Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

የጃፓን_መንገድ_ቋሚ_ጥቅም_እንጂ_ቋሚ_ጠላት_የለም.pdf


  • word cloud

የጃፓን_መንገድ_ቋሚ_ጥቅም_እንጂ_ቋሚ_ጠላት_የለም.pdf
  • Extraction Summary

የአጫዕካ ኤቸ ለክ ል ሃና የመረጠበት ዋነና ምበነየት በወቅቱ በከተጣዋ በርከት የቡ የ የጦር ሰፈሮት የነበረ በመሆነ ነው። ሾገኖቹ የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በጊላ ጃፓንን ለረሂ ዘመናት ሲገዛ የኖረውን ንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ጎን በመግፋት ነ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ሚና ብቻ እንዲኖረው አድርገዋል የቶኩጋዋው ዞማ መሪዎች ምዕራባውያን ወደ ጃፓን ገበያዎች ሰተት ብለው ገቡ ምዕራባውያኑ የጃፓንን መንግሥት በተጽዕኖ በማንበርከክ የአገሪቱን መሠረታዊ ጥቅም የሚፃረሩ የኢኮኖሚ ስምምነቶችን ከጃፓን ጋር ተፈራረሙ። ግብ ሳያሳካ ከወዲሁ ፈርሷል የመንግሥታቱ ማኅበር ዓላማውን ሳያሳካ አንዲፈርስና ዓለማችን ሌላ አሰቃቂ ጦርነት እንድታረግዝ ጃፓን የአንበሳው። ጃፓን የከበርቴዎቹን አገራት ጎራ ተመልሳ በመቀላቀል የዓለማችን ግንባር ቀደም እርዳታና ብድር ሰጪ አገር ለመሆን ቃች በየዓመቱ ከ የሚበልጡ የዓለማችን ታዳጊ አገራት የጃፓን ዳታና ብድር ተቀባይ ሆኑ በ ቀና ብላ ወደ ላይ ትመለከታቸው የነበሩትን እነ እንግሊዝ እና ይህፃባይ። በሁሱም ጓሰም የኃፅ ከይ ያ ገ ታሳቅ ከደሪ ነው። ሌአ የገር በከጫሪካና በከነጓቢዝ ሳዩ ጦርነት ዐውደነ ነበርክ ነገር ዓነ የሆነው ካሰምነውና ከጠበቅነው ነ ነዑ።

  • Cosine Similarity

ም የአገሪቱ በ ር በ ው ከ በ ነ መንቀጥቀጥ ጎርፍና ሌሎችም ሰ በሩ ወና መኩ ደጋግመው ው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ቦየ አየጎበኗት ብዙ ውድመት ደርሶባታል ይሁንና ይህቺ ትንሽ አገር በኢኮኖሚ ብልጽግና በቴክኖሎጂና በሌሎች መስኮች በዓለም ሳይ የፈጠረችው ተጽዕና አጅግ የሚያስደንቅ ነው በየዘመኑ የገጠሟትን ፈተናዎች በብቃት ለማለፍ ያደረገችው ጥረትም ለሌሉች አርአያ የሚሆን ነው በመጽሐፉ ውስጥ በቅርብ ዘመናት በዓለማችን ላይ የ ጦርነቶችን በተመለከተ ለማካተት ጥረት ተደርጓል ምንም አንኳን ዋናው ትኩረት ጃፓን በአነዚህ ጦርነቶች ውስጥ የነበራትን ሚና ማሳየት ቢሆንም የጦርነቶቹን መንሥኤና ያስከተሉትን ውድመቶች በተመለከተ በመጽሐፉ ውስጥ ለማመሳከት ጥረት ተደርጓል የጃፓንና የቻይና ጦርነት የጃፓንና የራሺያ ጦርነት የአንደኛው የዓለም ጦርነት ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የኮሪያ ጦርነት የቪዬትናም ጦርነትና የኢራቅን ጦርነት በተመለከተ ጦርነቶቹ በምን ምክንያት ተከሠቱ። በሜጂው ዘቦን ነቡ የሜጂቡ ዘመን የጀመረው በ ንጉ መዲ በሓርካን ከመካ ግል ዘሜ ኮታሪ አረት ጎመ ሐት ወ ጃፐንን ከኒላ ቀርነት ወደ ሥልጣ ብልፅግና ያሸጋገራት በመሆነ ጂፐናች የሜጂውን ዘመን የብርፃን ወይም የፀሐይ ዘመን ብለው ነው የሚጠሩት በዓለም ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ጃፓን ከምዕራቡ ዓለም መካከል ቀድማ የሠለጠነችና የበለፀገች ብቸኛ አገር ነች ማለት ዶ ሻም ከኢንዱስትሪ አብዮት በኋላ ከጻፓን ቀድሞ አሜሪካና ምዕራብ አውር። በስልጣኔ የተገዳደረ ምዕራባዊ ያልሆነ ሌላ አገር የለም ታዲያ ከጊላ ቀርነት ተነሥታ በአጭር ጊዜ ከምፅራባውያኑ ኃያላን አኩል እንድትቀም ያደረጓት የሜጂው ዘመን መሪዎች ናቸው መሪዎቹ ሀብታምና ሥልጡን አገር ሠርተው ለትውልድ ያስተላለፉ በመሆናቸው አሁንም ድረስ በአገሬው ዜጎች ዘንድ አዘማኞቹ እጠ ተብለው ነው የሚጠሩት ከሜጂው ዘመን በፊት ጃፓን ለ ዓመታት በቶኩጋዋ ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጭ ሥርውመንግሥት ሥር ስትተዳደር ቆይታለች በተዮኩጋዋው ዘመን አገሪቱ ከምዕራቡ ዓለም ጋር የነበራት ግንኙነት እንዲቋረጥ ተዴርጎኀል ግንኙነቱ የተቋረጠበት ዋናው ምክንያት ደግሞ አገሪቱ በቅኝ አገዛዝ ቀበር ሥር እንዳትወድቅ መንግሥቱ የነበረው ስጋት ነው በቶኩጋዋው ከመ የማዕከላዊ መንግሥቱ በፊውዳል የጦር አበጋዞች ቦገኖች ተይኮ በመላ አገሪቱ በመደብ ክፍፍል ላይ የተመሠረተ ጥብቅ አገዛዝ እንዲስፍን ተ። ሾገኖቹ የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በጊላ ጃፓንን ለረሂ ዘመናት ሲገዛ የኖረውን ንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ጎን በመግፋት ነ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ሚና ብቻ እንዲኖረው አድርገዋል የቶኩጋዋው ዞማ መሪዎች ምዕራባውያን ወደ ጃፓን እንዳይገቡ ጃፓናውሀሆንም ወጩደ ም አገራት ዝር እንዳይሉ ጥብቅ ክልከላ በመጣል ጃፓንን ለሁለት ክፍለ ዞም ተኩል በሯን ዘግተው አስተዳድረዋል የሾገኖቹ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ከአልሆትት አ ገራተ ኣትድረሱብን እኛም አንደርስባችሁም የሚል ነበር በዚህ ረጂም ወታደራዊና ፊውዳላዊ የአገዛዝ ዘመን ጃፐን በምዕራቡ ዓለም እየሆነ ላለው ነገር ቦታ ሳትሰጥ ከራሷ ጋር ብች ስትወዳደር ኖራለች በቶኩጋዋው ወታደራዊ የአገዛዝ ዘመን በመላ አገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ቆይቷል በዚህም የተነሣ የቶኩጋዋው ዘመን በታሪክ ጸሐፊዎች ዘንድ ወርቃማው የሰላምና የመረጋጋት ዘመን ከፀ ከ ጄዉ ዞፀ ተብሉ ይጠራል ይሁንና ዘመን እያለፈ ሲመጣ ምዕራባውያን የጃፓንን ዙሪያ መቃኘት መሩ ለኢንዱስትሪ ምርቶቻቸው የገበያ ዕድልና ጥሬ ዕቃ ፍለጋ ዓለምን በማሰስ ላይ የነበሩት የምዕራብ ኃያላን አገራት የጃፓንንም በር አንኳኩ የአሜሪካው የባሕር ኃይል አዛዥ ኮሞዶር ማቲው ፔሪ ጃፓናውያን አይተውት የማያውቁትን መሣሪያ በግዙፍ የጦር መርከብ ላይ ደግኖ በ በጃፓኗ የቶኪዮ ወደብ ደረሰ ኮሞዶር ፔሪ ወደ ጃፓን የመጣበት ዋነኛ ዓላማ በውድም ሆነ በግድ የጃፓንን ወደቦች ለአሜሪካ መርከቦች ለማስከፈት ነው የጃፓን መሪዎች ኮሞዶር ፔሪ ይዞት የመጣውን ግዙፍ መርከብና አላዩ ላይ የተደገኑትን ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች ከተመለከቱ በኋላ ጃፓን ለሁለት ክፍለ ዘመን ተኩል በሯን ዘግታ በኖረችበት ዘመን የምዕራቡ ዓለም በሥልጣኔ የትየለሌ ጥሏት እንደነጎደ ለመረዳት አላዳገታቸውም ጃፓን ለአሜሪካው የባሕር ኃይል አዛዥ ከመንበርከክ ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበራትም እጅ ሰጠች በቶኩጋው ሾገኖች ለሁለት ክፍለ ዘመን ተኩል ተዘግታ የኖረችው አገር በሯ በኃይል ተከፈተ ኮሞዶር ማቲው ፔሪ በቀደደው መንገድ ምዕራባውያን ሸቀጦቻቸውን ይዘው ወደ ጃፓን ገበያዎች ሰተት ብለው ገቡ ምዕራባውያኑ የጃፓንን መንግሥት እጅ እየጠመዘዙ ፍትሐዊ ያልሆኑ የንግድ ስምምነቶችንም አስፈረሙት አሜሪካ እንግሊዝ ራሺያ ኔዘርላንድና ሌሎችም የምዕራብ አውሮፓ አገራት የጃፓንን መንግሥት በተጽዕኖ በማንበርከክ የአገሪቱን መሠረታዊ ጥቅም የሚፃረሩ የኢኮኖሚ ስምምነቶችን ከጃፓን ጋር ተፈራረሙ። ሣፍ ሥርዓት ወደ ጥንት ቦታው መለሱ ሕፃኑ ሙሱሂቶ ሜጂ የብርሃን ዘመን በሚል ስያሜ መስከረም ቀን ነግሦ የጃፓን ንጉሠ ነገሥት ጠዩፀ ሆ ይህንኑ ተከትሎ ጃፓን አዲሱን የብርዛን ዘመን ጀመረች የሜጂው መሪዎች አሮጌውን ሥርዓት በዐመፅ አስወግደው አዲስ ሥርዓት ከአቆሙ በኋላ ብዙ ጊዜ ሳያባክኑ ወደ ኋላ የቀረችውን አገራቸውን ወደፊት ለማራመድ የሚያግዛቸውን ተሞክሮ ለመቅሰም ወደ አሜሪካና አውርፓ ተጓዙ ለሁለት ዓመታት ያህል በመላው አሜሪካና አውሮፓ በመዘዋወር በርካታ አገራትን ጎበኙ የጉፈቸው ዋነኛ ዓላማ አገራቸውን ለማሠልጠን የሚረዱ ልምዶችን መቅሰምና አዲስ የመሠረቱትን ንጉሣዊ መንግሥት ማስተዋወቅ ነበር በቀድሞው መንግሥት ዘመን ጃፓን ከምዕራባውያን ጋር ተገዳ የፈረመቻቸውን ፍትሐዊ ያልሆኑ ስምምነቶች እንዲለወጡ መደራደር የመሪዎቹ ሌላው የጉዚቸው ዓላማ ነበር መሪዎቹ በአውሮፓና በአሜሪካ የአደረጓቸው ጉብኝቶች አገራቸው ጃፓን በብዙ መንገድ ወደ ኋላ አንደቀረች ወለል አድርጎ አሳይቷቸዋል ጃፓን ፈጥና ከአልሠለጠነች በቀላሉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሥር እንደምትወድቅ መሪዎቹ ጥርጣሬ አልነበራቸውም እናም አዲሶቹ መሪዎች ከጉብኝታቸው በላ በቀድሞው መንግሥት ዘመን የተዘረጉ ኋላ ቀር አሠራሮችንና አወቃቀሮች። በማፈራረስ ከምዕራቡ ዓለም በቀሰመት ተሞክር መሠረት በአዲስ እንዲተኩ አደረጉ ከዚህም ባሻገር የሳይንስና የምህንድስና ባለሙያዎችን ከምዕራቡ ዓለም በገፍ ቀጥረው ወደ ጃፓን በማምጣት በተለያዩ ተቋማት ውስጥ እንዲሠሩና ለወጣቶቻቸው ሥልጠና እንዲሰጡ አደረጉ በተመሳሳይ ሁኔታ ልዩ ችሎታ የአላቸውን የአገራቸውን ወጣቶች ወደ ሠለጠኑት የምዕራብ አገራት በብዛት በመላክ ዕውቀት ቀስመው አንዲመለሱ ተደረገ በሜጂው ዘመን የነበረው ገዢ አስተሳሰብ ጃፓንን ላ ቀር ከሆነው የኤዥያ አህጉር በማውጣት ከሠለጠነው የምዕራቡ ዓለም ጎራ መቀላቀል ቦ ለ ኋበበ ርርከበ ህሀ ቪከ ከፀ ነ የሚል ነበር በመሪዎቹ እምነት እየተስፋፋ የመጣውን የምዕራቡን ዓለም ሥልጣኔ መከላከል ወይም ማስቀረት ስለማይቻል የተሻለው መንገድ በሥልጣኔው ባሕር ውስጥ ገብቶ አብሮ በመዋኘት ጃፓንን እንደ ምዕራባውያኑ ሥልጡን አገር ማድረግ ነው የሜጂው መሪዎች በወሰዲቸው ሥር ነቀል የፖሊሲና የአሠራር ማሻሻያዎች የተነሳ ጃፓን በኢኮኖሚና በቴክኖሎጂ ወደ ፊት መስፈንጠር ጀመረች ኢንዱስትሪ በመላው አገሪቱ ተስፋፋሱ ከመላው አውሮፓና አሜሪካ የተቀዱ የተኮረጁ ቴክኖሎጂዎች ለጃፓን በሚመች መንገድ አየተሻሻሉ ሥራ ላይ ዋሉ ትምህርት በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፋ የሜሚው መሪዎች ሀብታም አገር ጠንካራ መከላከያ ርከ ርዕሀህበከሃ ከርበ እልባ ለመገንባት ያስቀመጡት ራእይ በሚያስደንቅ ፍጥነት እውን እየሆነ መጣ ጃፓን ገናና የኋላ ታሪክ ሰፊ ግዛትና ግዙፍ ወታደራዊ ዐቅም የነበራቸውን ራሻና ቻይናን ጦርነት ገጥማ ድል አደረገች አገሪቱ ራሷን ከቅኝ አገዛዝ ከመከላከል አልፋ ብቸኛ ምዕራባዊ ያልሆነች ቅኝ ገዢ ኃያል አገር ሆና ብቅ አለች በ በወቅቱ የዓለም ቁጥር አንድ ልዕለ ኃያል አገር ከነበረችው ከአንግሊዝ ጋር በአቻ ደረጃ ተቀምጣ የጦር ቃል ኪዳን ውል ለመፈራረም በቃት ኮሪያን ታይዋንና ሌሎች የኤዥያ ግዛቶችን በቅኝ ግዛት በመያዝ ከስድስቱ የዓለም ኃያላን አገራት መካከል አንዲ ለመሆን በቃች እንግሊዝ ፈረንሳይ ጀርመን ጣሊያን አሜሪካ እና ጃፓን የዘመነ ኃያላን አገራት ሆነ ጃፓን ምዕራባዊ ሳትሆን ከኃያላኑ የምዕራባውያን ጎራ የተቀላቀለች ብቸኛ አገር ሆነች በመጨረሻም በ የንጉሥ ሜጂን ፀሐዩ ንጉሥ ሞት ተከትሎ ጃፓንን በሥልጣኔ ማማ ላይ ያደረሳት የሜጂው ዘመን ተቋፅኤ ከፀሐዩ ንጉሥ ኅልፈት በኋላ አገሪቱ ወደ ሌላ ምዕራፍ ተሸጋገረች በአውሮፓ እያቆጠቆጠ በመጣው ጽንፈኝነትና አክራሪ ብሔርተኝነት የተነሣ አንደኛው የዓለም ጦርነት በ ሲፈነዳ ጃፓን የቅርብ አጋሯ ከነበረችጡ ከእንግሊዝ ጎን ተሰለፈች ጦርነቱ በጀርመንና አጋሮቿ ሽንፈት ከተቋጨ በጎላ ድል አድራጊዎቹ አገራት በ በፈረንሳዩዋ የቨርሳይ ከተማ ተሰብስበው ቀድሞ በጀርመን ቅኝ አገዛዝ ስር የነበሩትን አገራት ሲከፋፈሉ ጃፓንም ከእነ እንግሊዝና ፈረንሳይ ጋር በእኩል ደረጃ ተቀምጣ ግዛት ለመከፋፈል በቃች ቀድሞ በጀርመን ቅኝ አገዛዝ ሥር የነበሩት በሩቅ ምሥራቅ የሚገኙ አገሮች ማይክሮኔዥያ ማርሻል ደሴት እና ሰሜን ማሪያና ደሴተ ጃፓን እንድትረከባቸው ተደረገ በአፍሪካና በኤዥያ በጀርመን ሥር የነበሩት ሌሉች አገራት ደግሞ ለእንግሊዝ ለፈረንሳይና ለሌሎች ቅኝ ገዢ ኃያላን አገራት ተሸጋገሩ ከኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በአውሮፓ እየተንሰራፋ የመጣው ጽንፈኝነትና ብሔርተኝነት ከሜጂው ዘመን