Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
የምዕራባውያን ሥልጣኔና ኢትዮጵያውያን በሰሜን አሜሪካና በሌሎች ምዕራባውያን ሀገሮች የሚኖረው የኢትዮጵያ ትውልድ ለሀገሩና ሰወገሩ የሚያደርገው አስተዋጽኦ ምን እንደሆነ በታሪክ እየተጠበቀ ነው። ዓለም የደረሰበትን ደረጃ ባቦታው ተገኝቶ ማየትና ጥበብን መቅሰም ራሱን የቻለ ታላቅ ዕውቅት ነው። በዛው ቀልጦ መቅረት ግን ታላቅ ውድቀት ነው። የጃፓን ኅብረተሰብ እዚህ ከፍተኛ ደረጃ ሳይ ሲደርስ የቻለው ከራሰ ወዳድነት በሽታ የተላቀቀ ሕዝብ በመሇኑ ነው። አያንዳንዱ የከበርቴ ዝርያም የሚጣጣረው ገንዘብ ለመሰብሰብ ሳይሆን ጃፓንን ታላቅ ሰማድረግ ነው የሚያስደስታቸውና የሚያረካቸው ጃፖን ከዓለም አንደኛ መሆኗ ነው። የጃፖን ኅብረተሰብ ታሪክና የሕዝቡ ባሕርይ እጅግ የተለየ ነው።
ማውጣ አርእስት መቅድም ተ ተ ተ ጨመተ መ መግቢያ ሥሥሥ መ ምዕራፍ አንድ የሥልጣኔ ጽንሰ ኃሳብ ምዕራፍ ሁለት የምዕራባውያን ሥልጣኔ ፅ ምዕራፍ ሦስት ሥልጣኔ በኢትዮጵያ ሠ ምዕራፍ አራት የአሜሪካ ኅብረተሰብ ሥነ ባሕርይ ምዕራፍ አምስት የኢትዮጵያውያን ባሕልና የአሜሪካ ኅብረተሰብ ምፅራፍ ስድስት አዲሱ ትውልድና የባሕል ግጭች ምዕራፍ ሰባት የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ድርጅቶች በኣሜሪካ ምዕራፍ ስምንት የውጭ ሀገር ኑሮና የሚያስከትለው የባሕርይ ለውጥና ምዕራፍ ዘጠኝ የኢትዮጵያ ሴቶች በአሜሪካ ሠ ዕ ምዕራፍ አሥር የቤተሰብ ምሥረታና የልጆች አስተዳደግ በአሜሪካ ምፅራፍ አሥራ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሜሪካ ምፅራፍ አሥራ ሁለት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በአሜሪካ ምዕራፍ ኣሥራ ሦስት ትምህርትና ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ምዕራፍ አሥራ አራት ማጠቃለያ ኢትዮጵያውያን በሰሜን አሜሪካ ከየት ወደየት መጻሕፍት ዝርዝር ተመመ መ ዕ መቅድም የምዕራባውያን ሥልጣኔና ኢትዮጵያውያን በሰሜን አሜሪካ የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በከፍተኛ ደረጃ የታቀደው ኑሯቸውን በሰሜን አሜሪካና በሴሎች ምፅራባውያን ሀገሮች ለመሠረቱ ኢትዮጵያውያንና እንዲሁም ለወደፊቱ ዕድሉ አጋጥሟቸው ኑሯቸውን በምዕራባውያን ሀገሮች ውስጥ ለመመሥረት ሰሚያቅዱ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ነው። በክፍተኛ ደረጃ ልንገነዘበው የሚገባን ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የረጅም ጊዜ ታሪክ የራሷ የሆነ የረጅም ጊዜ ሥልጣኔ የራሷ የሆነ የረጅም ጊዜ ባህል የረጅም ጊዜ የሃይማኖት ታሪክ የራሷ የሆነ የስነ ጽሑፍ ቋንቋ ከዓለም ሕዝብ ለየት ያለ የታሪክ ሂደት ያላት ሀገር ናት ይሀንን ለየት ያለ ታሪክ መሠረት በማድረግ የምዕራባውያን ሥልጣኔ ሰኢትዮጵያውያን ምን ዓይነት ትርጉም ሊሰጥ እንደሚችል የኢትዮጵያውያንን ስነ ልቡና ከምዕራባውያን ስነ ልቡና ጋር እንዴት ማገናዘብ እንደሚቻል ተገቢውን አመለካከት ሊሰጥ የሚችል ማኀበራዊና ስነ ልቡናዊ ትንተና የሚያቀርብ መደበኛ ጽሑፍ በጣም አስፈላጊ ነው። የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላትና የሰው ልጅ ሥልጣኔም የተጀመረባት ሀገር መሆኗን ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፍ የአዲሱን ትውልድ ስነ ልቡና መቅረጵ ይኖርብናል። ሰው የያዘውን ክወረወረ ፈሪ አይባልም እንደሚባለው የዓለም ሕዝብ በሥልጣኔ አንዴት እንደተለያየ ስለሰሥልጣኔ ትርጉም ስለሥልጣኔ ጽንሰ ሃሳብ የኢትዮጵያ ባህል ሰአሜሪካ ኅብረተሰብ አኗኗር ምን ያህል እንደሚያዘጋጃቸው በተለያዩ የምዕራባውያን ሀዓሮችና በሰሜን አሜሪካ ስሰሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኑሮ ሁናቴ በሳይንስና በቴክኖሎጂ በመጠቁ ሀገር ውስጥ ሰመኖር ፅድል ያፕኙ ኢትዮጵያውያን ያፈሩትን ፅውቀት ለሀገራቸው እንዴት ማካፈል እንደሚችሉሌ ኢትዮጵያውያን በምዕራባውያን ሥልጣኔ ውስጥ ተቀሳቅለው ሲኖሩ ማድረግ ስለገባቸው ማኅበራዊና ስነ ልቡናዊ እገቅስቃሴ ሁሌ ለመወያየት እነሆ ይህንን መጽሐፍ በታላቅ ትህትና አቀርባለሁ። ዛሬ ከምዕራባውያን ሥልጣኔ ትምህርት ለማግኘት የምዕራባውያን ሥልጣኔ ተካፋይ ለመሆን የዓለም ሕዝብ ወደ ምዕራባውያን ሀገሮች እየጎረፈ ነው። የሰው ልጅ ሥልጣኔ የራሱ የታሪክ ሂደት አለው የሰው ልጅ በዋሻ መኖር ከጀመረበት ጊዜ እንስቶ የዕለት ኑሮውን ለማሸነፍ ከእንስሳትና ከአራዊት ራሱን ለመከላከል የፅለት ምግቡን ለመሰብሰብ ያደርገው የነበረ የኑሮ ውጣ ውረድ ሁሌ የሥልጣኔ ጥንስስ መሆኑን እንረዳለን የሰው ልጅ ጥንታዊ የሥልጣኔ ታሪክ ኣጅግ ከፍተኛ ቦታ ይዞ የሚገኘው ባጋጣሚ ይሁን በተፈጥሮ ምርምር ድንጋዮችን በማጋጨት ለመጀመሪያ ፄዜ እሳትን ብፈጠረበት ጊዜ ነው። የሰው ልጅ ሥልጣኔን ከሰው ልጅ መደበኛ ባሕርይ ጋር በማገናዘብ ጠሰቅ ያለ ስነ ልቡናዊ ትንተና ማድረግ ተገቢ ነው። የሰው ልጅ ሥልጣኔ የተጀመረባት ጥንታዊ የሰው ልጅ ዝርያ የተገኘባት በአፍሪካ ውስጥ የራቧ የጽሑፍ ቋንቋ ያላት ሀገር ናት። ይህ ከፍተኛ ታሪካዊ ኃላፊነት በመሆኑ ባንድ ወቅት የዓለም ሥልጣኔ ቁንጮ የነበረችውን የመላው የሰው ልጅ ዝርያ የበቀሰባትን የዓለም ። ምዕራፍ አንድ የሥልጣኔ ጽንሰ ሃሳብ አሁን በምንኖርበት በኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ ሥልጣኔ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሥልጣኔ በመሠረቱ የሰው ልጅ የፈጠራና የመመራመር ችሎታ ውጤት ነው። ሥልጣኔ የሰው ልጅ ሥራ ነው። የሰው ልጅ ከፈጠራ ችሎታ ጋር የተፈጠረ በመሆኑ ሥልጣኔን መፍጠር የሰው ልጅ ስጦታ ሃሰው ልጅ መደበኛ ባሕርይ ነው ማለት ይቻሳል። በዘመናችን ቶማስ ኤዲሰን የኤሌክትሪክ ብርሃንን እና የኤሌክትረክ ኃይልን በፈለሰፈበት ጊዜ በሰው ልጅ ታሪክ ከፍተኛ የሥልጣኔ ምጥቀትና ከፍተኛ የሥልጣኔ ዕድገት የታየበት እንደነበረ ሁሉ የሰው ልጅም ለመጀመሪያ ጊዜ እሳትን ሲፈጥር በሰው ልጅ ታሪክ ከፍተኛ ምጥቶት ከፍተኛ ፅድገች የታየባት የታሪክ ወቅት ነው። ቀደም ሲል እንደተገለጸው ሥልጣኔ የሰው ልጅ የፈጠራ ችሎታ ውጤት ነጡ። የሰው ልጅ በተፈጥሮው የሥልጣኔ ምንጭ ነው። ክርክሩ እንዳለ ሆኖ የሰው ልጅ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ የሰው ልጅ ይህንን ችሎታ ማሳየቱ የሚዶይነቅ ነው። ይህ ከፍተኛ የአእምሮ ደረጃ ይህ ከፍተኛ የአእምሮ ብስለት የሰው ልጅ የተፈጥሮ ፀጋ ነው። ዛሬ የሰው ልጅ በተለያየ ደረጃ በተለያየ የኑሮ ሁናቴ ቢኖርም ይህ ከፍተኛ የአእምሮ ደረጃና የአኣምሮ ብስለት ያጠቃላይ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ባሕርይ ነው ። ባጭሩ ሥልጣኔ የሰው ልጅ ። ዓለም የደረሰችበትን ከፍተኛ የሥልጣኔ ደረጃ ስንመለከት የሰው ልጅ የተለየ ፍጡር መሆኑን መገንዘብ አያዳግተንም። የሥልጣኔ ምንጭ ከዚህ ልዩ ከሆነ የሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመጣ ነው። በነዚህ በተለያዩ የሰው ልጅ የፅድገት ዘመናት የሰው ልጅ ባሕርይ እንዴት እንደሚለዋወጥ የሰው ልጅ ባሕርይ እንዴት እንደሚዳብር ራሱን የቻለ ትልቅ ርእስ ነው። ሥልጣኔ ያንድ አገር ያንድ ኅብረተሰብ ጀብዱ ሥራ ሳይሆን ሥልጣኔ የዓለም ሕዝብ አጠቃላይ አስተዋጽኦ ነው። ለዓለም ሥልጣኔ የሰው ልጅ በያለበት አስተዋጽኦ አድርጓል። ሥልጣኔ የደረሰበትን የአሁኑን ደረጃ ስናይ ሰልጣኔን በዓለም ላይ ያስተዋወቁት ሥልጣኔን ሰመጀመሪያ ጊዜ የቆረቆሩት ሥልጣኔን ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠሩት በታሪክ የሥልጣኔ መብቀያ እየተባለ የሚጠራውን የመጀመሪያውን የሰው ልጅ ሥልጣኔ የመሠረቱት የሚሴፖታሚያ አካባቢ ሰዎች ናቸው ይባሳል። ሥልጣኔ የሰውን ልጅ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ኣድርሳዋለች። ሥልጣኔ የሰውን ልጅ ባሕርይ እጅግ ለውጦታል። ሥልጣኔ የሰውን ልጅ ዕምነት የሰውን ልጅ አስተሳሰብ የሟለውጥ ትልቅ ኃይል ነው። የዚህ ምፅራፍ ዓላማ ደግሞ የምሰፅራባውያን የሥልጣኔ ቁልፍ ሃሳብ ምን እንደሆነ የምዕራባውያን ሥልጣኔ እንዴት እዚህ ደረጃ እንደ ደረሰ ስነ ልቡናዊ ምሥጢሩን መግንዘብ ይኖርብናል። የአሜሪካንን የሥልጣኔ ሂደት እጅግ የተሰየ የሚያደርገው አውሮፓ ዘመናዊ ሥልጣኔ ላይ ሰመድረስ አያሌ ዘመናት ሲወስድባት አሜሪካ ግን እዚህ ከፍተኛ የሥልጣኔ ደረጃ ላይ የደረሳችው በሁለት ትውልድ ነው ለማለት ይቻላል። በእርግጥ ጃፓንም የምዕራባውያንን ሥልጣኔ ጽንሰ ሀሳብ ወሰዳ ከፍተኛ የሥልጣኔ ደረጃ ላይ የደረሰችው ባጭር ጊዜ ውስጥ ቢሆንም ጃፓን ብዙ ዘመናት የኖረች ሀገር ናት። የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ ለኢትዮጵያውያን ሥልጣኔ ማለት ምን ማስት እንደሆነ ኢትዮጵያውን የምዕራባውያንን ሥልጣኔ እንዴት እንደሚያዩትና እንደሚቀበሉት በተለይም ከኢትዮጵያ ውጭ በምፅራባውያን ሥልጣኔ ውስጥ በሚኖሩበት ጊዜ ከምፅራባውያን ሥልጣኔ ጋር አብረው ለመኖር እንዴት እንደሚችሉ ለመገንዘብ ስለሆነ ይህንን ሁናቴ ከመተንተናችን በፊት ኢትዮጵያ የምዕራባውያንን ሥልጣኔ እንዴት እንደምታየውና ባጠታላይ ሥልጣኔ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት እንደሚተረጐምና የሥልጣኔ ጽንሰ ሀሳብ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት አንደሆነ አስቀድመን መተንተን ይኖርብናል ኢትዮጵያንና ሥልጣኔን የሚገልጸው ይሀ ምዕራፍ ከዚህ መጽሐፍ ውስጥ እጅግ ከባድና በጣም አስቸጋሪ የሆነ የመወያያ ርእስ ነው የሦስት ሺሀ ዘመን ታሪክ ስላሳት ሀገር ስለኢትዮጵያ ሥልጣኔ መናገር ወይም ትንተና ማቅረብ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው ይህንን ትንተና በይበልጥ የሚያከብደው ደግሞ ዓለም በአዙኑ ወቅት በሥልጣኔ እጅግ በተራቶቀችበት ከፍለ ዘመን የዓለም ሕዝብ ባኢኮኖሚና በልሣት ከፍተኛ እንትስቃሴቤ በሜያደርግበት ወቅት ዓለም ባጠቃላይ የደረሰበትን የሥልጣኔ ደረጃ ስንመለከት ኢትዮጵያ የምትገኝበት ሁናቴ እጅግ አሳሳቢ ነው። አሁን ያለው ታሪክ ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ቢሆንም ይህ ረጅም ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት እንዳለፈ ባንድ በኩል ማጥናቱ ለአእምሯችን እጅግ የሚያጓጓ ርእስ ነው ባለፈው ምዕራፍ የምዕራባውያንንና በተለይም የአሜሪካንን የሥልጣኔ ሂደት ለመረዳት ስንሞክር ከ ዓመታት ያልበለጠ ታሪካ ያላት አሜሪካ በዚህ ባጭር ጊዜ ውስጥ የዘመኑ ታላላቅ መንግሥታት ከሚባሉት አንዷ መሆኗንና ከፍተኛ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ መድረሷን ስናነፃጽር እንቆቅልሽ ይመስላል አዲሲቷ አሜሪካ ባጭር ጊዜ ውሰጥ የዘመኑን የዓለም ኢኮኖሚ ከሚመሩት ሀገሮች አንዷ በመሆኗ ይህ ሥልጣኔ በኢትዮጵያ የሟለው ርእስ በታሪክ ጸሐፊዎች ዘንድ ሰፋ ያለ ምርምር የሚያስፈልገው ሊሆን ይችሳል የዚህ መጽሐፍ ዓላማ ግን ከኢትዮጵያ የታሪክ ሂደት የሥልጣኔን ጽንሰ ሀሳብ ለመገንዘብ ስለሆነ መተንተን የምንፈልገው ለኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማለት ምን ማለት እንደሆነና ጽንሰ ሐሳቡን ለመገንዘብ ነፁ ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ከሚሟባሱት አንዱ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ እንደሆነ የታወቀ ነው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ዓም ኣፋር አካባቢ የተገኘችው ሉሲ ተብላ የተሰየመችው ጥንታዊ የሰው ዘር ያሳት ኢትዮጵያን በዓለም ደረጃ የጥንታዊው ሰው የተፈጠረባት ዘገር አድርጓታል የኢትዮጵያን ታሪክ ስንመለካት ባንድ ወቅት በሰሜን እስከ ሜድትራኒያን በምሥራቅ እስከ ሕንድ ውቅያኖስ በምዕራብ እስከ ሰሃራ በረሃ በደቡብ እስከ ማደጋስካር ድረስ በመስፋፋት ግማሹን አፍሪካ የያዘች ሀገር እንደነበረች ብዙ የታሪክ መጸሐፎች ያስረዱናል በንለም ታሪክ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የምትታወቅ ኖናት። ከዓለም ሥልጣኔ ትምህርት መቅሰም ከውጭ ሥልጣኔ መማር ለማንኛውም ኅበረተሰብ ቁልፍ ቢሆንም የሀገርን ሥልጣኔ የሀገርን ታሪክ መናቅ ማንቋሸሸና ማዋደቅ የሥልጣሄ ምልክት መሆን የለበትም የኢትዮጵያውያን ሥልጣኔ የምፅራባውያንን ሥልጣኔ ማጋፈፍ መሆን የለበትሥ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሥልጣኔ ማለት ምዕራባዊ መስሎ መቅርብ የምፅራባዊ ቋንቋን መናገር የምዕራባውያንን ዘይቤ መያዝ ይመስላል። ይህ ከፍተኛ የስነ ልቦና ተጽእኖ የፀገራችንን ሥልጣኔ በጅምር ትተን ወደ ውጭ ሥልጣኔ እንድናተኩር አድርጎናል በአንፃሩ የምዕራባውያንን ሥልጣኔ ስነ ልቦናዊ ሁናቴ ብንመለከት ምዕራባውያን የራሳቸው የሆነውን የታሪክ ቅርሳቸውን በከፍተኛ ደረጃ ይንከባከቡታል። የምዕራባውያንን ሥልጣኔ ተመልክተን ኢትዮጵያ በሥልጣኔ እንድትራመድ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ ማንሳት ይኖርብናል የምዕራባውያንን የሥልጣኔ ሂደት በገለጽንበት ምዕራፍ ውስጥ እንደተወያየንበት የምዕራባውያን ሥልጣኔ ቁልፍ የሆነጡ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ እንደሆነ ሰመገንዘብ ችለናል። ሥልጣኔ ማለት ይህ ነው።