Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ሁሉም ወንጀሎች በሚያደርሱት ጉዳት በወንጀሉ አደገኛነት የአጥፊው የአእምሮ ሁኔታየጥፋተኛው ያለፈ የወንጀል ታሪኩን በማገናዘብ እንደሁኔታው ቅጣቱ ከድርጊቱ ጋር ተመጣጣኝ ሊሆን ይገባል ማለት ነው ከዚህ በላይ የተጠቀሰው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ እና ላይ እንደተመለከተው የወንጀለኛው ጥፋት በጣም ከባድ ካልሆነና የዝምድና ወይም የወዳጅነት ትስስሩ ግንኙነቱ እጅግ ጥብቅ ከሆነ ወንጀለኛውን በማስጠንቀቅ ወይም በወቀሳ ብቻ ፍርድ ቤቱ አምኖበታል ተከሣሽ የእስራት ቅጣቱ የተገደበለት በመሆኑ የገንዘብ ቅጣቱን እንደከፈል ከእስር እንዲፈታ በማለት ፍቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል የቅጣት አወሳሰን ላይ የሚታዩ ችግሮች አጠቃላይ የህጉን አቀራረጽ ስንመለከት ዳኛው ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችን መሰረት አድርጎ በቅደም ተከተል ቅጣቱ እንደሚወሰን ይደነግጋል ይሁንና ማክበጃውን ተግባራዊ ለማድረግ መነሻ ቅጣቱ ስንት ነው።
ብላክስ ሎዉ የህግ መዝገበ ቃለት ኛ እትም ገፅ ሀ የሞት ቅጣት የሞት ቅጣት የሰውን ህይወት የሚያሳጣ ፍርድ ነው የሞት ፍርድ በአጠቃላይ በተለዬ ሁኔታ ከባድ ተብለው ለሚገመቱ ወንጀሎች የሚደነገግ የቅጣት ዓይነት ነው በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ ላይ እንደተመለከተው የሞት ቅጣት የሚወሰነው የተፈፀመው ወንጀል የሞት ቅጣት የሚያስቀጣ ስለመሆኑ ወንጀሉን በሚያቋቁመው የሕጉ ልዩ ክፍል በግልፅ ተደንግጐ በተገኘ ጊዜ ለወንጀለኛው ቅጣትን የሚያቃልልለት ምክንያት በማይኖርበት ጊዜ ወንጀለኛው ወንጀሉን በፈፀመበት ጊዜ ዕድሜው ቢያንስ አስራ ስምንት ዓመት የሞላው ሲሆን ነው ከቀድሞው የወንጀል ህግ በተቃራኒ አዲሱ የወንጀል ሕግ የሞት ቅጣት በሕዝብ ፊት በአደባባይ በስቅላት ወይም በሌላ ኢሰብአዊ በሆኑ ዘዴዎች መፈፀም እንደሌለበት ደንግጓልአንቀጽ ኹ የአፈፃፀም ዘዴው ግን ጉዳዩ በሚመለከተው የፌዴራል ወይም የክልል ማረሚያ ቤት የበላይ ሕግ አስፈፃሚ አካል እንዲወሰን ተደርጓል ይህም የሆነው ጉዳዩ የሚመለከተው የማረሚያ ቤቶች የበላይ ሕግ አስፈፃሚ አካል በየአካባቢው ባሉት ሁኔታዎች መሠረት አቅም በፈቀደ መጠን ሰብአዊ በሆነ መንገድ የሞት ፍርድ የሚፈፀምበትን ዘዴ እንዲወስን ለማስቻል ታስቦ ስለመሆነ ተመልክቷል የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሰው በፍፁም ኢኃላፊነት ወይም ከፊል ኃላፊነት ላይ የሚገኝ ከሆነ የአዕምሮ ሁፄታው እስኪስተካከል ማለትም የማመዛዘን ችሎታው እስኪመለስ ድረስ በፅኑ የታመመ ሰው ከሆነ ሕመሙ እስኪሻለው እስኪፈወስ ድረስ ያረገዘች ሴት ከሆነች እስክትወልድ ድረስ አፈጻጸሙ ታግዶ ይቆያል እንዲሁም የሞት ቅጣት ሊለወጥ የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉ ይኸውም ያረገዘች ሴት ህይወት ያለው ልጅ የወለደች እንደሆነና ልጁን መመገብና ማሳደግ የሚኖርባት የሆነ አንደሆነ ቀደም ሲል ተፈርዶባት የነበረው የሞት ቅጣት ወደ ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ይቀየርላታል ከዚህ በተለዬ ደግሞ የሞት ፍርድ በሚመለከተው አካል በሚሰጥ ይቅርታ ቅጣቱ ሊለወጥ ወይም ሙሉ በሙሉ ቀሪ ሊሆን የሚችል ሲሆን እንዲሁም ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ሰው በመንግስት የተሰጠ ምህረት ተጠቃሚ ከሆነ ቅጣቱ ሊቀርለትና ጥፋተኛ የተባለበትን ወንጀል ጭራሽ እንዳልፈፀመ ሊቆጠር ይችላል ለ የእስራት ቅጣት እስራት በሁለት ይከፈላል እነርሱም ቀላል እስራት እና የማረፊያ ቤት እስራት ናቸው ቀላል አስራት ይህ ከባድነታቸው መካከለኛ ለሆኑ ወንጀሎችና ለሕብረተሰቡ አደገኛ ላልሆኑ ወንጀሎች የተደነገገ የቅጣት ዓይነት ነው የወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል የቀላል እስራቱን የታች ወይም የላይ ወሰን በግልፅ የሚደነግግበት ጊዜ ያለ ሲሆን ይህ የማይሆንበት ሁኔታም አለ አንዳንድ ጊዜ የቀላል አስራት ቅጣቱ የታች ወይም የላይ ወሰን በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል አንቀጾች ሊገለፅ የሚችል ሲሆን አንዳንድ ጊዜም የቅጣቱ ወሰን ሳይገለፅ ቅጣቱ ቀላል አስራት መሆኑ ብቻ ይጠቀሳል አንዲህ በሚሆንበት ጊዜ በቀድሞው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግም ሆነ በአዲሱ የወንጀል ሕግ የቀላል አስራት ቅጣቱ መነሻ አስር ቀን የላይ ጣራው ደግሞ እስከ ሦስት ዓመት ይደርሳል ምንም እንኳን በመርህ ደረጃ የቀላል እስራት ጊዜ ከአስር ቀን እስከ ሦስት ዓመት ቢሆንም በተለዩ ምክንያቶች የቀላል እስራት እስከ አምስት ዓመት ሊደርስ እንደሚችል ተመልክቷልአንቀጽ ዐ እነዚህም ምክንያቶች ከወንጀሉ ከባድነት የተነሳ በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል ተደንግጐ ሲገኝ ቀላል አስራት ከሶስት ዓመት ገደብ አልፎ እስከ አምስት ዓመት ሊደርስ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል በቀላል አስራት የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈፅመው ሲገኙ የቀላል እስራት ቅጣት እስከ አምስት ዓመት ሊደርስ ይችላል ይሁንና ፍርድ ቤቱ የሚወስነው የቀላል እስራት ቅጣት ድምሩ ከአምስት ዓመት ማለፍ አይችልም የእስራቱን ዘመን ማርዘም እንዲቻል በማሰብም ቅጣቱን ከቀላል እስራት ወደ ፅኑ እስራት ፍርድ ቤቱ ሊቀይር አይችልም በቀላል እስራት በሚያስቀጡ ወንጀሎች በተደጋጋሚ ሲቀጣ የቀላል እስራት ቅጣት እስከ አምስት ዓመት ሊደርስ ይችላል አዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ነጥብ በተደጋጋሚ ሲቀጣ ማለት ጥፋተኛው ደጋጋሚ ወንጀለኛ ሲሆን ማለት አይደለም ከቀላል እስራት ጋር በተያያዘ ሌላው ሊነሳ የሚገባው ነጥብ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ እስከ ስድስት ወር የሚደርስ የቀላል እስራት ቅጣት በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ በሚያጋጥምበት ጊዜ ሁሉ በቀላል አስራቱ ምትክ ፍርድ ቤቱ የግዴታ ሥራን ሊወስን እንደሚችል ተመልክቷል አንቀጽ ዐሃ ፅኑ እሥራት ፅኑ አስራት ለከባድ ወንጀሎችና ለሕብረተሰቡ አደገኛ በሆኑ ወንጀለኞች ላይ የሚወሰን የቅጣት ዓይነት ነው የወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል የእስራቱን ጣራ ወይም የአስራቱን የታች ወለል ወይም ሁለቱንም በግልፅ የሚደነግግበት ጊዜ ያለ ሲሆን ይህ የማይሆንበት ሁኔታም አለ አንዳንድ ጊዜ የፅኑ እስራት ቅጣቱ የታች ወይም የላይ ወሰን በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል አንቀጾች ሊገለፅ የሚችል ሲሆን አንዳንድ ጊዜም የቅጣቱ ወሰን ሳይገለፅ ቅጣቱ የፅኑ እስራት መሆኑ ብቻ ይጠቀሳል እንዲህ በሚሆንበት ጊዜ በቀድሞው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግም ሆነ በአዲሱ የወንጀል ሕግ የፅኑ እስራት ቅጣቱ መነሻ አንድ ዓመት የላይ ጣራው ደግሞ እስከ ሀያ አምስት ዓመት ይደርሳል ሆኖም በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል በግልፅ ተደንግጎ በተገኘ ጊዜ የፅኑ አስራት ዘመን እስከ ወንጀለኛው የዕድሜ ፍፃሜ ድረስ ሊቀጥል ይችላል በፅነ እስራት የተቀጣ ወንጀለኛ አደገኛ ነው ተብሎ ስለሚገመት የአፈፃፀም ሁኔታ ከቀላል አስራት የአፈፃፀም ሁኔታ በይበልጥ ይከብዳል በማለት ደንግጓል አንቀጽ ዐ በዚህም መሠረት በቀላል እስራት የተቀጣ ሰው በፅኑ አስራት ከተቀጣ ወንጀለኛ የተሻለ የመንቀሳቀስና ሌሎች መብቶች ባለበት ሁኔታ የተፈረደበትን አስራት እንዲፈፅም ይደረጋል ወይም ሊደረግ ይገባል በቀድሞው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ላይ ቀላል አስራት የሚፈፀመው በእስር ቤቶች ፅኑ አስራት የሚፈፀመው ደግሞ በወህኒ ቤቶች ስለመሆኑ ተመልክቶ የሚገኝ ሲሆን ቁጥር ዐ እና ቁጥር ዐ አዲሱ ሕግ ደግሞ እስረኞቹ በተለያዬ ሥፍራ መታሰር ያለባቸው መሆኑና በእስራቱ አፈጻጸም ላይ ልዩነት ያለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ቀላልም ሆነ ፅኑ አስራት የተወሰነባቸው ወንጀለኞች ቅጣታቸውን የሚፈፅሙት ለዚሁ ሥራ በተሰናዱ ማረሚያ ቤቶች ስለመሆኑ ደንግጓል አንቀጽ እና አንቀጽ በቀላልም ሆነ በፅኑ አስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው ወንጀለኞች የመስራት ግዴታ አለባቸው በዚህም መሠረት ሥራ የየትኛውም ዓይነት የአስራት ቅጣት አፈጻጸም አካል ነው ሐ የገንዘብ ቅጣት መቀጮ መቀጮ ወይም የገንዘብ ቅጣት የወንጀል አድራጊውን የገንዘብ ወይም የንብረት ባለቤትነት መብት የሚነካ ቅጣት ነው መቀጮ የሚከፈለው በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ገቢ የሚደረገውም ለመንግሥት ነው የገንዘብ ቅጣት በወንጀል የደረሰ ጉዳትን የማስተካከል ዓላማ የለውም መጠኑም የሚለካው ከደረሰው ጉዳት አንጻር አይደለም የሚለካው ከተፈፀመው ወንጀል ከባድነትና ከተቀጭው የመክፈል አቅም አንጻር ነው መቀጮ ለብቻው ወይም ከሌሎች ቅጣቶች ጋር ሊወሰን ይችላል ብዙውን ጊዜ ሕጉ መቀጮን ከቀላል እስራት ጋር በአማራጭ የሚደነገግ ሲሆን በሕጉ ልዩ ክፍል የሚገኙ አንቀጾች በግልፅ ባይደነግጉም መቀጮ የአስራት አማራጭ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ ፍርድ ቤቱ አስፈላጊነቱን ካመነበት ሁለቱንም ዓይነት ቅጣት አጣምሮ መወሰን እንደሚችል ተደንግጓል ቁጥር አንዳንድ ጊዜ የመቀጮው ቅጣት የታች ወይም የላይ ወሰን በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል አንቀጾች ሊገለፅ የሚችል ሲሆን አንዳንድ ጊዜም የቅጣቱ ወሰን ሳይገለፅ ቅጣቱ መቀጮ መሆኑ ብቻ ይጠቀሳል እንዲህ በሚሆንበት ጊዜ በአዲሱ የወንጀል ህግ የመቀጮ ቅጣቱ መነሻ አስር ብር የላይ ጣራው ደግሞ አስር ሺህ ብር ነው ተቀጪው ህጋዊ ሰውነት ያለው ሲሆን ደግሞ የመቀጮ ቅጣቱ መነሻ አንድ መቶ ብር ጣሪያው ደግሞ አንድ መቶ ሺህ ብር ነውቁጥር ፀዐ የወንደል ሕጉ ልዩ ክፍል የእስራትን ቅጣት አስቀምጦ መቀጮን በአማራጭ በሚደነግግበትና ተቀጪው የሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በሚሆንበት ጊዜ እስራት ወደ መቀጮ የሚለወጥበትን ሁኔታ የሚያመለክት አዲስ ድንጋጌም አለ ቁጥር ዐ በዚህ መሠረት እስከ አምስት ዓመት ቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ አስር ሺህ ብር እስከ አምስት ዓመት ፅነ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ ሃያ ሺህ ብር ከአምስት ዓመት እስከ አስር ዓመት ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ ፃምሳ ሺህ ብር ከአስር ዓመት በላይ ፅኑ አስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በሕግ የሰውነት በተሰጠው ድርጀት ላይ የሚወሰነው የገንዘብ ቅጣት እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጓል እንዲሁም ወንጀልን በሚያቋቁመው የወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል ውስጥ መቀጮ ብቻ በተደነገገ ጊዜ እና ተቀጪው የሕግ ሰውነት ያለው አካል በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቱ የቅጣቱን መጠን የሚወስነው ለተፈጥሮው ሰው ከተቀመጠው ቅጣት አምስት እጥፍ በማድረግ ስለመሆኑ በወንጀል ሕጉ ቁጥር ላይ ተደንግጓል የተፈጥሮ ሰውን በተመለከተ ወንጀሉ የተፈፀመው በአፍቅሮ ንዋይ የሆነ እንደሆነ ቅጣቱ አስከ ዐ ሺህ ብር ሊደርስ ይችላል ተብሎ በቀድሞው ሕግ ላይ ተደንግጎ የነበረው ቁጥር በአዲሱ የወንጀል ሕግ ቅጣቱ እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር ሊደርስ ይችላል ተብሎ ተሻሽሏል ቁጥር በመሠረቱ የገንዘብ ቅጣት ወዲያውኑ መከፈል ይኖርበታል ተቀጭው ገንዘቡን ወዲያው መክፈል ባይችል አስከ ስድስት ወር የመክፈያ ጊዜ ሊፈቀድለት እንደሚችል ተደንግጓል ቁጥር ኹ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተቀየጭው መቀጮውን በየጊዜው እየከፈለ እንዲጨርስ ፍርድ ቤቱ ከሶስት ዓመት ላልበለጠ የመክፈያ ጊዜ ሊሰጠው እንደሚችል ተደንግጓል ቁጥር ኃ በቀድሞው የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ አንድ ጥፋተኛ የተወሰነበትን መቀጮ መክፈል ካልቻለ ወደ እስራት እንደሚለወጥ ይደነግግ የነበረው ቁጥር ተሠርል ለመሠረዙ በምክንያትነት የተሰጠው ድሀውን ወገን የሚጐዳ የቅጣት አፈፃፀም በመሆኑ ፍትሐዊ አይደለም የሚል ነው በአዲሱ የወንጀል ሕግ መሠረት ጥፋቱ ቀላልም ይሁን ከበድ ያለ የመቀጮው መጠን አነስተኛም ይሁን ከፍ ያለ የተወሰነበትን መቀጮ መክፈል ያቃተው ሰው ለመንግስት ወይም ለሕዝባዊ አገልግሎት ድርጅት በማገልገል ወይም የግዴታ ሥራ በመስራት ቅጣቱን እንዲፈፅም ይደረጋል ፍርድ ቤቱ ተቀጭው ለምን ያህል ጊዜ ሥራውን ሊሠራ እንደሚገባው መግለፅ ያለበት ሲሆን የሚወሰነው ጊዜ ከሁለት ዓመት ሊበልጥ አይችልም መ የግዴታ ሥራ የግዴታ ሥራ በወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ሰው ሰርቶ የሚያገኘውን ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ የሚያደርግበትን ሁኔታ የሚመለከት ሲሆን ጥፋተኛው የፈፀመው ወንጀል የሚያስከትለው ቅጣት ከስድስት ወር የማይበልጥ ቀላል እስራት የሆነ እንደሆነና ጥፋተኛውም ለህብረተሰቡ አደገኛነት የሌለው መሆኑ ከታመነበት ፍርድ ቤቱ በእስራቱ ምትክ ከአንድ ቀን እስከ ስድስት ወር ለሜደርስ ጊዜ ወንጀለኛው የግዴታ ሥራ እንዲሰራ ለመወሰን ይችላል አንቀጽ በዚህም መሠረት አስራት ወደ ግዴታ ሥራ እንዲለወጥለት አንድ በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው በይገባኛል የሚጠይቀው ጉዳይ ሳይሆን ፍርድ ቤቱ በሕግ የተቀመጠውን መመዘኛ ግምት ውስጥ በማስገባት እንደ አግባብነቱ እስራቱ ወደ ግዴታ ሥራ እንዲለወጥ ወይም አስራቱ እንዲፈፀም የሚያደርግበት ነው የግዴታ ሥራ የነገሩ ሁኔታን ግምት ውስጥ በማስገባት የተቀጪውን ነጻነት ከመገደብ ጋር እንዲፈፀም ፍርድ ቤቱ ሊወስን የሚችል ሲሆን በተለይም ደግሞ ተቀጪው ነጻነቱ ሳይገደብ የግዴታ ስራ እንዲሰራ ቅጣት ተወስኖበት ይህን የተወሰነበትን ቅጣት በአግባቡ ሳይወጣ ከቀረ ተቀጪው ከአንድ የስራ ቦታ ከአንድ አሰሪ ዘንድ ከአንድ የስራ ተቋም ሳይለቅ ወይም ከመኖሪያ ሥፍራው ሳይወጣ ወይም በመንግሥት ባለሥልጣኖች ከሚጠበቅ ከአንድ የተወሰነ ሥፍራ ሳይለይ የግዴታ ሥራውን እንዲያከናውን ፍርድ ቤቱ ሊያደርግ ይችላል በአስራት ምትክ በግዴታ ሥራ ጥፋተኛው እንዲቀጣ በፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ ከተቀጪው ገቢ ላይ እየተቀነሰ ለመንግሥት ገቢ የሚሆነውን የገንዘብ ልክ የግዴታ ሥራው የሚፈፀምበትን ሥፍራ ቅጣቱ የሚቆይበትን ጊዜ እንዲሁም በተቀጪው ላይ የሚደረገውን የቁጥጥር ዓይነት ማመልከት ያለበት ሲሆን ለመንግስት ገቢ እንዲሆን የሚወሰነው መጠን ከተቀጪው የድካም ዋጋ ወይም በሥራ ፍሬው ከሚያገኘው ጥቅም ከአንድ ሦስተኛ መብለጥ አይችልም በአስራት ምትክ በግዴታ ሥራ እንዲቀጣ የተወሰነበት ወንጀለኛ በፍርድ ቤቱ የተጣለበትን ውሳኔ የጣሰ ወይም በውሳኔው መሠረት ለመፈፀም ፈቃደኛ ሳይሆን የቀረ አንደሆነ ሳይፈፀም የቀረው የግዴታ ሥራ ወደ ቀላል እስራት ተለውጦ ቅጣቱን እንዲፈፅም ይደረጋል አንቀጽ ይህም ማለት ለምሳሌ ከተወሰነበት የግዴታ ሥራ ዘመን ውስጥ ግማሹን በትክክል ፈፅሞ ከሆነ ይኸው ተይዞለት ላልፈፀመው የግዴታ ሥራ ዘመን ብቻ የቀላል አስራት ቅጣት ይጣልበታል ማለት ነው ሠ ተጨማሪ ቅጣቶች ህጉ ከዚህ በላይ ከተቀመጡት ቅጣቶች በተጨማሪ ተጨማሪ ቅጣቶችንም ፍርድ ቤቱ ሊጥል እንደሚችል ያመለክታል ተጨማሪ ቅጣቶች ራሳቸውን ችለው የሚጣሉ ቅጣቶች ሳይሆኑ በማሟያነት የሚወሰዱ አርምጃዎች ናቸው ተጨማረ ቅጣቶችን ለመጣል በልዩ ክፍሉ በወንጀል ድንጋጌው ላይ ተዘርዝረው መገኘት አይኖርባቸውም ማስጠንቀቂያ ወቀሳ ጥፋተኛው ይቅርታ እንዲጠይቅ ማዘዝ በተጨማሪ ቅጣትነት የሚጠቀሱ ናቸው ወንጀሉ በጣም ቀላል በሆነ ጊዜ እነዚህ ቅጣቶች ለዋናው ቅጣት ምትክ ሆነው ሊያገለግሉ አንደሚችሉም ተደንግጎ እናገኛለን ቁጥር ከዚህ በተጨማሪ ከመብት መሻር ከመከላከያ ሰራዊት አባልነት ማስወገድ ወይም ከደረጃ ዝቅ ማድረግ በተጨማሪ ቅጣትነት ሊወሰኑ የሚችሉ ናቸው ረ የጥንቃቄ እርምጃዎች የወንጀል ህጉ ከዚህ በተጨማሪ ወንጀለኛው የተወሰነ ቦታ እንዳይደርስ ወይም ከተወሰነ ቦታ አንዳይወጣ ወዘተ የጥንቃቄ አርምጃዎችን ፍርድ ቤት ሊወስን እንደሚችል ያስቀምጣል ከቁጥር የመወያያ ጥያቄዎች በፅኑ እስራት ቅጣትና በቀላል አስራት መካከል ያለው አንድነትና መሠረታዊ ልዩነት ምንድን ነው። በመቁ በፌዴራል ከፍተኛ ፍቤት በቀረበ አንድ የወንጀል ጉዳይ ላይ ኛ እና ኛ ተከሳሾች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ኛ ተከሣሽ ደግሞ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ ሀ ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ጥፋተኛ ናቸው ከተባለ በኋላ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ሲሰጥ በግራ ቀኙ የቀረበ የቅጣት ማክበጃ ወይም ማቅለያ ምክንያት የለም የታሰሩት የሚታሰብላቸው ሆኖ ኛ እና ኛ ተከሣሾች እያንዳንዳቸው በስምንት ወራት ቀላል አእስራት ኛ ተከሣሽ በሶስት ዓመት ቀላል አስራት እንዲቀጡ በማለት ፍርድ ቤቱ ወስኗል የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አግባብነት ይመርምሩ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን ከ ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች የሚለያቸው ምንድን ነው ብለው ያስባሉ። ተወያዩበት በመቁ በፌዴራል ከፍተኛ ፍቤት በቀረበ አንድ የወንጀል ጉዳይ ላይ ተከሳሽ በ ዓም በወጣው ልዩ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ ለ ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ በፈፀመው በሥልጣን አላግባብ መገልገል ወንጀል ጥፋተኛ ነው በፍርድ ቤቱ ከተባለ በኋላ ዐቃቤ ሕግ በሚከተለው መልኩ የቅጣት አስተያየት አቅርቧል በተከሣሹ ላይ ከተጠቀሰበትና ከቀረበበት ክስ በኛው ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቷል በዚህ መሠረት በወሕቁ ለ አና መ መሠረት ተከሣሹ ወንጀሉን ያደረገው ከግብረአበሮቹ ጋር በመሆኑ በዚህ መሠረት በተከሣሹ ላይ ቅጣት ከብዶ እንዲወሰን አንጠይቃለን በማለት አመልክቷል የዐቃቤ ሕግን የቅጣት አስተያየት በወንጀል ሕጉ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንጻር ይመርምሩ በመቁ በፌዴራል ከፍተኛ ፍቤት በቀረበ አንድ የወንጀል ጉዳይ ላይ ስድስት ተከሣሾች ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ በላ ዐቃቤ ሕግ የቅጣት አስተያየት ሲያቀርብ ኛ እና ኛ ተከሣሾች ወደ ፍርድ አደባባይ ቀርበው መከራከር ሲገባቸው መሰወራቸው ቅጣቱን እንዲያከብድ የሚያደርግ በመሆነ ቅጣቱ ከብዶ እንዲወሰንለት ሲጠይቅ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ደግሞ ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ የተደረገው ተከሣሾች መሰወራቸው አደገኛነታቸውን የሚያሳይ ነው በማለት በቅጣት ማክበጃ ምክንያትነት ወስዶታል የዐቃቤ ሕግን የቅጣት አስተያየት አና የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በወንጀል ሕጉ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንጻር ይመርምሩ ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያዎች ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያዎች በቁጥር የተመለከቱት ሲሆኑ እነርሱም ሀ ወንጀለኛው ወንጀሉን እስካደረገበት ጊዜ ድረስ የዘወትር ጠባዩ መልካም እንደሆነና ያጠፋውም በእውቀት ማነስ ባለማወቅ በየዋህነት ወይም ባልታሰበና ድንገተኛ አጋጣሚ እንደሆነ ለ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው በተከበረና በግል ጥቅም ላይ ባልተመሰረተ ፍላጎት ወይም ከፍ ባለ ሀይማኖታዊ ሞራላዊ ወይም ማህበራዊ እምነት ተነሳስቶ እንደሆነ ሐ ወንጀለኛው ወንጀሉን የፈጸመው ከፍተኛ ቁሳዊ እጦት ወይም የህሊና ስቃይ ደርሶበት ከፍ ያለ አደጋ የሚያመጣ ነገር የተቃጣበት መስሎት መሰረት ያለው ፍርሀት አድሮበት ወይም ደግሞ ሊታዘዝለት በሚገባው ወይም በስልጣኑ ስር በሚያስተዳድረው ሰው ተጽእኖ ምክንያት እንደሆነ መ ወንጀለኛው ወንጀሉን የፈጸመው የተበደለው ሰው ጠባይ ከብርቱ ፈተና ላይ ጥሎት በከባድ ጸብ ቀስቃሽነት ወይም በአስጸያፊ ስድብ ምክንያት ወይም ደም ከሚያፈላ ንዴት ስቃይ ወይም ብስጭት ላይ ጥሉት እንደሆነ ወይም ከፍ ያለ አስገዳጅነት ባለው ስሜትን በሚለውጥ ሁኔታ ወይም ምክንያት ባለው የመንፈስ ሁከት ላይ ሆኖ አንደሆነ ወይም ሠ ወንጀለኛው ወንጀሉን ካደረገ በኋላ በአውነት የተጸጸተ መሆኑን በተለይም በደል ላደረሰበት ሰው አስፈላጊውን እርዳታ በማድረግ ወይም ጥፋቱን በመገንዘብ ራሱን ለፍትህ አካላት በማቅረብ ወይም የወንጀሉ ጥፋት ላደረሰው ጉዳት በተቻለ መጠን በመካስ መጸጸቱን በተግባር አሳይቶ አንደሆነ ወይም ተከስሶ ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ በክስ ማመልከቻው ላይ የተመለከተውን የወንጀል ዝርዝር በሙሉ ያመነ እንደሆነ ነው የሚሉ ናቸው ከእነዚህም ውስጥ ከፊሎቹ በቁጥር ውስጥ ያሉትን መልሰው የሚጠቅሱ ናቸው ከዚህ በላይ በህጉ ከተመለከቱት ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶች ሌላ በቂ የሆነ ምክንያት ዳኛው ካገኘ በዚህ መሰረትም ቅጣቱን ማክበድ ወይም ማቅለል እንደሚችል በቁጥር ተደንግጓል ይሁንና ዳኛው እነዚህን ምክንያቶች ሲቀበል ለምን እንደተቀበለ መግለጽ እንደሚኖርበት ተመልክቷል ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ ቅጣቱ የሚከብድበትን መጠን ወይም የሚቀልበትን ደረጃ በሚመለከት በወንጀል ህጉ ከቁጥር ተዘርዝረው አናገኛለን የመወያያ ጥያቄዎች ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን ከ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች የሚለያቸው ምንድን ነው ብለው ያስባሉ። አንድ ሰው በፈፀመው አንድ ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቶ ቅጣቱ በሚወሰንብት ወቅት ብዛት ያላቸው እና ክብደታቸው ከፍተኛ የሆነ ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ቢኖሩ በአጥፊው ላይ የሚወሰነው ቅጣት ተከሳሹ ጥፋተኛ በተባለበት አንቀጽ ለተደነገገው የቅጣት ዓይነት በወንጀል ሕጉ ጠቅላላ ክፍል ከተመለከተው ዝቅተኛ የቅጣት ወለል ሊወርድ አይችልም ይህ አቀራረብ ትክክል ነው ብለው ያስባሉ። ተወያዩበት በመቁ በፌዴራል ከፍተኛ ፍቤት በቀረበ አንድ የወንጀል ጉዳይ ላይ ተከሳሽ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በፈፀመው ወንጀል ጥፋተኛ ነው ከተባለ በኋላ ፍርድ ቤቱ በሰጠው የቅጣት ውሳኔ ሟችን ከአደጋው በላ ወደ ህክምና ተቋም ማድረሱ ለህግ አካል እጁን መስጠቱ የቅጣት ማቅለያ ሊሆኑት እንደሚገባ በወንጀል ሕግ ቁጥር ሀ ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ እንዲሁም አባትና ወንድሙን ጨምሮ የቤተሰብ አስተዳደሪ መሆኑም የቅጣት ማቅለያ ሊሆኑት እንደሚችሉ ፍርድ ቤቱ ወስጻል የወንጀሉ አፈጻጸምም በድንገት የተፈፀመ መሆኑንም ሆነ ካሳ ለመክፈል ሞክሬ ነበር የተባለውንም ለቅጣቱ ማቅለያነት ግምት ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል በማለት ተከሣሹ በአንድ ዓመት ቀላል አስራትና ሦስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ወስኗል የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በወንጀል ሕጉ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንጻር ይመርምሩ ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ህጉ ከዚህ በላይ ከተገለጹት ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶች በተጨማሪ ልዩ የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ምክንያቶችን ዘርዝሮ እናገኛለን ደጋጋሚ ወንጀለኛነት አንድን ሰው ደጋጋሚ ወንጀለኛ ነው ለማለት በወንጀል ህጉ ሊሟሉ የሚገባቸው መመዘኛዎችን እናገኛለን ከወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ቁጥር ድንጋጌ ይዘት ለመረዳት እንደሚቻለው ደጋጋሚ ወንጀለኛ ለማለት የመጀመሪያው መመዘኛ በወንጀለኛው ላይ ከዚህ ቀደም የወንጀል ክስ ቀርቦበት የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆን አለበት አዲሱን ወንጀል በፈፀመበት ወቅት ቀደም ሲል ፈፅሞት በነበረው የወንጀል ድርጊት ምክንያት የወንጀል ክስ ያልቀረበበት ወይም ክስ ቢቀርብበትም ገና በጉዳዩ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔና ቅጣት ያልተጣለበት ከሆነ የደጋጋሚ ወንጀለኛነት መስፈርት አልተሟላም ማለት ነው ከዚሁ ጎን ለጎን ሊረሳ የማይገባው ነጥብ በመጀመሪያው ወንጀል ቅጣቱ የእስራት ሊሆን የሚገባው መሆኑ ነው በዚህም መሠረት አንድ ሰው በመጀመሪያው ወንጀል የተፈረደበት የገንዘብ መቀጮ የግዴታ ሥራ ወይም ወቀሳና ማስጠንቀቂያ ከሆነ ለደጋጋሚነት ማሟያ ነጥብ አይሆንም ማለት ነው አንድን ሰው ደጋጋሚ ወንጀለኛ ለማለት በሶስተኛነት ሊታይ የሚገባው መመዘኛ ወንጀለኛው ከዚህ ቀደም የተወሰነበትን ቅጣት በሙሉ ወይም በከፊል ከፈፀመበት ወይም በምህረት ወይም በአዋጅ ምህረት ቅጣቱ ከቀረለት ጊዜ ጀምሮ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሌላ ወንጀል የፈፀመ መሆን አለበት አራተኛው የደጋጋሚ ወንጀለኛነት መመዘኛ ወንጀለኛው አዲሱን ወንጀል የፈፀመው አስቦበፀበከበዜሄ መሆን አለበት የሚል ነው በዚህ መሰረት በቸልተኝነት የተፈፀመ ወንጀል ደጋጋሚ ወንጀለኛ አያሰኝም ማለት ነው አምስተኛው መመዘኛ ወንጀለኛው የፈፀመው አዲስ ወንጀል ቢያንስ አስከ ስድስት ወር ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ሊሆን ይገባል በወንጀለኛው የተፈፀመው አዲስ ወንጀል ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት በህጉ ላይ በተደነገጉት የደጋጋሚነት መስፈርቶች መሰረት ደጋጋሚ ወንጀለኛ ነው የሚያሰኘው ከሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ ላይ እንደተደነገገው በመርህ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ለአዲሱ ወንጀል በሕጉ ልዩ ክፍል ወንጀለኛው ጥፋተኛ የተባለበት ድንጋጌ የቅጣት ጣራ አጥፍ እስኪሆን ድረስ ቅጣቱን አክብዶ መወሰን ይችላል በመሆኑም ወንጀለኛው ጥፋተኛ የተባለበትን የሕጉ ልዩ ክፍል ድንጋጌ የቅጣት ጣራ አልፎ ወንጀለኛው ጥፋተኛ ለተባለበት ወንጀል ከተመለከተው የቅጣት ጣራ እጥፍ እስኪሆን ድረስ ፍርድ ቤቱ መወሰን ይችላል ማለት ነው ከዚህ በላይ የተጠቀሰው በወንጀል ሕጉ የተካተተው ለደጋጋሚ ወንጀለኛ በመርህ ደረጃ የሚኖረው የቅጣት አወሳሰን ዘዴ ነው የተደጋገሙት ወንጀሎች ቁጥር ብዛት ያላቸው ከሆነ እንዲሁም የወንጀለኛው የአጥፊነት ደረጃና የድርጊቱ አደገኛነት ከባድ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ለአዲሱ ወንጀል በሕጉ ልዩ ክፍል ወንጀለኛው ጥፋተኛ በተባለበት ድንጋጌ ላይ የተጠቀሰውን የቅጣት ጣራ በማለፍ በወንጀል ሕጉ ጠቅላላ ክፍል ለቅጣቱ ዓይነት እአስከሰፈረው ከፍተኛ ቅጣት ድረስ ሊወስን ይችላል የወንጀል ሕግ አንቀጽ እንዲሁም ወንጀለኛው ልማደኛ ደጋጋሚ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ለመጨረሻው አዲስ ወንጀል የሚጥለው ቅጣት በሕጉ ልዩ ክፍል ወንጀለኛው ጥፋተኛ በተባለበት ድንጋጌ ላይ ከተጠቀሰውን ቅጣት ጣራ የግድ በማለፍ መሆን ያለበት ስለመሆኑ በፍርድ ቤቱ ላይ አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ በዚሁ ንዑስ አንቀጽ ላይ ተደንግጓል የመወያያ ጥያቄዎች በደጋጋሚ ወንጀለኛነት በተደጋጋሚ መቀጣት ወይም ሪኮርድ ያለው በመሆን መካከል ያለው አንድነትና ልዩነት ምንድን ነው። አይጣረዝም ይላሉ ተደራራቢ ወንጀሎች ተደራራቢ ወንጀሎች በርህቨዩበርፀ ዐቨበር በአጠቃላይ በአንድ ሰው ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ወንጀሎች ተፈፅመው ሲገኙ ያለውን ሁኔታ የሚመለከት ሲሆን ሁለት ወይም ቁጥራቸው ከዚያ በላይ የሆኑ ወንጀሎች ተደራራቢ ናቸው ሊባሉ የሚችሉት ሁለተኛው ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት መጀመሪያ በተፈፀመው ወንጀል ላይ ፍርድ አልተሰጠ እንደሆነ ነው አንድ ሰው ተመሳሳይ ድርጊቶችን በተለያዩ ጊዜያት በመፈጸም እንደ አንድ ወንጀል የማይቆጠሩ ወንጀሎችን ሲፈፅም ወይም ተመሳሳይ ያልሆኑ ማለትም የተለያዩ ድርጊቶችን በተለያዩ ጊዜያት በመፈጸም በተለያዩ የወንጀል ድንጋጌዎች ሥር የሚወድቁ ወንጀሎችን በመፈፀም ወይም በአንድ ድርጊት ከአንድ በላይ የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎችን በመጣስ ወይም ደግሞ በአንድ ድርጊት የጣሰው አንድን የሕግ ድንጋጌ ብቻ ቢሆንም ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሆኑ ሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዳት ካደረሰ ተደራራቢ ወንጀሎችን እንደፈፀመ ይቀጠራል የወንጀል ሕግ አንቀጽ ዐ ለተደራራቢ ወንጀሎች የሚኖረውን የቅጣት አወሳሰን ስንመለከት ከተደራራቢ ወንጀሎች ውስጥ በአንደኛው ምክንያት የሞት ወይም የዕድሜ ልክ አስራት ወይም ወንጀሎቹ ተመሳሳይ ዓይነት የእስራት ቅጣት የሚያስቀጡ ሆኖ በአንደኛው ምክንያት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት ከተወሠነ ይህ ውሳኔ ለሌሎች ተደራራቢ ወንጀሎች የሚወሠነውን ቅጣት ሁሉ አጠቃሉ ይይዛል አንቀጽ ሀ ይህም ማለት ከተደራራቢ ወንጀሎች ውስጥ በአንዱ ምክንያት የሞት ቅጣት ወይም የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት የ ዓመት ፅኑ አስራት ወይም የአምስት ዓመት ቀላል አስራት ከተወሠነ በሌሎች ተመሣሣይ ዓይነት ቅጣት በሚያስፈርዱ ወንጀሎች ምክንያት ከተገለፀው ቅጣት በላይ መወሠን አይቻልም በአንቀጽ ሀ የተደነገገው ሁኔታ ቅጣቱ ቢከብድም ከተደራረቡት ወንጀሎች በአንደኛው ውስጥ በሕጉ ልዩ ክፍል ቅጣቱ ተካትቶ ተሸፍኖ የምናገኝበትን ሁኔታ የሚመለከት ነው ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ከባድ ለሆነው ለአንደኛው ወንጀል የሞት ቅጣት የዕድሜ ልክ አስራት ወይም ለእስራቱ ዓይነት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መወሰኑን ትቶ ዝቅ ያለ ቅጣት ከወሠነ በሌሎቹ ተደራራቢ ወንጀሎች ምክንያት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል እስከተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት ድረስ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን አክብዶ መወሠን ይችላል ሯ ጥፋተኛው ከፈፀማቸው ተደራራቢ ወንጀሎች ውስጥ የየትኛውም ወንጀል ቅጣት የቀሪዎችን ወንጀሎች ቅጣት የሚያጠቃልል ካልሆነና ወንጀሎቹ በእስራት የሚያስቀጡ ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች ከሆኑ ለእያንዳንዱ በተደራራቢነት ለተፈፀመው ወንጀል ተገቢ የሆነው ቅጣት ተወስኖ ሁሉም እንዲደመር ይደረጋል ሆኖም ምንጊዜም ቢሆን ለእስራቱ ዓይነት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል ከተደነገገው ጣራ ቅጣት ማለፍ አይቻልምአንቀጽ ለ አንድ ሰው የፈፀማቸው ተደራራቢ ወንጀሎች በገንዘብ ቅጣት በመቀጮ የሚያስቀጡ ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች የሆኑ አንደሆነ ወይም ከሌሎች ቅጣት ጋር ተጣምረው ለተደራራቢ ወንጀሎቹ የገንዘብ ቅጣቶች በጥፋተኛው ላይ የሚጣሉ በሚሆንበት ጊዜ ለእያንዳንዱ በተደራራቢነት ለተፈፀመው ወንጀል ተገቢ የሆነው የገንዘብ ቅጣት ተወስኖ ሁሉም ይደመራል ሆኖም ወንጀሉ በአፍቅሮ ንዋይ የተፈፀመ ካልሆነ በቀር ምንጊዜም ቢሆን በወንጀለኛው ላይ የሚጣለው የመቀጮ ቅጣት አጠቃላይ ድምር በሕጉ ጠቅላላ ክፍል ከተመለከተው ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ወሠን ማለፍ አይችልም የመውረስና የገንዘብ መቀጮ በሚያጋጥምበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሊከተለው የሚገባው የቅጣት አወሳሰን ዘዴ ምን ሊሆን ይገባል የሚለውን በተመለከተ በቀድሞውም ሆነ በአዲሱ የወንጀል ሕግ የተካተተው ሀሳብ ተመሳሳይ ነው ከተደራራቢዎቹ ወንጀሉች በአንዱ ምክንያት የተቀጪው ንብረት እንዲወረስ ከተወሰነ በሌላው ወንጀል ምክንያት መቀጮ በተጨማሪ ሊወሠን አይችልም ቁጥር ሠ አንቀጽ ሠ በአንድ ድርጊት አንድ ሰው ተደራረቢ ጣምራ ወንጀሎች የፈፀመ እንደሆነ ደግሞ ጣምራ ወንጀሎቹን የፈፀመው ከዚህ በታች ከተጠቀሰው ሁኔታ ውጭ ከሆነ በሕጉ ልዩ ክፍል ለከባዱ ወንጀል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት ወሰን ባለማለፍ ፍርድ ቤቱ ቅጣትን አክብዶ ይወስናል አንቀጽ ወንጀለኛው አስቦና አቅዶ ሕጉን ጥሶ ከሆነ ወይም ግልፅ የሆነ መጥፎ ፀባይ አሳይቶ አንደሆነ ግን በአንቀጽ መሰረት ማለትም ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ጊዜ ቅጣት በሚወሰንበት መንገድ ቅጣቱ ከብዶ ይወሰንበታል ግዙፍ ውጤት የሚያስከትሉ ጣምራ ወንጀሎች ተፈፅመው በተገኙ ጊዜ ግን ጥፋተኛው ከተደራራቢ ጣምራ ወንጀሎች ውስጥ ቢያንስ አንደኛውን አስቦ ያደረገ እንደሆነ በአንቀጽ መሰረት ማለትም ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ጊዜ ቅጣት በሚወሰንበት መንገድ ቅጣቱ ከብዶ ይወሰንበታል አንቀጽ ሀጪ ጥፋተኛው ጣምራ ወንጀሎቹን የፈፀመው በቸልተኛነት ከሆነ በሕጉ ልዩ ክፍል ለከባዱ ወንጀል ከተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት ወሰን ባለማለፍ ይወሰንበታል አንቀጽ ለ የመወያያ ጥያቄዎች አንድ ሰው በአንድ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ ከተቀጣ በላ ሌላ ወንጀል ሲፈጽም አና ሁለት ወንጀሎችን በተከታታይነት ሲፈጽም ያለው የቅጣት አወሳሰን ዘዴ ልዩነት ምንድን ነው። የወንጀል ሕጉን ዓላማስ ያሳካል ብለው ያምናሉገ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በአዲሱ የወንጀል ሕግ በልዩ ሁኔታ ቅጣትን ለማቅለል የሚያስችሉ ሁኔታዎች በቁጥር ላይ በግልፅ የተጠቀሱት ምክንያቶች ዝምድናና የጠበቀ ወዳጅነት ቢሆኑም በሕጉ ጠቅላላ ወይም ልዩ ክፍል ውስጥ ፍርድ ቤቱ በመሠለው ቅጣት ማቅለል ይችላል የተባለባቸው ምክንያቶች ሁሉ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ናቸው ቁጥር ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ ያለውን የቅጣት አወሳሰን በተመለከተ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ እና ላይ እንደተመለከተው የወንጀለኛው ጥፋት በጣም ከባድ ካልሆነና የዝምድና ወይም የወዳጅነት ትስስሩ ግንኙነቱ እጅግ ጥብቅ ከሆነ ወንጀለኛውን በማስጠንቀቅ ወይም በወቀሳ ብቻ ፍርድ ቤቱ ሊያልፈው ይችላል ከዚህ ውጭ ባሉ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ግን ፍርድ ቤቱ በመሠለው ቅጣትን ማቅለል የሚችል ቢሆንም የሚወሰነው ቅጣት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል ለየቅጣቱ ዓይነት ከተደነገገው መነሻ ቅጣት ዝቅ ሊል አይችልም አንቀጽ ዐ ይህም ማለት የገንዘብ ቅጣት በአንቀጽ ዐ መሠረት ከብር አስር ሊያንስ አይችልም » የቀላል እስራት ቅጣት በአንቀጽ ዐ መሠረት ከአስር ቀን ሊያንስ አይችልም የፅኑ አስራት ቅጣት በአንቀጽ ዐ መሠረት ከአንድ ዓመት ሊያንስ አይችልም የመወያያ ጥያቄዎች በ የወንጀል ሕጉ ዝምድና ለአንዳንድ ዓይነት ወንጀሎች እንደ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ተደርጎ እንደሚወሰድ የደነገገ ቢሆንም የዝምድናውን ደረጃ በግልፅ አላመለከተም ዝምድና አለ ወይም የለም የሚለውን ለመወሰን የሚቻለው እንዴት ነውገበተለይም አገራችን በምትከተለው የፌዴራል ሥርዓት ምክንያት እያንዳንዱ ክልል በመርህ ደረጃ የራሱን መመዘኛ በመከተል በራሱ የቤተሰብ ሕግ ውስጥ ስለዝምድና ሊደነግግ የሚችል መሆኑ አዚህ ላይ ልብ ሊባል ይገባል የጠበቀ ወዳጅነት አለ የሚባለውስ በምን መመዘኛ ነው። በጥፋተኛው ላይ ለጊዜው ጥፋት አለመጣልና በገደብ ስለመልቀቅ ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ሰው ላይ ቅጣት አለመጣል ለቅጣት ውሳኔ ጊዜ መስጠት የወንጀል ህጉ ወንጀል አድራጊው ጥፋተኛ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ሁሉ ቅጣት እንዲጣልበት ማድረግ ዋናው አቅጣጫ ቢሆንም በተወሰኑ ሁኔታዎች ዳኛው ቅጣት ከመጣል ወይም ቅጣቱን እንዲፈጽም ከማድረግ መወሰን የሚያስቸል ስልጣን እንዳለው በህጉ ተመልክቷል በአንድ ተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛውን ሲመዝን በወንጀለኛው ላይ ጥፋተኛ በተባለበት የወንጀል ድንጋጌ ላይ የተቀመጠውን ቅጣት መወሰኑ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራው ያመዝናል ብሉ በሚያምንበት ወቅት የቅጣት ውሳኔውን ከመወሰን ተቆጥቦ ለወንጀለኛው የፈተና ጊዜ ሊሰጠውና የፈተና ጊዜውን በተገቢው ሁኔታ ከተወጣ የጥፋተኝነት ውሳኔውን ሊሰርዝለት ይችላል በወንጀል ሕጉ አንቀጽ ላይ እንደተመለከተው ፍርድ ቤቱ እንዲህ ዓይነት የፈተና ጊዜ በመስጠት ወንጀለኛው ጥፋተኛ ለተባለበት ወንጀል ቅጣት ሳይጥል የሚተወው ወንጀለኛው ለወደፊት ጠባዩን ለማረም እንዲችል