዝም እምነት መሪ ለመሆን እየተፈጸመለት ያለ ሲመት ነዉ በዚህ ሰአት አንድ ነገር ማድረግ እነዳለበን ተላለፈ ከዉጪ ያሉት ጓደኞቻችን ሁሉም በሮች በኛ ብቻ እንድከፈቱ ተቆጣጥረዉታል ወድያዉ የቤቱን አቅጣጫና ወዴት መሄድ እንዳለብን ላኩልን እኔ ከተነሳዉ ከአምስት ደቂቃ በኺላ ጓደኛዬ እንዲነሳ ተነጋግረን ሄድኩኝ እየሆነ ያለዉን ነገር መጸዳጃ ቤት ዉስጥ ሆፔ ካጣራዉ በኺ እሱም ወድያዉ መጣ ከዚህ በኺላ ማንም ከአዳራሹ መዉጣትና መግባት አይችልም የኛን አሻራ ብቻ በሩ እንዲቀበል ተደርጓል ልጆቹ ያሉበት ክፍል ስንደርስ አንዷ ልጅ የለችም ህጻናቶቹን ስንጠይቃቸዉ አሁን ይዘዋት እንደሄዱ ነገሩን ዉጪ ካሉት ጓደኞቻችን ጋር ተገናኝተን ልጅቷ ያለችበትን ቦታ በአስቸኳይ እንዲነግሩን ላከንባቸዉ የሚያሳዝነዉ አንዷ ልጅ እህቴን ወሰዱብኝ አያለች ታለቅሳለች ነጭ ልብስ ለበብሳ አንድ ሽማግሌ እየጎተታት ወደ መሰዉያዉ ቤት እየሄደ እንደሆነ ነግረዉን ቦታዉንም አስገቡልን ሕጻናቱን ጓደኛዬ ይዚቸዉ እንድሄድ ነግሬዉ የተላከልኝን አቅጣጫዉን ተከትዬ መሮጥ ጀመርኩ የመሰዉያዉን በር ለመከፈት ሲታገል ደረስኩበት ልጅቷ አይኗ መንታ መንታ ያነባል ተጠግቼ በሰላም አናገርኩተና አንገቱን ሳያስበዉ ቆለፍኩለት ልጅቷን ይዢ ወደ መዉጫዉ አመራሁ ጓደኛዬ መኪናዉ ዉስጥ ህጻናቶቹን አስገብቷቸዉ እየጠበቀኝ ነበር መኪናዉ ዉስጥ ከእህቷ ጋር አስቀመጥኳት በስስት ተቃቀፉ ይቺ ታላቋ ነበረች አያጽናናዋቸዉ ይዘናቸዉ ወጣን ልጆቹን ለቤተሰቦቻቸዉ አፈላልገን በሁለት ቀን ዉስጥ ሁሉንም አስረከብን በጣም እያሳሰብናቸዉ ነዉ የሰጠናዉቤተሰብ በለቅሶ ነበር የተቀበለን ልጆቹ እንዴት ወዴት እንደሄዱባቸዉም አንዳንዶቹ አያዉም አንዲት ልጅ ግን ለሥራ ብለዉ ከከፍላገር ወደ አዲስ አበባ ዘመዶቻቸዉን ለምነዉ ካመጡ አንድ ወር ቢሆነዉ ነዉ ልጅቷ እንደምትለዉ ከሆን እዛዉ አስቀምጠዋት እንደወጡ ነዉ ምናልባት ተስለዉም ልሆን ይችላል ጥር በአሁን ሰአት ኢትዮጵያ እኮ የመሀይመሞች መተራመሻ ሆናለች አየህ መሀይም ስትሆን አዉቀትን ትፈራለህ መሀየምነትህ ላይ ትንጥዬ ስልጣን ደግሞ ከተጨመረች የምትፈራዉን ነገር ማየት ስለማትፈልግ ታጠፋዋለህ የሚያስብ ጭንቀቅላት ሳይሆን የተሰጠዉን ተቀብሎ ባቀኑበት መንገድ የሚሄድ የማይጠይቅ የሚነዳ ትዉልድ ትፈጥራለህ የዚህ ትዉልድ ባህረ ደግሞ ነዉርን እንደ ከብር ይቆጥራል እዉነተኛ ማንነቱን ዋጋ ያሳጣዋል ሀሳብ ሳይሆን ቡድን ዋጋ ያገኛል ለሀገራችን የምንመጣበት ሰአት እየደረሰ ነዉ ይህ ሕዝብ በራሱ ፍልስፍናና አስተሳሰብ ሕይወቱን እንዲመራ ፍላጎታችን ነዉ ማንም ተነስቶ ህዝቡ ላይ የሚጋልብበት ሰኣት ያበቃል ከመከራና መአት የምንጠብቀዉ ታላቅ አደራ ለዚህ ሕዝብ ስለተቀበልን ነዉ የሚገርመዉ የሚበጀዉንና የሚጠቅመዉን አያዉቅም በሰዉ ወርቅ ካላጌጥኩ ይላል ከብር የሚመጣዉ ወደራስ ከመመለስ ነዉ ማንነትን በማግኘት ነዉ ቁልፉን በአጃችን አንጠልጥለን በረሀ ለበረሀ እንሽሸከረከራለን ጥበብና ሀብት በማይገባዉ አጅ ብትወድቅ ምን እንደምትሆን ታዉቃለህ መጫወቻ ትሆናለች ያላግጡባታል ያለስፍራዋ ያስቀምጧታል ለዚህ ነዉ እኮ የተጋረደብን በጉያችን ስር ይዘነዉ አናየዉም ጥር ሺካሙ በስዋሂሊ ሰላምታ መጠየቄ ነዉ የስዋሂሊ ቋንቋ በአፍሪካ ብዙ ተናጋሪቆች ያሉት ሰሆን ለአላማችን መሳካት ቀልፍ ሚና ስለምጫወትልን ከፍተኛ ቦታ የምንሰጠዉ ቋንቋ ነዉ በአሁን ሰአት ሁላችንም መሰረታዊ ከምባል ሁኔታ ትንሸ ከፍ ያልን ተነጋሪዎች ነን ለአላማችን ስኬት ቋንቋ ከፍተኛ አስስዋጽኦ ያደርግልናል ሰዎችን በምትፈልገዉ መንገድ የምትወስዳቸዉ በተቻለ መጠን ተመሳሰይ እሳቤን በመፍጠር ሲሆን የአንድን ማህበረሰብ እምነት ባህልና የጋራ አመለካከታቸዉን ከቋንቋቸዉ በቀላሉ መገብየት ትችላለህ ሰዎችን በሂደትም አብዛኛወን ጊዜ ደግሞ የነሱን እሳቤዎችና ንግግሮች በማስተጋባት ትገዛቸዋለህ ምንም ይሁን ምን የምትቆምለት አላማ የብዙዎችን በር ማንኳኳት አለበት ይሄ አላማህ ብዙ ሰዉ ጋር ከደረሰ የመሪነት በትርህህ ከዝያ ቀን ጀምሮ ተረከበሀል ማለት ነዉ ሀዝብ እንደ እንፋሎት ነዉ እንፋሎት ዝም ብሎ ሲተን የአየሩን ሙቀት ከመጨመር ዉጪ ምንም ጥቅም አይሰጥም ነገር ግን ይሄን እንፋሎት ተቀብለን በተገቢዉ መንገድ እንድሄድ ካደረግን ትልቅ ሥራዎችን ልንሰራበት ያስችለናል ሕዝብም የሚሰማረበት አላማ ይፈልጋል ያን ደግም የሚሰራለት መሪዉ ነዉ የካቲት ባለፈዉ ረቡዕ ጥናት ላይ እያለን ነበር አንድ ምርመራ የመጣልን የስንዴ ኮንቴይነር የጫነ መርከብ አንድ ኮንቴይነር ግማሹን አይጦች ብቻ እንዳሉበት የደረሰን መርከቡ ከአንድ ቀን በኺላ ወደብ ላይ ስለሚደርስ ቀጥታ ወደ ምርመራ ገባን ከአንድ ወር በፊት ኮኒን በተባለ ድርጅት ከዚሁ ከኢትዮጵያ የታዘዘ አስር ቶን የሚጠጋ ስንዴ ነበር ይህን ያህል አነስ የለ መሆኑም ጥያቄን