አጋማሽ ጀምሮ በጃፓንም ሥር አየሰደደ መጥቷል የጃፓን መሪዎች የኤዥያ ጎረቤቶቻቸውን ዝቅ አድርገው በመመልከት ራሳቸውን ለመነጠል የተከተሉት አሳቤ የኋላ ኋላ አገሪቱን የአክራሪ ብሔርተኝነትና ጽንፈኝነት ሰለባ አድርጓታል በጃፓን እየተስፋፋ የመጣው ብሔርተኝነትና ጽንፈኝነት አገሪቱ በቅርብ ጎረቤቶቿ ላይ ግፍ አንድትፈጽም ምካንያት ሆኗል ቻይናውያን ኮሪያውያንና የታይዋን ዜጎች የጃፓን የግፍ አገዛዝ ሰለባ ሆነዋል ከሜጂው ዘመን መጨረሻ አንሥቶ አስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድረስ ጃፓን በጎረቤቶቿ ላይ የፈጸመችው ግፍና ሰቆቃ ቁስሉ ገና አሁንም ድረስ ጨርሶ አልሻረም በአንደኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ ላይ የዓለም ሰላም ወዳድ ኃይሎች ተሰባስበው የመንግሥታቱን ማኅበር ህ አጸከበ መሠረቱ የመንግሥታቱ ማሕበር የተመሠረተበት ዋነኛ ዓላማ ዓለማችንን ከሌላ አውዳሚ ጦርነት ለመከላከል ነበር ይሁንና ማኅበሩ የተመሰረተበት። ድርሻ ተጫውታለች ጃፓን በ የቻይናዋን ግዛት ማንቹሪያን በወረረችበት ወቅት የዓለሙ የመንግሥታት ማኅበር ወረራውን በማውገዙ የተነሣ በ ማኅበሩን ጥላ ወጥታለች ለዓለሙ ማኅበር መዳከምና በኋላም ጨርሶ መፍረስ የጃፓን ማኅበሩን ጥሎ መውጣት አንዱ ምክንያት ተደርጎ ይጠቀሳል በእርግጥ ለማኅበሩ መፍረስ ሌሎች ምክንያቶችም እንደነበሩ የሚካድ አይደለም በአንደኛው የዓለም ጦርነት የሚሊዮኖች ሕይወት ከተቀጠፈና ለመገመት የሚያዳግት ንብረት ከወደመ በኋላ ሰላም ፈላጊ ኃይሎች የመንግሥታቱን ማኅበር በማቋቋም በዓለም ላይ ሌላ አውዳሚ ጦርነት እንዳይከሠት ጥረት ያደረጉ ቢሆንም ሊሳካ አልቻለም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ግዛት ለማስፋፋትና በሌላው ላይ የበላይነትን ለመቀዳጀት መሽቀዳደማቸውን አጠናክረው ገፉበት ለአንደኛው የዓለም ጦርነት መቀስቀስ ዋነኛ መንሥኤ የነበረው አክራሪ ብሔርተኝነት ከከበ በመላው ምዕራብ አውሮፓ ከቀድሞው በባሰ ሁኔታ እየገነነ መጣ በዚህም ዓለም ሌላ አውዳሚ ጦርነት አረገዘች ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው እንደ ምዕራብ አውሮፓ ሁሉ ጃፓንም የአክራሪ ብሔርተኝነት ሰለባ ከመሆን አላመለጠችም በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች መካከል በጃፓን በተስፋፋው ጽንፈ ኝነት የተነሣ በሥራ ላይ ያሉ ሁለት የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትሮችና ሌሎ ች በርካታ ባለሥልጣናት በፅንፈኞች ግድያ ተፈጽሞባቸዋል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ ጃፓን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የነበራትን አሰላለፍ በመቀየር የቀድሞ አጋሮቿን እነ እንግሊዝን ወደ ጎን ትታ ከናዚ ጀርመንና ከፋሺስት ኢጣሊያ ጋር የጋራ የጦር ቃል