አምነት ሊጣልበት የሚገባው መሆኑንና ጥፋተኛ ነህ መባሉ ብቻ ማስጠንቀቂያ ሆኖት አስከመጨረሻው ጠባዩን ለማሻሻል የሚያስችለው መሆኑን የገመተ እንደሆነ ነው ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ድንጋጌ ላይ ወንጀለኛው ሊታረም ይችላል ተብሎ የሚገመትባቸው ሁኔታዎች የተዘረዘሩ ሲሆን በዚህም መሰረት ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጀል የፈፀመ ጠባዩም አደገኛነት የሌለው ስለመሆኑ የሚታመንበት ዓይነት እንደሆነና አሁን ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘበት ወንጀል በመቀጮ በግዴታ ሥራ ወይም ከሦስት ዓመት ባልበለጠ ቀላል አስራት የሚያስቀጣ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛነቱን ካረጋገጠ በኋላ የፈተና ጊዜ በመስጠት የቅጣት ውሳኔውን ከመወሰን ገድቦ ማቆየት ይችላል ፍርድ ቤቱ ለጥፋተኛው የሚሰጠው የፈተና ጊዜ ከሁለት ዓመት ሊያንስና ከአምስት ዓመት ሊበልጥ የማይችል ሲሆን በዚህ ፍርድ ቤቱ በወሰነው የፈተና ጊዜ ወቅት ጥፋተኛው ሊከተለው የሚገባውን የጠባይ አመራር የአጠባበቅና የመቆጣጠር ደንቦችን በተመለከተ በውሳኔው ላይ የሚያሰፍር ሲሆን እነዚህ ደንቦች በአንድ የጥበብ መስክ ሙያ መማርን በተወሰነ ሥፍራ መቀመጥን ከአንዳንድ ሰዎች ጋር አለመገናኘትን አልኮል ከመጠጣት መቆጠብንወዘተ ሊያካትቱ ይችላሉ በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ እንዚህን የጠባይ አመራር የአጠባበቅና የመቆጣጠር ደንቦችን ጥፋተኛው ተከትሎ እየፈፀመ ስለመሆኑ ክትትልና ቁጥጥር አድርጎ ቢያንስ በየሦስት ወሩ ወይም አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ሁሉ ለሚመለከተው የጠባይ መሻሻል ጥበቃ ኮሚሽን ሪፖርት የሚያቀርብ አሳዳሪ ሞግዚት የጠባይ መሻሻል ጥበቃ ኃላፊን ወይም የጠባቂነት ሥልጣን የተሰጠው አካል የጥበቃ ባልደረባን ያዝዛል ፍርድ ቤቱ ለጥፋተኛው በወሰነው የፈተና ጊዜ ውስጥ ምንም ዓይነት ጥፋት ካልፈፀመ ማለትም ጥፋተኛው የፈተና ጊዜውን በጥሩ ሁኔታ ካሳለፈና ፈተናው መልካም ፍሬ ካስገኘ የጥፋተኝነት ውሳኔው እንዳልተሰጠ ይቆጠራል ቅጣት እንዳይፈጸም ማገድ ፍርድ ቤት አንድ ተከሳሽ ጥፋተኛ መሆኑን ካረጋገጠና የሚገባውን ቅጣት ከወሰነ በላ ወንጀለኛው ለወደፊቱ ጠባዩን ለማረም እንደሚችል እምነት ሊጣልበት የሚገባውና ይህ ፅኑ ማስጠንቀቂያ ብቻ አስከመጨረሻው ጠባዩን እንዲያሻሽል እንደሚያደርገው የገመተ እንደሆነ የቅጣቱን አፈጻጸም አግዶ የፈተና ጊዜ ለወንጀለኛው ሊሰጠው ይችላል አንቀጽ ፍርድ ቤቱ ቅጣት እንዳይፈጸም የሚሰጠው ትአዛዝ የጥንቃቄ አርምጃዎችን ሊመለከት የማይችል ሲሆን ከዋና ቅጣቶች በተጓደኝ የሚጣሉ ተጨማሪ ቅጣቶችን በተመለከተ ግን እንደአግባብነቱ አብረው ታግደው እንዲቆዩ ወይም ተፈጻሚ መሆናቸው እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ ሊወስን ይችላል በአንድ ወንጀለኛ ላይ የተወሰነ ቅጣት ሊገድብ የማይችልባቸው ሁኔታዎች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ ላይ የተመለከቱ ሲሆን እነርሱም ከዚህ በፊት የፅኑ እስራት ቅጣት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ ቀላል እስራት ቅጣት ተወስኖበት የነበረ ከሆነና አሁን እንደገና በፈፀመው አዲስ ወንጀል ምክንያት ከእነዚህ ቅጣቶች አንዱ የሚወሰንበት የሆነ እንደሆነ የተወሰነበት ቅጣት ሊገደብለት አይችልም ር ምንም እንኳ ወንጀለኛው ከአሁን በፊት ወንጀል ፈጽሞ ያልተቀጣ ቢሆንም አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ ፅኑ አስራት ቅጣት የሚፈረድበት ከሆነ ቅጣቱ ሊታገድለት አይችልም ይህ መስፈርት በወንጀል ሕጉ እንዲካተት የተደረገ አዲስ መስፈርት ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋተኛ የሆነ ሰው ከምን በላይ ቢፈረድበት ቅጣቱ ሊገደብለት እንደማይችል በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ላይ የተደነገገ ነገር አልነበረም ስለዚህ ጉዳይ ሳይደነገግ በመቅረቱ ፍርድ ቤቶች ከፈለጉ አስከ ዕድሜ ልክ ፅኑ አስራት ሊገድቡ ቢችሉ የሚያግዳቸው ነገር አልነበረም ፍርድ ቤቱ ለወንጀለኛው የሚሰጠውን የፈተና ጊዜ በፈተና ጊዜው ወቅት ወንጀለኛው ሊከተለው የሚገባውን የመልካም ጠባይ አመራር የአጠባበቅና የመቆጣጠር ደንቦችን በተመለከተ ከዚህ በላይ በወንጀል ጥፋተኝነት ከተወሰነ በኋላ ቅጣት ሳይጣል ስለሚሰጥ ገደብ በቀረበው ላይ የተገለፁት ጉዳዮች ቅጣት እንዳይፈጸም ፍርድ ቤቱ በሚያግድበት ጊዜም ተፈጻሚነት ያላቸው ጉዳዮች ናቸው ፍርድ ቤቱ ለጥፋተኛው በሰጠው የፈተና ጊዜ ውስጥ ምንም ዓይነት ጥፋት ካልፈፀመ ማለትም ጥፋተኛው የፈተና ጊዜውን በጥሩ ሁኔታ ካሳለፈና ፈተናው መልካም ፍሬ ካስገኘ በጥፋተኛው ላይ ተወስኖበት የነበረው ቅጣት እስከ መጨረሻው ቀሪ ይሆንለታል የመወያያ ጥያቄዎች በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ሰው ላይ ቅጣት ለመጣልላለመጣል ለቅጣት ውሳኔ ጊዜ ለመስጠት መሟላት ካለባቸው መስፈርቶች ውስጥ ለዳኞች የተተው ፍቅድ ሥልጣኖች ሀከበ እና ለዳኞች ያልተተውት ጉዳዮች የትኞቹ እንደሆኑ ተወያዩባቸው የወንጀል ሕጉ ዳኞች በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ሰው ላይ ቅጣት ሳይጥሉ የፈተና ጊዜ መስጠት እንዲችሉ የሚፈቅድ ቢሆንም በዚህ መሠረት ሲፈፀም ብዙም አይስተዋልም ምክንያቱ ምን ይመስለዎታል።