Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

የሰብዓዊ_መብቶች_ዓለም_አቀፍ_ቃል_ኪዳኖች_በአማርኛ፣_2001_ዓ_ም.pdf


  • word cloud

የሰብዓዊ_መብቶች_ዓለም_አቀፍ_ቃል_ኪዳኖች_በአማርኛ፣_2001_ዓ_ም.pdf
  • Extraction Summary

አንቀጽ ማንም ሰው ለነፃና የተሟላ ስብእናው ብቸኛ መሰረት ለሆነው ማህበረሰብ ግዴታዎች አሉበት የሌሎች ሰዎች መብቶችና ነፃነቶች ለመጣስ በሚያስችል ድርጊት ወይም እንቅስቃሴ የመሳተፍ መብት አላቸው ኮሚቴውም ከስምምነቱ አፈፃፀም አንፃር እነሱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የታወቀ ችሎታ ያላቸውን አስር ኤክስፐርቶች በአባልነት የሚይዝ ይሆናል የኮሚቴው አባሎች የሥራ ዘመን የመጀመሪያው ምርጫ እንደተካሄደ የዘጠኙ የኮሚቴው አባላት በኮሚቴው የተሰጣቸው የስራ ሃላፊነት በሚያከናውኑበት ወቅት የሚያስፈልጋቸው ወጪ የመሸፈን ግዴታ አለባቸው አንቀጽ ይህንን ስምምነት የተቀበለ አንድ አገር ስምምነቱን የተቀበለ ሌላ አገር የስምምነቱን ድንጋጌዎች ተግባራዊ አላደረገም የሚል እምነት ከያዘ ጉዳዩን ለኮሚቴው ማቅረብ ይችላል። የተመዘገበው ተአቅቦ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከአንድ ዓመት በኋላ ይሆናል አንቀጽ በስምምነቱ አተረጓጎም ወይም አፈፃፀም ዙርያ በሁለት ወይም ከሁለት በላይ በሆኑ የስምምነቱ ፈራሚ አገሮች የሚነሳ ውዝግብ በውይይት ወይም በስምምነቱ በሰፈሩ ስነ ስርዓቶች መፍታት ካልተቻለ የጉዳይ ባለቤት ከሆኑት አገሮች መካከል በአንዱ በኩል ወደ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት ለውሳኔ መቅረብ ይችላል።

  • Cosine Similarity

እነዚህ ዘገባዎችም የድርጅቶቹ አካላት በአፈፃፀም ረገድ ያደረጓቸውን ውሳኔዎችና ያቀረቧቸውን ሃሳቦች ዝርዝር ሊያካትቱ ይችላሉ አንቀጽ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክር ቤት በአንቀፅ እና መሰረት አገሮች ያቀረቡለትንና በአንቀጽ መሰረት ልዩ ተልእኮ ከተሰጣቸው አካላት የቀረቡለትን ሰብአዊ መብቶችን የሚመለከቱ ዘገባዎች ለጥናት ለውሳኔና እንደየሁኔታው ለመረጃ እንዲያገለግለው ለሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሊያስተላልፍለት ይችላል አንቀጽ የዚህ ቃል ኪዳን ተዋዋይ አገሮችና የሚመለከታቸው ልዩ ተልእኮ የተሰጣቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላት በአንቀጽ መሰረት በሚቀርብ ማናቸውም የወሳኔ ሃሳብ ወይም በሰብአዊ መብት ኮሚሽን በሚቀርብ ሰነድ ወይም በሰነዱ በተመለከተ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክር ቤት ማቅረብ ይችላሉ አንቀጽ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክር ቤቱ በቃል ኪዳኑ የተገለፁትን መብቶች በማስከበር ረገድ የተሰወዱ እርምጃዎችን እና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ በተመለከተ አጠቃላይ ዘገባዎችንና የውሳኔ ሃሳቦች እንዲሁም በዚህ ረገድ ከአባል አገሮችና ልዩ ተልእኮ ከተሰጣቸው አካላት የሚቀርቡለትን መረጃዎች በማጠናቀር ለጠቅላላ ጉባኤው በየጊዜው መግለጫ ያቀርባል አንቀጽ የቃል ኪዳኑን ድንጋጌዎች በማስከበር ረገድ ባላቸው የስልጣን ክልል ውስጥ ተገቢ የሆኑ እርምጃዎች ለመውሰድ ይችሉ ዘንድ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክር ቤት በዚህ የቃል ኪዳኑ ክፍል መሰረት የሚቀርቡለትን ዘገባዎች ወይም ዘገባዎቹ ካካተቱዋቸው ጉዳዮች ተገቢ የሆኑትን ፍሬ ነገሮች ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሌሎች አካላትና ለእነርሱ ተጠሪ ለሆኑ ክፍሎች እንዲሁም ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት ረገድ ልዩ ተልእኮ የተሰጣቸው አካላት እንዲያውቋቸው ሊያደርግ ይችላል አንቀጽ የዚህ ቃል ኪዳን አባል አገሮች በዚህ ቃል ኪዳን ውስጥ ዕውቅና ያገኙትን መብቶች ለማስከበር የሚደረግ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ቃል ኪዳኖችን መፈፀም የውሳኔ ሃሳቦችን መቀበል የቴክኒክ ዕርዳታ ማቅረብ ከሚመለከተው አገር ጋር በመተባበር ለምክክርና ለጥናት የሚደረጉ አካባቢያዊ ቴክኒካዊ ስብሰባዎችን ማካሄድና የመሳሰሉትን እንደሚችሉ ተስማምተዋል አንቀጽ የዚህ ቃል ኪዳን ማንኛውም ድንጋጌ በቃል ኪዳኑ የተገለፁትን ጉዳዮች በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር ወይም ልዩ ተልእኮ የተሰጣቸው አካላቱ በተቋቋሙባቸው ደንቦች ውስጥ የሚገኙትን የአካላቱን ተግባርና ኃላፊነት የሚወስኑ ድንጋጌዎችን እንደሚያፋልስ ሆኖ አይተረጎምም አንቀጽ ማንኛውም የዚህ ቃል ኪዳን ድንጋጌ ማንኛውም ሕዝብ የተፈጥሮ ሃብቱን በሙሉና በነፃ ለመጠቀም ያለውን ተፈጥሮአዊ መብት እንደሚገድብ ተደርጎ አይተረጎምም ክፍል አምስት አንቀጽ ይህ ቃል ኪዳን ለማንኛውም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል አገር ወይም ልዩ ተልእኮ የተሰጣቸው አካላት አባል አገር የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መተዳደሪያ ሕግን ለተቀበለ አገር በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ የዚህ ቃል ኪዳን ፈራሚ እንዲሆን ለተጋበዘ አገር ለፊርማ ክፍት ነው ይህ ቃል ኪዳን በየአገሩ የሕግ አውጪ አካል ፀድቆ ተቀባይነት ማግኘት አለበት ቃል ኪዳኑ የፀደቀበት ማረጋገጫ ሰነድ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ መቅረብ አለበት ይህ ቃል ኪዳን በዚህ አንቀጽ ቁጥር ውስጥ ለተጠቀሱት አገሮች እንዲቀበሉት ክፍት ይሆናል የአገሮች መቀበል የሚረጋገጠው የመቀበያ ሰነዱን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ዘንድ በማኖር ነው የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ይህን ቃል ኪዳን ለፈረሙ ወይም ለተቀበሉ አገሮች የማፅደቁያ ወይም የስምምነት ማረጋገጫ ሰነዶችን መረከቡን ያስታውቃቸዋል አንቀጽ ይህ ቃል ኪዳን ሰላሳ አምስተኛው የማፅደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ከቀረበበት ከሶስት ወራት በኋላ የፀና ይሆናል ሠላሳ አምስተኛው የማፅደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ ከቀረበ በኋላ ይህንን ቃል ኪዳን ያፀደቀ ወይም የተቀበለ እያንዳንዱ አገር የራሱን የማፅደቂያ ወይም የመቀበያ ማረጋገጫ ሰነድ ካስረከበበት ከሶስት ወራት በኋላ ቃል ኪዳኑ በአገሩ የፀና ይሆናል አንቀጽ ፌዴራላዊ አስተዳደር ባላቸው አገሮች የዚህ ቃል ኪዳን ድንጋጌዎች በሁሉም የአስተዳደር ክልሎች ያለምንም ገደብ ወይም ልዩነት ተፈፃሚ ይሆናሉ አንቀጽ ማንኛውም የዚህ ቃል ኪዳን አባል አገር የማሻሻያ ሃሳብ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ማቅረብ አና ይሄው ሃሳብም በፀሐፊው ዘንድ እንዲቀመጥለት ማድረግ ይችላል። ሮቻ ዳዲያወሮድሪቋፖ ዳና አሕዲፇፅታሥ ያፇረያ ኃራ ይ ያዎኃያፖ ሪፖ ዕሳፇሪ « መሥረሦፖ ማሜደቻ ፇ ም ኃታ መግቢያ የዚህ ቃል ኪዳን ተዋዋይ አገሮች በተባበሩት መንግስታት ቻርተር መርሆች መሰረት የሰው ዘር በሙሉ አብራቸው የተፈጠረ ክብር ያላቸው መሆኑን እኩል እና ከስብእናቸው ሲነጠሉ የማይችሉ መብቶች የሏቸበው መሆኑን አውቆ መቀበል ለነባነትለፍትሕና ለአለም ሰላም መሰረት መሆኑን በመገንዘብ እነዚህ መብቶች ሰው በሰውነቱ ከተጐናፀፈው ተፈጥሮአዊ ክብር የሚመነጩ መሆናቸውን በማወቅ በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ መሰረት ሰዎች ከፍርሃትና ከድህነት ነፃ ሆነው የሚኖሩበት ዓለም ሊፈጠር የሚችለው እያንዳንዱ ሰው የሲቪል አና የፖለቲካ መብቶቹን እንደሁም የኢኮኖሚ የማህበራዊ እአና የባህላዊ መብቶቹን ለመቀዳጀት የሚያስችሉት ሁኔታዎች ሲፈጠሩለት ብቻ መሆኑን በማወቅ ሰብዓዊ መብቶችና ነፃነቶች በመላው ዓለም እንዲከበሩና እንዲጠበቁ ለማድረግ በተባበሩት መንግስታት ቻርተር መሰረት አገሮች ያለባቸውን ግዴታ በመገንዘብ ግለሰቡም ለሌሎች ግለሰቦችና ለሚኖርበት ሕብረተሰብ ኃላፊነት ስለአለበት በዚህ ቃል ኪዳን የተደነገጉት መብቶች እንዲከበሩና እንዲጠበቁ የበኩሉን ጥረት ማድረግ ያለበት መሆኑን በመረዳት በሚከተሉት አንቀጾች ላይ ተስማምተዋል ክፍል አንድ አንቀጽ ሁሉም ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት አላቸው ይህንን መብት በመጉጐናፀፋቸው የፖለቲካ ሕልውናቸውን በነፃነት የመወሰን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ባሕላዊ ዕድገታቸውን በነፃነት የማራመድ መብት አላቸው ሁሉም ሕዝቦች በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት እና በጋራ ጥቅም መርሆ ላይ የተመሰረተውን ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትብብር ግዴታቸውን ሳይጥሱ የተፈጥሮ ሀብታቸውንና ሌሎች ሃብቶቻቸዉን ለየራሳቸው አላማ በነፃነት መጠቀም ይችላሉ በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን አንድ ሕዝብ ለኑሮው አስፈላጊ የሆኑትን ጥቅሞች ሊነፈግ አይገባም ራሳቸውን ለማያስተዳድሩና በሞግዚት ለሚተዳደሩ ግዛቶች የማስተዳደር ሃላፊነት ያለባቸው አገሮችን ጨምሮ የዚህ ቃል ኪዳን ተዋዋይ አገሮች ሁሉ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ከተባበሩት መንግስታት ቻርተር ድንጋጌ ጋር በሚጣጣም ሁኔታም ተግባራዊ እንዲሆን ይጥራሉ ይህንን መብት ያከብራሉ ክፍል ሁለት አንቀጽ እያንዳንዱ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበለ አገር በግዛቱ ውስጥ ለሚኖርና በስሩ ለሚተዳደር ማንኛውም ግለሰብ በዘር በቀለም በጾታ በቋንቋ በሃይማኖት በፖለቲካ ወይም ሌላ አመለካከት በብሔራዊም ሆነ ማህበራዊ አመጣጡ በሀብት በትውልድ ወይም በሌላ መለኪያ ምንም ልዩነት ሳያደርግ በዚህ ሕግ ዕውቅና ያገኙትን መብቶች ሊያስከብርለትና ሊያረጋግጥለት ተስማምቷል በስራ ላይ ባሉት የአገሩ ሕጎች ወይም ሌሎች እርምጃዎች መሰረት እነዚህ መብቶች ከአሁን በፊት ፅውቅና ያልተሰጣቸው ከሆነ እያንዳንዱ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበለ አገር በአገሩ የሕግ አወጣጥ ስርዓትና በዚህ ቃል ከዳን ውስጥ ባሉት ድንጋጌዎች መሰረት መብቶቹን ተግባራዊ የሚያደርጉ ሕጐች ለማውጣትና ሌሎች አስፈላጊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ተስማምቷል እያንዳንዱ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበለ አገር የሚከተሉትን ለመፈፀም ተስማምቷል ሀ ማንኛውም ሰው በዚህ ሕግ ዕውቅና ያገኙት መብቶቹና ነፃነቶቹ ሲጣሱበት እነዚህ መብቶችና ነፃነቶች የተጣሱበት በመንግስት ባለስልጣኖች ቢሆንም እንኳ ለደረሰበት በደል ውጤታማ መፍትሔ እንዲያገኝ ለማድረግ ለ ለደረሰበት በደል መፍትሔ የሚሻ ማንኛውም ሰው ስልጣን ባለው የፍትሕ የአስተዳደር ወይም የሕግ አውጪ አካል ወይም በአገሪቱ የሕግ ስርዓት መሰረት ስልጣን በተሰጠው ሌላ አካል መብቱ እንዲረጋገጥለት ለማድረግና ፍትሕ እንዲያገኝ ለማመቻቸት ሐ የፍትሕ ውሳኔ ሲያገኝም ስልጣን በተሰጣቸው አካላት ውሳኔውን ለማስፈፀም አንቀጽ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች በዚህ ድንጋጌ የሰፈሩትን የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ወንዶችና ሴቶች በእኩልነት በመጠቀም ረገድ ያላቸውን መብት ለማረጋገጥ ተስማምተዋል አንቀጽ ይሀን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች የአገራቸውን ሕልውና የሚያናጋ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሲከሰትና ይህም በይፋ የታወጀ ሲሆን ሁኔታውን ለመቆጣጠር በሚያስፈልገው መጠን ልክ ብቻ በዚህ ቃል ኪዳን ከተቀበሏቸው ግዴታዎች ለየት ያሉ አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ ሆኖም የሚወስዷቸው እርምጃዎች በሌላ ዓለም አቀፋዊ ሕግ የተደነገጉትን ግዴታዎች የሚጥሱና በዘር በቀለም በጾታ በቋንቋ በሃይማኖት ወይም በማህበራዊ አመጣጥ ምክንያትነት ልዩነት የሚያደርጉ መሆን አይገባቸውም በዚህ አንቀፅ የተገለፀው ቢኖርም በዚህ ቃል ኪዳን ውስጥ በአንቀጽ ንዑስ አንቀጽ እና እና የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች የሚቃረን አርምጃ መውሰድ አይቻልም ይህን ቃል ኪዳን የተቀበለ ማንኛውም አገር በአስቸኳይ ግዜ ሁኔታ ምክንያት በቃል ኪዳኑ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ጋር የማይጣጣሙ እርምጃዎችን የመውሰድ መብቱን ለመጠቀም በሚፈለግበት ጊዜ የማያከብራቸውን ድንጋጌዎች ከነምክንያቶቻቸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ በኩል ለዚህ ቃል ኪዳን አባል አገሮች ያስታውቃል ሁኔታው ሲለወጥም ወዲያውኑ ሌላ ማስታወቅያ በተመሳሳይ መንገድ ለአባል አገሮች መስጠት ይኖርበታል አቀንጽ በዚህ ቃል ኪዳን የተጠቀሰ ማንኛውም ድንጋጌ ማንኛውም አገር ቡድን ወይም ግለሰብ በቃል ኪዳኑ የተደነገጉትን ማናቸውንም መብቶችና ነፃነቶች ለመግፈፍ ወይም በቃል ኪዳኑ ከተደነገገው በበለጠ ሁኔታ ለመገደብ የታቀደ ድርጊት ለመፈፀም የሚያስችል መብት እንዳለው ተደርጎ ሊተረጎም አይችልም ይህ ቃል ኪዳን ዕውቅና አይሰጣቸውም ወይም እኩል አያያቸውም በሚል ሰበብ ይህን ቃል ኪዳን በተቀበለ በማንኛውም አገር በሕግ በስምምነት በልማድ በባህል ወይም በሌላ ደንብ ሲሰራባቸው የቆዩ መሰረታዊና ሰብአዊ መብቶች መገደብ ወይም መጻረር አይፈቀድም ክፍል ሶስት አንቀጽ ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር ተፈጥሮአዊ መብት አለው ይህ መብት በህግ ይከበራል ማንኛውም ሰው ያላግባብ ሕይወቱን አይነፈግም የሞት ቅጣትን እንዲቀር ባላደረጉ አገሮች ውስጥ የሞት ፍርድ የሚወሰነው ወንጀል በሚፈፀምበት ጊዜ በነበረው ሕግ መሰረት በጣም ከባድ ለሆነ ወንጀል ነው ፍርዱም ሲወሰን የዚህን ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ድንጋጌዎችና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመከላከልና ለመቅጣት የወጡ ሕጐችን በማይፃረር መልኩ ነው ቅጣቱ የሚፈፀመው በሕግ በተቋቋመ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ሲሰጥ ብቻ ነው የተፈፀመው የህይወት ማጥፋት ተግባር የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓይነት የሆነ አንደሆነ በዚህ አንቀፅ ውስጥ የተደነገጉት አንዳቸውም ድንጋጌዎች ይህንን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች በዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከያ አና መቅጫ ስምምነት መሰረት የገቧቸውን ግዴታዎች የሚፃረሩ እርምጃዎች እንዲወስዱ እንደሚፈቅዱላቸው ተደርገው ሊነበቡ አንደሚችሉ ግንዛቤ ተወስዶበታል ማንኛውም የሞት ቅጣት የተፈረደበት ሰው ይቅርታ የመጠየቅ ወይም የሞት ቅጣቱ ወደ እስራት እንዲለወጥለት የመጠየቅ መብት አለው በሁሉም ጉዳዮች ይቅርታ ወይም ምሕረት ማድረግ ወይም የሞት ቅጣቱን ወደ እስራት ቅጣት መለወጥ ይቻላል ዕድሜያቸው ከ ዓመት በታች በሆኑ ወንጀል ፈፃሚዎች የሞት ፍርድ አይወሰንም ነፍሰ ጡር በሆኑ ሴቶች ላይም ቅጣቱ አይፈጸምም የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች የሞት ቅጣትን ለማስወገድ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለማዘግየት ወይም ለማስቀረት በቃል ኪዳኑ አባል አገሮች በምክንያትነት ሊጠቀሱ አይችሉም አንቀጽ ማንም ሰው ስቃይ ወይም ጭካኔ ለተሞሳላበት ኢሰብዓዊ ወይም ክብርን ለሚያዋርድ አያያዝና ቅጣት መጋለጥ የለበትም በተለይም በማንኛውም ሰው ላይ ያለፈቃዱ የሕክምና ወይም ሳይንሳዊ ሙከራ መደረግ የለበትም አንቀጽ ማንኛውም ሰው በባርነት አይያዝም ባርነትና የባርያ ንግድ በማንኛውም መልካቸው የተከለከሉ ናቸው ማንኛውም ሰው ተገዶ በአገልጋይነት አይያዝም ሀ ማንኛውም ሰው በፃይል ተገዶ ወይንም የግዳጅ ስራዎችን እንዲያከናውን አይደረግም ለ በንኡስ አንቀፅ ሀ የተደነገገው ድንጋጌ የግዳጅ ስራ ከአስራት ጋር እንደቅጣት በሚወሰንባቸው አገሮች ውስጥ ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ከባድ የጉልበት ስራን እንደቅጣት እንዳይወሰን የሚከለክለው አንደሆነ ተደርጐ አይተረጉምም ሐ በዚህ ንዑስ አንቀጽ ለተመለከተው ጉዳይ «በሃይል ተገዶ ወይንም የግዳጅ ስራ» የሚለው አነጋገር የሚከተሉትን አይጨምርም በንዑስ አንቀጽ ለነ ውስጥ ያልተጠቀሰና በፍርድ ቤት ውሳኔ በእስር ላይ ባለ ሰው መፈፀም ያለበት ማንኛውም ስራ ወይም አገልግሎት ወይም ከሕጋዊ እስራት በገደብ በተለቀቀ ሰው መፈፀም ያለበት ማንኛውም ስራ ወይም አገልግሉት ማንኛውም ወታደራዊ ባሕርይ ያለው