ኪዳን መሠረተች ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ ከመፈንዳቱ በፊት ጃፓን በ ማንቹሪያን በኋላም በ መላውን ቻይና በመውረር ጦርነቱን ቀድማ ጀመረች በመቀጠልም ጦርነቱ በመላው አውሮፓ መቀጣጠል ሲጀምር ዳፓን በአሜሪካ ላይ ያልተጠበቀ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር አሜሪካ ባልጠበቀችው ሁኔታ ተገዳ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ እንድትገባ አድርጋታለች አሜሪካ አገር ሆና ከተፈጠረች ጀምሮ ከሌላ አገር ጋር ብዙ አልቂት ያስከተለ ጦርነት ያካሄደችው ከጃፓን ጋር ነው አሜሪካና ጃፓን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ለተከታታይ አምስት ዓመታት ከባድ ጦርነት አካሂደዋል በጦርነቱ ከሁለቱም ወገን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወታደሮችና ንጽሐን ዜጎች አልቀዋል ጃፓን ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ቀድማ ጀምራ እጅ የሰጠችው ከሁሉም ተሸናፊ አገራት በኋላ ነው ናዚ ኢጣሊያ ተሸንፈው የአውሮፓው ጦርነት ከአበቃ በኋላ ዓዎችን ከአሜሪካና አጋሮቹ ጋር ለወራት ጦርነቱን ቀጥላለች ግ ፓን በቀላሉ እጅ እንደማትሰጥ የተረዳችው አሜሪካ ጃፓንን ሰማንበርከክና ጦርነቱን ለመቋጨት በኒኩሊዬር ቦንብ እንድትመታ አድርጋለች በሰው ዚ ሪክ ውስጥ ከጃፓን በስተቀር በኒኩሊዬር ቦንብ የተመታ ሌላ አገር የለም ጃፓን በኒኩሊዬር ቦንብ ከተመታች በኋላ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተሸንፋ እዩ ለመስጠት ተገዳለች በቢህም በማሸነፍ የተሞላው የአገሪቱ ታሪክ ተቀይሯል በሥልጣኔ ቁንጮ ላይ ደርሳ ከቅኝ ገዢዎቹ ኃያላን ተርታ ተስልፋ የነበረችው አገር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ ቁልቁል ወርዳ በአሜሪካ ጠረራ ሥር ወድቃለች ለዘመናት የተገነባው የአገሪቱ ኢኮኖሚም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወድሟል ጃፓን በ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተሸንፋ በአሜሪካ ወረራ ሥር ስትወድቅ በመላ አገሪቱ የሚላስ የሚቀመስ ወይም የሚለበስ አልነበረም ለዓመታት በአገሪቱ ላይ በተካፄደው የአየር ድብደባ ለዘመናት አገሪቱ የገነባቻቸው ኢንዱስትሪዎችና የመሠረተ ልማቶች ወዐ አመድነት ተቀይረዋል በጦርነቱ ማብቂያ ላይ በከተማ ይኖር የነበረው የጃፓን ሕዝብ የቤት ዕቃውንና ጌጣጌጡን አየያዘ በሚበላ ነገር ለመለወጥ ወደ ገጠር ለመሰደድ ተገዲል ዳፓን በሁለተኛው የዓለም የኒኩሊዬር ጥቃት መሪዎች «ሀብታም ጦርነት በየትኛውም ሌላ አገር ላይ ያልደረሰ መከራ ከደረሰባት በኋላ መንገዲን ቀይራለች የሜጂው አብየት አገር ጠንካራ መከላከያ ለመፍጠር ራእይ ሰንቀው ሌት ተቀን በመሥራት ላ ቀር የነበረችውን አገር በአጭር ጊዜ ውስጥ ከበለፀጉት አገራት ተርታ አሰልፈዋታል ሆኖም ከእነርሱ በኋላ የመጣው ትውልድ ቦምብ ወደ አመድነት ስትቀየር በዐይናቸው ተመልክተ በኋላ የመጡት መሪ የጦርነት ዋል እናም ከሠ ዎች የአባቶቻቸውን መንገድ እርግፍ አድርገው በመተወ ተሰናፊ የሆነችውን አገራቸውን የሰላም አሸናፊ ለማድረግ ቆርጠወ ተነሠ መሪዎቹ ከጥንት ጀምር በዋለችበት የጦር ሜዳ ሁሉ ተሸንፋ የማታውቀው አገራቸው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በታሪክ የመደመሪያውን ሽንፈት ከተጎነጨች በኋላ አካሄዳቸውን ሙሉ በሙሉ በመተየር በጦርነተ ብቻ ሳይሆን በሰላምም ማሸነፍ እንዳለ ለዓለም አሳይተዋል መላውን ኤዥያ ለዓመታት በጦርነት ስታምስ የኖረችው አገራቸው አሁን የሰላምና የወንድማማችነት ተምሳሌት ሆና ላለፉት ዓመታት በጽናት ዘልቃለጥተ የመንግሥታቱ ማኅበር ሀ ክጸከበ እንዲፈርስና የዓለም ሰላም እንዲናጋ ትልቅ አፍራሽ ሚና ስትጫወት የነበረችው አገር አሁን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ዋነኛ አጋዥና ጠበቃ ሆናለች በጦርነት ጉዳት ያደረሰችባቸውን ጎረቤቶቷን ይቅርታ በመጠየቅ የሞራልና የገንዘብ ካሳ ከፍላለች ከሰሜን ኮሪያ በስተቀር ከሁሉም የዓለም አገራት ጋር ወዳጅነት በመመሥረት ዓለም አቀፋዊ አጋርነትና ወንድማማችነት እንዲያብብ ተግታ እየሠራች ነው ከሰሜን ኮሪያም ጋር ቢሆን መልካም ጉርብትና ለመመሥረት ብዙ ያልተሳኩ ሙከራዎችን አድርጋለች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የመጡት የጃፓን መሪዎች ሕዝባቸውን ከዳር ዳር በማነቃነቅ በጦርነት የወደመችውን አገራቸውን መልሶ ለመገንባት ትኩረታቸውን ሁሉ በኢኮኖሚ ግንባታ ላይ አደረጉ የዱሮውን መንገድ አርግፍ አድርገው ትተው በአዲስ መንገድ መጓዝ ጀመሩ ሕዝቡም እንደመሪዎቹ ጦርነትን አርም ብሎ ትኩረቱን ሁሉ ሥራ ላይ አደረገ የአገሪቱ ዜጎች ያለ ፅረፍት ሌት ተቀን ሠርተው በጦርነተ የወደመው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ፈጥኖ እንዲያገግም አደረጉ በ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ የሚላስ የሚቀመስ አጥታ እሰው እጅ ላይ ወድቃ የነበረችው አገር ዓሥር ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መልሳ ወደ ላይ ተነሣችት የአገሪቱ ኢኮኖሚ ቀድሞ በየትኛውም ሌላ አገር ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት ማደግ ጀመረ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በመላ አገሪቱ እንደገና ተስፋፋ ከዎቹ አጋማሽ ጀምሮ የጃፓን የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ውጤቶች የዓለምን ገበያዎች እያጥለቀለቁት መጡ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact