Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ጩ ሄጋ ህጋ ሠጋ ቴፍቲቴቴቲቴቲቴቲቱቴቲቴቲቴቱቴቲቴቲቴቴዬሩፋቱ ጭ ወይቤሎሉሙ ሑሩ መሠረተ ዜማ ብርሃናተ ዓለም ደም ወማይ ጊዮርጊስ ኃያል ኮከብ ብሩህ ገብረመንፈስ ቅዱስ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ጊዮርጊስ በዚያች ቀን ለምለም የነበረው በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተውጠው ጌታ መወለዱን የምሥራች ሰምተው እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ ትር ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና ይገባዋል በምድር እርቅ ተጀመረለሰው ግዕዛነነፃነቱ ሊሰጠው እንዲሆነን ቤዛለዓለሙ ሁሉ ለበሰ የማርያምን ሥጋ በጐል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ ቤዛ ከኣሉ ዓለም ዮም ተወልደ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ የዓለም መድኃኒት ትንቢት ተናገሩ ነቢያቱ በሙሉ አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ አዝ ሰብአሰገል መጡ እጅ መንሻ ይዘው ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው አዝ ሕፃናት እንሂድ ከልደቱ ቤት ውኃ ሆኗልና ማርና ወተት አዝ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ምንተንብሉ ናስተማስሉ ለመድኃኒነ አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራድዮን ትርጉምከእመቤታችን የተወለደውን ምን ብለን እንጠራዋለን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በምን እንመስለዋለን በዱር አንበሳ ነው ወይስ ከራድዮን በሚባል ወፍ ነው።
ጩ ሄጋ ህጋ ሠጋ ቴፍቲቴቴቲቴቲቴቲቱቴቲቴቲቴቱቴቲቴቲቴቴዬሩፋቱ ጭ ወይቤሎሉሙ ሑሩ መሠረተ ዜማ ብርሃናተ ዓለም ደም ወማይ ጊዮርጊስ ኃያል ኮከብ ብሩህ ሂዩቨ ቴቱቲውዬሑ ርካ ገጽ አምላኬ ሆይ የቅዱሳን አምላእክ መንገድህን አሳየኝ አባታችን ሆይ በብዙ አህጉር ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ጴና አልባሲ ጻድቃንሰ ኢሞ ጻድቃን ቡሩካን ኮከብ ብሩህ ገብረመንፈስ ቅዱስ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ጊዮርጊስ በዚያች ቀን እንደ አናንያ መዝሙረ ንሰሐ የትይሆን መግቢያዬ አልተወኝም ጌታ በረቀቀው ፍቅርህ አቤቱ አንተን እጠራለሁ አቤቱ ፈጣሪያችን ጊዜዬ እስኪደርስ ደካማው ልጅህን አቤቱ በመንግሥትህ አስበ ጌታ ያለው ንሰሐ እንግባ ምሕረትህ የበዛ ኑ እንቅረብ አንድ ጊዜ የአግዚአብሔር ሆኛለሁ አይደለም ምድራዉዊ ወደ ሕይወት መንገድ ቸሩ መድኃኔዓለም ወዳንተ እሰግዳለሁ ላይቀር መሞት መመኪያዬ አንተ ነህ አለኝታችን ዴማስ ሆይ ተመለ ልቤ አቤት በል እንጅ ማረኝ ምሕረትን እንለምን ዓለምን ዞሬ በሞት ጥላ ወድቀን አታውኪኝ ነፍሴ እንማልድሃለን እንደ በደሌ እንደቸርነትህ እያለፈ ነው ዘመኔ አባታችን ሆይ የሰው ልጅ ሁልጊዜ የሰው ልጆች ሁላችን እንማ የአዋጅ ነጋሪ ቃል ቅዱሳን በሙሉ ምግባርም አልሠራሁ በእንተ ጾም ንጹም ጸጾመ«»»» ፍቅርና ሰላምን ማርያም በስምሽ ቲጸ ኒጸ ኒል ሂል ሂጸ ኒል ሂል ሂል ኒጸ ል ሠ ዕ ዕ ዕ ዕ ዕ ሪ ሪዕሪመመጩርፎጩ ፎጩ ጩ ፎጩ ህ ህ ፅቁውውውውውውውሠሠ ር ር ከ መዝሇመፈረ ቃፖረ ተናገሩ ተናገሩ ድንቅ ሥራውንም መስክሩ ተአምሩን ለዓለም ንገሩ ድንቅ ሥራውን መስክሩ ልዑል አግዚአብሔር ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይገባሃል ለዚች ዕለት ለዚች ሰዓት በሰላም በጤና አደረስከን እስመ አልብነ ረዳኢ እስመ አልብነ ረዳኢ በጊዜ ምንዳቤ ወኃዘን እስመ ዘእንበሌከ ባዕደ ኢነአምር ትርጉም በችግርና በሐዘን ጊዜ የሚረዳን የለም እኛ ከአንተ በቀር ሌላ አናውቅምና ፉ ረድቶኛል እና እግዚአብሔር ይመስገን በወጀብ በዐውሎ ውስጥ በመከራዬ ቀን ረድቶኛልና እግዚአብሔር ይመስገን አድኖኛልና እግዚአብሔር ይመስገን ስብሐት ለአምሳክነ ስብሐት ለአምላክነ ወመድኃኒነ ወአድኃንከ ኅሊናነ ፊ ኩሎ ዘፈቀደ ኩሎ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር በሰማይኒ ወበምድርኒ ወበባሕርኒወበኩሩሉ ቀላያት ትርጉምእግዚአብሐር በሰማይና በምድር በባሕርም በፈሳሾችም ሁሉ የወደደውን አደረገ ፖ ከክርስቶስ ፍቅር ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማነው መከራ ስቃይ ወይስ መራቆት ነው አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም በትጋት ተራምደን እንግባ በጠዋት በደሙ መሥርቶ ከሠራልን ቤት ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት የውኃ ግድግዳ የደም መሠረት የውኃ ግድግዳ የደም መሠረት ይኸው እዚህ አለ የአማኑኤል ቤት ዶ ኖላዊ ትጉህ ኖላዊ ትጉኅ ዘኢትነውም ማኅበረነ ዕቀብ በሠላም የማታንቀላፋ ተጉሀ እረኝችን ጠብቅልን በሰላም ማኅበራችንን ኦ አባ ቅዱስ ዕቀቦሙ ኦ አባ ቅዱስ ዕቀቦሙ በስምከ ወበኃይልከ ዕቀቦሙ ከመይኩኑ አሐደብነ ከማነ ከመይኩኑ ትርጉም ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው ዐ ነአምን በአብ ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ በወልድ ወነአምን ነአምን በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን በአብ እንምናለን በወልድ እናምናለን በመንፈስቅዱስ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማን ነው አምላኬ መመኪያዬ ነው መድኃኔዓለም አዳነን መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ ደስ ይበለን እልል በሉአዳነን በማይሻር ቃሉ አድርገህልኛልና አድርገህልኛልና በቸርነተህ አመሰግንሃለሁ እልል ለዓለመ ዓለም አማኑኤል እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ የችግር አረንቋ ፊቴ ተደቅኖ ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ ፈጽሞ አራቅህልኝ የልቤን ትካዜ አዝ አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ ካለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ አዝ ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ የምመልስልህ ባላገኝ ሥጦታ በቀንም በሌሊትም ሁሌ ለሚያበራ መንክር ለባሕርይህ ዕጹብ ለአንተ ሥራ አዝ አምላክ ሆይ ምስጋና ለአንተ ይገባሃል ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሰጥተሃል ድሃ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና ማሰሮዬ ሞልቷል ላይጎድል እንደገና ፈ ለዚህ ቀን ላበቃውት ለዚህ ቀን ላበቃውት ወንድማችንንእኅታችንን እናቅርብ ምስጋና ለፈጣሪያችን በሰላም ላመጣ በሰላም ላመጣ እንግ ችንን እናቅርብ ምስጋና ለፈጣሪያችን ምስጋና ይገባል ይገባል ለአብ ዓለምን ሁሉ ለያዘ ይገባል ለወልድ ዓለምን ሁሉ ለፈጠረ ጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስ በየዓመቱ ክረምትን ለሚከፍት ሥፖ አማን በአማን አማን በአማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም ትርጉም እውነት በእውነት የሥላሴ መንግሥት ዘለዓለማዊ ነው የኃያላን ኃያል የኃያላን ኃያል ልዑል እግዚአብሔር ተአምራትህ ብዙ በሰማይ በምድር ተአምራትህ ብዙ በሰማይ በምድር ፍቅር ሰሐቦ ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እምመንበሩ ወአብጽሖ እስከለሞት ትርጉም ፍቅር ኃያል ወልድን ከልዑል መንበሩ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው ሠ ንሴብሖ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሓ ዘተሰብሓ እናመስግነው እግዚአብሔርን ምስጉን ነው የተመሰገነ ጸጋ ነሳዕነ ጸጋ ነሳዕነ ወሕይወተ ረከብነ በኃይለ መስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ በኃይለ መስቀሉ ኪያከ እግዚኦ ነአኩት ወንሴብሓከ እግዚአብሔር ሰላም ለዝክረ ስምከ ሰላም ለዝክረ ስምከ ጥዑመ ዜና መድኃኔዓለም ጥዑመ ዜና መድኃኔዓለም መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል በለኒ መሃርኩከ በለኒ መሃርኩኪ በእንተ ያም ድንግል እስመ ሔር አልቦ እንበሌከ ቃል በቀራንዮ የተሰቀልክ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ ስለ ድንግል ማርያም ብለህ ይቅር አልኩህሽ በለኝ ያለ አንተ ይቅር ባይ የለምና የሰማይ ምስጋና የሰማይ ምስጋና ሃሌ ሉያ ያሬድ የሰማው የመላእክት ዜማ ቅዱስ እግዚአብሔር የማይሞት ሕያው ቅዱስ በኪሩቤል አድሮ የተቀደሰው ቅዱስ መንበሩ በእሳት የተከበበው ሚካኤል ገብርኤል ከፊቱ ቆመው ያመሰግኑታል በአንድ ቃል ሆነው ቅዱስ ብለው ገጽ በክንፈ ረድኤትህ እንደ ዓይን ብሌን አምላክ ሆይ ጠብቀኝ በክንፈ ረድኤትህ ከመዓትም ጋርደኝ ኃይል የእግዚአብሔር ነው ኃይል የእግዚአብሔር ነው ማዳን የእግዚአብሔር ጥበብ የእግዚአብሔር አንመካም በጉልበታችን እግዚአብሔር ነው የኛ ኃይላችን ዘሰማየ ገብረ ዘሰማየ ገብረ ሰማየ ገብረ ወምድረ ሣረረ አልቦ ዘይመስሎ ለአምሳክነ ሰማይን የዘረጋ መሬትን ያጸና ኃያል ጌታ ሕያው አምላክ ያለ እርሱ ማን አለና እናመስግን እናመስግን አምላካችንን እናመስግን ፈጣሪያችንን ለዚህ ያደረሰንን ጨለማውን ገፎ ብርሃንን ለሰጠን ምስጋና ለእርሱ ይሁን ለኃያሉ ንጉሣችን ዘመናትን በዘመናት ያፈራርቃል ስለሁሉም ሁሉን ያውቃል ሳንለምነው የወደድነውን ይሰጠናል ከፈቃዱም ይሰማናል ውዳሴውን አዘጋጁ ያለዕረፍት በአዲስ ቅኔ ተቀኙለት በአዲስ መዝሙር ዘምሩለት እንደ ወዳጁ እንደ ዳዊት ዝናማትን ይሰጠናል በጊዜያቱ ፍጥረቱንም ይመግባል በየዕለቱ ኅልፈት የለው በመንግሥቱ ውዳሴውን ስሙ ታላቅ ኃያል ንጉሥ የሚሉለት ቅዱስ መላእክቱ በሰማያት ምስጋናውን ያቀርባሉ ያለዕረፍት የተቤዣህ ፍጥረትህን ክብር ምስጋና ለአንተ ይሁን ውዳሴውን እንዘይብሉ እንዘይብሉ ይዜምሩ በልሳን ዘኢያረምም መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም ትርጉምበማያቋርጥ አንደበት እንዲህ እያሉ ያመሰግናሉ የሥላሴ መንግስት ዘላለማዊ ነው ኑ ተመልከቱልኝ ኑ ተመልከቱ የአምላኬን ቸርነት አንደበት የለኝም ሥራውን ለማውራት ሠላምና ፍቅር በልቤ ተሞልቷል በምን ቋንቋ ላውራ ቃላት አጥረውኛል ሰማይ ጉም ቢመስል ቀላያት ቢናጉ የጥፋት አጋንንት እጅጉን ቢተጉ እኔን የሚጠብቅ ኃይሉን አይሠውርም እረኛዬ ከእኔ ዘወትር አይርቅም አዝ ፍርኃት ከእኔ ራቅ ጨለማ ተወገድ በጌታዬ ትምክህት እንደልቤ ልሂድ የሞት አበጋዞች ተስፋችሁ ጨልሟል እግዚአብሔር ሊያድነኝ ከአጠገቤ ቆሟል አዝ ቅዱሳን በሙሉ ለእኔ ዘብ ቆመዋል ወደ እነርሱ ኅብረት ሊስቡኝ ጓጉተዋል ዘወትር ወደ እኔ ድንግል ትመጣለች በብርሃን እጆቿ ትባርከኛለች እሲይ እሰይ እሰይ አምላክ ከእኔ ጋር ነው እሰይ ያጣ ሰው ብመስል እሰይ ንብረት ባይኖረኝም እሰይ የአምላኬ ፍቅር እሰይ ትቶኝስ አያውቅም እሰይ አዝ በድህነት ስኖር እሰይ አካሌ ተራቁቶ እሰይ ደስ ብሎኝ እኖራለሁ እሰይ ኅሊናዬ ረክቶ እሰይ አምላክ ስለጠራኝ እሰይ ለታላቅ ደስታ እሰይ ከፊቴ አይለይም እሰይ ዘወትር ፈገግታ እሰይ ድንቢጦችን እንኳን እሰይ ያልተዋቸው ጌታ እሰይ ይመስገን ዘወትር እሰይ በእውነት ጠዋት ማታ እሰይ ሠርቼ በረከት እሰይ ዘወትር አላጣም እሰይ እግዚአብሔር ይመስገን እሰይ አላሳፈረኝም እሰይ ንሰሐ እንግባ ንሰሐ እንግባ ኃጢአት መሥራት ይቅር የአምላክ ባለሟሎች እንሁን በምግባር የአምላክ ባለሟሎች እንሁን ሰላምህን ስጣት ሃሌ ሃሌ ሃሌሉያ ሀባ ሰላምከ ለኢትዮጵያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሰላምህን ስጣት ለኢትዮጵያ ሀበነ እግዚኦ ሀበነ እግዚኦ ዓዕይንተ አእምሮ ወትረ ኪያከ ይርአያ ወአእዛንነሂ ቃለ ዘባህቲትከ ይስምዓ ንሴብሖ ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ ለምስጋና ቀሰቀስከኝ በእኩለ ሌሊት በተመስጦ ስለፍቅርህ ልጀምር ማኅሌት ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ ስመለከት ወደ ሰማይ በጨረቃ ብርሃን አስገረመኝ ከዋክብቱ ሲያወሩ ሥራህን ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ አእዋፉ በማለዳ መዝሙር ሲዘምሩ በቋንቋቸው የአንተን ክብር በምሥጢር ሲያወሩ ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ ከበሮ ሆይ ጸናጽል ሆይ ለምስጋና ተነስ በማለዳ ለጌታችን ምስጋና እናድርስ ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን በመንፈስ እንዘምር እልል እንበል በምስጋና ስለሁሉም ነገር ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ የዘመናት ጌታ የዕለት የዓመት የዘመናት ጌታ ለዚህ ላደረስከኝ ዘመኔን ሳትገታ አቀርብልሃለሁ የክብር ሰላምታ ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዩን አባታችንን ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን የሰው ልጆች እድሜ ጥንቱንም ሲጀመር ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር አንድ ቀን አይሞላም እንደ አንተ አቆጣጠር አዝ ስለዚህ አምላክ ሆይ ንዑድ ነው ክቡር ነው ወደአንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸው ሰው ደካማ ነውና ሰው እድሜ ከራበው አዝ እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ ምድርን በአበባ ሰማዩን በኮከብ እንዳሸበረቀ አስተውዬ ሳስብ አዝ ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ ደግሞም በጠቅላላው ዓለምን ብገ አዝ ወርኃ ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ ምድር በልምላሜ ስታጌጥ በአበባ እናምናለን ለአንተ ምስጋና እንዲገባ አዝ ገጽ ኢትዮሏያ ታበህ እደዊሃ ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሃ ኃበ እግዚአብሔር እንዘትብል አምላኪዬዩ ነጽረኒ ወአድኅነኒ ኃይለ ጸላኢ ወፀር በምሕረት ዓይን ተመልከተን ከጠላት ነይል አድነን እያለች ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ አግዚአብሔር ትዘረለች ለጌታዬ ለእግዚአብሔር ለጌታዬ ለእግዚአብሔር ስላደረገልኝ ምን እከፍለዋለሁ ተመስገን ነው እንጂ ሌላ ምን እላለሁ እናመስግን አማኑኤልን እናመስግን አማኑኤልን የሞተልንን ጌታ በሞቱ ሞትን ቫረልን እንዳንረታ አምላካችን ተመስገን ችን ተመስገን ለዛሬ ያደረስከን ን ተመስገን ለዚህ ቀን ያደረስከን በኃጢአት ስንማቅቅ በምሕረትህ ጠራኸን በዓለም ስንባዝን ነበር በይቅርታህ መራኸን አምላክ ሆይ ተመስገን ትእግስትህ ብዙ ነው አያልቅም ርኅራጌህ የምከፍልህ ምን ይሆን ብዙ ነው ውለታህ አምላክ ሆይ ተመስገን አዝ ከቶ የማትፈልግ ከሰው ልጆች ወረታ ቸር ፈጣሪ ነህና ሥራህ ድንቅ ነው ጌታ አምላክ ሆይ ተመስገን ይቅር ባይ አምላካችን ሆይ አንተን እናመልካለን ከመዓትህ ታግሰህ ሁሉንም ይቅር አልከን አምላክ ሆይ ተመስገን አዝ ኃጢአታችን ጨለማ ቢያደርገው ኑሮአችንን በአንተ ተጉናጽፈናል የማዳንን ብርሃን አምላክ ሆይ ተመስገን ስለአደረክልን ሁሉ ስለ ግሩም ሥራህ የራስህን እንስጥህ ተመስገን እንበልህ አዝ ያከበርዋ ለሰንበት ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት ወኩሉ ፍጥረት ዓሣት ወአናብርት እለ ውስተ ደይን ያዕረፉ ባቲ እስመባቲ አዕረፈ እምኩሉ ግብሩ ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት ጻድቃንም በገነት ፍጥረታት በሙሉ ዓሣዎችና አንበሪዎች በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ ቸርነት አድርዝህ እድሜ ለንሰሐ እንደ ሕዝቅያስ ሰጥተህ ጠማማውን ልቤን በቃልህ አቃንተህ አላውቀውም ብሎ ሲጠየቅ ያመፀው ዶሮ እስኪጮህ ድረስ ሦስት ጊዜ የካደው የጅረት ወንዝ ነው የሰጠኸው እንባ ጴጥሮስ ተፀፅቶ ንስሐ እንዲገባ አዝ ጽዋው እንዳይደርሰኝ የይሁዳ እድል ልጅህ ሆኖ ውሎ ማታ መኮብለል ጴጥሮስ እድለኛ አልቅሶ ተማረ በትዕቢቱ ይሁዳ እንደወጣ ቀረ አዝ ዘመኗን በሙሉ በዝሙት አቃጥላ ለንስሐ ጠራት ጌታ በገሊላ ታድሳ ተነሳች በእንባዋ ብዛት በእግሩ ሥር ተደፍታ ማርያም እንተእፍረት ምሥጋና ደመረ ምሥጋና ጀመረ ብሎ ሃሌ ሉያ ማኅሌታይ ያሬድ ዘኢትዮጳያ ምሥጋና ጀመረ ብሎ ሃሌ ሉያ ይበል ሃሌ ሉያ ጥዑመ ልሳን ያሬድ ዘኢትዮጵያ ብሉይን ከሐዲስ ሐዲስን ከብሉይ አስተባብሮ ይዞ ያሬድ ማኅሌታይ ምሥጢር ተገልጾለት ከምድር እስከ ሰማይ አዝ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ምሥጢር እያስማማ ምሥጋና ጀመረ በነዚህ ከተማ ለቅድስት ሥላሴ በሦስት ዓይነት ዜማ አዝ በገና ጸናፅል ሲመታ ከበሮ ዜማው ሲንቆረቆር በሰው ልጆች ጆሮ የያሬድ ዝማሬ ያድሳል አእምሮ አዝ ምእመናን እናቅርብ ለአምላክ ምሥጋና በእዝራ መሰንቆ በዳዊት በገና ዜማውን ከያሬድ ተምረናልና በእንተ ልደቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት የዓለም መድኃኒት የተወለደብሽ አንቺ ቤተልሔም የተቀደስሽ ነሽ የአማልክት አምላክ ንጉሠ ነገሥት ኃያላን በሙሉ የሚሰግዱለት በጨርቅ ተጠቅልሎ ተኛ በበረት አዝ የጥበብ ሰዎች በቅን ሀሳባቸው ወደአንቺ ተጓዙ ኮከብ ሲመራቸው አዝ ለተከታይ ትውልድ ምሳሌ ለመሆን ሰግደው ገበሩለት ወርቅ ዕጣን ከርቤን አዝ የሚያድለው ጌታ እውቀት ለሕጻናት የሚመሰገነው በአፈ መላእክት ከእንስሳት ጋራ አደረ በበረት አዝ ሥጋ ለብሶ ቢታይ ረቂቅ መለኮት በአንድ ላይ ዘመሩ ሰውና መላእክት የድንግል ልዕልና አሁን ተገለጠ የድንግል ልዕልና ከእርሷ ተወለደ ሰማያዊ መና አምላከ አማልክት ቀዳማዊ ቃል በአንቺ ላይ አደረ ማርያም ድንግል ከሰማይ ወደ ምድር አብ ቢመለከት ምንምአላገኘም እንደ አንቺ ንጽሕት መላእክት በሰማይ እኅታችን ይሉሻል በንጽሕ በድንጋሌ እነርሱን መስለሻል በኮከብ መፅኡ በኮከብ መፅዑ መፅዑ ሰብአ ሰገል ለአማኑኤል ይስግዱ ለአማኑኤል ትርጉምየጥበብ ሰዎች በኮከብ እየተመሩ መጡ ለአማኑኤል ይሰግዱ ዘንድ ሣር ቅጠሉ ሠርዶው ሣር ቅጠሉ ሠርዶው ሠንበሌጥ ቄጠማው በዚያች ወር በዚያች ቀን ለምለም የነበረው በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተውጠው ጌታ መወለዱን የምሥራች ሰምተው እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ የታደሉ እረኞች ያደሩ በትጋት ብርሃን ሆነላቸው በዕኩለ ሌሊት ጥሪ ተደርጎለት ከሰማይ ሠራዊት ለመመልከት በቃ የጌታውን ልደት አዝ እረኝነት ትንሽ የወራዳ ግብር ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር አምላክ የመረጠው መሆኑን እረኛ ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ አዝ የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ ጌታ ተወለደ የምሥራች በሉ ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉሥ ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ አዝ የሩቅ ምሥራቅ ሰዎች ሰብአ ሰገል ሰምተው ሊሰግዱለት መጡ በኮከብ ተመርተው ዕጣንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ እንደየሥርዓቱ እጅ መንሻን ሰጡ አዝ ስለተወለደ መድኅን የኛ ተስፋ በደል ተወገደ ኃጢአትም ጠፋ አዝ ገጽ ስብሐት ለእግዚአብሔር ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ትር ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና ይገባዋል በምድር እርቅ ተጀመረለሰው ግዕዛነነፃነቱ ሊሰጠው እንዲሆነን ቤዛ እምሰማያት ወረደ ወእም ማርያም ተወልደ ተወልደ ከመይኩን ቤዛለኩሉ ፃለም ወለብሰ ሥጋ ማርያም ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ እንዲሆነን ቤዛለዓለሙ ሁሉ ለበሰ የማርያምን ሥጋ በጐል ሰከበ በጐል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ ቤዛ ከኣሉ ዓለም ዮም ተወልደ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ የጥበብ ሰዎች መጡ ሰማይና ምድር የማይወስኑት ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ የጥበብ ሰዎች መጡሰምተውት በዜና እያበራላቸው ኮከብ እንደ ፋና ድንግል እመቤቴ ሰላምታ ይድረስሽ ለአምላክ ወገኖች መመኪያቸው የሆንሽ ካንቺ ተወለደ የዓለም መድኅን ኩነኔን አጥፍቶ ጽድቅን ሊያወርሰን አዝ ጌታችን ሲወለድ በቤተልሔም ሐዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት ወንዞች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት አዝ ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ የእሥራኤል ንጉሥ ወዴት አለ እያሉ እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየሥርዓቱ ዕጣኑን ለክህነት ወርቁን ለመንግሥቱ ከርቤውን ለሞቱ አዝ ይኸው ተወለደ ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት ትንቢት ተናገሩ ነቢያቱ በሙሉ አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ አዝ ሰብአሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ የእስራኤል ንጉሥ ተዋልዷል እያሉ አዝ ሰብአሰገል መጡ እጅ መንሻ ይዘው ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው አዝ ሕፃናት እንሂድ ከልደቱ ቤት ውኃ ሆኗልና ማርና ወተት አዝ ለዘተወልደ እምቅድስት ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ምንተንብሉ ናስተማስሉ ለመድኃኒነ አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራድዮን ትርጉምከእመቤታችን የተወለደውን ምን ብለን እንጠራዋለን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በምን እንመስለዋለን በዱር አንበሳ ነው ወይስ ከራድዮን በሚባል ወፍ ነው። በእንተ ጥምቀቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሖረ ኢየሱስ ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኅበ ዮርዳኖስ ፈለገዮርዳኖስ ከመያጥምቆ ኢየሱስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወረደ በዮርዳኖስ ወንዝ ለመጠመቅ ወረደ ወልድ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት ወልድ ክርስቶስ ከሰማያት ወደ ወንዞች ወረደ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኅደረማኅፀነ ድንግል ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ ሰማይ ወምድር በማይ ተጠመቀ ትርጉም ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ በእመቤታችን ማኅጸን አደረ በውሃ ተጠመቀ መጽዐ ቃል መጽዐ ቃል እም ደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር መጣ ቃል ከደመና እንዲህ የሚል የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው የዓለምን በደል የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ የሰማዮች ሰማይ የማይችለው ንጉሥ ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደፈረስ አዝ ባሕር ተጨነቅች ጠበባት መሬቱ ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ አዝ ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቅን ሲመሠርት መጣ በደመና ሰማያዊው አባት እየመሰከረ የልጁን ጌትነት አዝ እንደምናነበው በወንጌል ተጽፎ መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ በርግብ ምሳሌ ክንፉን አሰይፎ አዝ ባሕር ስትጨነቅ ተራራ ሲጨፍር ሰማዩ ሲከፈት ደመና ሲናገር ዓለም በዛሬው ቀን አየች ይህን ምሥጢር አዝ አማን በአማን አማን በአማን አማን በአማን መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ እውነት ነው በእውነት ድንቅ ነው የጌታ ጥምቀት እንዘ ሕፃን እንዘ ሕፃን ልህቀ በዮርዳኖስ ተጠምቀ በዮርዳኖስ ዮርዳኖስተጠምቀ በዮሐንስ ትርጉምሕፃን ሆኖ ጥቂት በጥቂቱ አደገ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ በእደ ዮሐንስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ ሰማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ ትርጉም ሰማያዊው የናዝሬቱ ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ ተጠምቀ ሰማያዊ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ተጠምቀ ሰማያዊ በዕደ መሬታዊ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በልደትህ አምላክ ሆይ ሕዝቦችህ ዳኑ በጥምቀትህ ኋፉ ያሄሐ ፖሪኖ ሆሣዕና እምርት ሆሣዕና እምርት እንተ አቡነ ዳዊት ቡርክት እንተ ትመፅዕ መንግሥት የታወቀች የድኅነት ቀን የምትመጣይቱ የአባታችን የዳዊት መንግሥት ቡርክት ናት ሰላምሽ ዛሬ ነው ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም ወደ አንቺ መጥቷልና አምሳክ ዘለዓለም ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በኢየሩሳሌም አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ አዝ ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት በኢየሩሳሌም አእሩግ ወሕፃናት አዝ ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙት መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት አዝ የኢየሱስን ሕማም ደናግል አይተው እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው ገጽ እም አፈ ደቂቅ እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐት በእንተ ፀላዒ ከመትንሥቶ ለፀሳዒ ወለገፋኢ ትርጉምከሕፃናት እንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ የጠላት ዲያብሎስ ምክሩን ታፈርስ ዘንድ ሆሣዕና በአርያም ሆግዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ቅድስት ሀገር ሆይ ኢየሩሳሌም ምስጋናሽ ብዙ ነው በመላው ዓለም አዝ በአህያ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ የገባው ኢየሱሰ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ነዉ አዝ ኃይልና ስልጣን በአንድ ላይ ስላለው ጠላቶችሽ ፈሩ ሕዝብሽም ደስ አለው አዝ በእንተ ስቅለቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተሃልና ስለእኔ ሞተሃልና ስለእኔ ምንም ሳይኖርብህ ጥፋት ተከሰህ ተወቅሰህ በሏላጦስ ፊት ኢየሱስ አምላከ ምሕረት ስብሐት ለከ የአንተ መንገላታት ሁል ጊዜ ያሳዝነኛል ሲወራ በመስቀል ላይ ሆነህ ያየኸው መከራ ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ስብሐት ለከ ከልዑል ቦታ ወርደህ ፈጣሬ ፍጡራን አምላክ በሰው ፊት ተዋርደህ ስለ ሰው የሞትክ በመስቀል ላይ ተጠማሁ እያልክ ስብሐት ለከ መሐሪ ጌታ አሁንም እንደቸርነትህ ብዛት የእኛን በደል ሁሉ ሳትመለከት አድነን ከዳግም ሞት ስብሐት ለከ የአብርሃም አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ የሐሰት ምስክር አቁመው ከሰሱት በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት ጴላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አሥርሃ ከሮማዊው መንግሥት እንዲኖር ተባብርሮ ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ እያየች በመስቀል ልጂ ሲንገላታ በብርሃን ዙፋን ላይ የቆሙት እግር በችንካር ላይ ሆነው ምንም አልሰለ የብርሃን አክሊልን ለሰማዕት ያደለ የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ ስለኛ ብሎ ስለኛ ብሎ ልጅሽ ተሰቅሎ ልብሽ በኅዘን ተወግቶ ቆስሎ ከመስቀሉ አውርደውት ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ደግፈውት ያለቀስሽው የዕንባሽ ብዛት ይጠብልን የእኛን ኃጢአት ሙታንን ያድን ዘንድ ሙታንን ያድን ዘንድ የሞትሞትን ሽሮሃ ወልደ አምሳክ ሄደ ወደ ኋላ ታሥሮ ግርማን ለኪሩቤል ያጐናጸፋቸው ዘውድን ለሱራፌል የሚያቀዳጃቸው ከለሜዳ ለብሶ ዋለ ከፊታቸው አዝ ቅዱሳን እጆቹ አዳምን የሠሩት ቅዱሳን እግሮቹ በገነት የዞሩት ተቸንክረው ዋሉ በጠንካራ ብረት አዝ ምን በበደለ ነው ምን ባደረገ ነው ወልድ እንደ ቀማኛ ሲገረፍ የዋለው አዝ አዳም በበደለ የግፍ ግፍ በሠራ ቸሩ ወልደ አምላክ ዋለ በመከራ አዝ ሁሉንም ታገሰ ሁሉን ቻለ ሆድህ ትልቁም ትንሹም ሲዘባበትብህ ሰቀሉ ምሰሌሁ ሰቀሉ ምስሌሁ ክልኤተ ፈያተበየማኑ ወበፀጋሙ ወበማፅከሉሙ ኢየሱስ ወበማዕከሎሉሙ ኢየሱስ ትርጉም ከርሱ ጋራ አንዱን በቀኙ አንዱን በግራው አድርገው ሁለትሽፍቶችን ሰቀሉ ኢየሱስንም በመሐል በጌቴ ሴማኒ በጌቴ ሴማኒ በአትክልቱ ቦታ ለእኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት ለእኛም ነበረብን የዘለዓለም ሞት መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ ይገርፉት ነበረ ሁሉም በየተራ ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ እያየች በመስቀል ልጂ ሲንገላታ በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው እንዲህ ሲል ጸለየ አባት ማራቸው በረቂቅ ሥልጣኑ ሁሉን የፈጠረ በሰዎች ተገርፎ ሞቶ ተቀበረ ፍቅሩን የገለጸው ተወልዶ በሥጋ ኢየሱስ ጌታ ነው አልፋና ዖሜጋ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን ሰቀሉህ ወይ የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት ንጹሕ ክርስቶስ ሆንክ ወንጀለኛ ብለህ ስለኛ መስቀል አሸክመው አሥረው ገረፉህ እያዳፉህ እጅና እግርህ በብረት ተመታ የዓለም ጌታ የእሾህ አክሊል ደፍተህ ጐንህም ተወጋ አልፋ ያዖሜጋ ግብዞች እንደራሳቸው መስሎአቸው ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጉዱ በመስቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል ሐሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው ይቅር ባይ በደላችንን ሁሉን ስታይ አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ መስክሪ ቀራንዮ መስክሪ ቀራንዮ ንገሪን ጉልጉታ ካሣ እንደሆነልን እንደ አዳነን ጌታ በአምላክነቱ ፈጥሮ ዓለማትን ሥጋን መዋሐዱን ሰዎችን ለማዳን ክብሩን ዝቅ አድርጎ በታላቅ ትኅትና ሞትን ሊያጠፋልን ያየውን ፈተና አዝ ለፍርድ ሲወስዱት ሊቀበል መከራ መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ አይሁድ በየተራ ሲገርፉት ሲያዳፉት እንደታገሳቸው በፍፁም ቸርነት አዝ ምንም ሳያጠፋ በደል ሳይኖርበት በመስቀል እንዲሞት ቅጣት ተፈርዶበት ወደ ኋላ ታሥሮ ተገርፎ ተመትቶ ያየውን መከራ የሾህ አክሊል ደፍቶ አዝ በሞቱ ሙታንን ከመቃብር ጠርቶ በእርሱ ውርደት ክብርን ለሰው ልጆች ሰጥቶ በሕይወት እንድንኖር ዳግም እንዳንሞት ትንሣኤን መስበኩን በከበረች ሰንበት አዝ ዘአልበስዎ ዘአልበስዎ አይሁድ ከለሜዳ ዘለይ እኸ ከለሜዳ ዘለይ ከለሜዳ ትርጉም አይሁድ ጌታችንን ቀይ ግምጃ አለበሱት እፎ ሰቀሉከ እፎ ሰቀሉከ ካህናተ ይሁዳ ወሌዊ መድኃኔዓለም ናዝራዊ መድኃኔዓለም ናዝራዊመድኃኔዓለም ናዝራዊ ትርጉም ናዝራዊ መድኃኔዓለም ሆይ የይሁደና የሌዊ ካህናት እንዴት ሰቀሉህ እስመ ለዓለም ምሕረቱ እስመ ለዓለም ምሕረቱ አያልቅም ብዙ ነው የአምጎክ ዛ አመስግኑት ጌታን ሁ በአንድነት መሐሪ ነውና ለሰው ልጆች ሕይወት አዝ የማይሞተው ሞቶ የተቀበረው ከገሃነም እሳት እኛን ሊያድን ነው አዝ ከማርያም የነሣው ያ ቅዱስ ሥጋው ቀራንዮ ሲውል የሚያሳዝን ነው አዝ በፈጠረው ፍጥረት እጅግ ተሰቃይቶ ትን አወጣ ከሲኦል ለይቶ አዝ ነቱ ሞተ ስለእኛ ሞተ ስለእኛ የነገሥታት ንጉሥ የኃያላን ዳኛ ሞተ ስለኛ ጐለጐታ እስኪደርስ ስቃይ ተቀበለ ሥጋው ተዳከመ በመከራ ዛለ በጅራፍ ተገርፎ ደም ነጠበ ገላው ሞተ ስለኛ ሚካኤል ዝም አለ ተገርሞ አስተዋለ ገብርኤል ሰይፉን ወደ ምድር ጣለ ከዋክብት ደንግጠው ረገፉ ዛሬ መላእክት አለቀሱ ቀረና ዝማሬ ሞተ ስለኛ ዑራኤል አምላኩን በመሰቀል ላይ አየ በብርሃን ጽዋ ደሙን ተቀበለ ዕንባው አላቆመም ጌታው ሲንገላታ ተገርሞ አስተዋለ በጥፊ ሲመታ ሞተ ስለኛ አዘነች እናቱ አዘነች እናቱም ጨነቃት እያየችው ልጂን በመስቀል ላይ ሰቅለውት እዩት ተመልከቱት የአምላክን ሥራ በመሰቀል ላይ ሆኖ ለዓለም ሲያበራ አይሁድ ወንበዴዎች ይዘው አሰቃዩት የሾህ አክሊል ሠርተው በላዩ ደፉበት አዝ የድንግልን ኃዘን ዕዕዋትም አይተው ያለቅሱ ጀመረ ከመሬት ረግፈው መች እ ብቻ ፀሐይም ጨለመች የጌታዬን እርቃን አላሳይም አለች አዝ የሰማይ ከዋክብት የአምላክን ሞት ሰምተው ወየውአሉ ከመሬት ተደፍተው ደማቋ ጨረቃ እርር ክስል አለች ይህንን ስትሰማ መልኳን አጠቆረች አዝ ምድርም አዝና ነበር በጣም ተቸግራ ሲገርፉት እያየች ጀርባውን በወይራ ወየው መጨከኑ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ጴላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ አዝ ማርና ወተቱን የሚመግብ ጌታ አጥቶ ተቸገረ የውኃ ጠብታ አዝ በእንተ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይለ ጽልመት ተሰደ ኃይለ ጽልመት ተሰደ በሰንበት ኃይለ ጽልመት ተሰደ ተስፋ ሕይወት ተሰርዐ በሰማያት ተስፋ ሕይወት ተሰርዐ ትንሣኤከ ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ ትንሣኤህን ለምናምን ለእኛ ብርሃንህን ላክልን ወደእኛ አማን በአማን አማን በአማን ተንሥአ እምነ ሙታን እውነት በእውነት ተነሣ ዛሬ ከሙታን እም እቶነ እሳት እም እቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ ብርሃናተ ዘይትአጸፍ ተንሥአ ለነ ከሚነደው እሳት ከነበልባሉ አወጣን ብርሃናትን ተጎናጽፎ ተነሣልን ተገርፎ ተሰቅሎ ተገርፎ ተሰቅሎ የሞተው አንበሳ ተገንዞ በጨርቅ ተቀብሮ እንደሬሳ በሞት እጅ ተይዞ አልቀረም ተነሳ እናምናለን ትንሣኤህን በሥልጣንህ መነሣትህን አርአያ ነውና ለሁላችን ሄሮድስ ፈልጎ ተቀብሮ እንዲቀር በመቃብሩ ዙሪያ ጭፍሮቹንም ቢያሰፍር ምድር አልቻለችም ትንሣኤን ልታስቀር አዝ ክርስቶስ ስትነሣ ከህቱም መቃብሩ ሴቶች ትንሣኤህን ደፍረው ተናገሩ እንሞታለን ብለው ማንንም ሳይፈሩ አዝ እንግዲህ አልፈራም ሞትና ኩነኔ አምላክ ከሞተልኝ ተሰቅሎ ስለእኔ ተደምስሶአልና የሞት ሥልጣኔ አዝ «ፉ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ ምድር ጸዳች ሐሴት አረገች በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች በእንተ ዕርገቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዐረገ በስብሐት ዐረገ በስብሐት ዐረገ በዕልልታ በስብሐት በዕልልታ ዐረገዝ በዕልልታ ሞትን ድል አድርጐ የሠራዊት ጌታ ዐረዝ በዕልልታ መዝሙረ ጳራቅሊጦስ አንትሙሰ ንበሩ አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከትለብሱ ኃይል እም አርያም እናንተ ግን ቆዩ በኢየሩሳሌም ሀገር እስከምታገኙ ኃይል ከሰማይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ መንፈስ ቅዱስ ወረደ ላዕለ ሐዋርያት ተመሲሎ በነደ እሳት ትርጉም መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳያ በሐዋርያት ላይ ወረደ በእንተ ምፅአቱ ለእግዚአነ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆይ ማረን እውነተኛው ንጉሥ ለፍርድ ሲመጣ ጻድቁን ሊያከብር ኃጥኡን ሊቀጣ መለከት ሲነፋ ነጉድጓድ ሲሰማ ክርስቶስ ሲገለጥ በሚያስደንቅ ግር አምላክ ሆይ ማረን ማረን አምላክ ይቅር በለን የነበረው ሁሉ ሲሆን እንዳልነበር ተነሥተው ሲቆሙ ሙታን ከመቃብር ፀሐይ ስትጨልም ሰማያትም ሲያልፉ ምድር ቀውጢ ስትሆን ቀላያት ሲጠፉ አዝ ፍጥረት ሲናድ ሲርድ ግርማው እያስፈራው የአዳም ዘር በሙሉ ሲቆም ከነሥራው ማነው የሚገኘው በጉ ምግባር ሠርቶ ቅዱሳንን መስሎ በሃይማኖት ጸንቶ አዝ በምድራዊ ሕይወት ትሩፋት የሠሩ ጻድቃን ሲደሰቱ ተግተው ሲዘምሩ ኃጥአን ሲጠፋቸው የሚሰወሩበት እኛስ ከየት ይሆን የምንገኝበት አዝ አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ ለብሰህ የማርያምን ሥጋ ባክኖ የነበረው የአዳም ልጅ ውጤቱ ነበር የሚያሰጋ በዚያ ዓመት በዚያች ወር በዚያች ቀን ድኅነትን ለሰው ልጅ ስትሰጥ የበዛ ነበር ትኅትናህ ትዕግሥትህ የማይለወጥ የሾህ አክሊል ደፍተው በራስህ ጉንህን ሲወጉህ በጦር አንተ ግን ለእነርሱ ከአባትህ ምሕረትን ትለምን ነበር ግን መቼ አወቁህ እነርሱ በኃጢአት ደንድኖ ልባቸው መድኃኒታቸውን ገረፉህ ሰቀሉህ አንተም ሞትክላቸው ዳግም ስትመጣ ለፍርድ ከዓለም ፍፃሜ በኋላ ሽረ እንዴት እድለኞች ናቸው በፊትህ የሚያገኙ ተድሳ በዚያች በደብረዘይት ቦታ ደስታና ለቅሶ ሲፈልቅ ከቶ ወዴት ይሆን እጣዬ ያንጊዜ የእኔ አወዳደቅ የፀፀት እሮሮ በፊትህ እንዳያቃጥለኝ እኔን እርዳኝ ፈጣሪዬ ከአሁኑ አድሰው የዛገው ልቤን ገጽ ፀንተን እንጠብቅ ከመላእክት ጋር ሲገለጥ በሰማይ ፀንተን እንጠብቀው ክብሩን ሁሉ እንድናይ በግርማ ሲመጣ በአስደንጋጭ ሁኔታ ወዮልሽ ነፍሴ ሆይ ወየው የዛን ለታ ሽኸ ምሥጋና ይድረስህ ሁልጊዜ ጠዋት ማታ ሃሌ ሃሌሉያ የሠራዊት ጌታ ሰማይና ምድር ከፊቱ ሲሸሹ መግቢያ አጥቶ ይጮሃል ትልቁም ትንሹ ጻድቃን ሲደሰቱ የኃጥአን ፋንታ ሆኖ ጠበቃቸው ለቅሶና ዋይታ እዝ ስለማይታወቅ አምላክ አመጣጥህ በሃይማኖት አፅናን ተግተን እንጠብቅህ ጠላት እንዳይዝን በእርሱ እንዳንረታ እግዚአብሔር አድነን ሁንልን መከታ አዝ አንድ ቀን አለ አንድ ቀን አለ የሚያስፈራ ለጻድቃን የሚያበራ ጌታ በዚያች ቀን ይመጣል በግርማ ይገለጣል የፍርድ አዋጅ ይታወጃል ነፍስ ሁሉ ይጨነቃል ኃጥአን ያለቅሳሉ በግራህ ይቆማሉ ቅዱስ ቃሉን ሰምተው ያመኑ የፀኑ በኪዳኑ ተከብረው በቀኙ ይቆማሉ ከኃዘን ይሰወራሉ መሐሪ ጌታ ፈጣሪያችን ይድረስህ ልመናችን በዚያች ግሩም ቀን እባክህ አቁመን በቀኝህ አቤት የዚያን ጊዜ አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ ትንሹም ትልቁም መድረሻውን ሲያጣ ከምሥራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ ነፋሳት ሲላኩ መዓትን ለማዝነብ ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሐዱ የት ይሆን መድረሻው የት ይሆን መንገዱ አዝ ጻድቃን በቀኝ በኩል ኃጥአን በግራ ሲነፋ መለከት ሲደለቅ እንዚራ ምድር ቀውጢ ስትሆን አፅም ሲሰበሰብ ፍጥረት ይይዘዋል ሰው ለፍርድ ሲቀርብ አዝ ጩኸት ሲበረታ የማይጠቅም ልቅሶ እንደ ቁራ ጠቁሮ ፅልመትን ተላብሶ ገነትን ሲያገኙ ጻድቃን በሥራቸው ኃጥአን ወደሲኦል ተፈረደባቸው አዝ መዝሙር ዘዘወትር ዘድንግል ማርያም ፀሐይኑ ንብለከ ፀሐይኑ ንብለከ ወልደ ማርያም ንብለከ በመኑ በአምሳለ መኑ ናስተማስለከ ፀሐይኑ ንብለኪ ወላዲተ ቃል ንብለኪ በመኑ በአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ እንበለ ምግባር እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይፀድቅ አነ ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ ትርጉም ምንም እንኳ ሥራዬ ለዚያ የሚያበቃ ባይሆን መንግሥተ ሰማያትን የምወርሳት ካልሆነ እመቤቴ ሆይ ቃል ኪዳንሽ ለከንቱ ነውን ኦ ርኅርኅተ ኅሊና ኦ ርኅርኅተ ኅሊና አፍቅሮተ ሰብእ ልማዳ ለእለጌሰሙ ትመስልእንግዳ ትርጉም ሰውን ማፍቀር ልማዷ የሆነ እመቤትችን በየጊዜው ወትር አዲስ ትምስል ነበር ለምኝልን ማርያም ለምኝልን ማርያም ለምኝልን የንፁሐን አክሊል የቅዱሳን ብርሃን ነይ ነይ ነይ ነይ ማርያም ወላዲተ አምላክ የፃድቃን እመቤት የመላእክት እኅትኮ ሁላችሁ እመኗት ከልብ አማላጅ ናትና በእውነት እናመስግናት እናወድሳት አማላጅ ኪዳነ ፖቷረት ጐሟ እንተ በምድር እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን ድንግል ሐረገ ወይን ትርጉምእመቤታችን ሥሯ በምድር ቅርንጫፏ በሰማይ የሆነ የወይን ሐረግ ናት በምድራዊ ሕይወት በምድራዊ ሕይወት በፈተና ቦታ ማርያም ትጠብቀን እጆቿን ታ ድንግል ትጠብቀን እጆቿን ዘርግታ ኪዳነ ምሕረት ኪዳነ ምሕረት እመቤት ለዓለም ሁሉ መድኃኒት ቅድስተ ቅዱሳን ብፅዕት አንቺ ነሽ ለአምላካችን እናት ጌታችን ፈጠረሽ ልዩ አድርጐ በሚያስደንቅ ምሥጢሩ ለተዋሕዶ ለልዑል ማደሪያነት የተመረጥሽ ያለ ሕማም ወለድሽው ድንግል ሆነሽ እናትነት ድንግልና አስተባብረሽ ይዘሻልና ድንግልም እናትም እመብርሃን ንጽሕተ ንጹሐን እኛን አማልጅን ሰላም ለኪ ማርያም ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምሳክ ወልድኪ ይጹውአኪ ውስተ ሕይወት ኑ ወመንግሥተ ክብር ትርጉም የአምላክ እናት ማርያም ሰላም እልሻለሁ ወደ ሕይወትና ክብር ወዳለው ጌትነት ልጅሽ ይጠራሻል በዝናመ ንጽሕከ በዝናመ ንጽሕኪ ሐረገ ወይን ጸየ ወሮማን ወሮማን ወሮማን ሐዋዘ ፈረየ ለአዳም ተስፋ የሆንሽው ማርያም እመቤቴ አማልጂኝ ቶሎ ብለሽ ሳልጠፋብሽ ልጅሽ የዳዊት መሰንቆ ነሽ የኢያሱም ሐውልት በምን ልመስልሽ ወደርም የለሽ እመቤቴ ጥላዬ ሁኝልኝ ከለላዩ ያለ አንቺ ማን አለኝ አለሁሽህ በይኝ አዝ በአንዱ በልጅሽ ተማጽኙሻለሁ በቃል ኪዳንሽ ተማጽፔሻለሁ ድንግል ሆይ ጠብቂኝ ክፉ እንዳልናገር ከምስጋናሽ ከበጉ በስተቀር አዝ በአምስቱ ኃዘኖችሽ ተማፅኙሻለሁ በረሃብ በጥምሽ ተማፅኙሼሻለሁ በኃዘን በስደትሽ ተማፅኙሻለሁ ከልጅሽ አስታርቂኝ ድንግል ብዬሻለሁ አዝ ከፍቅርሽ አትለይኝ ደግሞም ከሃይማኖት ሕጉንም ጠብቄ እንድኖር በሥርዓት ከለላዬ ሁኝልኝ ጠብቂኝ ከጠላት ከዚያ ከዲያቢሎስ ከኃጢአት አባት ማርያም ድንግል ማርያም ማርያም ድንግል ማርያም ርኅርኅተ ኅሊና ማርያም የወርቅ መሠላል ነሽ ድንግል ማርያም የወርቅ መሰላል ነሽ መሰላል ነሽ የወርቅ መሰላል ነሽ ሰውና አምላክን ያገናኘሽ አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ አሸልቦት እንቅልፍ ተኝቶ ከጤዛ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላል ምሳሌሽን አየ ማርያም ድንግል አዝ መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ከሰማይ እንዳየ ያዕቆብ ተኝቶ መንገድ ላይ ተስፋ አድርጉ ሲኖር የሰላሙን ዘመን ይኸው ተፈጸመ በአንቺ በእናታችን አዝ በአንቺና በልጅሽ ሆነልን ሰላም በአንቺ ተፈጸመ የያዕቆብ ሕልም ሰውና መላእክት ተለያይተው ሲኖሩ በልጅሽ መወለድ በአንድነት ዘመሩ አዝ ገጽ ማርያም ደል ናት ማርያም ደል ናት የሁሉም መማሪያ በንጽሕና በንጽሕና ተጽፋለችና ሐመልማላዊት ዕፅ ሙሴ ዘርእየ በደብረ ሲና ሐመልማላዊት ዕፅ ሐመልማላዊት ትር የለመለመች ዕፅ ናት የለመለመች ሙሴ ያያት በደብረሲና የለመለመች ዕፅ ናት የለመለመች ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል እመ አምሳክ ንዒ ማርያም ንዒ ንዒ ንዒ እመ አምላክ ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል እመ አምላክ ንዒ ማርያም አዝ ምስለ ራጉኤል ወሩፋኤል እመ አምሳክ ንዒ ማርያም አዝ ምስለ ፋኑኤል ወሳቁኤል እመ አምላክ ንዒ ማርያም አዝ ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል እመ አምላክ ንዒ ማርያም አዝ ምስለ ወልድኪ አማኑኤል እመ አምሳክ ንዒ ማርያም መሠረተ ሕይወት መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ ቅድመ ዓለም የነበረ መድኃኒት ከሚባል የተገኘሽ የህይወት መሠረት ማርያም አንቺ ነሽ መሠረትነትሽም የልጅሽ የደሙ ምሳሌ ነው ጽላት ጽላት ዘሙሴ ጽላት ሕግ ወሥርዓት ሙሴ ከፈጣሪ የተቀበላት አሥርቱ ትዕዛዛት የተጻፈባት ጽላት ዘሙሴ ጽላት ድንግል ሆይ ስላንቺ ድንግል ሆይ ስላንቺ ነውና መሐሪ አማልጂኝ ከአንዱ ልጅሽ ከፈጣሪ ስሙን እንዳልጠራ አንደበትም የለኝ ፊቱንም እንዳላይ ሥራዬ አሳፈረ ታውቆኛል ጥፋቴ ብዙ እንደበደልኩኝ ትዕዛዙን እንደሻርኩ ሕጉን እንደጣስኩኝ አዝ አንተ ክቡር መልአክ ልደቱን አብሳሪ አማልደኝ ከጌታዬ ከፈጣሪ በፊቱ እንዳላፍር የተጠራሁ ለታ እለምነዋለሁ ከአሁኑ ይቅርታ አዝ ጻድቃን ሰማዕታት እናንተ ሁላችሁ አማልዱኝ ከጌታዬ ከአምላካችሁ አዝ ይዌድስዋ ይዌድስዋ መላእክትለማርያም በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት ወይብልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ ትርጉምበመጋረጃ ውስጥ መላእክት ማርያምን ያመሰግኗታል ሰላምታ ይገባሻል ማርያም አዲስቷ እንቦሳ ይሏታል ርግብዬ ርግብዬ ማርያም እሙ ለእግዚእየ በቀለመወርቅ ጸአፊ ስምዬ በዓምደብርሃን ጸአፊ ስምዬ በቀለመወርቅ ጸአፊ ስምዬ የተመረጥሽ ጌጤ ፈርጤ ሽልማቴ የክብሬ አክሊል ነሽ ለኔ እመቤቴ ርግብዬ ወደአንቺ እጮሃለሁ በችግሬ ጊዜ እንድታርቂልኝ የልቤን ትካዜ ርግብዬ አዝ የማትፈርሺ መቅደስ ንፅሕት አዳራሽ የመለኮት እሳት በማሕፀንሽ የያዝሽ ርግብዬ የድኅነቴ ምክንያት የሕይወቴ ፋና የችግሬ ደራሽ ርኅርኅተ ኅሊና ርግብዬ አዝ ስጠራ ስምሽን ከጧት እስከ ማታ ፈጥነሽ ድረሽልኝ እንዳልንገላታ ርግብዬ የነቢያት ትንቢት የሰማዕታት አክሊል ምዕራገ ጸሎት የወርቅ መሰላል ርግብዬ አዝ ምርኩዝ መደገፊያ የሃይማኖት በትር ሆነሽ የተገኘሽ የሕይወት ማኅደር ርግብየ መንገዴ ጨልሞ ወድቄ እንዳልቀር ደግፈሽ አሻግሪኝ ያን የኃጢአት ባሕር ርግብዬ አዝ እመቤቴ ማርያም እመቤቴ ማርያም እለምንሻሁ በለቅሶ በዋይታ ፊትሽ ወድቄአለሁ እመቤቴ ስሚኝ አለምንሻለሁ ኃዘኔን ጭንቀቴን ለማን እነግራለሁ ችግሬን ጉዳቴን ለማን አዋያለሁ እመቤቴ ስሚኝ ተማፅኙሻለሁ ኃዘኑም በዛብኝ ፈተናው ከበደኝ እንደምን ልቻለው እኔ ደካማ ነኝ የአማኑኤል እናት ፈጥነሽ ድረሺልኝ በጣም ተንገዳገድኩ ልወድቅ ነው እኔ እመ አምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጉኔ ምንም አጋር የለኝ ከአንቺ በቀር ለኔ የብርሃን መውጫ የብርሃን መውጫ የሕይወት መሰላል የተነበየላት ነቢዩ ሕዝቅኤል የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር ሆና የተገኘች የአምላክ ማኅደር የዳዊት መሰንቆ የጌዴዎን ጸምር አፍርታልናለች ያለ ወንድ ዘር እስኪ እናመስግናት እንዲህ በማለት ቅድስት እናታችን ስብሕት ወቡርክት አንቀፀ ብርሃን ምዕራገ ሕይወት አዘክሪ ድንግል ለልጅሽ በእውነት በደኅና እንዲያደርሰን ለመጪው ዓመት ሰአሊለነ ቅድስት ሰአሊለነ ቅድስት እንልሻለን እንደ ኤፍሬም እንደአባታችን ጉ ለምኝልን እመቤታችን ተስፋቸው ነሽና ለፍጥረት ዓለም እየተመኩብሽ እስከዘላለም ኃጢአታቸው ተደምስሶላቸው ጉጆ በአንቺ ጸሎት ዳነች ሕይወታቸዉ አዝ ስምሽም ሥልጡን ነው በእግዚአብሔር መንበር ቃልኪዳን ገባልሽ ዓለሙን ሊምር በአንቺ ጸሎት ይተማመናሉ ጠዋት ማታ ቅድስት ሆይ ይላሉ አዝ ዓለም ስትዋጋን በምኞት ስለት ነፍሳችን ስትዝል ሲከብዳት ኃጢአት ጨልሞብን ግራ ሲገባን ጉጆ ብርሃናችን ነይ እናታችን አዝ የልባችን ኅዘን እጅጉን ከብዶናል ኃጢአታችን በዝቶ መቆም ተስኖናል አንደ ኤልሳቤጥ አንደዘመድሽ ጉጆ ደስ አሰኝን ይሰማ ድምፅሽ አዝ ኢያቄም ወሐና ኢያቄም ወሐና እናት አባትሽ ቤተ እግዚአብሔር ወስደው ስዕለት የሰጡሽ መና ከሰማያት የወረደልሸ ፍጹም ድንግል የሆንሽ ማርያም አንቺ ነሺ ኦ እመ ክርስቶስ ማርያም አንቺ ነሺ የአማኑኤል እናት የአማኑኤል እናት ጸለየች ኢትዮጵያን አድናት ጌታሆይ አድናት እያለች የጌታዬ እናት ጸለየች ኢትዮጵያን አድናት ጌታ ሆይ አድናት እያለች የምወደው ሕዝቤ አሥራት የሰጠኸኝ በረሃብ በእርዛት ምነው ተጉዳብኝ የፍቅር ረሃብ የሰላም ጥማቱ ምነው መንገላታት ምነው መዋተቱ ሆና ተሠርታለች መንፈሳዊት በአት የድንግል አሥራቷ ቃል የተገባላት ሐሰቱ ቅጥፈቱ ስለማይስማማት ከእንግዲህ ወገኔ መመለስ አለበት ገጽ አንቀፀ ብርሃን አንቀፀ ብርሃን ድንግል ማርያም ሰማያዊ ዙፋን የመድኃኔዓለም ሰማይና ምድር የማይችሉትን እረ እንደምን ቻልሽው መለኮትን የእሳት መጋረጃ ወዴት ተጋረደ ልዑል በጥበቡ ከአንቺ ተዋሐደ ሰማያዊ ንጉሥ የከተመብሽ የመለኮት ዙፋን ድንግል አንቺ ነሽ ሚካኤል ገብርኤል ሰግደው ዘመሩልሽ ሩፋኤል ራጉኤል ሰግደው ዘመሩልሽ ማኅደረ መለኮት ማኅደረ መለኮት ማርያም እመብዙኃን ት የመለኮት ማደሪያ የሆንሸ እመቤታችን ማርያም የብዙኃን እናት ነሽ አዛኝ እናታችን አዛኝ እናታችን ቤዛዊተ ከኣሉ ስሟን ለሚጠሩ አድፒን ለሚሉ የምሕረት አማላ አይዞህ ልጄ አለ ልቤ እየአመነታ በቀቢጸ ተስፋ መከራ ጸንቶብኝ ፈጽሞ ሳልጠፋ ድንግል ብታነሣኝ እጆቿን ዘርግታ በምልጃዋ ዳንኩኝ አገኘሁ ይቅርታ አባ ሕርያቆስ ይፈተን እውቀቱ ምኑን ይቀድሣል ብለው ሲዘብቱ በምስጋና ምስጢር ልቡን የቃኘችው በብር የልቤን የውስጤን መናገር ፈርቼ ዝም ባልኩኝ ጊዜ አንገቴን ደፍቼ ምስጢሬን ነግሬ ስማፀን በደጂ ለክብር አበቃችኝ አማልዳ ከልጂጃ ምክሆን ለደናግል ማርያም ድንግል ምክሆን ለደናግል ይእቲኬ ቤተ ምስአል ዘአስተአጸቡ ታቀልል ለኩሉ ፍጥረት ትተነብል በአክናፈ መላእክት ትትኬለል ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል ወትፈደፍድ እምሱራፌል ማርያም ድንግል መመኪያቸው የደናግል እርሷም እኮ የምልጃ ቤት ናት የሚያስጨንቀውን የምታቀልል ለፍጥረት ሁሉ ትማልዳለች በመላእክት ክንፎችም ትጋረዳለች እርሷ ትበልጣለች ከኪሩቤል ደግሞም ትልቃለች ከሱራፌል እመአምላክ ሙሽራ ነሽ እመአምላክ ሙሽራ ነሽ ለቃል ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ እዝኸ አሥራሁለት ዓመት ቤተመቅደስ የኖርሽ የመመረጥ ጸጋ ከጌታ ያገኘሽ በአብሣሪው መልአክ እጹብ ድንቅ ዜና ከሰማይ መጣልሽ አቋርጦ ደመና በስድስተኛው ወር ተልኮ ገብርኤል ቤተመቅደስ ገባ ሊያበሥራት ለድንግል በልዩ ሰላምታ ሰላም ለኪ ያለሽ የክርስቶስ እናት በጣም ደስ ይበልሽ መላእክት በሰማይ ያመሰግኑሻል ክብር ለአምላክ እናት ይድረሳት ይሉሻል በማኅፀንሽ ቢያድር የሠራዊት ጌታ ለመሆን ተመረጥሽ የአምላክ ቅዱስ ቦታ የፈጣሪ እናት መሆንሽን ተረድቶ ሰላም ላንቺ ይሁን አለሽ እጅ ነሥቶ ከፍጡራን ሁሉ አንቺ ትበልጫለሽ ገብርኤል ተልኮ ደስታን አበሰረሽ ምንኛ ድንቅ ነው ድንግል የአንቺ ብሥራት ጌታን ትወልጃለሽ የሚል ቃልን መስማት ይሁንልኝ ብለሽ ቃሉን የተቀበልሽ ድንግል ሆይ እናቴ እጅግ ልዩ እኮነሽ ሶበሰ ኪዳንከኪ ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድጊን ኢሀሎ ፈለገ እሳት ወደይን እምአስጠመ ኩሉ ፈለገ እሳት ወደይን እምአስጠመ ከሉ ትርጉምየመዳን ምክንያት የሆነ ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የእሳት ማዕበል ሁሉን ባሰጠመ ነበር ዳግሚት አርያም የአባ ሕርያቆስ ድርሳነ ቅዳሴው የእነ አባ ኤፍሬምም ኃይለ ጸሎታቸው ማርያም ድንግል ነሽ የእምነት ሙዳያቸው ወይነ ሕይወት ክርስቶስ የተመላብሽ ጽዋዐ መድኃኒት ነውር የሌለብሽ የማይቻለውን በማኅፀን የቻልሽ ምንኛ ድንቅ ነው መቅደስነትሽ አዝ አርፌም አልተኛ ዙፋኔን ትቻለሁ የያዕቆብን አምላክ ማደሪያ ካላየሁ ብሎ የናፈቀሽ ዳዊት አባትሽ ኢያቄም ወሐና ገና ሳይወልዱሽ አዝ እንደምን ታደሉ ሐናና ኢያቄም የእነርሱ ናትና ዳግሚት አርያም በሥጋዊ ፈቃድ ሊያስገኙሽ ያልቻሉ የእግዚአብሔር ስጦታ መድኃኒተ ኩሉ አዝ የድኅነት ምልክት የምእመናን ዓርማ ተናጋሪ ገነት የጻድቃን ከተማ ማኅደረ መለኮት የአብ ቃል መገኛ የሕይወት ውኃ ምንጭ የአዳም ዘር መዳኛ አዝ አትለይን አትለይን ድንግል ሆይ ድረሽልን ከዲያብሎስ እጅ አንቺ አድኝን ምሕረት ከልጅሽ ለምኝልን ንጽሕተ ንጹሐን ንጽሕተ ንጹሐን ከዊና ከመታቦት ዘዶር ዘሲና ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በድንግልና ነበረት ሲሳያ ኅብስተ መና ውስቴሃኒ ስቴ ሙና ትርጉም ከንጹሐን ንጹሕ ሆና በሲና እንደ ነበረችው ምግቧ ታቦት በድንግልና በቤተመቅደስ ውስጥ ኖ ኅብስተ መና መጠጣም የፀጥታ መጠጥ ነበር በአባቶች ልመና በአባቶች ልመና እስኪ ልለምንሽ እኔማ ግብር የለኝ ለመቆም በፊትሽ ርሃብሽን አሳስቢ ድንግል ሆይ እባክሽ ግብሬን ዐውቀዋለሁ ምንም ምን ጽድቅ የለኝ ውኃ ያልጎበኘው አዳፋ ልብስ ነኝ አዝ ጥምሽን ለብሼ ሲያምርብኝ ጻድቅ እመስላለሁ ድንግል ሆይ ታውቂያለሽ ውስጤን ጐስቁያለሁ አዝ ልቅሶሽን በኃጢአቴ ሳለቅስ ከጧት እስከማታ ድንግል ሆይ አትርሺኝ ሁኝልን አለኝታ አዝ ስደትሽን ካጠጣሸው ውሻ ያን ጊዜ ተጠምቶ እኔም በምግባሬ አልሻልም ከቶ አዝ ኃዘንሸን ቄም ወለዳ ኢያቄም ወለዳ ኢያቄም ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ ትርጉምየኢያቄም ልጅ የዳዊት ዘመድ ናት ምሥራቀ ምሥራቃት ምሥራቀ ምሥራቃት ሙውዕፅዐ ፀሐይ እግዝእትየ ዘመና ሙዳይ ዘመና ሙዳይ ማርያም ዘመና ሙዳይ ትርጉም የኅብስት ክርስቶስ መገኛ የወርቅ መሶብ ከፀሐይ መውጫዎች ሁሉ የምትበልጥ የፀሐይ መውጫ ምሥራቅ አንቺ ነሽ በመኑ በመኑ በአምሳለ መኑ አስተማስለኪ እመቤቴ የኔ አማላጅ አዛኝቷ ኦ ድንግል ምልዕተ ውዳሴ ትርጉም ማን በተመሰለው ምሳሌ እመስልሻለሁ እመቤቴ የኔ አማላጅ አዛኝቷ ምስጋናን የተመላሽ ነሽ ተወልዳለችና ተወልዳለችና የጌታ እናት የእኛ መድኃኒት እናመስግናት እናወድሳት እንውደዳት እናመስግናት እናወድሳት እርሷ ናት እና የአዳም ሕይወት ገጽ እመቤታችን ማርያም እመቤታችን ማርያም ማኅበራችንን ጠብቂልን በምልጃሽ ከመናፍቃን ከከሃድያን ከጠላት ሰይጣን ሰውረሽ እንድትጠብቂን በምልጃሽ ለእናታችን ቅድስት ታችን ቅድስት የዓለም ርኅርኅት እንስገድላት እንስገድ በእውነት ለአምላክ እናት እመቤታችን እመቤታችን ለአንቺ እናቀርባለን ምስጋና አንቺ የወለድሽው ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ሆኗልና ምእመናን ስለአወቁ ደግነትሽን በሙሉ ወደ አንቺ ሁል ጊዜ ይማልዳሉ ከፈጣሪሽ አማልጂን እያሉ ማርያም እመቤቴ ማርያም እመቤቴ የአምላክ እናት ማደሪያ የሆንሽው ዙፋን ለመለኮት ከሴቶቹ ሁሉ አንቺ ነሽ የተባረክሽ የነፃሸ በእውነት ከቶ እንደምን ቻልሽው መድኃኔዓለምን ሰማይና ምድር የማይችሉትን ድንግል እናታችን ለዚህ የተመረጥሽ ለምኝልን ለኛ ምሕረትን ከልጅሽ አዝ የነቢያት ሞገስ የሐዋርያት የሰማዕታት አክሊል የጻድቃን እናት የእኛ መመኪያችን የኃጥአን ተስፋ ወልድን በመውለድሽ ኃዘናችን ጠፋ አዝ ቅዱሳን በገነት ሲያመሰግኑሽ መላእክት በሰማይ ሲያገለግሉሽ እኛም የአዳም ልጆች ከመሬት ሆነን ሰአሊለነ ቅድስት እንልሻለን ማርያም ኃዘነ ልቦና ማርያም ኃዘነ ልቡና ታቀልል ኃዘነ ልቦና ታቀልል ማርያም የልብን ኃዘን ታቀላለች የልብን ኃዘን ታቀላለች ያሲና ሐመልማል የሲና ሐመልማል የሙሴ ጽላት የሲሉሎንዲስ ጥበብ ዕፀ መድኃኒት አሁን በምን በምን እንመስልሻለን ዕፁብ ድንቅ እያልን እናወድስሻለን አዝ ያረጁ ፍጥረታት የታደሱብሽ የሕይወት መሰላል ማርያም አንቺ ነሽ አዝ የነቢያት ትንቢት የልባችን ተስፋ በአንቺ መመኪያነት ማኅበራችን ይስፋ አዝ እመቤታችን ለአንቺ እመቤታችን ለአንቺ ሰላምታ ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተመርጠሻል ሐርና ወርቁን እያስማማች ስትፈትል ተበሰረላት የመመረጥ ክብር አዝ እያረጓጓት የሰማይ መላእክት ቤተመቅደስ ኖረች አሥራ ሁለት ዓመት አዝ መንፈስ ቅዱስም እንደቀረባት አውቀ ሰገዳላት ዘካርያስ ታጥቆ መሠረተ ሕይወት ይወት ማርያም በረድኤት ነይ ተን ይዘሽ ከሰማይ ተን ይዘሽ ከሰማይ ማርያም ድንግል በረድኤት ነይ የእኛ እመቤት ነይ ነይ የእኛ እመቤት ነይ ነይ የዓለም መድኃኒት ሙዳይ የአዳም ዘር ሁሉ ሲሳይ ነይ ነይ ማርያም ነይ ነይ አምላክ ከሰማይ ያየሽ የወገኖችሽ ክብር ነሸ የአሕዛብ ሁሉ ድኅነት ከአንቺ ተገኘ በእውነት አዝ ክብርሽ ተገልጧል በልጅሽ መንፈስ ቅዱስም ቀደሰሽ የቃሉ ሕንፃ ሆነሻል አብ ከሰማያት መርጦሻል አዝ ፀሐይ ወጣልን ከእቅፍሽ ሰማዕታት ሁሉ ከበቡሽ ምክንያት ሆነሽ ሊድኑ በልጅሽ ሥራ ያመኑ ማርያምሰ ማርያምሰ ተኃቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመባሕርይ ጸዐዳ እስመ በእንቲአሃ ወበእንተ አዝማዲሃ ተሰቀልኩ ዲበ ዕፅ ይቤ መድኃኔዓለም ማርያምማ ታበራለች ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እርሷን ደስ ይበላት ብሎ ስለ ወገኖቿ ተሰቀልኩ አለ በእንጨት መስቀል ላይ መድኃኔዓለም ሰላም ለኪ እምነ ዮን ሰላም ለኪ እምነ ዮን ማርያም ውድስት የሕይወት ብርሃን ሰላም ለኪ እምነ ዮን ድንግል የአብርሃም ድንኳን ሰላም ሰላም ሐረገ ወይን ያዕቆብ ያየሽ መሰላል የሰሎሞን ክብር አክሊል አዝ ጽላተ ሙሴ የኦሪት የአሮን በትር መድኃኒት የዋህ ርግብ የኢያቄም የነቢያት ተስፋ የአዳም አዝ እሳተ መለኮትን የያዝሽ ምሉዕ አምላክን የወሰንሽሸ ቤተመቅደስ የልዑል ሰላም ለኪ እም ወድንግል ማርያም ኅዘነ ልቦና ማርያም ኅዘነ ልቦና ታቀልል ኅዘነ ልቦና ኅዘነ ልቦና ታቀልል ሕይወታችን አንችን ባየች ቁጠር ትፈካለች ብሩህ ፋና የመዳን መሰላል ነችን ነሽ ላዘኑ መጽናኛ ለደከሙ ብርታት ካንቺ ተገኘልን የዘላለም ሕይወት አዝ ርስትሽን ኢትዮጵያን አስቢያት በጸሉት ታለቅሳለች ሰላምን ብታጣ ሳትታክት ባንቺ መታመኗ ስምሽን መጥራቷ ስለሆንሽላት ነው ረዳቷ አዝ ማርያም የልቦናን ኅዘን ታቀላለች የልብን ኀዘን ታቀላለች ብንከፋ በአማላጅነትሽ ተጽናናን ከጥላሽ ሥር ሰላምና ፍቅርን አገኘን ጽድቅን የተጠሙ የተራቡ ሁሉ በስምሽ ተማጽነው ይረካሉ አማናዊት ኪዳን አማናዊት ኪዳን የሰው ልጆች ተስፋ ድንግልሆይ አማልጅን በሞት እንዳንጠፋ የአባቶች ነቢያት ተስፋ ትን የሐዋርያትም ጣዕመ ስብከታቸው የሰማዕታት እናት የጻድቃን እመቤት ደግሞም እኅታቸው ለሰማይ መላእክት አዝ የነቅዱስ ኤፍሬም ድንቅ ድርሰታቸው የነ ቅዱስ ያሬድ ድጓ ዝማሬያቸው የእምነታቸው ቅመም አንቺ ነሽ በእውነቱ የአባ ጊዮርጊስም ጸሉተ ሰዓታቱ አዝ የአባ ሕርያቆስ ምሥጢረ ቅዳሴ የመነኮሳት ስንቅ የኤፍሬም ውዳሴ የሊቃውንት አበው የምሥጢር ቋንቋቸው የደናግል ተስፋ የጽድቅ አክሊላቸው አዝ ሁኝልን መመኪያ በሞት እዳንሰጋ በዚች ዓለም ፈቃድ ከቶ እንዳንወጋ ስለሌለን ተስፋ በዚህ ዓለም ስንኖር አስታርቂን እመአምላክ ከቸሩ ልጅሽ ጋር ገጽ ድንግል ሆይ ወላዲተ አምላክ የሁሉ እመቤት ለምኝልን ለኛ ከልጅሽ ምሕረት በአንች አማላጅነት በእርሱ ቸርነት እንዲያወጣን ነፃ ከፍርድ ቅጣት ድንግል ሆይ ለምኝልን በበደል ተዳክሞ ፈቃደ ነፍሳችን በምድራዊ ምኞት ናውዞ ልቡናችን ፍቅርና ትኅትና ጠፍቶ ከፊታችን ለሞት እንዳይሰጠን ይህ ክፉ ሥራችን አዝ የምስኪኖች ተስፋ የደካሞችም ኃይል ጠውልገናልና ጥላ ሁኝን ድንግል እምነት ጨምሪልን ልቡናችን ይጽና እመአምላክ አብሪልን የመዳንን ፋና አዝ ፍፁም እንዳናዝን እንዳናፍር ኋላ ተነጥቀን እንዳንቀር ከዘላለም ተድላ በፍቅርሽ መልሽን ከሲአል ጉዳና ድንግል መመኪያችን ተስፋችን ነሽና አዝ የአርያም ንግሥት የሰማይ የምድር የአርያም ንግሥት አንቺ ነሽ እመቤት የአምላክ እናት ጸኸ ድንግል አማልጅን ሽኸ ቅድስት ተራጅን የሔዋን ተስፋዋ ለአዳም ዘር ሕይወት የድኅነቱ ምክንያት አንቺ ነሽ ንጽሕት የኦሪት መጽናኛ የአዲስ ኪዳን በር የወንጌል መሠረት የአምላክ ማኅደር አዝ የአብርሃም እርሻ የምሥጢር ዋሻው እናትና ድንግል ሁለቱን ሆንሽው የኤፍሬም ውዳሴ የያሬድ ውብ ዜማ የማትጠልቂ ፀሐይ የሃይማኖት ሻማ አዝ የሰማይ የምድር የአርያም ንግሥት አንቺ ነሽ እመቤት የአምላክ እናት አዝ በእንተ መስቀሉ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ መርሕ ለፍኖት ሃሌ ሉያ መርሕ ለፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን ሞገስ ዝንቱ መስቀል ለአዳም ዘአግብኦ ውስተ ገነት ሃሌ ሉያ መሪ ነው በመንገድ ሞገሳቸው ለጻድቃን ሞገስ ይኸ መሰቀል ነው አዳምን የመለሰው ወደ ገነት መስቀል ብርሃን መስቀል ብርሃን ኩሉ ዓለም መሠረተ ቤተክርስቲያን ወሀቤ ሰላም መድኃኒዓለም መስቀል መድኅን ለእለ ነአምን መስቀል ብርሃን ነው ለመላው ዓለም መሠረት ነው ለቤተክርስቲያን ሰላምን ሰጪ ነው መድኃኔዓለም መስቀል አዳኝ ነው ለኛ ለምናምን መስቀልከ መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ ይኩነነ ቤዛ መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ ይትቀደስ ስምከ ይትቀደስ ስምከ በኃይለ መስቀልከ በዕፀ መስቀልከ ክቡር ዘአእበይኮ ለስምከ ስብሐት ለከ ለባሕቲትከ ልዑል በመስቀሉ ወበቃሉ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ በወንጌሉ ያመናችሁ በወንጌሉ ያመናችሁ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ ኃይልነ ወጸወንነ ኃይልነ ወጸወንነ ወሞገስ መሞገስነ ዝንቱ ውእቱ መስቀል ጥልን በመስቀሉ ገደለ ጥልን በመስቀሉ ገደለ በመስቀሉ ለሰው ልጅ ሰላምን አደለ መስቀል ኃይልነ መስቀል ኃይልነ መስቀል ንእነ መስቀል ቤዛነ መድኃኒትነ ለእለ አመነ ኅበ ቀራንዮ ኅበ ቀራንዮ ደብረ መድኃኒት ቀራንዮ ኅበ ቀራንዮ የመስቀሉ ቃል ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው ለማያም ሞኝነት ነው ለእኛ ግን ሕይወት ነው እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ እንመነው አንካደው ፈጣሪያችን እንመሰክራለን ድንግል አማ እንመሰክራለን ማርያም አማላጅ ናት እንመናት አንካዳት የአምላክ እናት ናት ኅበ ጥበባት ኅበ ልሳናት ዮሐንስ ወንጌለ ስብከት በመስቀሉ ቤዘወነ በመስቀሉ ቤዘወነ ወበደሙ ተሰሃለነ አምላከ ምሕረት ውእቱ መድኃኒነ አምላከ ምሕረት ውእቱ በመስቀሉ ቤዛ ሆነን ሞትን ሽሮ ከሞት አዳነን የምሕረት ጌታ ነውና ይቅር አለን የምሕረት ጌታ ነውና እሌኒ ንግሥት እሌኒ ንግሥት ሐሠሠት መስተቀሉ ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ክብሩ ብርሃን ወጣ ብርሃን ወጣ ከመስቀ የአምላክና የሰው ደስ ይበለን በመስቀሉ ብርሃን እልል እንበል በአንድነት ሆነን ተነሳልን መድኃኒታችን ከፊት ለፊት በመሳሉ የመስቀሉ ነገር የሚወደው ሐዋርያ የወንጌል መምህር ዮሐንስም ስቅለቱን በማየቱ ሲያዝን ኖረ በምድራዊ ሕይወቱ ቢያሰቅቀው ሞቱ ግርፋቱ ነው ና አዝ ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናኪያቸው በዓለም ጥበብ ለሚኖሩት እውነት ተስኗቸው ለጠቢብ ሰው በመንፈስ ለሚኖረው የመዳን ቀን እውነተኛ ዓርማ ነው ከዝሀነም እሳት የሚያድን ነው አዝ እስከመስቀል ላልተለየው ቅዱስ ሐዋርያ ለዮሐንስ የወንጌል ሰው የፍቅር ባለሞያ ምስጋናችን ከምድር ይድረሰው እንድናለን በሰጠው ምሳሌው ሰዎች ሁሉ እንከተለው ወሪዶ እምመስቀሉ ወሪዶ እምመስቀሉ እምመስቀሉ አብርሃ ለኩሉ እምመስቀሉ ለኩሉ አብርህ ዮምሰ ለእሊአየ ዮምሰ ለእሊአየ አበርህ በመስቀልዩ በእንተ ቅዱሳን መላእክት ገብርኤል ምልዐኒ ገብርኤል ምልዐኒ መንፈሰ ልሳን ለተናብቦ መንፈሰ ልሳን ሞጣሕተ ብርሃን ዘይትገለብቦ ሞጣሕተ ብርሃገ ትርጉም ገብርኤል ለመናገር ጥሩ ልሳን ስ ስጠኝ መንፈስ ቅዱስን አሳድርብኝ የብርሃን መጎናጸፊያ እንድጎናጸፍ አድርገኝ በምልጃህ ተራዳኝ ገጽ ሰአሉ አስተምሕሩ ለነ ሜካኤል ወገብርኤል ሱራፌል ወኪሩቤል ዑራኤል ወሩፋኤል ብርናኤል አቅናኤል ሱባኤል ወፍናኤል ሰላታኤል ሰዳታኤል ኤልናኤል መላእክተ ምሕረት እለ ድልዋ ለሳህል ሰአሉ አስተምህሩ ለነ እስመ በጸሉተ ትንብልናክሙ ትድኅን ወኢትማሰን ሀገር ባሕራንኒ ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕር ርኢክዎ ለሚካኤል ወሰአንኩ ጠይቆቱ ዘይብል ትር ባሕርን አቋርጦ የሔደ ባሕራን ሚካኤልን አይቼ መረዳት ተሳነኝ አለ ውእቱ ሊቆሙ ውእቱ ሊቆሙ ለመላእክት ወመልአኮሙ ስሙ ሚካኤል ልብሱ ዘመብረቅ ዓይኑ ዘርግብ ሊቀመላእክት ትርጉም የመላእክት አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ልብሱ የመብረቅ ዓይኑም የርግብ ነው ልፁል ውእቱ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ሚካኤል ልዑለ መንበር ትርጉም ከፍ ከፍ ያለነው መቀመጫውም ከፍ ከፍ ያለነው ሚካኤል መቀመጫው ከፍ ከፍ ያለነው ካኤል ሊቅ ሚካኤል ሊቅ ልብሱ ዘመብረቅ ዓይኑ ዘርግብ ዓይኑ ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ ትር አለቃ የሆነው ሚካኤል ልብሱመብረቅ ነው ዓይኖቹም የርግብ ዓይን ይመስላሉ ሚካኤል የወርቅ ሐመልማል ነው ሚካኤል አማልደን ሚካኤል አማልደን ከአምላካችን እንዳንጠፋ እንዳንሞት በነፍሳችን ቀዋምያን ለነፍሳት ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት ዑራኤል ወሩፋኤል ይትፌነው ለሳሕል እም ኅበ ልዑል ለነፍሳት የቆሙ እነዚህ መላእክት ዑራኤልና ሩፋኤል ከልዑል ዘንድ ለይቅርታ ይላካሉ ከልዑል አምላከ እሥራኤል አምላከ እሥራኤል ታማኝ ጌታችን ለእሥራኤል ለሙሴ የሆንከው መድኅን ፈርዖን ቢጸና በትዕቢት ቢገን ለእሥራኤል አርበኛ መረጥከው ሙሴን አማላጅ ነው ሚካኤል የአምላክ ባለሟል ለነሙሴ ለሕዝበ እስራኤል ፈርዖን እንደገና ልቡ ተጸጽቶ ቢከተላቸውም ጦሩን አስከትቶ ይመራቸው ነበር ሚካኤል በፋና ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና አዝ ሙሴ እንደታዘዘው አነሣ በትሩን እጆቹን ዘረጋ ከፈለው ባሕሩን እንደ ግንብ ቆመ ባሕረ ኤርትራ በደረቅ አለፉ እሥራኤል በተራ አዝ መልአከ ሰላምነ መልአከ ሰላምነ ሊቀመላእክት ዑራኤል ሰአል ወጸልይ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለመድኃኔዓለም ትርጉምየሰላም መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ስለ እኛ ለምንልን ጸሎታችንንም በመድኃኔዓለም ፊት አሳርግልን እልፍ አእላፋት እልፍ አእላፋት ወትእልፊት ቅዱሳን ንጹሐን መላእክት ቆሙ ለአገልግሉት ፀንተው በአንድነት ቅዱስ አምላክ በማለት ኢዮር ራማ ኤረር የመላእክት አገር የሃይማኖት የፍቅር የእምነት ምስክር እውነት የታየብሽ የመላእክት ክብር አዝ እንጽና ሲል ገብርኤል ባለንበት ቦታ በሳጥናኤል ነገድ ነበረ ሁካታ ግማሹ እየካደ ቀሪው ሲያመነታ አዝ የሳጥናኤል ምኞት እንደአበባ ረግፎ ሚካኤል ተሾመ በእምነት ተደግፎ ሳጥናኤል ወደቀ ጸጋውን ተገፎ አዝ ቅዱሳን መላእክት በእምነት የጸናች በታላቅ አክብሮት ሰላም እንበላችሁ ስግደት ዘበጸጋ እንስገድላችሁ በእንተ ቅዱሳን ቅዱሳን መስክሩ ተአምሩን ያያችሁ ቅዱሳን መስክሩ ፍቅሩን ቸርነቱን ለዓለም ንገሩ በየዋሕ ልቡና ንጹሕ መሰዋትን አቤል ግለጥልን ለጽድቅ መሞትን ኖኅም ተናገረው ለአንተ የታየህን ዛሬን ብቻ ትተህ ነገን ማሰብህን ሁ አዝ ተናገር አብርሃም የአምላክን ሥራ እንዴት እንደነበር ያኔ ስትጠራ ልጅህን ያሠጠህ ፍቅሩን ግለጥልን በእምነት መታዘዝን ለእኛም አስተምረን አዝ ግለጥልን ዮሴፍ እንዴት እንደነበር ፍትዎትን ድል ነሥቶ ለሃይማኖት ማደር ከራስ ተድላ ይልቅ ለወገን መሞትን አስተምረን ሙሴ ፍቅርና ጽናትን አዝ ለጠላት መጸለይ በማድረግ ይቅርታ አሳይ እስጢፋኖስ የፍቅርን እውነታ በፈተና ብዛት እንዳናመነታ ቂርቆስ ጽኑ በለን ልባችን ይበርታ አዝ ወይቤሎሙ ሑሩ ወይቤሎሙ ሑሩ ወመሐሩ ለዘየአምን ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት በሕይወታችሁ ስበኩ በኑሮአችሁ ከጽንፍ አስከ ጽንፍ በዓለም ዙሪያ አዳርሱ ሳትሰለቹ ደመና ጠቅሳችሁ እንደወፍ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት በኃጢአት ገመድ ተይዞ ለታሠረው በዓለም ጽልመት ለተዋጠው የእውነተ መንገድ ብርሃኑ ለጠፋበት በሁለንተናው ፈንጥቁበት ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት የጽድቅ እንጀራ በማጣት ለተራበው የሕይወትን ውኃ ለተጠማው ቀቢፀ ተስፋ በልቡ ላረበት የወንጌልን ማእድ አቅርቡለት ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት አርድዕተ ወንጌል ካህናት ሊቃውንት ለተልዕኮ የጠራችሁ ከእውነተኛው ምንጭ ከጌታ ከባዕሉ የሕይወትን ውኃ የጠጣችሁ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት ሁለንተናችሁ ይነበብ ፊደል ይሁን በትዕዛዙ ሄዳችሁ ሥራችሁ ይብራ በዓለም እንደሻማ በሕይወታችሁ ሰብካችሁ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት ወይቤሎሙ ሑሩ ወመሐሩ ለዘየአምን ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት መሠረተ ዜማ መሠረተ ዜማ ወጠነ ያሬድ ካህን ያሬድ ያሬድ ካህን ጥዑመ ልሳን ትርጉምየዜማ መሠረትን ያሬድ ጀመረ ካህኑ ያሬድ አንደበቱ ያማረ ነው ብርሃናተ ዓለም ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሉስ ጻድቁ አባታችን ገብረመንፈስ ቅዱስ የመረጣችሁ ፈጣሪያችን አምላካችን እንድናገኝ ሰላምን አማልዱን እኛን ከፈጣሪያችን ገጽ ደም ወማይ ደም ወማይ ወሀሊብ እምነ ክሳዱ ፈልፈለ ሶበ ተከለለ ተከለለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ትር ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰይፍ አንገቱን በተሰየፈ ጊዜ ደም ውኃና ወተት ፈሰሰ ጊዮርጊስ ኃያል ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል ገባሬ ተአምር ኮከበ ክብር ጊዮርጊስ አርበኛ ኃይለኛ ተጋዳይ ነው አስደናቂ ተአምር የሚሠራ ተጋዳይ ነው ኮከብ ብሩህ ኮከብ ብሩህ ቅዱስ ማርቆስ ዘሠረቀ እም እስክንድርያ ቤተክርስቲያን ዘንሰምያ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ በከመ ጳውሉስ ሐዋርያ ትርጉም ከእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን የተገኘዉ ብሩህ ኮከብ የሆነው ቅዱስ ማርቆስ እንደ ቅዱስ ጳዉሎስ ለኢትዮጵያና ለግብፅ ሰዎች አባት ሆናቸወ በብዙ አህጉር በብዙ አህጉር የዞርክ የጌታን ወንጌል ያስተማርክ የዲቁናን ግብር በክብር የፈፀምክ ብፁዕ ነህ ብፁዕ ነህ እስጢፋኖስ ብፁዕ ነህ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገብረመንፈስ ቅዱስ የዓለም ብርሃን ናቸው ይኸው ለዘላለም ያበራል ሥራ ቸወ ተክለሃይማኖት ተክለሃይማኖት የዓለም ብ ይኸው ለዘላለም ያበራል ሥ ዜና አልባሲሁ ጴና አልባሲሁ ለገብረመንፈስ ቅዱስ ከመጴና ስሒን አልባሲሁ ዘሜላት ዘወረደ ውስተገነት ጉምየገብረመንፈስ ቅዱስ ልብሳቸ ከገነት እንደ ወረደ ነጭ ሐር ነው አባ አቡነ አባ አቡነ መምህርነ አባተክለሃይማኖት እምአእላፍ ኅሩይ አባ አቡነ ተክለሃይማኖት መምህራችን አባ ተክለሃይማኖት ከብዙዎቹ መካከል የተመረጥክ ነህ ጻድቃንሰ ኢሞቱ ጻድቃንሰ ኢሞቱ ኅበ እግዚኦሙ ነገዱ በመንግሥተ ሰማይህ ይሁቦሙ ዘፈቀዱ ነገር ግን ወደ ጌታቸው ዱ እርሱም በሰማያዊ ቤቱ የወደዱትን ሰጣቸው ጻድቃን ቡሩካን ጻድቃን ቡሩካን ዓለምን ንቃችሁ የክርስቶስን ፈለግ የተከተላችሁ በመንግሥተ ሰማይ እጥፍ ነው ዋጋችሁ ሰአሉ ለነ አሰተምሕሩ ለነ እስመ በጸሎተ ጻድቃን ትድኅን ወኢትማስን ሀገር ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ ዲያቆን ወቅዱስ ጊዮርጊስ መክብበ አሚን ወኢየሉጣ ወቂርቆስ ሕፃን አዝ ገብረመንፈስ ቅድስ ዘእምአቅሌስያ ወተክለሃይማኖት ዘኢትዮጳያ ወማርቆስ አብ ዘእስክንድርያ ኮከብ ብሩህ ገብረመንፈስ ቅዱስ ኮከብ ብሩህ ገብረመንፈስ ቅዱስ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ ቤተክርስቲያን ዘንሠምያ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ አማን ገብረመንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ ትርጉምቤተክርስቲያን ብለን ከምንጠራት ከአቅሌስያ የወጣ ብሩህ ኮከብ ነው ለግብፅና ለኢትዮጳያ ሰዎች አባት ሆናቸው በእውነት ገብረመንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ ነው ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ለተክለሃይማኖት ጻድቅ መጠነ በዝኃ ሕማሙ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍለሰተ ሥጋሁ ወአፅሙ አዝ እምነ አድባራት ኩሉን ዘተለዓለት በስሙ አዝ ኢየሱስ ክርስቶስ እንተ ቀደሳ በደሙ አዝ ትርጉምጻዱቁ ተክለሃይማኖት ብዙ ሕማም የተቀበለባት የሥጋውና የአፅሙ ፍልሰት የተደረገባት በስሙ ከተሰየሙ አድባራት በላይ የሆነች ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የቀደሳት ደብረሊባኖስ ተክለሃይማኖትን ታመሰግናለች ጊዮርጊስ በዚያች ቀን ጊዮርጊስ በዚያች ቀን ከፈተናው አንፃር ስለሃይማኖቱ የታየው ምን ነበር ያመነውን አምላክ አላውቀውም እንዲል በሥልጣን በገንዘብ እርሱን ለመሸንገል የዱድያኖስ ጭፍሮች ነገር ሲያሴሩበት ልቡናው ምን አለ ሲቀርብ ለመሥዋዕት አዝ ስገድ ባሉት ጊዜ ሰው ለሠራው ምስል ትዝ አለው ጊዮርጊስ የአምላኩ ሕያው ቃል ከሠለስቱ ደቂቅ ከዳንኤል ጋራ በእሳት ነበልባል ውስጥ ተአምር ሲሠራ አዝ ቂርቆስ ኢየሉጣን ከመቃጠል ዋጅቶ ያቀዘቀዘውን ፍሉን ውኃ አጥፍቶ አስታውሷል ጊዮርጊስ ያንን ኃያል ጌታ መስቀል መሸከሙን በዚያች ጉልጐጉታ አዝ ጴጥሮስና ጳውሎስ አባቶቹን መስሎ ሞትን አሸነፈ በእምነት ተጋድሎ እንድንጸና በእምነት ይህችን ዓለም ንቀን በሰማዕቱ ምልጃ አምላክ ይጠብቀን አዝ እንደ አናንያ እንደ አናንያ እንደ አዛርያ እንደ ሚሳኤል አጽናን እኛን አጽናን እኛን አጽናን እኛንም በእምነታችን መዝሙረ ንሰሐ የትይሆን መግቢያዬ በሥራዬ የትይሆን መግቢያዩ ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍሴ ወዲያልኝ ተሸክሜ የኃጢአት ክምር ይመሻል ይነጋል በከንቱ ስዞር ገሰገሰ ቀኑ ጨለመብኝ ዋ ለነፍሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩኝ በድያለሁ ወደ አንተ እጮሀለሁ ይቅር በለኝ እማፀንሃለሁ ችላ አትበለኝ ከፊትህ ቆሜአለሁ አለፈብኝ በከንቱ ጊዜዬ እየጓጓሁ ለዚች ለሥጋዩ በንስሐ ሳላጥበው እድፌን ልትደርስ ነው ያች የፈተና ቀን አዝ አልተወኝም ጌታ አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል ዛሬም ስበድለው ልጄ ነህ ይለኛል ዛሬም ስበድለው ልጄ ነሽ ይለኛል በበደል ጉራንጉር በኃጢአት ጫካ ብጠፋበት እንኳን አልተወኝም ለካ ዛሬም ልጄ ብሎ ዳግም ይጠራኛል ለካስ አልጠሳኝም ጌታ ይወደኛል አዝ ለስልጣን ለክብር ብዬ ስክደው ለገንዘብ አድልቼ እኔ ብረሳው ለእኔ ያለው አልቀነሰብኝም ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልጠላኝም አዝ ታዲያ ለዚህ ፍቅሩ ለሌለው ወሰን ከጭንጫ መቃብር ላወጣኝ እኔን በሕይወቴ ሁሉ ፍጹም ለመራኝ ክብርና ምስጋና አቀርባለሁኝ እዝ ገጽ በረቀቀው ፍቅርህ በረቀቀው ፍቅርህ አንተ ብትጠራኝ ዛሬ ይኸው ዳግመኛ መጣሁ በኃጢአት ዓለም ኖሬ ከቤትህ እርቄ ብሄድ ለዓለም ተገዛሁ አንተ ይቅር ትለኝ ዘንድ እንደገና መጣሁ በቆረስከው ሥጋህ ባፈሰስከው ደምህ ከዓለም ግዞት አውጥተህ አኑረኝ በቤትህ ዳግመኛ እንዳልበድልህ በዓለም ተታልዬ በቅዱሳንህ ምልጃ ጠብቀኝ ጌታዬ በዓለም የሠራሁትን ያሳዘንኩህን ሁሉ ይቅር በለኝ አምላኬ ስለ እግዝእትነ ኩሉ አቤቱ አንተን እጠራለሁ አቤቱ አንተን እጠራለሁ ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለሁ ዝም አትበለኝ እጮሃለሁ የኃጢአቴ ሸክም ከብዶኛል የሥጋ ወጥመድም አስሮኛል የሠይጣን ፍላጻ አጥቅቶኛል አዝ ደካማ ነኝ በጣም ችግረኛ ምስኪን ተስፋ ቢስ አነስተኛ ከመንጋው የራቅሁኝ ብቸኛ አዝ የቤትህ ናፍቆት አቃጠለኝ የቃልህ በረከት እራበኝ እባክህ ጌታ ይቅር በለኝ አዝ ከአንተ ኩብልዬ ተንከራተትኩ ምንም ላይረባኝ ከንቱ ባከንኩ ለበስባሽ ሥጋዬ ተገዛሁ አዝ ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ የንስሐን በር ክፈትልኝ መጣሁኝ ጌታ ተቀበለኝ አዝ አቤቱ ፈጣሪያችን አቤቱ ፈጣሪያችን መድኃኒታችን አምላካችን አባታችን በአንተ ላይ ነው ዘለዓለም ተስፋችን ቀንና ሌሊቱን የምታፈራርቅ አምላክ አንተ ብቻ ሥራህ የሚያስደንቅ አዝ መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ በረቂቅ ሥልጣንህ ሁሉን የምትገዛ አዝ በበደልነው በደል በሠራነው ሥራ ስለኛ ተቀበልክ ያን ሁሉ መከራ አዝ ሰይጣን በተንኩሉ እንዳያጠምደን በሕይወት ጉዳና ወደአንተ ምራን አዝ የዘላለም አምላክ የፍቅር የሰላም አቤቱ ተመስገን እስከዘለዓለም አዝ አምላኬ ሆይ አምላኬ ሆይ አትተወኝ ፈጣሪዬ ተመልከተኝ ምንም ብበድልህ የእጆችህ ሥራ ነኝ በዓለም ፍላጐት ታሥሬ እንዳልጠፋ አውጣኝ ከፈተና አንተው ሁነኝ ተስፋ ሥጋዊ ፈቃዴ ተበረታቶ ነፍሴ እጁጉን ተዳክማለች የእጆችህን ማዳን ተስፋ ታደርጋለች አዝ የሞትክልኝ አምላክ መድኃኒት ሆነህ መድኃኒት አንተ ለኔ አንዳይሠለጥኑብኝ ፍዳና ኩነኔ አዝ በሥጋህ በደምህ የገዛኸኝ የዋጀኸኝ ጌታ ኃይል የለኝምና ሁንልኝ መከታ አዝ ጊዜዬ እስኪደርስ ጊዜዬ እስኪደርስ ወደአንተ መምጫዬ ለንስሐ አብቃኝ አቤቱ ጌታዬ ብርሃኔ መድኃኒቴ ተስፋህ ይመልሰኝ ጥፋቴን ደምስሰህ ይቅርታ አድርግልኝ ተስፋዬ ረዳቴ አንተ አትጣለኝ አምላኬ አታጥፋኝ ከሲኦል አድነኝ አዝ መሓሪ ይቅር ባይ ምሕረትህ ይጉብኘኝ ከኃጢአት ፍላጻ ጸጋህ ይታደገኝ አዳጌ መድኃኒቴ ሰላምን ላክልኝ የድኅነት ደጆችህን በፍቅር ክፈትልኝ አዝ አቤቱ ምህረትህ በእኔ ላይ ይሁን ተጨነኩ ጌታዬ ስጠኝ ሰላምን ከክፉ እንድሸሽ አድነኝ እኔን በጎ እንድሠራ ምራኝ መንገዱን አዝ የበደሌ ብዛቱ የሚያስከፋም ቢሆን በሥጋ በደምህ እጠብ ኃጢአቴን ወደ አንተ እመጣለሁ አደራ ነፍሴን በሰማያዊ ቤት አኑር ሕይወቴን ደካማው ልጅህን ደካማው ልጅህን ሳትንቀኝ ጠርተኸኛልና እግዚአብሔር ሆይ ይድረስህ ምሥጋና አመፀኛ ነበርኩ የሸፈትኩኝ ከአንተ ተለይቼ ዛሬ ተመለስኩኝ በንስሐ ጥሪህን ሰምቼ ለካ አንተ አለህ ዘወትር ከአጠገቤ የበደሌ ብዛት ሳያግድህ ፈፅሞ ሳትንቀኝ በዓለም ስንከራተት ስቅበዘበዝ በምሕረት አይተኸኝ ተከትለኸ ወደ አንተ ጠራኸኝ ሳይገባኝ በቤትህ አኖርከኝ ኃጢአት ሸክም ሆኖ በመከራ ስኖር ተጨንቄ የሚያነሳኝ ጠፍቶ ተረስቼ ከትቢያ ወድቄ አንሥተኸኝ ጸጋህን ሰጠኸኝ ልጄ ብለህ ለክብር አበቃኸኝ የምሕረት እንጀራ ለሕይወቴ ባርከህ ስትሰጠኝ ዓይኔ ተገለጠ ብርሃን በራ መንገድህም ታየኝ ረጅም ነው የበዛው ፈተና የጠራኸኝ እርዳኝ እንድጸና አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ በበደሌ ብዛት አይተህ አትጣለኝ ሳስበው በደሌ ብዙ ነው በጨለማ ነፍሴን በላት ውድማ ሆዴ ባባ አፈስሳለሁ እንባ እርቃኔን ቀረሁኝ ተገፈፈ ልብሴ መድረሻው ጠፋብኝ ተጨነቀች ነፍሴ የብርሃን ጸዳሌ ከዓይኔ ተገፈፈ ከፊትህ ለመቆም ጉልበቴ ታጠፈ አዝ አልቻልኩም ደግፈኝ እንድቆም ለገነት ያበቃህ ያን ቀማኛ ሽፍታ እኔንም ደግፈኝ አውጣኝ የዛንለታ ጌታ ያለው ጌታ ያለው ሁሉም አለው የዘላለም ሕይወት ባለቤት ነው እመኑ በጌታ ይህ ብቻ ይበቃል የቀረውን እርሱ በፍቅሩ ይሰጣል አዝ ሰላም ላጡ ሰላም ፍቅርን ላጡ ፍቅርን ለታረዙ ልብስን ለተራቡ እንጀራን አዝ ለተጠሙ ውኃን ለታመሙ ፈውስን ተስፋ ላጡ ተስፋን ለደካሞች ኃይልን ንሰሐ እንግባ ንሰሐ እንግባ ኃጢአት መሥራት ይቅር የአምላክ ባለሟሎች እንሁን በምግባር ገጽ ምሕረትህ የበዛ መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ እውነተኛው አምሳክ የዓለም ሁሉ ቤዛ ከራስ ፀጉሬ ይልቅ ኃጢአቴም ቢበዛ በዓለም ተቅበዝብዝዢ እንዳልቀር በዋዛ ጥራኝ ልጄ ብለህ ድምፅህን አሰማኝ ብቸኛ ነኝና አለሁልህ በለኝ እንደእኔማ ቢሆን እንደ መኮብለሌ አይገባም ነበር ልጅህ ነው መባሌ ብርታት ሆነኝና ውለታህ መጣሁኝ አምላኬ ይቅር በለኝ ልልህ ንስሐን የሠራህ ገና ከጅምሩ ለጻድቃን አይደለም በሕግህ ለኖሩ እኔ በደለኛው መጥቻለሁና አንሣኝ በምሕረትህ አጅህን ዘርጋና የዓለም ፍቅር ስቦኝ ዳግም እንዳልጠፋ ከቤትህ ሳልወጣ እንድኖር በተስፋ በምሕረት እጆችህ ደግፈኝ ጌታዬ ከቅዱሳን ጋራ እንዲሆን ኑሮዬ ኑ እንቅረብ ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ ሥጋውን እንብላ ደሙንም እንጠጣ የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው ተሰውቶልናል እንመገበው እድፉን ኃጢአታችን በንስሐ አንጽተን እንቀበል አምነን በልጅነታችን መቅረብ ወደ ጌታ በእውነት የሚገባው በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው አዝ ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱለት ከዋክብተ ሰማይ የተነጠፉለት ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት አዝ ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ ለግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በእልልታ በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ አዝ ይኸን እድል ፈጥነን እንጠቀምበት ዓለምን አልያዝንም ብ ከአሁኑ ቅረቡ ታውጂሕ የይለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ ይኸ ዓለም ጠፊ ነው በሃብት አትመኩ ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ አድኅነነ አድኅነነ እግዚኦ አድኅነነ አምላክነ ዘአድኃንካ ለነነዌ ሀገር በትንብልና ትንብልና ሣሕልክ አድነን ጌታ ሆይ አድነን አምላካችን ያዳንካት ሀገረ ነነዌን በይቅርታህ በአምላካዊ ይቅርታህ አንድ ጊዜ የአግዚአብሔር ሆኛለሁ አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ሆኛለሁ በፍቅሩ ተስቤ በደሙ ድኛለሁ ዓለም ተይኝ ንቄ ትቼሻለሁ ጥበበኛው ሰይጣን በመጣው ቢመጣ ዳግም ተመልሼ ከእግዚአብሔር ላልወጣ ከመስቀሉ ግርጌ አርፌ እኖራለሁ ዓለም ተይኝ ንቄ ትቼሻለሁ አዝ ቢያሙኝ ቢያንቋሽሹኝ ቢሳለቁብኝ ውርደትም ተንኩልም ቢሸርቡብኝ ለኔ እንደው ደስታ ነው ኃዘንም የለኝ ሰይጣን እፈር የክርስቶስ ነኝ አዝ ጓደኞቼም ጠሉኝ ተለውጩያባቸው የጥንቱን ጠባዬን ስለነፈኳቸው ብቻዬን የሆንኩኝ ቢመስለኝም ለኔ ጌታ እንደሆን አለልኝ ከጉኔ አዝ አይደለም ምድራዊ ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍጹም ሰማያዊ እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ አምላካችን ሆይ አንተ ይቅር ባይ እንደቸርነትህ በደልን አትይ አሜን አሜን ብለን ተቀብለናል በድፍረትም ሳይሆን በፍርሃት ቀርበናል አዝ ማክበር ይገባናል በትኅትና ሆነን ደፍረን አናቅለው እንዳያቃጥለን እንደምታዩት ይህ ቁርባን ፈራጅ ነው እንደሌላው ሳይሆን የተቀደሰ ነው አዝ ሱራፌል ኪሩቤል ጸወርተ መንበር ለመያዝ ያልቻሉት ፈርተውት በክብር እኛ ተመገብነው አገኘን ድኅነት ለነፍስ ለሥጋችን ሆነልን ሕይወት አዝ ወደ ሕይወት መንገድ ወደ ሕይወት መንገድ ይመራኛል ጌታ በጨለማው መንገድ እንዳልንገላታ ፈጣሪ ብቻ ነው ሕይወቴና ክብሬ ለርሱ ደስ ይለኛል ሳቀርብ ዝማሬ ጉልበት ሁሉ ላንተ በፍርሃት ይሰግዳል ምሕረትን አድለን ፈጣሪ ቸል አትበል የሕይወትን ውኃ የተጠሙ ሁሉ ከኃያሉ ጌታ ከአንተ ይረካሉ በምሕረትህ ማረን አቤቱ ፈጣሪ ታት ሁሉ ነህና መሐሪ አድላት ለኢትዮጵያ እጆቿን ዘርግታ ስትል ሃሌ ሉያ ቸሩ መድኃኔዓለም ቸሩ መድኃኔዓለም የአዳም ልጆች ቤዛ አትበለኝ ችላ በደሌም ቢበዛ እመካብሃለሁ ቀንም ሆነ ማታ አንተ ነህ ጉልበቴ የድኅነቴ አለኝታ ያለአንተ ማን አለኝ ቸሩ ፈጣሪዬ የሕይወቴ ተስፋ አምባ መጠጊያዬ ልመናዬን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ እባክህ ጌታዬ አውጣኝ ከኃጢአት ማጥ አዝ ጐስቋላ ነኝ እና ኃጢአት ያሳደፈኝ ወደቤትህ ጠርተህ በንሰሐ እጠበኝ ፍቅርና ትኅትናን ጽድቅን ረስቼ አሳዝሼሃለሁ አምላኬ አንተን ትቼ አዝ በዚያች በፍርድ ቀን በቀኝ የሚያቆመኝ ገድልና ትሩፋት ምንም ስለሌለኝ እንዳልጣል ከእሳት ለዘላለም ስቃይ በቅዱሳን ጸሎት ማረኝ ጌታዬ ሆይ ወዳንተ እሰግዳለሁ ወዳንተ እሰግዳለሁ ሳለሁ በሕይወቴ ላንተም እዝለሁ እስከ ዕለተ ሞቴ አንተ ነህና መድኃኒቴ የዘለዓለም ቤቴ ሳይመሽብኝ ቀኑ ሳይጨልም ድንገት በጽድቅህ ጐዳና ልጓዝ ወደፊት ነሃ መንገዱን አሳየኝ እንዳልሳሳት የነፍስ የሥጋዬ የሕይወቴ ቤዛ አትበለኝ ችላ በደሌ ቢበ አንተን አምሼ እኖራለሁ ወዴት እሄዳለሁ አንተን አም እኖራለሁ ወዴት እደርሳለሁ ላይቀር መሞት ላይቀር መሞት አፈር መልበስ መግባት ከመቃብር መስሎኝ ቋሚ ይህ ሥጋዬ ለእርሱ ብቻ ስጥር ግን ለነፍሴ ቀረ ማስታወሴ ዘመን መቁጠር ዕለት ወራት ክረምትና በጋ ሌትና ቀን ሲፈራረቅ ሲጨልም ሲነጋ በማየቴ ይሆን መደሰቴ እረ ወዲያ ወዲያልኝ ዋ ይብላኝ ለነፍሴ አድርጐኛል የኃጢአት ምንጭ ደካማው መንፈሴ ላልኖር በዓለም ቆሜ ለዘለዓለም መሐሪ አምሳክ ለጋስ ጌታ ቸሩ ፈጣሪዬ አንተ እኮ ነህ ለዘለዓለም የኔ መመኪያዬ ይቅር በለኝ ምሕረትህ አይራቀኝ ገጽ መመኪያዬ አንተ ነህ መመኪያዬ አንተ ነህ የነፍሴ መዳኛ ተመልከት ወደ እኔ አትስጠኝ ለዳኛ ሕይወቴን ላንተ ብያለሁ አምላክ የኔ ጌታ የት አገኝሃለሁ ከበደሌም አንፃኝ ደግሞም ከኃጢአቴ በመንፈስ ይታደስ መላው ሰውነቴ አዝ አቀበቱ ልቤ በጭንጫ ትፅቢት አሸብርቆ ነበር አልፈርስም መስሉት አዝ የክብር ንጉሥ መምጣት ስለተነገረ መደልደል አለበት እየተሰበረ አዝ አለኝታችን አለኝታችን ይሁን ወደ ፈጣሪያችን እርሱ ስለሆነ የሕይወት ተስፋችንሃ ኢየሱስ ተሰቅሎ በቅዱስ መስቀሉ ሙሉ ተስፋ ሆነ ለአዳም ልጅ ሁሉ ለምታልፈው ዓለም መጨነቅ ይቅርብን ተስፋችንም ሁሉ በክርስቶስ ይሁን ዴማስ ሆይ ተመለስ የይሁዳ ጉዞ አያዋጣምና ዴማስ ወደ ሕይወት እባክህ ቶሎ ና ከወንጌል ገበታ መመገብ ጀምረህ ወንድሜ ተመለስ ወዴት ትሄዳለህ ይጠራሃልና መስቀሉን ተመልከት የወንጌል ቡቃያ እውነተኛ ሕይወት አዝ ብዙ ክርስቲያኖች መንገዱን ጀምረው የዓለም አሸንክታብ ድምቀት ሲጠራቸው ፈተና ሲመጣ ወንጌሉን ወርውረው ሞትን ይመርጣሉ ሕይወትን ሰርዘው አዝ የመስቀሉ ኅትመት ከልብህ ሳይጠፋ በእግዚአብሔር ጉባኤ መስክረህ በይፋ ልጁ የተባልከው በጥምቀት ቀለበት እንዴት ትሄዳለህ ተነድተህ ወደ ሞት አዝ የክብር አክሊሉ ተዘጋጅቶልሃል አምላክ ለሽልማት ዴማስ ሆይ ይልሃል ወዴት ትሄዳለህ እባክህ ተመለስ ክብርህን አትተው ከጫፉ ስትደርስ አዝ ባርከን ባርከን ልጆችህን ባርከን በቅዱስ መንፈስህ አንድ ሐሳብ አድርገን ባርኪን ልጆችሽን ባርኪን ድንግል ሆይ በምልጃሽ አንድ ሐሳብ አድርጊን ድንግል ሆይ በምልጃሽ ከልጅሽ አስታርቂን ጥሪህን ስንሰማ ወዳንተ እንድንመጣ በሕግህ ልንኖር ከቤትህ ሳንወጣ በሕይወት ስንደክም እንዳንጠፋ በዓለም እርዳን ፈጣሪያችን ቸሩ መድኃኔዓለም ባርከን ከተፈረደብን የባርነት ሕይወት ከመጣብን መርገም በመብል ምክንያት ከሲኦል እሥራት እኛ የዳንብሽ ድንግል ሆይ ምንጊዜም አይለየን ምልጃሽ ባርኪን አንድነት ስናጣ ፍቅር ስትመነምን በምግባር ስንደክም ሲጐድል እምነታችን በሥጋችን ፈቃድ ወድቀን እንዳንጠፋ በምሕረትህ ጉብኘን አንተ ሁነን ተስፋ ባርከን ርኅርኅተ ኅሊና ቅድስት እናታችን አሳስቢ ሁልጊዜ ስለኃጢአታችን ሊያድነን ነውና ክርስቶስ መሞቱ አሥምሪን እአምላክ ድንግል ወላዲቱ ባርኪን ልቤ አቤት በል አንጅ ልቤ አቤት በል እንጅ አምላኬ ሲጣራ ኃጢአትን ተውና መልካም ምግባር ሥራ በደሌን አውቄ ይቅርታ ልጠይቅ ሁሉን ቻይ ነህና ፍጥረትን የማትንቅ አለቅሳለሁ ዘወትር አነባለሁ አውቃለሁ አምላኬ ብዙ በድያለሁ ለቅሶና ጩኸቴን ተቀበለኝ ጐስቋላ ሆኛለሁ ኃጢአት ያደከመኝ መንገድ ተላልፌ ፈጣሪ አስቀየምኩህ በሚጠፋ ንብረት አምላኬ ለወጥኩህ አሁን ግን አምኙ ብዙ እንደበደልኩህ ምሕረትን እንዳገኝ ይቅርታ ለመንኩህ አዝ የኃጢአት መጋረጃ ፊቴን ሸፍኖታል ኃይሌ ከኔ ርቆ መቆም ተስኖኛል ነሽና በፊቱ ክብር ሞገስ ያለሽ ድንግል ልመናዬን አድርሽ ከልጅሽ አዝ ጉልበት አንተ ሁነኝ መተማመኛዬ በደሌን አጥፋልኝ ሁን አስተማሪዬ ከበደል እንድርቅ እጅህን ዘርጋና ዳግም እንዳልበድል አጽናኝ በምስጋና አዝ ማረ ማረኝ ይቅር በለኝ ማረኝ በኃጢአቴ ብዛት ወድቄአለሁና ነፍሴም ለሥጋዬ ተገዝታለችና ልቦናዬ ዝሉ በበደል ወድቄ እንድመለስ እርዳኝ ፍቅርህን አውቄ አዝ ኑሮዬ በዓለም ፈቃድ ተገንዞ ንስሐን እምቢ አለ በክፋት ደንዝዞ አንተው ካልመለስከው ልቤን በኃይልህ ኃጢአቴ ብዙ ነው አልችልም ላይህ አዝ ለዓለም መዝዛቴን ድካሜን እይና ጎብኘኝ በምሕረትህ በእምነት እንድጸና ምግባሬን አድሰህ ፍቅር አጎናጽፈህ አንጽተህ ሕይወቴን ልኑር በቤትህ ምሕረትን እንለምን በሥጋችን ፈቃድ የታሠርን ሁላችን ምሕረትን እንለምን ከቸሩ አምላካችን በኃጢአት ምክንያት መጉስቆልን አይቶ አይጨክንም ጌታ ይምረናል ራርቶ ምንም ብንበድለው ኃጢአት ቢበዛብን ታማኝ ነው ጌታችን ሁሉን ይቅር ሊለን ስለዚህ ወገኖች ክርስቲያኖች ሁሉ ንስሐ ለመግባት ዛሬ ነገ አትበሉ ለዓለም ፈቃድ መኖር እንግዲህ ይብቃና ለአምላክ እንገዛ እንመለስና ዓለምን ዞሬ ዓለምን ዞሬ አየሁት ሁሉን በተራ ቀመስኩት ፈጽሞ የለም ሰላም እንደልጅሽ ቤት ሀብት ንብረቴን ጨረስኩና ጉልበቴ ሁሉ ደከመና ጐስቋላ ሆንኩኝ ደካማ የሌለው ጤና ስቃ አሳስቃ ተቀብላ መልኳን አስውባ ተኳኩላ ዛሬ ጣለችኝ ይህች ዓለም አይረባም ብላ የትናንትና ወዳጆቼ ዛሬ ሲሆኑኝ ጠላቶቼ ባክ ቀረሁ በዓለም ላይ ተንከራትቼ የአባቴ ቤት ሲናፍቀኝ ፍቅሩ ምሕረቱ ትዝ ሲለኝ ሁሉንም ትቼ ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁኝ ልጁም እንድባል ባይገባኝ ባርያው እሆን ዘንድ ቢፈቅድልኝ ጐስቋላው ልጁ ደካማው ልጁ ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁኝ እናቴ አንቺን ንቄ ትቼ የአባቴን ቤት እረስቼ ተሰቃየሁኝ ተንከራተትኩኝ ልደሰት በዓለም ገብቼ አባቴ ሲያየኝ ተደስቶ ጐረቤቶቹን ሁሉ ጠርቶ ሠርጉን ደገሰ የበደልኩትን ረስቶ አስከ አሁን ድረስ በድያለሁ ዓለም ደህና ሁኝ አብቅቻለሁ ወደ አባቴ ቤት ዳግመኛ ተመልሻለሁ ገጽ በሞት ጥላ ወድቀን በሞት ጥላ ወድቀን ስንከራተት በረቀቀው ፍቅሩ ዋጀን ከጥፋት በጐልጐታ የታየው ፍጹም መድኃኒት ሃሌ ሃሌ ሉያ ለአንተ ለኃያሉ ጌታ ስለኛ ተዋረድክ በጐጉልጉታ የሞት ሸክም ከብዶን በጣር ስንባዝን ወረደ ከሰማይ መጣ ሊያድነን ከባርነት ሸክም ነፃ ሊያወጣን አዝ ምንም ባልበደለው ምንም ባላጠፋው ሁሉን ማድረግ ሲችል ደካማ የሆነው ሕይወትን ሊያድለን ስለወደደን ነው አዝ እስቲ አስተውሉ የፍቅሩን ብዛት በመስቀል ተሰቅሎ እኛን ያዳነበት ምንም አቻ የለው የጌታ ቸርነት አታውኪኝ ነፍሴ አታውኪኝ ነፍሴ አታስጨነቂኝ በዓለም መድኃኒት በእግዚአብሔር ታመኝ ዋልያ እንደ ሚና ወደ ውኃ ምንጮች አቤቱ ወደ አንተ ነፍሴ ናፈቀች አዝ መቼ ተነስቼ መቼ እደርሳለሁ የአምላኬን ፊቱን መቼ አየዋለሁ አዝ የሕይወትን ውኃ እያስታወሰች ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች አዝ እንማልድሃለን እንማልድሃለን ጌታ ሆይ በአፀደ ቤተክርስቲያን ተሰብሰበን ሥራችንም እንዲቃና ተገኝ በማዕከል በማዕከላችን የነፍሳቸን ቤዛ የዓለም መድኃኒት ለእውነተኞች ጸጋ ለአዳም ሕይወት ፈቃድህ ትምጣልን በዛሬዋ ዕለት ጀምረናልና በስምህ ጸሎት አዝ ስምህን ለመቀደስ በረቂቅ ምሥጢር አንድነት በመሆን በመተባበር እውነትን አጉልተን እንድንናገር አድለን ለሁሉም አምላክ የአንተን ክብር አዝ ፈቃድህ ሆኖልን ንበር ከእኛ ጋራ ነው ጸሎት ፍሬን እንዲያፈራ በሕግህ ተመርተን ክብርህን እንድናይ እንደ በደሌማ እንደ በደሌማ ከሆነ ቅጣቴ አያልቅም ተነግሮ ብዙ ነው ጥፋቴ እንጃልኝ ፈራሁኝ አዬ ሰውነቴ እመለሳለሁኝ እያልኩኝ ጠዋት ማታ ዘመኔን ጨረስኩት ሳስብ ሳመነታ ምን እመልስ ይሆን የተጠራሁ ለታ በላዬ ሲያንዣብብ ሞት እጁን ዘርግቶ ሥጋዬን ሲውጠው መቃብር ተከፍቶ የነፍሴ ማረፊያ ወዴት ይሆን ከቶ ይቅር ባይ ነህና የበደሉህን አቤቱ ጌታ ሆይ እኔን ባሪያህን ይቅር በለኝና ልየው ፊትህን እንደቸርነትህ እንደቸርነትህ አቤቱ ማረኝ አንደ ምሕረትህም ይቅርታን ስጠኝ ከኃጢአቴም አንፃኝ ከብዙ በደሌ ለዚያች ክፉ ኃጢአት እንዳልሆናት ሎሌ እኔም አመፃዬን በደሌን ሳውቀው ከቶ የሚያድነኝ ቸርነተህ ነው አንተን ብቻ በደልሁ ክፉም አደረግሁ አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቅሁ ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን መውደቄን ተመልከት አምላክ ብርሃን እያለፈ ነው ዘመኔ እያለፈ ነው ዘመኔ ትዕዛዙን ሳልፈጽም ወየው ለኔ በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ ና ብሉ ወደ እኔ በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ ብዙ አዝመራ ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ ልኑር ከአንተ ጋራ የማስብበት በየዕለቱ ንጹሕ ልብን ስጠኝ አቤቱ ከትዕዛዝህ ውጭ በመሆን እንዳልቀር በከንቱ እንደየሥራው ለመክፈል በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፈተናን የወጣ እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ እየተማራችሁ ከቃሉ ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ ትዕግሥትን በመያዝ ሁላችሁ እስከ መጨረሻው ጠንክሩ ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ አባታችን ሆይ አባታችን ሆይ የምትኖር በሰማይ መንግሥትህ ትምጣልን ክብርህን እንድናይ ፈቃድህ በሰማይ ሕይወት እንደሆነ እንዲሁም በምድር ሰላምን ስጠነ ስጠን ለዛሬ የዕለት ምግባችንን በደላችንንም ይቅር እንድትለን ጌታ ሆይ አታግባን ከክፋ ፈተና አንተ ካልረዳኸን ኃይል የለንምና ኃይልና ምስጋና መንግሥትም የአንተው ናት አሜን ለዘላለም ይሁንልን እረፍት የሰው ልጅ ሁልጊዜ የሰው ልጅ ሁልጊዜ በጣም ደስ ቢለው ደግሞም የጭንቁን ቀን ማሰብ ተገቢ ነው ምንም ቢደሰቱ ቢበዛ ምቾት አይቀርም በኋላ መወሰድ በሞት ችግር ቢፈራረቅ ኅዘን ቢከበን ከክርስቶስ ፍቅር ማንም አይለየን ሳናውቀው ዲያብሎስ እንዳይነጣጥለን ነቅተን እንጠብቀው የእምነትን ሰይፍ ይዘን የሰው ልጆች ሁላችን እንማር የሰው ልጆች ሁላችን እንማር አስተባብረን ሃይማኖት ከምግባር የሰው ልጆች ሁላችን እንማር መልካም ሥራ በመሥራት እንኑር የሰይጣን ድል መንሻ የክብር መውረሻ ሃይማኖት ናትና እውነተኛ ጋሻ አዝ ለእውነተኛ ሥራ ሁላችን እንበርታ ጻድቃን ሰማዕታትን አድርገን መከታ አዝ ፍዳ ዓለምን አልፈን እንድንሄድ ሁላችን ፀንተን መገኝት ነው በሃይማኖታችን አዝ እምነታችን ሁሉ ይሁን በፈጣሪ ይቅር ባይ ነውና ፈጽሞ መሐሪ አዝ የአዋጅ ነጋሪ ቃል የአዋጅ ነጋሪ ቃል በበረሃ አየለ የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክሉ እያለ ምስክርነቱን ዮሐንስ ካስረዳን ልባችን ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም ዐውደ ዓመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና ካለተስተካከለ መንገድ የለምና የእግዚአብሔርን መንገድ እንመሥርት ሁላችን ማለፊያ እንዲሆነን ለመጭው ሀብታችን አዝ ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ ጽድቅና ርኅራሄ በኛ ላይ ይስፋፋ ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል ሕይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል አዝ ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን ከበደላችንም አንፃን አደራህን በክፉ እንዳንጠፋ እኛ ባሮችህን አዝ ገጽ ቅዱሳን በሙሉ ቅዱሳን በሙሉ ከአምላክ አማልዱን ልንጠፋ ነውና በዝቶ በደላችን ጻድቃን ሰማዕታት ንጹሐን ሁላችሁ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ዓለምን ንቃችሁ ለሰማያዊ ክብር ለአክሊል የበቃችሁ ወደ አምላክ አቅርቡ በጽኑ ምልጃችሁ ድንግል እናታችን ኪዳነ ምሕረት ቅድስተ ቅዱሳን የጻድቃን እናት ርኅርኅተ ኅሊና አሳስቢ ከልጅሽ ይቅርታ እንድናገኝ በፍጹም ልመናሽ ምግባርም አልሠራሁ ምግባርም አልሠራሁ እምነትም ጉደለኝ በቃልህ አንፀህ በሕይወት አቁመኝ ኃጢአት የጋረደኝ ደካማ ነኝና አስበኝ አምላክ ሆይ በሃይማኖት ልፅና አንሳኝ በምሕረትህ ፈፅሜ እንዳልጠፋ በሥጋዊ ድካም በቀቢፅ ተስፋ በቅዱሳን መላእክት ፊትህ በሚቆሙ በድንግል እናትህ በአክባሪተ ኩሉ በቅዱሳንና በፃድቃን ሰማዕታት በቃል ኪዳናቸው አድነኝ ከጥፋት ለቀደሙት አበው በገባኸው ኪዳን አቁመኝ በቀኝህ በመጨረሻው ቀን ምንም ብበድልህ ኃጢአት ቢነግሥብኝ ስለወዳጆችህ አምላክ ይቅር በለኝ ልቦናዬን አንፃው ሕይወቴም ትታደስ አቁመኝ በቀኝህ ፍቅርህን እንድቀምስ በሥጋህ በደምህ የሆንክልኝ ቤዛ ትሁት ሰው አድርገኝ ለአንተ የምገዛ የቅዱሳን አምላክ አብርሃምን ከካራን የጠራኸው ጌታ ለሙሴ በሲና የሆንከው መከታ ልጠፋ ነውና በሥጋ ፍላጉት የይስሐቅም ቤዛ ሕይወቴን ታደጋት የኤርትራን ባሕር በኃይልህ የከፈልክ በሲና በረሃ ሕዝብህን የመገብክ ኖኅ ከጥፋት ውኃ የዳነብህ አምላክ ሎጥን እንዳዳንከው ፍጹም ምሕረትህን ላክ የተነበዩልህ ነቢያት በሙሉ አምላክ ሰው ይሆናል ይወለዳል ሲሉ ከዓሣ አንበሪ ሆድ ዮናስን ያወጣህ ዓለም ልትውጠኝ ነው አይለየኝ ጸጋህ ሥጋን ተዋሕደህ በወሰንክው ሰዓት የሞትክልኝ አምላክ ያዳንከኝ ከሞት ሞት እንደወንጌልህ ሕግ የምኖር አድርገኝ በመጨረሻው ቀን በቀኝህ እንድገኝ አልቻልኩኝምና ልፈፅም ሕግህን የሐዋርያት አፅናኝ ስጠኝ ብርታትህን ምግባረ ጉደሉ ሆኛለሁኝና የቅዱሳን አምላክ እርዳኝ እንድፀና መንገድህን አሳየኝ መንገድህን አሳየኝ እከተልሃለሁ ይህን ከንቱ ዓለም ስለ አንተ እተዋለሁ በእውነት ይቅር በለኝ ብዙ በድያለሁ ኃጢአቴ እ በዝቶ ማየት ተስኖኛል ብርሃኔ ጠፍቶብኝ ጨለማው ከቦኛል ከራስ ፀጉሬ በዝቶ የኔማ በደል ልቤ ትታኝ ሄደች አለመታደል አዝ ጨለማ ዙሪያዬ ብርሃን የሌለበት የዓለም ግዞተኛ አደረገኝ ኃጢአት ልቤ ታሥሮ ቀርቷል በምኞት ገመድ ነፍሴም ተስኗታል መውጣት ከወጥመድ አዝ ሥጋዬ አሸንፎኝ ከመንገዴ አውጥቶኝ እግሬ እንዳይራመድ ጉልበቴ ደክሞብኝ ከድካሙ ብዛት ሥጋዬ አንቀላፋ ነፍሴ ሆይ ተመለሽ አትቁረጪ ተስፋ አዝ ኃጢአቴ ተጭኖኝ ሸክሙ ከብዶብኛል በበደል መኖሬ አሁን ጸጽቶኛል በዓለም ስባዝን አምላክ አግ ራስህን ለካህን አሳይ ብሎኛል አባታችን ሆይ አባታችን ሆይ የሁላችን ጌታ ቅዱስ መንፈስህ አይራቀን ጧት ማታ ወደአንተ መልሰው የሰውን ልቡና ባላወቀው መንገድ አርሱ ሄጻልና እዝነ ልቡናህን ወደ እኛ አዘንብል ይቅርታ ልንጠይቅ ከፊትህ ቆመናል ይቅርታ ልንጠይቅ ከፊተህ የቆመነው መሐሪ መሆንክን ስለምናውቅ ነው ትዕግስትህ ሰፊ ነው አያልቅም ምሕረትህ የፍቅር ባለቤት ይቅር ባይ አንተ ነህ አይቶ እንዳላየ ታልፈዋለህ ሁሉን መዓቱም ምሕረቱም ሁሉም ያንተው ሲሆን ሥልጣንህ ረቂቅ ነው አይመረመርም ዘመንና ወራት ሊሽሩት አይችሉም የፍቅር ባለቤት ቸሩ አምላካችን አድሜን ለንሰሐ ስጠን ለሁላችን እንማልድሀለን በለቅሶ በኃዘን የይቅርታህ ብዛት ከኛ ጋር አንዲሆን በእንተ ጾም ንጹም ጾመ ንጹም ጾመ ወናፍቅርቢጸነ ወንትቅፋቀር ንትፋቀር በበይናቲነ ትርጉም ጾምን እንጹም ወንድሞ እንውደድ እርስ በእርሳችን እንዋደድ ፍቅርና ሰላምን አምላክ ተፈተነ በክፉ ጠላት ፆምን ሲመሠርት ስለኛ ሕይወት ፍቅርና ሰላምን ታፈራለች ፆም ፍፃሜ የሌለው እስከ ዘለዓለም የፆምንም ፍሬ ሁላችን አውቀን ተግተን እንያዘው ፍሬው አይለፈን ማርያም በስምሽ ማርያም በስምሽ ይዘናል ቀኖና ትንሣኤሽን ልጅሽ ያሳየናልና ፆም ማለት እንግዲህ ይኸው ነው ሥርዓቱ ሐዋርያት ፆመው ለእኛ አበረከቱ ነፍስና ሥጋችን በመብል ተጣልተው ሽማግሌ ሆኖ ፆም አስታረቃቸውወ አብረው እያደሩ አብረው እየዋሉ አያምርም አይመስልም በመብል ሲጣሌ ነፍስም ከሥጋዋ መለየቷን አውቃ የዓለም ተድላዋን ደስታዋንም ንቃ በፆም በሱባኤ ትኖራለች ታጥቃ ነፍስም ለሥጋዋ ትመክረው ጀመረች በብዙ ምሳሌ እያመሳሰለች ሥጋዬ ሞኝ ነህ መብልን አትውደደው ከአዳም አንሥቶ ከመጀመሪያው ሰው ለመብል መዝዛት ሲጠቅም መች አየኸው ገጽ።