አገልግሎት ወይም የሕሊና ተቃውሞ ዕውቅና ባገኘበት አገር ውስጥ የሕሊና ተቃዋሚዎች በሕግ ማሟላት ያለባቸውን ብሔራዊ አገልግሉት በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ወይም የሕብረተሰቡን ሕይወት ወይም ደህንነት ለጥፋት በሚያጋልጥ አደጋ ጊዜ መፈፀም ያለበት ማንኛውም አገልግሉት መደበኛ የሲቪል ግዴታዎች አካል የሆነ ማንኛውም ስራ ወይም አገልግሎት አንቀጽ ማንኛውም ሰው የነፃነትና የደህንነት መብት አለው ማንኛውም ሰው በዘፈቀደ አይያዝም አይታሰርም ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ምክንያትና ስርዓት ውጭ ነፃነቱ አይገፈፍም ማንኛውም ሰው በሚያዝበት ጊዜ የተያዘባቸውን ምክንያቶችና የቀረቡበትን ክሶች ምንነት ወድያውኑ የማወቅ መብት አለው በወንጀል ክስ የተያዘ ወይም የታሰረ ሰው ከዳኛ ወይም በሕግ ስልጣን ከተሰጠው አካል ዘንድ በአፋጣኝ ሊቀርብ ይገባል ተገቢ በሆነ ጊዜ ውስጥም ዳኝነት የማግኘት ወይም የመለቀቅ መብት አለው ዳኝነት የሚጠባበቁ ሰዎችን በእስር ማቆየት እንደመደበኛ አፈጻጸም ሊታይ አይገባውም ይሁን እንጂ ከአስር መልቀቁ ግለሰቡን ጉዳዩ በሚታይበት ጊዜ እንዲቀርብ ወይም ፍርዱ እንዲፈጸምበት ለማድረግ እንዲያመች በዋስትና ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል ማንኛውም በመታሰሩ ወይም በመያዙ ምክንያት ነፃነቱን የተነፈገ ሰው ፍርድ ቤቱ የእስራቱን ሕጋዊነት ወዲያውኑ መርምሮ እንዲወስንለት ያላግባብ መታሰሩን ካረጋገጠ ደግሞ በነፃ እንዲለቀቅ እንዲያዝለት ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አለው ማንኛውም በሕገ ወጥ ሁኔታ የተያዘ ወይም የታሰረ ሰው ካሳ የማግኘት መብት አለው አንቀጽ በሕግ ነፃነታቸውን የተገፈፉ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ አያያዝ ሊደረግላቸውና ሰው በመሆናቸው በተፈጥሮ የተጐናፀፉት ክብር ሊጠበቅላቸው ይገባል ሀ የተለየ ሁኔታ ካላጋጠመ በስተቀር ክስ የተመሰረተባቸው ሰዎች ከተፈረደባቸው ሰዎች ሊለዩና ጥፋተኛ ላልሆኑ ሰዎች የሚሰጠው አያያዝ ሊደረግላቸው የገባል ለ ወጣት አጥፊዎች ከአዋቂዎች በተለየ ቦታ መጠበቅና ባስቸኳይ ፍርድ ቤት መቅረበ አለባቸው የእስራት ዓላማ አስረኞች ከጥፋታቸው እንዲታረሙና የተሻሻሉ የሕብረተሰብ አባላት እንዲሆኑ ማድረግ ነው ወጣት አጥፊዎች ከአዋቂ እስረኞች በተለየ ቦታ የመጠበቅና ከዕድሜያቸውና የሕግ አቋማቸው ጋር የሚስማማ እንክብካቤ የማግኘት መብት አላቸው አንቀጽ ማንኛውም ሰው የውል ግዴታውን ባለማሟላቱ ብቻ አይታሰርም አንቀጽ በአንድ አገር የግዛት ክልል ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ያለ ማንኛውም ሰው በዚያ አገር ውስጥ በነፃነት የመንቀሳቀስና የመኖሪያ አካባቢውን በነፃነት የመምረጥ መብት አለው ማንኛውም ሰው የትኛውንም አገር የራሱንም ጭምር ለቆ የመውጣት መብት አለው ብሔራዊ ጸጥታን ሰላምና ደህንነትን የሕዝብን ጤና መልካም ስነ ምግባርና እንዲሁም የሌሎችን መብቶችና ነፃነቶች ለመጠበቅ ሲባል በዚህ ቃል ኪዳን ከሰፈረሩት ድንጋጌዎች ጋር በሚስማማ አኳኋን በሚወጣ ሕግ መሰረት ካልሆነ በስተቀር ከላይ በተጠቀሱት መብቶች ላይ ምንም አይነት ገደብ አይደረግም ማንኛውም ሰው ወደ ራሱ አገር የመግባት መብቱ በዘፈቀደ አይከለከልም አንቀጽ ይህን ቃል ኪዳን በተቀበለ አገር ውስጥ በሕጋዊ መንገድ የሚኖር የውጭ አገር ሰው አስገዳጅ አገራዊ ፀጥታ ካላጋጠመ በስተቀር ከዚያ አገር ሊባረር የሚችለው ሕግን ተከትሎ በሚሰጥ ውሳኔ ብቻ ነው ግለሰቡም ይህንንም እርምጃ በመቃወም ጉዳዩ እንደገና እንዲታይለት ስልጣን ላለው አካል ወይም በዚህ አካል ለተሰየመ ሰው ወይም ሰዎች ራሱ ወይም በወኪሉ አማካይነት አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው አንቀጽ ሰዎች ሁሉ በፍርድ ቤቶችና በዳኝነት አካላት ፊት በእኩልነት ይታያሉ በቀረበበት የወንጀል ክስም ሆነ ስለ መብቶቹ እና ግዴታዎቹ በሚወሰንበት ማንኛውም ጉዳይ ማንኛውም ሰው በሕግ በተቋቋመ ስልጣን ባለው ነፃና ገለልተኛ በሆነ የዳኝነት አካል ዘንድ የመቅረብና አድልኦ የሌለበትና ግልፅ የሆነ ዳኝነት የማግኘት መብት አለው ለዴሞክራሲያዊ ሕብረተሰብ አስፈላጊ የሆኑትን የመልካም ስነ ምግባር የሕዝብ ደህንነት ወይም ብሔራዊ ፀጥታን ለመጠበቅ ሲባል ወይም የተከራካሪ ወገኖች የግል ሕይወት የሚነካ ሲሆን አለበለዚያም ፍርድ ቤቱ የጉዳዩ ይፋ መውጣት የዳኝነትን ስራ አካሄድ የሚያሰናክል መሆኑን በማመን በሚሰጠው ትአእዛዝ አንድ ጉዳይ በዝግ ችሎት ሊታይ ይችላል ይሁን እንጂ የወጣት ጥፋተኞችን መብትና ጥቅም ለመጠበቅ ወይም በፍች ክርክር ጊዜ የሚወሰዱ የሕፃናት አጠባበቅን እርምጃዎች የሚመለከቱ ካልሆኑ በስተቀር በዝግ ችሎት የተሰጡ ማናቸውም የወንጀልና የፍትሐ ብሔር ውሳኔዎች ይፋ ይደረጋሉ ማንኛውም በወንጀል ጥፋት የተከሰሰ ሰው በሕጉ መሰረት ጥፋተኛነቱ እስከሚረጋገጥ ድረስ እንደ ንጹሕ ሰው የመቆጠር መብት አለው የቀረበበት የወንጀል ክስ በሚታይበት ጊዜ ማንኛውም ተከሳሽ ቢያንስ የሚከተሉትን ዋስትናዎች በእኩልነት የማግኘት መብት አለው ሀ የቀረበበትን ክስና ምክንያቱን በሚገባው ቋንቋ በፍጥነትና በዝርዝር የማወቅ ለ ለቀረበበት ክስ መከላከያ ለማዘጋጀት አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮችና በቂ ጊዜ የማግኘትና አማካሪ እንዲሆን የመረጠውን ሰው የማማከር ሐ አግባብ ባልሆነ ሁኔታ ሳይዘገይ የመዳኘት መ ራሱ በተገኘበት የመዳኘት ራሱን በግል ወይም በመረጠው ጠበቃ በኩል የመከላከል ጠበቃ ከሌለው የሕግ አማካሪ እርዳታ የማግኘት መብት እንዳለው የማወቅ ትክክለኛ ዳኝነት የሚጓደል ሆኖ ሲታይና የገንዘብ አቅሙ የማይፈቅድ ሲሆን ሳይከፍል ጠበቃ የማግኘት መብቱ ሠ የሚመሰክሩበትን ምስክሮች በግሉም ሆነ በጠበቃው አማካይነት የመመርመር እንዲሁም በራሱ ላይ በተቆጠሩበት ምስክሮች ሁኔታ የራሱ ምስክሮች ቀርበው እንዲመረመሩለት የማድረግ ረ ፍርድ ቤቱ የሚጠቀምበትን ቋንቋ የማይናገር ወይም የማይረዳ ከሆነ በነፃ አስተርጓሚ የማግኘት ሰ በራሱ ላይ እንዲመሰክር ወይም ጥፋተኛነቱን እንዲያምን ያለመገደድ በወጣት ተከሳሾች ላይ የሚካሄድ የዳኝነት ስራ የዕድሜያቸውን ለጋነትና ከጥፋተኝነት ታርመው የሜታነፁበትን ስርዓት ግንዛቤ ውስጥ ያስገባል ማንኛውም በወንጀል የተፈረደበት ሰው በሕግ መሰረት ፍርዱም ሆነ ቅጣቱ በበላይ ፍርድ ቤት እንደገና እንዲታይለት የማድረግ መብት አለው በአንድ ሰው ላይ ተላልፎ የነበረው የመጨረሻ ፍርድ በማያሻማ አኳኋን ኢፍትፃዊ የነበረ ስለመሆኑ አዲስ በተገኘ ማስረጃ አማካኝነት የተረጋገጠ የሆነ እንደሆነ አና በዚህም ምክንያት ይህ ሰው ምህረት ካገኘ አልያም ደግሞ ተላልፎበት የነበረው ውሳኔ የተሻረ አንደሆነ በእንዲህ ዓይነቱ ፍርድ ምክንያትነት ደርሶበት ለነበረው ቅጣት በህጉ መሰረት ሊካስ ይገባል ይህ የሚፈፀመዉ ለፍርዱ መቀልበስ ምክንያት የሆነው መረጃ ሳይታወቅ የቆየው በከፊልም ሆነ በሙሉ በተከሳሹ ምክንያት ያለመሆኑ ሲረጋገጥ ነው ማንኛውም ሰው በአገሩ ሕግና በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ መሰረት ለመጨረሻ ጊዜ በተፈረደበት ወይም ነፃ በወጣበት ጥፋት ዳግመኛ አይዳኝም ወይም አይቀጣም አንቀጽ ማንኛውም ሰው የፈፀመው ወይም ማድረግ ሲገባው ያልፈፀመው ተግባር በአገራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ሕግ መሰረት እንደ ወንጀል ባልተደነገገበት ግዜ እንደ ወንጀለኛ ሊወሰድ አይገባውምፎ እንዲሁም ጥፋቱን በፈፀመበት ጊዜ ስራ ላይ ውሎ ከነበረው ቅጣት የከበደ ቅጣት አይፈጸምበትም ጥፋቱ ከተፈፀመ በኋላ ለእንዲህ ዓይነቱ ወንጀል ቀለል ያለ ቅጣት የሚያሰጥ ሕግ ከተደነገገ ጥፋተኛው ሰው የዚህ ሕግ ተጠቃሚ ይሆናል አገሮች እውቅና በሰጧቸው አጠቃላይ የሕግ መርሆች መሰረት የተፈፀመው ወይም መደረግ ሲገባው ሳይፈፀም የቀረው ድርጊት እንደ ወንጀል የሚቆጠር ከሆነ የጥፋተኛውን ለፍርድ መቅረብና መቀጣት ይህ አንቀጽ አይከለክልም አንቀጽ ማንኛውም ሰው በየትም ቦታ በሕግ ፊት እንደ ሰው የመታወቅ መብት አለው አንቀጽ በማንኛውም ሰው የግል ሕይወት ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ወይም ደብዳቤ ላይ ያለ አግባብ ወይም ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ጣልቃ ገብነት አይፈጸምም መልካም ዝናውም ከሕግ ውጭ አይደፈርም ማንኛውም ሰው ከእንዲህ ዓይነቱ ጣልቃ ገብነት ወይም መደፈር የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት አለው አንቀጽ ማንኛውም ሰው የሀሳብ የኅሊናና የሃይማኖት ነፃነት መብት አለው ይህም መብት የመረጠውን ፃይማኖት ወይንም