የሚያጭር ነበር አስር ቶን ብቻ ለምን ከሌላ ሀገር እንዲመጣ ተደረገ ከዝያ የሚያስጭነዉ የካሜሪላካይሮ ሜዲካል ኤንደ ሪሰርች ላቦራቶሪ ድርጅት ከግብፅ በመአርሴከ ትራንስፖርት አማካኝነት እንዲደርስ ልኳል የኮኒን ድርጅት ስንዴ ሲሆን የጠየቀዉ ለምንድነዉ ካሜሪላ እነዚህን አይጦች መላክ የፈለገዉ ሁለቱም የስንዴዉም የአይጡም ናሙና በጥንቃቄ መጥቶ ተወስደዉ እንዲመረመሩ አደረግን ስዴዉ ምንም ጉዳት የማያደርስ ለምግብነት ፍጆታ ብቻ መዋል ያለበት ነዉ የመጣዉን አይጥ ሌሎች ለመመርመርያነት ከሚዉሱ አምስት አይጦች ጋር ነበር የሳደርነዉ በሀያ አራት ሰአት ዉስጥ አራት የኛ አይጦች ሞተዋለ አንዱ ደግሞ ሰዉነቱ አባብጦ አፍንጫዉ አካባቢ ደም ይታያል ከመጣዉ አይጥ የደም ናሙና ተወስዶ ሲመረመር ዚበቭ የተባለ ቫይረስ ተገኘበት በዚህ አይነት ሁሉም አይጦች የዣይረሱ ተሸካሚዎች ናቸዉ ማለት ነዉ ይሄ ቫይረስ በጣም በቀላሉ በትንፋሽ ከሰዉ ወደ ሰዉ የሚተላለፍና አደገኛ ሲሆን አንድ ሰዉ በሱ ከተያዘ በሰአታት ዉስጥ የማስታወክ የሰዉነት ሙቀቱ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ደም ከአፍና አፍንጫዉ መፍሰስ ምልክቶችን ያሳያል በቀናት ዉስጥ ደግሞ ይገድላል እዚህ ጋር አንድ ነገር እርግጠኛ የሆነዉ እዚህ አንዲመጣ የተፈለገዉ የአይጦቹ ኮንቴነር ሲሆን ስንዴዉ ደግሞ ማጀብያ ነዉ ኮኒን የተባለዉን ድርጅት ለማጣራት ወደ ስራ ገባን የተለያዩ መረጃዎችን የዋና ቅርንጫፉን ጨምሮ አገኘነዉ የዋናዉን ጽህፈት ቤት መረጃዎን እንድትልከልን ሰራሪ አዘጋጅተን ወደ ዋናዉ የመረጃ ቋታቸዉ ላከናት ከሁለት ሰአት በኺላ የምንፈልጋቸዉ መረጃዎች በተለይ ከካሜሪላ ጋር የተላላኩትን መልእከት መላክ ጀመረ ኮኒን የተባለዉ ድርጅት በሁለት ወንደማማቾች ጥምረት የተመሰረተ ሲሆን የተለያዩ ምርቶችን ከዉጪ ወደ ሀገር ዉስጥ የሚያስገባ የምያከፋፍል ተቋም ነዉ ይሄ ኮንቴነር ደግሞ በካሜሪላ ጥሪ አቅራቢነት በከፍተኛ ጥቅም የኮኒን ድርጅት ጥሪዉን እንዲያቀርብ ተደርጎ የተሰራ ሴራ ነዉ ይሄ ድርጅቱን ብቻ ሳይሆን የምስርንም መንግስት ጥያቄ ዉስጥ የምከት ነዉ ወደ ካይሮ ባደረግነዉ የተወሰኑ ምርመራዎች ያገኘነዉ መረጃ ይሄ ተልኮ ስልሳ ሰባት አርኮ የሚባል ስር የተካተተ ሲሆን የምስር መንግስት ወደ ኢትዮጵያ እንዲላከ ያደረገበት መሆኑን ደርሰንበታል እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች የምያመለከቱት እንደዚህ አይነት ሌሎች ተልከዎች በሌላ መንገድ ሊኖሩ እንደሚቸሉ ሲሆን ሁሌም ንቁ ሆነን መከታተል አንዳለብን የሚያስገነዝቡ ናቸዉ የኮኒን ድርጅት የሚያስገባቸዉ እቃዎች ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ አለባቸዉ በፍቅረ ነዋይ ተታሎ ሀገር ላይ እንደዚህ አይነት ደባ የሚሰራ ተቋም ትከከለኛ ምርት ያስገባል ብዬ አላምንም አላማዉ ህዝብን ማገልገል ሳይሆን ህዝብ ላይ መነገድ ስለሆነ ገንዘብ ያስገኝለት እንጂ የሚያስገባዉ እቃ ስለሚያመጣዉ ጉዳት ማሰብ አይፈልግም ይሄ ደግሞ ፈቃዱን በሚሰጠዉ አካል መጤን አለበት የሚገባዉ ኮንቴነር የሚያመጣዉን ችግር ከተለያዩ አካላት ጋር ሆነን ይመለከታቸዋል የሚባሉ የምንግስት ተቋማትንና ግለሰቦችን ለማናገርና ለማስወገድ ፈለግን በጣም የገረመን ማንም ከቁብ የቆጠረ አልነበረም ሁሉም ምን አገባችሁ በሚል አስተያየት ነበር የሚየሰተናግዱን አንድ ሰዉ ይሄ ነገር ያገባኛል አንዴት እናድርግ የሚል አላየንም ሙሉ ኮንቴነር አይጥ ተጭኖ ስንዴ ነዉ ብለዉ የሚያሳልፉት አካላትስ እየተነገራቸዉ ምንም ሳያዩ ማሳለፋቸዉ ትልቅ የሞራል ድቀት ነዉ ለካ በልዩ ትዕዛዝ አቃዉ ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከላይ ጭምር ግፊት እየተደረገ ነበር እንደ ሌላዉ ኮንተይነር አንድ ሁለት ቀን ወደብ ላይ ይቆያል ብለን ያሰብነዉ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እየገባ እንደሆነ መረጃዉ ደረሰን አመራሮቻችን ግን ምን ነካቸዉ ማስተዋል የሚባል ነገር ጠፋ ሕዝብ ቤት ንብረቱን ህይወቱንም ጭምር አምኖ ሠጥቷቸዉ በተራ ነገረ ተደልለዉ ለሆዳቸዉ አድረዉ ሕዝቡን ለማጥፋት ቆርጠዉ የተነሱ ይመስላሉ ችግር ይፈጥራል ብለህ የምትነግረዉን ዋጋ አይሰጡትም ችግሩ እስኪፈጠርና ሕዝቡ ላይ አደጋ እስኪያደርስ ይጠብቃሉ ያኔ ዋና አስተዛዛኝና ተቆርቋሪ ሆኖ መቅረብ ነዉ ስራቸዉ አስመሳይ ይሄ አይደለም የመሪነት ተግባት ማዘኑንና ማልቀሱን ለህዝቡ ተዉለት ችግር እንዳይፈጠር ማድረግ ስትችሉ አዛኝ ቅቤ አንጓች ለናንተማ የልባችሁ እንደደረሰ ነዉ ምንቆጥረዉ ወድያዉ እርምጃ መዉሰድ ነበረብንና ኮንቴነሩን በበረሀ ዉስጥ ሰላሳ ሜትረ ጉድጓድ ቆፍረን ቀበርነዉ ይቀጥላል።