አምነት የመከተል ወይንም የመያዝ ነባነትን እንዲሁም ለብቻም ሆነ ከሌሎች ጋር በመሆን ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን በአደባባይም ሆነ በግል በአምልኮ የመግለጽ ስርዓቱን የማክበር በተግባር የማዋልና የመስበክ ነፃነትን ይጨምራል ማንም ሰው የመረጠውን ዛይማኖት ወይንም አምነት የመከተል ወይንም የመያዝ ነፃነቱን በሚነካ አኳኋን አይገደድም የራስን ሃይማኖት ወይም እምነት የመግለጽ ነፃነት ሊገደብ የሚችለው በሕግ በተደነገገው መሰረትና የሕዝብን ደህንነት ፀጥታ ጤና ወይም ስነ ምግባር ወይም የሌሎችን መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች ለማስከበር አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ነው ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች ወላጆችና ሁኔታው ሲፈቅድ ሕጋዊ ሞግዚቶች የልጆቻቸው የሃይማኖትና የግብረ ገብነት ትምህርት የራሳቸውን እምነት የተከተለ መሆኑን የማረጋጥ መብታቸውን ለማክበር ተስማምተዋል አንቀጽ ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የራሱ አመለካከት ሊኖረው መብት አለው ማንኛውም ሰው ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት መብት አለው ይህም መብት መረጃና ማንኛውም ዓይነት ሀሳብ ያለምንም የድንበር ገደብ በቃል በሑፍ ወይም በሕትመት በስነ ጥበብ ወይም ሌላ በመረጠው የመገናኛ ዘዴ የመፈለግ የማግኘትና የማስተላለፍ መብትን ያጠቃልላል በዚህ አንቀጽ ንዑስ ቁጥር የተደነገጉት መብቶች ያጠቃቀም ሁኔታ ልዩ ግዴታዎችንና ኃላፊነቶችንም ጭምር ይዘዋል በዚህም ምክንያት የተወሰኑ ገደቦች ሊደረጉበት ይቻላል ይሁን እንጂ ገደቦቹ በሕግ የተደነገጉና ሀ የሌሎችን መብቶችና ክብር ለማስጠበቅ ለ ብሔራዊ ጸጥታን የሕዝብ ደህንነትን ወይም ጤናን ወይም ስነ ምግባርን ለማስከበር አስፈላጊ መሆን አለባቸው አንቀጽ ማንኛውም ለጦርነት የሚደረግ ፕሮፓጋንዳ በሕግ የተከለከለ ነው አድልዎን ጠላትነትን ወይንም ሁከትን ሊያስነሳ የሚችል የብፄር የዘር ወይንም የፃይማኖት ጥላቻን የሚፈጥር ቅስቀሳ በህግ የተከለከለ ነው አንቀጽ ሰላማዊ ስብሰባ የማድረገ መብት አውቅና ይሰጠዋል በዴሞክራሲያዊ ሕብረተሰብ ውስጥ ለብሔራዊ ደህንነት የሕዝብ ሰላምና ፀጥታ ጥቅም ወይም የሕዝብን ጤናና ስነ ምግባር ለመጠበቅ ወይም የሌሎችን መብቶችና ነፃነቶች ለማስከበር ከሚያስፈልገው አና በሕግ ከተደነገገው በቀር በዚህ መብት አጠቃቀም ላይ ምንም ዓይነት ገደብ አይደረግም አንቀጽ ማንኛውም ሰው ኬሌሎች ጋር በመሆን የመደራጀት መብት አለው ይህም መብት ጥቅሞቹን ለማስከበር የሰራተኛ ማኅበራትን የማቋቋም እና አባል የመሆን መብትን ያጠቃልላል በዴሞክራሲያዊ ሕብረተሰብ ውስጥ ለብሔራዊ ደህንነት ለሕዝብ ሰላምና ፀጥታ ጥቅም ወይም የሕዝብን ጤናና ስነምግባር ለመጠበቅ ወይም የሌሎችን መብቶችና ነፃነቶች ለማስከበር ከሚያስፈልገው እና ህግ ከሚደነግገው በቀር በዚህ መብት አጠቃቀም ላይ ምንም ዓይነት ገደብ አይደረግም ይህ አንቀጽ በጦር ኃይሎች እና በፖሊስ ሰራዊት አባላት ላይ በዚህ መብት አጠቃቀም ረገድ ሊደረግ የሚችለውን ሕጋዊ ገደብ አይከለከልም ይህ አንቀጽ «ማህበር የማቋቋም ነፃነትና የመደራጀት መብት ጥበቃን» የሚመለከተውን የ እኤአ የዓለም አቀፍ የስራ ድርጅት ስምምነት የተቀበሉ አገሮች በስምምነቱ የተረጋገጡትን ዋስትናዎች የሚፃረር ሕግ እንዲያወጡ ወይም ሕጉን ዋስትናዎቹን ሊፃረር በሚችል መልክ እንዲጠቀሙበት አይፈቀድላቸውም አንቀጽ ቤተሰብ የሕብረተሰቡ ተፈጥሯዊ መሰረት እንደመሆኑ በመንግስትና ሕብረተሰብ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል ለጋብቻ የደረሱ ወንዶችና ሴቶች የመጋባትና ቤተሰብ የመመስረት መብታቸው እውቅና ተሰጥቶታል ያለ ተጋቢዎች ነፃና ሙሉ ፈቃድ ጋብቻ መመስረት የለበትም ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች ተጋቢዎች ጋብቻ ሲመሰርቱ ጋብቻው በሚቆይበት ጊዜ እና ጋብቻው ሲፈርስ እኩል መብትና ኃላፊነት ያላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ ጋብቻው በሚፈርስበት ጊዜ ለልጆቹ ጥቅም ተገቢውን ጥበቃ የሚያደርግ ሕግ ተግባራዊ መሆን አለበት አንቀጽ የዘር የቀለም የቋንቋ የሃይማኖት የብሔርም ሆነ የማሕበራዊ አመጣጥ የሃብት ወይም የትውልድ ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግበት ማንኛውም ልጅ ለአካለ መጠን ባለመድረሱ ምክንያት የሚያስፈልገውን ጥበቃና እንክብካቤ ከቤተሰብ ከህብረተሰቡና ከመንግስት የማግኘት መብት አለው ማንኛውም ሕፃን ወዲያውኑ እንደተወለደ ይመዘገባል ስም ይሰጠዋል እያንዳንዱ ልጅ ዜግነት የማግኘት መብት አለው አንቀጽ ማንኛውም ዜጋ በአንቀጽ የተጠቀሱት ልዩነቶች ሳይደረጉበትና አግባብነት የሌላቸው ገደቦች ሳይደረጉበት ሀ በቀጥታ ራሱ ወይም በነፃ በተመረጡ ተወካዮቹ አማካይነት በሕዝብ ጉዳዮች የመሳተፍ ለ ሁሉም በእኩልነት በሚሳተፍባቸውና የመራጮቹ ፈቃድ በነፃ የሚገለጥባቸው ለመሆኑ ዋስትና ባላቸው በምስጢር በሚካሄዱ እና እውነተኛ በሆኑ ወቅታዊ ምርጫዎች የመመረጥ እና የመመረጥ ሐ በአገር ውስጥ ለህዝብ በተዘረጉ አገልግሎቶች በእኩልነት የመጠቀም መብትና ዕድል ይኖረዋል አንቀጽ ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል ነው ያለምንም ልዩነት እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት አለው በዚህ ረገድ ሕጉ ማንኛውንም ልዩነት በመከልከል በዘር በቀለም በጾታ በቋንቋ በሃይማኖት በፖለተካ ወይም በሌላ አመለካከት በብሔር ወይም በማህበራዊ አመጣጥ በሀብት በትውልድ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት አድሎአዊ ልዩነት እንዳይፈፀምበት ለሁሉም ሰው እኩልና አስተማማኝ ጥበቃ ያደርጋል ዋስትናም ይሰጣል አንቀጽ በጎሳ በሃይማኖት ወይም በቋንቋ ንኡሳን የሆኑ ማህበረሰቦች ባሉበት አገር ውስጥ የንኡሳን ማህበረሰቡ አባል የሆኑ ግለሰቦች በጋራ ባህላቸውን እንዳያከብሩ ሃይማኖታቸውን እንዳያስፋፉ በቋንቋቸው እንዳይጠቀሙ መብታቸው ሊገፈፍ አይገባም ክፍል አራት አንቀጽ በዚህ ቃል ኪዳን መሰረት ኮሚቴ እየተባለ የሚጠቀስ የሰብአዊ መብት ኮሚቴ ይቋቋማል ኮሚቴው አባላት የሚኖሩት ሲሆን ከዚህ በታች የተደነገጉትን ተግባሮች ያከናውናል ኮሚቴው ስነምግባራቸው ከፍተኛ በሆነ እና በሰብአዊ መብቶች መስክ በችሎታቸው ዕውቅና ባገኙ የዚህ ቃል ኪዳን አባል አገሮች ዜጎች በሆኑ ሰዎተ የሚመሰረት ሲሆን በተለይ የህግ ልምድ ያላቸው ሰዎች ማሳተፍ የሚኖረው ጥቅም ግምት ውስጥ ይገባል የኮሚቴው አባላት በምርጫ የሚሰየሙና እራሳቸውን ወክለው የሚያገለግሉ ይሆናሉ አንቀጽ የኮሚቴው አባላት ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች ለዚሁ አላማ ከሚያቀርቧቸው እና በአንቀጽ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ በምስጢር ድምፅ አሰጣጥ ይመረጣሉ እያንዳንዱ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበለ አገር ከሁለት ዕጩዎች በላይ አይጠቁምምሖ እነዚህ ዕዕጩዎች የጠቋሚው አገር ዜቶች መሆን ይኖርባቸዋል አንድ ሰው ለኮሚቴው እንደገና የመጠቆም መብት አለው አንቀጽ የመጀመሪያው ምርጫ ይህ ቃል ኪዳን ከፀናበት ከስድስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይካሄዳል በአንቀጽ መሰረት ክፍት ቦታዎችን ለመሙላት ካልሆነ በስተቀር እያንዳዱ ምርጫ ከመካሄዱ ቢያንስ አራት ወራት ቀደም ብሎ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች በሶስት ወራት ውስጥ ለኮሚቴው አባልነት ዕጩዎቻቸውን እንዲጠቀሙ በጽሑፍ ይጠይቃል ዋና ፀሐፊው የተጠቆሙትን ዕጩዎች ዝርዝር በስማቸው ፊደላት ቅደም ተከተል አዘጋጅቶ የጠቆሟቸውን አገሮች ጭምር በማመልከት እያንዳንዱ ምርጫ ከመካሄዱ ከአንድ ወር በፊት ይህን ቃል ኪዳን ለተቀበሉት አገሮች ያቀርባል የኮሚቴው አባላት ምርጫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በድርጅቱ ዋና ጽሕፈት ቤት በሚጠራውና ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አባል አገሮች በሚያደርጉት ስብሰባ ይከናወናል ይህን ቃል ኪዳን ከተቀበሉ አባል አገሮች ሁለት ሦስተኛው በተገኙበት ምልዓተ ጉባኤ በስብሰባው ላይ አገሮቹን ወክለው ከተገኙትና ድምፅ ከሰጡት መካከል የአብላጫውን ድምፅ ያገኙት ዕጩዎች የኮሚቴው አባላት ይሆናሉ አንቀጽ ኮሚቴው ከአንድ አገር ውስጥ ከአንድ ዜጋ በላይ አባል አይኖረውም በኮሚቴው ምርጫ ረገድ የኮሚቴው አባልነት የተመጣጠነ የአካባቢ ስብጥርን እንዲያንፀባርቅና የተለያዩ የስልጣኔኬ ዓይነቶችንና አበይት የሕግ ስርዓቶችን እንዲወክል የማድረግ አስፈላጊነት ግምት ውስጥ ይገባል አንቀጽ የኮሚቴው አባላት ለአራት ዓመት የስራ ጊዜ ይመረጣሉ በድጋሚ ከተጠቆሙ ለሁለተኛ ግዜ ሊመረጡ ይችላሉ ይሁን እንጂ በመጀመሪያው ዙር ከተመረጡት ውስጥ የዘጠኙ አባላት የስራ ጊዜ በሁለተኛው ዓመት መጨረሻ ላይ ያበቃል የመጀመሪያው ምርጫ እንደተፈፀመ ወዲያውኑ በአንቀጽ ንዑስ ቁጥር የተጠቀሰው ስብሰባ ሊቀመንበር በሚያወጣው ዕጣ የዘጠኙ አባላት ስም ይታወቃል የኮሚቴው አባላት የስራ ጊዜ ሲያበቃ ምርጫዎች ቀደም ባሉት የዚህ ቃል ኪዳን አንቀጾች መሰረት ይከናወናሉ አንቀጽ አንድ የኮሚቴው አባል ጊዜያዊ ባልሆነ በማናቸውም ሌላ ምክንያት ስራውን ያቋረጠ መሆኑን የቀሩት አባላት ሁሉም በጋራ ከተስማሙ የኮሚቴው ሊቀመንበር ለተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ወዲያውኑ ያስታውቃል ፀሐፊውም በአባሉ ተይዞ የነበረው የኃላፊነት ቦታ ክፍት መሆኑን ይገልጻል አንድ የኮሚቴ አባል በሞት ከተለየ ወይም ስራውን በራሱ ፈቃድ ከለቀቀ የኮሚቴው ሊቀመንበር ሁኔታውን ለዋና ፀሐፊው ወዲያውኑ የሰታውቃል። ክፍት የስራ ቦታውን ለመሙላትም በዚህ የቃል ኪዳኑ ክፍል ውስጥ በተጠቀሱት አግባብ ባላቸው ድንጋጌዎች መሰረት ምርጫ ይካሄዳል በአንቀጽ መሰረት የተገለጸውን ክፍት ቦታ ለመሙላት የተመረጠ የኮሚቴ አባል በዚያው አንቀጽ መሰረት የቀድሞው አባል ሳይጨርሰው ለቀረው የስራ ጊዜ በኃላፊነት ይቆያል አንቀጽ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ሲፀድቅና ጠቅላላ ጉባዔው በሚወስነው ሁኔታዎች መሰረት እንዲሁም የኮሚቴውን የስራ ኃላፊነት ክብደት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለኮሚቴው አባላት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሀብት ላይ ምንዳ ይከፈሳቸዋል አንቀጽ ኮሚቴው በዚህ ቃል ኪዳን የተደነገጉትን ተግባራት በሚገባ ማከናወን ይችል ዘንድ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አስፈላጊውን የሰው ኃይልና ድርጅት ያሟላለታል አንቀጽ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ የኮሚቴውን የመጀመሪያ ስብሰባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት እንዲሰየም ያደርጋል ከመጀመሪያ ስብሰባ በኋላ ኮሚቴው በራሱ የስነ ስርዓት ደንብ መሰረት በየጊዜው ይሰበሰባል የኮሚቴው መደበኛ ስብሰባዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት ወይም ጄኔቫ በሚገኘው የድርጅቱ ሕፈት ቤት ይካሄዳሉ አንቀጽ እያንዳንዱ የኮሚቴው ኣባል መደበኛ ስራውን ከመጀመሩ በፊት በኮሚቴው ግልጽ ስብሰባ ላይ የተሰጠውን ኃላፊነት ያለ አድሎና በቅን ኅሊና ለመወጣት ቃል ይገባል አንቀጽ ኮሚቴው የስራ አስፈፃሚ አባላቱን ለሁለት ዓመት የስራ ጊዜ ይመርጣል እነዚህም እንደገና ሊመረጡ ይችሳሉ ኮሚቴው የራሱን የስነ ስርዓት ደንቦች ያወጣል ከእነዚህ ደንቦች ውስጥ የሚከተሉት ሊኖሩ ይገባል ሀ የኮሚቴው ምልዓተ ጉባኤ በ አባላት ይሟላል ለ የኮሚቴው ውሳኔ የሚፀድቀው በስብሰባው ላይ በተገኙት አባላት አብላጫ ድምፅ ሲደገፍ ይሆናል አንቀጽ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች በዚህ ቃል ኪዳን ተቀባይነት ያገኙትን መብቶች ለማክበር ስለሚወስዷቸው እርምጃዎችና መብቶቹን በማረገገጥ ረገድ ስለተመዘገቡት ውጤቶች ሪፖርት ሊያቀርቡ ይገባል ሪፖርቱ የሚቀርበውም ሀ የቃል ኪዳኑ አባል አገሮች ቃል ኪዳኑ ከፀናባቸው ጊዜ አንስቶ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ እና ለ ከዚያ በኋላ ኮሚቴው በጠየቀ ጊዜ ይሆናል ማንኛውም ዘገባ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ይቀርባል ዋና ፀሐፊውም የደረሱትን ዘገባዎች ኮሚቴው እንዲያያቸው ያስተላልፍለታል ዘገባዎቹም ከዚህ ቃል ኪዳን አፈጻጸም ጋር የተያያዙ ጉዳዮችንና ካሉም ችግሮችን ያመለክታሉ ዋና ፀሐፊው ከኮሚቴው ጋር ከተመካከረ በኋላ ከዘገባዎቹ በስራ ድርሻቸው ክልል ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎች ቅጂ ለሚመለከታቸው ልዩ ተልእኮ ለተሰጣቸው የተባበሩት መንግስታት አካላት ማስተላለፍ ይችላል ኮሚቴው ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች ያቀረቡለትን ሪፖርቶች ይመረምራል የራሱን ሪፖርትና ተገቢ ነው ያላቸውን አስተያየቶች ቃል ኪዳኑን ለተቀበሉት አገሮች ያቀርባልር በተጨማሪም ኮሚቴው አስተያየቱን ቃል ኪዳኑን ከተቀበሉ አገሮች የደረሰው ዘገባ ቅጂውን ጨምሮ ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ምክር ቤት ሊልከው ይችላል ቃል ኪዳኑን የተቀበሉት አገሮች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ መሰረት በቀረቡት አስተያየቶች ላይ ያላቸውን ሃሳብ ለኮሚቴው ማቅረብ ይችላሉ አንቀጽ አንድ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበለ አባል አገር በዚህ አንቀጽ የሰፈሩት ግዴታዎች በሌላው ፈራሚ አገር ተፈፃሚነት አላገኙም ብሎ አቤቱታ በሚያቀርብበት ወቅት ኮሚቴው ያንን ተቀብሎ ለመመርመር ላለው ስልጣን በማናቸውም ጊዜ ቢሆን ዕውቅና መስጠት ይችላል። ኮሚሽኑ የራሱን ሊቀመንበር ይመርጣል የሚመራበትን የስነ ስርዓት ደንብም ያወጣል የኮሚሽኑ ስብሰባዎች የሚካሄዱት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፅሕፈት ቤት ወይም በድርጅቱ የጄኔቫ ፅሕፈት ቤት ውስጥ ይሆናል ነገር ግን የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊንና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ቃል ኪዳኑን የተቀበሉ አገሮች በማማከር ኮሚሽኑ በሌሎች አመቺ ቦታዎች ስብሰባውን ማካሄድ ይችላል በአንቀጽ መሰረት የተቋቋመው ጽሕፈት ቤት በዚህ አንቀጽ መሰረት የሚቋቋሙ ኮሚሽኖችንም ያገለግላል ኮሚቴው የተቀበላቸውንና ራሱም ያጠናቀራቸውን መረጃዎችን ኮሚሽኑ ሊያያቸው ይችላል በተጨማሪም ኮሚሽኑ ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ቃል ኪዳኑን የተቀበሉ አገሮች ማግኘት ይችላል ኮሚሽኑ የተሰየመበትን ጉዳይ ከመረመረ በኋላ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አገሮች የሚተላለፍ ዘገባ ለኮሚቴው ሊቀመንበር ያቀርባልር በማናቸውም ጊዜ ዘገባው ኮሚሽኑ ጉዳዩን መመልከት ከጀመረ ከ ወራት ጊዜ በላይ ሊዘገይ አይችልም ሀ ኮሚሽኑ ጉዳዩን በ ወራት ውስጥ መርምሮ ማጠናቀቅ ካልቻለ ዘገባው ጉዳዩ ያለበትን ደረጃ ብቻ ባጭሩ የሚገልጽ ይሆናል ለ በዚህ ቃል ኪዳን ዕውቅና ያገኙትን ሰብአዊ መብቶች በማክበር ላይ የተመሰረተ የሚያግባባ መፍትሔ ከተገኘ የኮሚሽኑ ዘገባ ፍሬ ነገር በተገቢው መፍትሔ ላይ ያተኩራል ሐ በንዑስ አንቀጽ ለ መሰረት መፍትሔ ካልተገኘ የኮሚሽኑ ዘገባ ጉዳዩን በሚመለከት በተነሱት ጥያቄዎች ላይ የሱን ግኝቶችና ለችግሩ ማግባቢያ የተሰጠውን አስተያየቶች ይይዛል ይህ ዘገባ በተጨማሪ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቃል ኪዳኑን በተቀበሉ አገሮች የቀረቡትን የጽሑፍና የቃል መግለጫዎች ያጠቃልላል መ የኮሚሽኑ ዘገባ በንዑስ አንቀጽ ሐ መሰረት የቀረበ ከሆነ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አገሮች ዘገባው በደረሳቸው በሶሰት ወራት ጊዜ ውስጥ በዘገባው ይዘት መስማማት ያለመስማማታቸውን ለኮሚቴው ሊቀ መንበር ያስታውቃሉ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች በአንቀጽ ውስጥ የተጠቀሱትን የኮሚቴውን ኃላፊነቶች የሚነኩ አይሆኑም ጉዳይ የሚመለከታቸው ቃል ኪዳኑን የተቀበሉ አገሮች የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ በሚያቀርበው ተመን መሰረት የኮሚሽኑን አባላት ወጪዎች በሙሉ እኩል ይከፍላሉ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ መሰረት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች ክፍያውን ከመተካታቸው በፊት የኮሚሽኑን አባላት ወጪዎች የመሸፈን ስልጣን አለው አንቀጽ አግባብ ባላቸው በተባበሩት መንግስታት የልዩ መብቶችና የማይደፈሩ መብቶች ስምምነት ደንጋጌዎች መሰረት የኮሚቴውና በአንቀጽ መሰረት የተሰየሙት የጊዜያዊ አስታራቂ ኮሚሽኑ አባላት ለተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ ለሚሰማሩ ባለሙያዎች የሚገባውን ስራ ማከናወኛ ጥቅሞች አና ያለመከሰስ መብት አላቸው አንቀጽ ይህን ቃል ኪዳን በስራ ላይ ለማዋል የተቀመጡት ድንጋጌዎች የተባበሩት መንግስታትና ልዩ ተልእኮ የተሰጣቸው አካላት ስምምነቶችና ማስፈፀሚያ ደንቦች ውስጥ በሰብአዊ መብቶች መስክ የተዘረዘሩትን ስነ ስርዓቶች የሚነኩ አይሆኑምር በተጨማሪም ድንጋጌዎቹ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበሉ አገሮች በመካከላቸው ባሉት አጠቃላይ ወይም ልዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት በመካከላቸው ያለውን ክርክር ለመፍታት ሌሎች ዘዴዎችን ከመከተል አያግዷቸውም አንቀጽ ኮሚቴው በየዓመቱ ስለስራ እንቅስቃሴው የሚገልጽ ዘገባ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ምክር ቤት በኩል ለተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል ክፍል አምስት አንቀጽ የዚህ ቃል ኪዳን ማንኛውም ድንጋጌ የተባበሩት መንግስታት ቻርተር እና ልዩ ተልእኮ የተሰጣቸው የድርጅቱ አካላትና ልዩ ልዩ ክፍሎች በዚህ ቃልኪዳን ውስጥ ከተካተቱት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ያሏቸውን ኃላፊነትና ተግባር የሚወስኑት መተዳደሪያ ደንቦችን እንደሚያፋልስ ሆኖ አይተረጎምም አንቀጽ የዚህ ቃል ኪዳን ማንኛውም ድንጋጌ ሕዝቦች በተፈጥሮ ሀብታቸውና ችሎታቸው በሙሉና በነፃነት የመጠቀም መብታቸውን እንደሚቀንስ ሆነ አይተረጎምም ክፍል ስድስት አንቀጽ ይህ ቃል ኪዳን የተባበሩት መንግስታት አባል ለሆነ አገር ወይም ልዩ ተልእኮ ለተሰጣቸው አካላት አባል የሆነ አገር የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤትን መተዳደሪያ ደንብ ለተቀበለ አገር እንዲሁም ይህን ሕግ እንዲፈርም በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ለተጋበዘ ሌላ አገር ለፊርማ ክፍት ነው ይህ ቃል ኪዳን በፈራሚ አገሮች መፅደቅ ይኖርበታል የማጽደቂያ ሰነዶችም በተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ዘንድ ይቀመጣሉ ይህ ቃል ኪዳን በዚህ አንቀጽ የተጠቀሰው ማንኛውም አገር እንዲቀበለው ክፍት ይሆናል መቀበል የሚረጋገጠው የመቀበያ ሰነድን በተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ዘንድ በማኖር ነው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ቃል ኪዳኑን የፈረሙ ወይም የተቀበሉ አገሮች እሱ ዘንድ ስለተቀመጡት የማጽደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ እንዲያውቁ ያደርጋል አንቀጽ ይህ ቃል ኪዳን የሚፀናው ኛው የማጽደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ዘንድ ከተቀመጠ ዕለት አንስቶ ከሶስት ወራት በኋላ ነው ኛው የማፅደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ ከዋና ፀሐፊው ዘንድ ከተቀመጠ በኋላ ይህን ቃል ለሚያጸድቅ ለእያንዳንዱ አገር ቃል ኪዳኑን የሚፀናው የራሱን የማፅደቀያ ወይም የመቀበያ ሰነድ ካኖረበት ዕለት ከሶስት ወራት በኋላ ነው አንቀጽ ፌዴራላዊ አስተዳደር ባላቸው አገሮች የዚህ ቃል ኪዳን ድንጋጌዎች በሁሉም የአስተዳደር ክልሎች ያለምንም ገደብ ወይም ልዩነት ተፈጻሚ ይሆናሉ አንቀጽ ይህን ቃል ኪዳን የተቀበለ ማንኛውም አገር ለቃል ኪዳኑ ማሻሻያ ሀሳቦች ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ማቅረብ ይችላል ዋና ፀሐፊውም ስለቀረቡት የማሻሻያ ሀሳቦች ይህን ቃል ኪዳን ለተቀበሉት አገሮች በማስታወቅ በቀረቡት ሀሳቦች ላይ ለመወያየትና ድምፅ ለመስጠት ጉባኤ እንዲጠራ ይፈልጉ እንደሆነ እንዲገልጹለት ይጠይቃልፁ ቃል ኪዳኑን ከተቀበሉት አገሮች አንድ ሦስተኛው የጉባኤውን መጠራት የሚደግፉ ከሆነ ዋና ፀሐፊው በተባበሩት መንግስታት አማካይነት ጉባኤው እንዲካሄድ ስብሰባውን ያዘጋጃል ቃል ከዲኑን ተቀብለው በስብሰባው ከተገኙትና ድምፅ ከሰጡት አገሮች በአብዛኛው አባል የተደገፈው የማሻሻያ ሀሳብ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያጸድቀው ይቀርብለታል አንድ የማሻሻያ ሀሳብ በሕግ የሚፀናው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤና ይህን ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ከተቀበሉት መንግስታት ውስጥ ሁለት ሦስተኛው በአገራቸው ሕገ መንግስታዊ ደንብ መሰረት ሲያፀድቁት ነው ማሻሻያዎች ስራ ላይ ሲውሉ በተቀበሏቸው አገሮች ላይ አስገዳጅነት ይኖራቸዋል። ዋና ጸሐፊው በዚህ አኳኋን የተጠቆሙትን ዕጩዎች ዝርዝር በፊደል ቅደም ተከተል አዘጋጅቶ የጠቆማቸውን አገር በመጥቀስ ስምምነቱን ለተቀበሉት አገሮች ያቀርባል የኮሚቴው አባላት ምርጫ ዋና ጸሐፊው በተባበሩት መንግስታት ዋና ጽሕፈት ቤት ውስጥ በሚጠራው ስምምነቱን የተቀበሉ አገሮች ስብሰባ ላይ ይካሄዳል ስምምነቱን ከተቀበሉት አገሮች ሁለት ሦስተኛው ከተገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይኖራልር በዚሁ ስብሰባ የኮሚቴው አባላት የሚሆኑት በስብሰባው ተገኝተው ድምፅ ከሰጡት አገሮች መካከል የአብዛኞቹን ድምፅ በአብላጫነት ያገኙት ዕጩዎች ይሆናሉ የኮሚቴው አባላት ለአራት ዓመታት የስራ ጊዜ ያገለግላሉ ነገር ግን በመጀመሪያው ምርጫ ከተመረጡት መካከል የዘጠኙ አባላት የስራ ዘመን ለሁለት ዓመታት ብቻ ይሆናልር ከመጀመሪያው ምርጫ በኋላ ወዲያውኑ የነዚህ ዘጠኝ አባላት ማንነት በኮሚቴው ሊቀመንበር አማካይነት በዕጣ ይወሰናል «ኛው አገር ስምምነቱን ካፀደቀ ወይም ከተቀበለ በኋላ የአምስቱ ተጨማሪ የኮሚቴው አባላት ምርጫ በዚህ አንቀ ንዑስ አንቀጽ እና መሰረት ይካሄዳል ከእነዚህ ተጨማሪ አባላት መካከል የሁለቱ የስራ ዘመን ለሁለት ዓመታት ብቻ ይሆናል የሁለቱ አባላት ማንነት በኮሚቴው ሊቀመንበር አካማይነት በዕጣ ይወሰናል በኮሚቴው ውስጥ ክፍት የስራ ቦታ ሲፈጠር ስራውን ያቋረጠው አባል ዜጋ የሆነበት አገር ሌላ ባለሙያ ከዜጎቹ መሀከል መርጦ በማቅረብ ኮሚቴው አባልነቱን ተቀብሎ እንዲያፀድቀው ያደርጋል ጠቅላላ ጉባዔው ሲያፀድቅና ይኸው አካል የኮሚቴውን ኃላፊነት ክብደት ግምት ውስጥ በማስገባት በሚወስነው ደንብና ተመን መሰረት የኮሚቴው አባላት ለድካማቸው ከተባበሩት መንግስታት ጥሪት ወጭ የሚሆን አበል ይከፈላቸዋል ኮሚቴው በዚህ ስምምነት የተሰጠውን ኃላፊነት በትክክል እንዲፈፅም የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አስፈላጊውን የሰው ኃይልና ድርጅት ያሟላለታል አንቀጽ ይህን ስምምነት የተቀበሉ አገሮች ስምምነቱን ለማስፈፀም ስለወሰዲቸው ሕግ የማውጣት የዳኝነት አስተዳደራዊ ወይም ሌሎች እርምጃዎች የሚገልጽ ዘገባ በኮሚቴው እንዲታይ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ያቀርባሉ ይህን የሚያደርጉትም ሀ ለዚያ አገር ስምምነቱ በፀና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለ ከዚያ በኋላ አነሰ ቢባል በየአራት ዓመታት አንዴ እንዲሁም ኮሚቴው በጠየቀበት ጊዜ ይሆናል የሚያቀርቡት ዘገባም በዚህ ስምምነት ውስጥ የተደነገጉትን ግዴታዎች በመፈጸም ረገድ ያጋጠሙትን ችግሮችና ሁኔታዎች ሊገልጽ ይችላል አንቀጽ ኮሚቴው የራሱን የስነስርዓት ደንብ ይወስናል ኮሚቴው የስራ አስፈፃሚዎቹን ለሁለት ዓመታት የስራ ዘመን እንዲያገለግሉ ይመርጣል አንቀጽ በዚህ ስምምነት አንቀጽ መሰረት የቀረቡለትን ዘገባዎች ለማየት ኮሚቴው በየዓመቱ ከሁለት ሳምንታት ላልበለጠ ጊዜ ይሰበሰባል የኮሚቴው ስብሰባዎች በተባበሩት መንግስታት ዋና ጽሕፈት ቤት ውስጥ ወይም ኮሚቴው በሚያመቸው ሌላ ቦታ ይደረጋሉ አንቀጽ በኢኮኖሚና ማሕበራዊ ምክር ቤት አማካይነት ኮሚቴው ስለ እንቅስቃሴዎቹ የሚገልጽ ዘገባ በየዓመቱ ለተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል በዘገባውም ውስጥ ስምምነቱን ከተቀበሉት አገሮች የደረሱትን መረጃዎችና ዘገባዎች መርምሮ የራሱን አስተያየቶችና የእርምጃ ሀሳቦች ካሉት ማካተት ይችላል እነዚህ የሚቀርቡት ግን ከእነዚያ አገሮች አስተያየቶች ጋር ተዳምረው ነው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ የኮሚቴውን ዘገባዎች የሴቶችን ሁኔታ ለሚከታተለው ኮሚሽን እንዲያውቀው ያስተላልፍለታል አንቀጽ ልዩ ተልእኮ የተሰጣቸው ድርጅቶች የዚህ ስምምነት ድንጋጌዎች አፈፃፀም በሚታይበት ጊዜ የነሱን ተግባራት የሚመለከቱ ጉዳዮች ሲኖሩ በወኪሎቻቸው አማካይነት በስብሰባዎቹ ውስጥ የመሳተፍ መብት አላቸው ኮሚቴውም ከስምምነቱ አፈፃፀም አንፃር እነሱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ዘገባ እንዲያቀርቡ ድርጅቶቹን ሊጋብዝ ይችላል ክፍል ስድስት አንቀጽ በሴቶችና በወንዶች መካከል እኩልነት እንዲሰፍን ይበልጥ አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር ሀ ስምምነቱን የተቀበለ አገር ሕግወይም ለ በዚያ አገር ውስጥ የፀና ሌላ ዓለም አቀፍ ስምምነት ወይም ውል በዚህ ስምምነት አይሻርም አንቀጽ በዚህ ስምምነት ዕውቅና ያገኙትን መብቶች በሙሉ ለማስከበር ይህን ስምምነት የተቀበሉ አገሮች ሁሉ በብሔራዊ ደረጃ ማንኛውንም አስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ ተስማምተዋል አንቀጽ ሁሉም አገሮች እንዲፈርሙበት ይህ ስምምነት ክፍት ነው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ስምምነቱን እንዲረከብ ተመድቧል ይህ ስምምነት በየአገሩ መፅደቅ ይኖርበታል የማፅደቂያ ማረጋገጫዎች ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ መቅረብ አለባቸው ይህ ስምምነት በስራ ላይ ከዋለ በኋላም ቢሆን ማንኛውም አገር እንዲቀበለው ክፍት ነው የስምምነቱ መቀበያ ሰነድ ለተባበሩት መንግስታት ጸሐፊ ሲቀርብ አባልነት ይፈፀማል አንቀጽ ስምምነቱን የተቀበለ ማንኛውም አገር የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊን ስምምነቱ እንዲሻሻል በማንኛውም ጊዜ በፅሁፍ መጠየቅ ይችሳል የዚህ ዓይነት ጥያቄ በሚቀርብበት ጊዜ ምን እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ጠቅላላ ጉባዔው ይወሰናል አንቀጽ ኛው የማፅደቂያ ወይም ስምምነቱን የመቀበያ ሰነድ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ከቀረበበት ዕለት በኋላ በኛው ቀን ይህ ስምምነት የፀና ይሆናል ኛው ማፅደቂያ ወይም መቀበያ ከቀረበ በኋላ ስምምነቱን ለሚያፀድቁ አገሮች የራሳቸውን ማፅደቂያ ወይም መቀበያ ካስረከቡበት ዕለት በኋላ በኛው ቀን ስምምነቱን ለነሱም የፀና ይሆናል አንቀጽ በስምምነቱ ማጽደቂያ ወይም መቀበያ ሰነድ ላይ አባል አገሮች የሚያስመዘግቡትን ማንኛውንም ተአቅቦ ዋና ጸሐፊው በጽሑፍ ተቀብሎ ለሌሎቹ አገሮች ቅጂውን ያስተላልፋል የዚህን ስምምነት ዓላማና ግብ የሚፃረር ተአቅቦ ተቀባይነት አይኖረውም ማናቸውንም ተአቅቦ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ በማስታወቅ ማንሳት ወይም ማስቀረት ይቻላል ዋና ጸሐፊውም የተአቅቦውን መነሳት ለሌሎች ስምምነቱን ለተቀበሉ አገሮች ያስታውቃል እንዲህ ዓይነቱ ተአቅቦ የማንሳት ማስታወቂያ ለዋና ጸሐፊው ከደረሰበት ዕለት ጀምሮ የፀና ይሆናል አንቀጽ የስምምነቱ አተረጓጐም ወይም አፈጻጸም በሚመለከት ስምምነቱን በተቀበሉ ሁለትና ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ አገሮች መካከል የሚነሳ ማንኛውም ክርክር በድርድር ሊፈታ ካልቻለ በአንደኛው ጥያቄ ለግልግል ዳኝነት ሊቀርብ ይችላል። ዋና ፀሐፊው በበኩሉ ወደ ሌሎች የስምምነቱ ፈራሚ አገሮች ያሰራጫቸዋል እውቅናው በማናቸውም ጊዜ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በሚፃፍ ደብዳቤ ሊነሳ ይችላል እንደዚህ ዓይነቱ ዕውቅና የማንሳት ተግባር በዚሁ አንቀጽ መሰረት በማጣራት ሂደት ላይ የሚገኙ ጉዳዮች ላይ የሚደረገውን ምርመራ አያደናቅፍም ተጠቃሹ አገር የላከው እውቅና የማንሳት ጥያቄ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ እጅ ከገባ በኋላ እውቅና መስጠት የሚመለከት ደብዳቤ እንዳዲስ ካልተላከ በቀር ከግለሰብ ወይም ከተወካዩ ለኮሚቴው የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የለውም አንቀጽ የኮሚቴውና በአንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሠ በተደነገገው መሠረት የሚቋቋመው ጊዜያው አስታራቂ ኮሚሽን አባላት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መልዕክተኞች ሠራተኞች ተልዕኮአቸውን በሚፈጽሙበት ወቅት በድርጅቱ መልዕክተኛነታቸውና ሰራተኝነታቸው ሊያገጃቸው ስለሚገቡ ልዩ ሁፄታዎች ልዩ መብትና ከፃላፊነት ነባ የመሆን መብት ለመደንገግ በወጣው ስምምነት መሠረት የተመቻቹ ሁኔታዎች ልዩ ጥቅምና ከፃላፊነት ነፃ የመሆን መብት ተጠቃሚዎች ይሆናሉ አንቀጽ ኮሚቴው በዚሁ ቃልኪዳን የተጠቀሱትን የስራ እንቅስቃሴዎች በማስመልከት የሚያዘጋጀውን ዓመታዊ ሪፖርት የስምምነቱን ለተቀበሉ አገሮችና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል ክፍል ሶስት አንቀጽ ይህ ስምምነት ለሁሉም አገሮች ለፊርማ ክፍት ነው ይህ ስምምነት መፅደቅ አለበት የማፅደቂያ ሰነዶች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ዘንድ ይቀመጣሉ አንቀጽ ይህ ስምምነት ሥራ ላይ ከዋለም በጊላ አገሮች እንዲቀበሉት ክፍት ነው ስምምነቱን መቀበል የሚረጋገጠው የመቀበያ ሰነድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፅሕፈት ቤት በማስቀመጥ ነው አንቀጽ ይህ ስምምነት የስምምነቱን ሃያኛው የማጽደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ከረቀበበት ጊዜ ጀምሮ በሰላሳኛው ቀን የፀና ይሆናል የስምምነቱ ሃያኛው የማፅደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ከቀረበ በኋላ የማፅደቂያ ሰነድ ወይም የመቀበያ ሰነድ ለሚያቀርብ እያንዳንዱ አገር ስምምነቱ የሚፀናው የማፅደቂያ ሰነድ ወይም የመቀበያ ሰነድ ከአቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በሰላሳኛው ቀን ይሆናል አንቀጽ እያንዳንዱ አገር ስምምነቱ በሚፈርምበት ወይም በሚያፀድቅበት ጊዜ በዚሁ ስምምነት አንቀጽ መሰረት ለሚቋቋመው ኮሚቴ ስልጣን እውቅና እንደማይሰጥ መግለጽ ይችላል በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ መሰረት ተአቅቦውን ያቀረበ ማንኛውም የስምምነቱ አባል አገር በማንኛውም ጊዜ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በሚጽፈው ደብዳቤ በኩል ተአቅቦውን ማንሳት ይችላል አንቀጽ ማንኛውም የስምምነቱ አባል አገር የማሻሻያ ሃሳብ ሊያቀርብ ይችላል የማሻሻያ ሃሳቡንም የሚያቀርበው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ይሆናል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በበኩሉ የማሻሻያ ሃሳቡ እንደደረሰው ፈራሚ አገሮች ተሰብስበው በቀረበው የማሻሻያ ሃሳብ ላይ ለመነጋገርና ለመወሰን ይፈልጉ እንደሆነ በመጠየቅ የማሻሻያ ሃሳቡ ይልክላቸዋል ይህ ከሆነ በአራት ወራት ውስጥ ቢያንስ የአባሉቹ አንድ ሶስተኛ መሰብሰቡን ከደገፉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በድርጅቱ ስም የስብሰባ ጥሪ ያስተላልፋል የማሻሻያ ሃሳቡ በስብሰባው ላይ ተገኝተው ድምጽ ከሰጡት አባል አገሮች በብዙሐኑ ድምጽ የተደገፈ ከሆነ ሁሉም የስምምነቱ ፈራሚ አገሮች እንዲቀበሉት ዋና ፀሐፊው ያሰራጨዋል በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ መሰረት ተቀባይነት ያገኘውን የማሻሻያ ሃሳብ ይህን ስምምነት ከተቀበሉ አገሮች መካከል ሁለት ሶስተኛዎቹ የሕገ መንግስታቸውን አሰራር መሰረት በማድረግ የተቀበሉት መሆኑን በመግለፅ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ሲያሳውቁ የፀና ይሆናል የማሻሻያ ሃሳቡ ከፀና በኋላ ለተቀበሉት ፈራሚ አገሮች አስገዳጅ ይሆናልር ሌሎች የስምምነቱ ፈራሚ አገሮች ግን በስምምነቱ ሕጎችና ቀደም ሲል ራሳቸው የተቀበሏቸውን የማሻሻያ ሃሳቦች ያከብራሉ አንቀጽ የስምምነቱን አተረጓጎም ወይም አፈፃፀም በተመለከተ በሁለት ወይም ከሁለት በላይ የስምምነቱ አባል አገሮች መካከል የሚፈጠር አለመግባባት በውይይት መፍታት ካልተቻለ በአንዳቸው ጥያቄ ለግልግል ዳኝነት ይቀርባል ጉዳዩ በግልግል ዳኝነት እንዲታይ ጥያቄ ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ በስድስት ወራት ውስጥ በግልግል ዳኝነቱ አደረጃጀት ላይ ከስምምነት ላይ ካልደረሱ አንዱ አገር ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ሊያቀርበው ይችላልር ይህ የሚሆነው በፍርድ ቤቱ ደምብ መሰረት ነው እያንዳንዱ አገር ስምምነቱን በሚፈርምበት በሚያፀድቅበት ወይም በሚቀበልበት ጊዜ በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ እንደማይገደድ መግለጽ ይችላል ሌሎች አገሮችም ተዓቅቦውን ካስቀመጠ አገር ጋር በሚኖራቸው ግንኝነት በዚሁ ንኡስ አንቀጽ ሕግ አይገደዱም በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ተዓቅቦ ያስቀመጠ አገር በማንኛውም ጊዜ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በሚፅፈው ደብዳቤ በኩል ተዓቅቦውን ማንሳት ይችላል አንቀጽ ማንኛውም የስምምነቱ አባል አገር ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በሚፅፈው ደብዳቤ ከስምምነቱ አባልነት መውጣት ይችላል አባልነቱ የሚቀረውሃሸ ውሣኔው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ከአንድ ዓመት በኋላ ይሆናል ከስምምነቱ ለመውጣት የሚደረገው ውሳኔ ስምምነቱን የተቀበለ አገር ከስምምነቱ ለመውጣት ያደረገው ውሳኔ ከመጽናቱ በፊት ከስምምነቱ ድንጋጌዎች ውጭ በመፈፀሙ ድርጊት ወይም ባለመፈፀሙ ከሚደርስበት ተጠያቂነት ነፃ አያደርገውም አንዲሁም ከስምምነቱ ለመውጣት የተደረገው ውሳኔ ከመጽናቱ በፊት በኮሚቴው ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ያለ ጉዳይ አይቋረጥም የስምምነቱ አባል በሆነ አገር የሚቀርብ አባልነት የማቋረጥ ጥያቄ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ የሚቀርብ አዲስ ክስ በኮሚቴው ተቀባይነት አይኖረውም አንቀጽ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ለሁሉም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል አገሮችና ለሁሉም ስምምነቱን የፈረሙ ወይም የተቀበሉ አገሮች የሚከተሉትን ጉዳዮች ያሳውቃቸዋል ሀ በአንቀጽ እና መሰረት መንግስታት መረፈማቸውን ማጽደቃቸውንና መቀበላቸውን ለ በአንቀጽ መሰረት ስምምነቱ ተፈፃሚ የሚሆንበት ቀን እና በአንቀጽ መሰረት የማሻሻያ ሃሳቦች ተፈፃሚ የሚሆኑበትን ቀን ሐ በአንቀጽ መሰረት የሚቀርብ አባልነትን የማቋረጥ ውሳኔ አንቀጽ በዓረብኛ በቻይንኛ በእንግሊዝኛ በፈረንሳይኛና እስፓንኛ የተዘጋጁ የስምምነቱ ሰነዶች እኩል ተቀባይነት ያላቸው ሲሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መዝገብ ቤት ይቀመጣሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ትክክል መሆናቸው የተረጋገጡ የስምምነቱ ቅጂዎች ወደ ሁሉም አገሮች ያሰራጫል የሕጻናት መብቶች ስምምነት ይቀጎ ። ይሁን እንጂ የመፍትሄው ሂደት በአእምሮ ግምት ረጅም ጊዜ ከወሰደ ይህ ህግ ተፈፃሚነት አይኖረውም ለ ኮሚቴው በጉዳዩ አስተያየትና የመፈትሄ ሃሳቦች ካለው ለተከሳሹ አገርና ለከሳሹ ያቀርባል ኮሚቴው ባደረገው ጉዳዩን የማጣራት ግንኙነት ያገኘው ጭማቂ ሃሳብ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ክስ የቀረበበት አገር የሰጠው ማብራርያና መግለጫ እንዲሁም የራሱ አስተያየትና የመፍትሄ ሃሳቦች ያካተተ ፅሑፍ በሚያቀርበው ዓመታዊ ዘገባ ያካትታል ኮሚቴው በዚሁ አንቀፅ የተመለከቱ ተግባራትን ማከናወን የሚችለው በዚሁ አንቀፅ ንኡስ ዓንቀፅ መሰረት ስምምነቱን ከተቀበሉ አገሮች መካከል ቢያንስ አስሩ እውቅና ከሰጡት ይሆናል አንቀጽ እኤአ ዲሰምበር ቀን ዓም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጠቃላይ ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር ዐር የተደነገገውና በቅኝ ግዛት ስር የሚገኙት አገሮችና ህዝቦች ነፃነት ያቀዳጀው መግለጫ ተግባራዊነት እንደተጠበቀ ሆኖ በዚሁ የሰፈሩ ሕጎች እኒኝህ ህዝቦች በሌላ የዓለም አቀፍ አሰራር ወይም ልዩ ተልእኮ ባላቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላት የተጎናፀፉት ክስ የማቅረብ መብት በማንኛውም መንገድ አይገደብም ሀሀ በዚሁ ስምምነት አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ መሰረት የሚቋቋመው ኮሚቴ የአጠቃላዩ ጉባኤ ውሳኔ በሳ ተግባር ላይ በሚውልባቸው በሞግዚታዊ እና ራስ ገዝ ባልሆነ መስተዳድር የሚተዳደሩ ነዋሪዎች የሚያቀርቡት ክስ ቅጂ ይቀበላል ይህንን ክስ ለመመርመርና በዚሁ ስምምነት የሰፈሩት መርሆዎችና ግቦች በቀጥታ ለመፈፀም ለሚቋቋሙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላት በክሱ ያለውን አስተያየትና የመፍትሄ ሃሳቦች ያቀርባል ለ ኮሚቴው በዚሁ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ ሀ የተጠቀሱት ግዛቶች ለማስተዳደር የሚሰየሙት ጉዳዩን የሚመለከታቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላት ከቃል ኪዳኑ ዓላማ ጋር ትስስር ያላቸው የሕግ አውጪ ፍርድ ቤት አስተዳደራዊና ሌሎች ተግባራት በሚመለከት የሚያዘጋጁት ዘገባ ቅጂ ይቀበላል ኮሚቴው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጠቃላይ ጉባኤ በሚያቀርበው ዘገባ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ አካላት የተቀበለው ክስና ዘገባ እንዲሁም ኮሚቴው በክሱና ዘገባው በመመስረት የሚሰጠው አስተያየት መግለጫና የመፍትሄ ሃሳብ ያካትታል ኮሚቴው ለስምምነቱ ግቦች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችና በዚሁ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ ሀ ከተጠቀሱት ግዛቶች ትስስር ያላቸው ጉዳዮች በማስመልከት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ መጠየቅ ይችላል አንቀጽ የዚሁ ስምምነት ዓንቀፆች ከአድልዎና ልዩነት ተያያዥነት ያላቸው ውዝግቦችና ክሶች መፍትሄ ለመስጠት ከሚወጡት ሌሉች ስነ ስርዓቶች በማይቃረን መልኩ ተግባራዊ ይሆናሉ ልዩ ተልእኮ የተሰጣቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላት ከሚያወጡት ስነ ስርዓትና ስምምነቱን የተቀበሉ አገሮች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት በማድረግ ግጭት ለመፍታት ከሚደነግግዋቸው ስነ ስርዓቶችም አይቃረኑም ክፍል ሶስት አንቀጽ ይህ ስምምነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ልዩ ተልእኮ የተሰጣቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላት አባል የሆነ የዓለም አቀፍ ፍትሕ ፍርድ ቤት የተመሰረተበት ሕግ የተቀበለ ወይም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጠቃላይ ጉባኤ ይህንን ስምምነት እንዲቀበል ጥሪ የቀረበለት ማንኛውም አገር እንዲፈርምበት ክፍት ነው ይህ ስምምነት ተፈፃሚ የሚሆነው በፈራሚ አገሮች ሲፀድቅ ነው የማፅደቂያ ሰነዶቹም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፅቤት ይቀመጣሉ አንቀጽ ይህ ስምምነት በአንቀፅ ንኡስ አንቀፅ የተጠቀሱት አገሮች እንዲቀበሉት ክፍት ነው የመቀበያ ሰነዶችም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ መቅረብ አለባቸው አንቀጽ የስምምነቱ ሃያ ሶስተኛው የማፅደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በሰለሳኛው ቀን ስምምነቱ የፀና ይሆናል የስምምነቱ ሃያ ሰባተኛው የማፅደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከቀረበ በኋላ ስምምነቱን የሚያፀድቁ አገሮች የየራሳቸው የማፅደቂያ ወይም የመቀበያ ሰነድ ከአቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ በሰላሳኛው ቀን በስምምነቱ ይገደዳሉ አንቀጽ የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ስምምነቱን የሚቀበሉ አገሮች ስምምነቱን ሲያፀድቁ ወይም ሲቀበሉ ያስመዘገቡት ተአቅቦ ለሌሎች የስምምነቱ ፈራሚ አገሮች ያሳውቃል ተአቅቦውን የሚቃወም ማንኛውም አገር መልእክቱ ከደረሰው በኋላ በዘጠና ቀናት ውስጥ እንደማይቀበለው በመግለፅ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ማሳወቅ አለበት ከስምምነቱ መሰረታዊ ዓላማና ግብ ጋር በሚቃረን አኳኋን የተመዘገበ ተአቅቦ ተቀባይነት አይኖረውም በስምምነቱ መሰረት የሚቋቋም አካል የስራ እንቅስቃሴም አያደናቅፍም።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact