Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

የሕገ_መንግስት_ጉዳዮች_አጣሪ_ጉባዔ_ፅቤት_የሰራተኞች_ስነምግባር_መመሪያ.pdf


  • word cloud

የሕገ_መንግስት_ጉዳዮች_አጣሪ_ጉባዔ_ፅቤት_የሰራተኞች_ስነምግባር_መመሪያ.pdf
  • Extraction Summary

ሆ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሰራተኛ የልማትና ዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውጤታማነትና ዘላቂነት እንዲረጋገጥ የሴቶችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን የማክበር ግዴታ አለበት አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ ይህ መመሪያ ከ ቀን ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል።

  • Cosine Similarity

የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽቤት የሠራተኞች ስነምግባር መመሪያ መ ነ ዓም ኀሎ ንች ርርመፖ ፍ ጻ መግቢያ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽቤት በአዋጅ መሰረት ከተቋቋመለት ዓላማ አንጻር የተለያዩ አደረጃጀቶችን አሰራሮችን ወደ ስራ በማስገባት ለባለጉዳዮች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እያደረገ ይገኛል ጽቤቱ ከሚጠበቅበት ተልዕኮና ተግባር አንፃር የተቋሙ ሠራተኞችን ስነምግባር ለመቆጣጠር እና የስነምግባር መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል መመሪያው ለደንበኞች ተገልጋዮች ልዩ ትኩረት በመስጠት ከተቋሙ የሚጠበቀውን አገልግሎት በቅንነት በታማኝነት እና በቅልጥፍና እንዲያገኙ የሚያስችል ነው የዚህ የሥነ ምግባር መውጣት ሌላ አላማም ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዳ ለህዝብ አገልግሎት የሚተጋ እና የሥነምግባር መርሆዎችን ተግባራዊ የሚያደርግ ትጉህ ባለሙያ ለመፍጠር በሙያው ብቁና ውጤታማ በሥነምግባሩ ምስጉን ስራ ወዳድ ባለሙያና አመራር ለማፍራት እንዲሁም ተገልጋዮች በፍትሃዊና እኩልነት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት የሚያገኙበት ተቋም እንዲሆን ለማድረግና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ነው ይህን የሥነምግባር ደንብ በሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች ላይ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ የኢፌዴሪ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤን ለማጠናከር ስልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ መሠረት ወጥቷል ይህ ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች አንቀጽ አንድ አጭር ርዕስ መመሪያ የኢፌዲሪ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽቤት የሠራተኞች የሥነ ምግባር መመሪያ ቁጥር ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል የቃለ አንቀጽ ሁለት ትርጓሜ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ ጉጭባኤ ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪኾብሊክ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ነው ጉባኤ አባላት ማለት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ መሰረት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪኾብሊክ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የተወከሉ ናቸው ጽቤት ማለት የኢፌዴሪ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽቤት ነው በላይ ኃላፊ ማለት የኢፌዴሪ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽቤት ኃላፊና እና የጉባኤውና የጽቤቱ ልዩ ረዳት ነው ዳይሬክተሮች ማለት በጉባኤው ጽቤት የስራ ሂደት መሪዎች ናቸው መመሪያ ማለት የጉባኤው ጽቤት ሰራተኞች የስነ ምግባር ሠ ሠራተኛ ማለት በጉባኤው ጽቤት ውስጥ በሙከራ በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት ተቀጥሮ የሚሠራ ሰው ነው የሥነምግባር መኮንን ማለት በሚኒስትሮች ምቤት ደንብ ቁጥር መሠረት መልካም ሥነ ምግባር ያለውና በጉባኤው ጽቤት ሃላፊ ተመርጦ የተመደበ የሥነ ምግባር ባለሙያ ነው ሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ማለት በሚኒስትሮች ምቤት ደንብ ቁጥር አንቀጽ መሰረት የተቋቋፈመና በጽቤት ውስጥ የሥነ ምግባር ሁኔታን የሚያስተባብርና የሚያማክር የሥራ ክፍል ነው «ሥነምግባር ማለት በጽቤቱ ውስጥ ስህተት የሆኑት ድርጊቶች ወይም ተግባሮች እንዳይፈጸሙ ትክክል የሆኑት ደግሞ በበሳል አስተሳሰብ እንዲፈጸሙ የሚያስችል ድርጊት ነው በ ሥነምግባር መርሆ ማለት በጽቤቱ ውስጥ ጥሩና መጥፎ ድርጊት መደረግ ያለበትና የሌለበት ድርጊቶች የሚገለጽበት አጠቃላይ የአስተሳሰብ የአመለካከት እና የተግባር አፈጻጸሞች የሚመሩበት ሥርዓት ነው የሥኑምግባር ብልሹነት ማለት በዚህ የሥነምግባር መመሪያ የተጠቀሱትን የሥነ ምግባር መርሆዎች ወይም እሴቶች የሚቃረን ባህርይ ነው የጥቅም ግጭት ማለት የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ ቤተሰቡ ወይም የቅርብ ዘመዱ የፋይናንስ ወይም ሌላ ማናቸውም ጥቅም ከመንግሥታዊ ሥራው ወይም ከሥልጣኑ ጋር በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚጋጭ ወይም ግጭት ሊፈጥር የሚችል መሆኑ በበቂ ሁኔታ የሚታመን ጉዳይ ማለት ነው ህብት ማለት በሰራተኛ ይዞታ ስር የሚገኝ ማንኛውም የማይንቀሳቀስ ወይም የሚንቀሳቀስ ወይም ግዙፍነት ያለው ወይም የሌለው ንብረትን ይጨምራል ሞዋቅምን ማስመዝገብ ማለት በህግ ግዴታ የተጣለበት የሠራተኛውን ወይም የቤተሰቡን የፋይናንስ ጥቅምና ሀብትን በጽሑፍ አቅርቦ ማስመዝገብ ነው ስጦታ ማለት በጽቤቱ ውስጥ ባለው የሥራ ደረጃና ኃላፊነት ወይም በሥራው አጋጣሚ ምክንያት የተሰጠው ዋጋ ወይም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ነገር ማለት ነው መስተንግዶ ማለት ለጽቤቱ ሠራተኞችና ኃላፊ ወይም ለቤተሰቡ በሥራው ላይ እያለ የሚደረግለት ወይም የተደረገለት የምግብ የመጓጓዣ የሆቴል የመዝናኛ ወይም ሌላ ዓይነት አገልግሎት ነው ጥቆማ ማለት በጉባኤው ጽቤት የተፈፀመን ሙስና ብልሹ አሠራር የሥነ ምግባር ግድፈትና የበቀል እርምጃ አስመልክቶ በአካል በስልክ በጽሑፍ ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ የሚቀርብ መረጃ ወይም የሚሰጥ አስተያየት ነው ሟስጥር ማለት የጽቤቱ ሰራተኛ በስራው ምክንያት ያወቀውን የመንግስት የህዝብና የግለሰብ ጥቅም የሚጎዱ በመሆናቸው በህግ ወይም በሚመለከተው አካል ውሳኔ እንዳይገለጽ የተደነገጉ መረጃዎች ናቸው የዲሲፕሊን ኮሚቴ ማለት በኢፌፌሪ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽቤት የተቋቋመ ኮሚቴ ነው የቅሬታ አጣሪ ኮሜቴ ማለት በህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽቤት የተቋቋመ ኮሚቴ ነው ሣቢ ማለት ደመወዝ ከግል ድርጅት ሽርክና አክስዮን የሚገኝ ትርፍ የሎተሪ ገቢን የቁጠባ ገቢንና የመሳሰሉትን ይጨምራል ሰው ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው አንቀጽ ሶስት የተፈጻሚነት ወሰን ይሀ መመሪያ በማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ ሳይ ተፈጻሚ ይሆናል በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ስር የተደነገገው ቢኖርም ይህ መመሪያ የጉባኤው ጽቤት ኃላፊና የጉባኤው አባላትና የጽቤት ሃላፊ ልዩ ረዳት ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም አንቀጽ አራት የመመሪያው ዓላማዎች ይህ መመሪያ ሠራተኞች በጉባኤው ጽቤት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት መከተል የሚኖርባቸውን ሥነምግባር በግልጽ በመደንገግ በሥራቸው ሂደት እንዲመሩበት የማስቻል ሰራተኞች ሥራቸውን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው አሠራር እንዲያከናውኑ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በተቀላጠፈና ጥራት ባለው ሁኔታ እንዲወጡ በማስቻል ጉባኤው ተልእኮውን የተሳካ ለማድረግ እንዲያስችለው አስፈላጊውን ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ የማድረግ እና የህዝብ አገልጋይነትን ባሕል በማዳበር ለጉባኤው ወይም ለህብረተሰቡ ፍትሐዊ አገልግሎት የመስጠት ዓላማዎችን መሠረት ያደረገ ነው አንቀጽ አምስት ስለ ጾታ አገላለጽ በዚህ ሥነምግባር መመሪያ ውስጥ በወንድ ጾታ የተደነገገው የሴትንም ጾታ ያካትታል አንቀፅ ስድስት ኃላፊነት ማንኛውም በየደረጃው ያለ የሥራ ኃላፊ በሥሩ ያሉት ሠራተኞች ይህንን መመሪያ እንዲያውቁትና ተግባራዊ እንዲያደርጉት የማድረግ ግዴታ አለበት ከባድ በሆነ ጊዜ ለበላይ አመራር ወይም ለኮሚሽኑ ጭምር የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው በአዚህ መመሪያ ውስጥ የተመለከቱትን የሥነምግባር መርሆዎችን አፈፃፀም በሚመለከት የሥነምግባር መኮንኑ ወይም የሥነምግባር ሠራተኛ የጽቤት ሠራተኞችን የማስተማርና የማማከር በመቤቱ ስላለው መልካም ሥነምግባር ሁኔታ ለመቤቱ የበላይ ኃላፊ ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነት አለበት ማንኛውም የጽቤቱ ሠራተኛ ይህንን መመሪያ የመፈፀም ግዴታ አለበት ክፍል ሁለት አጠቃላይ የሥነ ምግባር መርሆዎች እና የሥነ ምግባር ግድፈቶች አንቀጽ ሰባት ቅንነትየተሟላ ስብእና ከከ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ የጉባኤውን አባላት ሠራተኞች ባለድርሻ አካላትንና ተገልጋዮችን በቅንነት ማገልገል አለበት ለጉባኤ አባላት ለጽቤት ኃላፊዎች ሠራተኞችና ወደ ጉባኤው ለሚመጡ እንግዶች ተገቢውን አክብሮት መስጠት ይኖርበታል ከህግ ውጭ ከመሥራት ተገቢ ካልሆነ አድራጎት ወይም ባህሪ ወይም ልማድና ከሥነምግባር ብልሹነት መቆጠብ ይኖርበታል የሙያ ሥነምግባሩ በሚጠይቀው መሠረት በሥራ ሰዓት በቅንነት ሙሉ እውቀቱንና ጉልበቱን ለሥራው ማዋል አለበት መብትና ጥቅሞቹ እንደተጠበቁ ሆኖ አስቸኳይ ሥራ ሲያጋጥም በቂ ምክንያት ከሌለው በስተቀር ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ ሥራ ለመሥራት ፈቃደኛ መሆን አለበት ሥራዎችን ሲያከናውን በኃላፊነት ስሜት የተቋሙንና የተገልጋዮችን እምነት ሊያስጠብቅና ሊያጎለብት በሚችል አኳኋን መሆን አለበት ከላይ የተመለከቱትን መርሆዎች ወይም በመርሆቹ ሥር የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በመተላለፍ የጉባኤውን ዝና የሚጎዳ ወይም ህዝቡ በጉባኤው ላይ የሚኖረውን እምነት ዝቅ የሚያደርግ ባህሪ ማሳየት ወይም ተግባር መፈፀም በመለገም ወይም ትኩረት ባለመስጠት ስራን መበደል ሱስ በሚያስይዝ መድሃኒት ወይም አደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ወይም በልማዳዊ መጠጥ ተፅእኖ ምክንያት ሥራን ማከናወን አለመቻል ወይም በሥራ ላይ በደል ማድረስ ጫትና መሰል ፅፆችን እና እንደ ካርታ የመሳሰሉ የቁማር መጫዎቻዎችን ወደ ጉባኤው ቅጥር ግቢ ይዞ መግባትና መጫወት ወይም እንዲገባ መርዳት ወይም በቢሮ ውስጥ እና ባልተፈቀዱ ቦታዎች ሲጋራ ማጨስ በቢሮና በስራ አካባቢ ወሲብና ወሲብ መሰል ተግባር ወይም ማንኛውንም አይነት የጾታ ጥቃት መፈጸም የጉባኤውን ክብርና ሞገስ የሟጻረር አለባበስ አነጋገር የጸጉር አስተዳደግና አቆራረጥ በጉባኤው ስብሰባና በስራ ሰዓት ስራን የሚያውክ ድምጸች ማሰማት ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ተግባብቶ ባለመስራት በሥራ ሂደት ላይ እንቅፋት መፍጠር ያስቀጣል አንቀጽ ስምንት ታማኝነት ሃቨ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ በማንኛውም ጊዜ ለህገመንግሥቱ እንዲሁም ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ለጉባኤ አባላት ለጽህፈት ቤቱ ተገልጋዮች ለሥራ ኃላፊዎቹና ለሥራ ባልደረቦቹ ታማኝ መሆን አለበት ለሥራው ማከናወኛ የተሰጠውን የጽህፈት ቤቱን ንብረትና ገንዘብ ለታቀደው ዓላማ ወይም አገልግሎት ብቻ በማዋል ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ በቁጠባ የመጠቀም ቀልጣፋና ውጤታማነትን መሠረት አድርጎ የመሥራት ኃላፊነት አለበት ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ለሥራ በአደራ የተሰጠውን ገንዘብ ወይም ንብረት መውሰድ ማስወሰድ መሰወር ወይም ለሌላ አካል አገልግሎት ማዋል የለበትም በጽህፈት ቤቱ ሀብትና ንብረት ላይ ወንጀል እንዳይፈፀም መጠበቅና መከላከል እንዲሁም ሲፈጸምም ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ አለበት የጽህፈት ቤቱን ተሽከርካሪ ያለ ፈቃድ ከመንግስት ስራ ውጭ ለግል ጥቅሙ ማዋል የለበትም ያ የዜጎችና የሕዝቡን ጥቅሞች ፍትሐዊ ቀልጣፋ ውጤታማ እንዲሁም ልዩ ትኩረት የሚሹ አካላትን በተገቢው መንገድ በታማኝነትና በጥንቃቄ ማከናወን አለበት ከላይ የተጠቀሱትን መርሆችንና በመርሆወቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተላለፍ ቅን ልቦናን በሚቃረን ሁኔታ ጥቆማ ማቅረብ የሥራ ባልደረባን ህገወጥ ድርጊት ወይም የሥነምግባር ጉድለት ወይም ተገቢ ያልሆነ አድራጎት ለሥራ ኃላፊው ወይም ለሥነምግባር መከታተያ ክፍል አለማሳወቅ አንድ መሰራት ያለበት ሥራ እንዳይሠራ ወይም መሰራት የሌለበት ስራ እንዲሰራ ወይም ውሣኔ እንዳይፈጸም እንቅፋት መፍጠር ወይም ከሚያውኩ ሰዎች ጋር መተባበር በጉባኤው ውሣኔ አሰጣጥ ሳይ ጉዳት የሚያደርስ መረጃ ሆን ብሎ መግለጽ ለጉባኤው የሚቀርቡ ማንኛውም መረጃዎችና የውሳኔ ሀሳቦች በቂ ዝግጅትና እርማቶች ሳይደረግ ማቅረብ በጽህፈት ቤቱ ሀብትንብረት ወይም አገልግሎት አላግባብ መጠቀም ወይም ሌሎች እንዲጠቀሙ ማድረግ በጽህፈት ቤቱ የሥራ ሰዓት የግል ወይም የሌላ ሰው ሥራን ማከናወን ያለበቂ ምክንያት በሥራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን ለሚመለከተው አመራር ወይም አካል በወቅቱ አለማሳወቅ በጽህፈት ቤቱ ንብረትና ሃብት ላይ የሥርቆት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈፀም በጽህፈት ቤቱ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ጉዳት ማድረስ በጽህፈት ቤቱ ንብረት ላይ በቸልተኝነት ከባድ ጉዳት ማድረስ ያስቀጣል አንቀጽ ዘጠኝ ሃቀኝነት ዘበከ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ በሀቅ በመሥራት በመንግሥት ሥራና በኃላፊነቱ የገባውን ቃል የማክበርና የመጠበቅ ግዴታ አለበት ዴሪ የሕል በሙያው በሜሰጠው አገልግሎት የህዝቡን ወይም የተገልጋዩን የመንግሥትንና የባልደረቦቹን አመኔታ በሚጠብቅና በሚያጠናክር አኳኋን የመንግሥትን ፖሊሲ ህጎች ዕቅዶችና መመሪያዎችን በሥራ ላይ ማዋል ይኖርበታል ከሙስና ከማጭበርበር ከማታለል ከሥነምግባር ብልሹነትና ከሌላ ህገወጥ ተግባር መቆጠብ አለበት መልካም ተግባር በመፈፀሙ አግባብ ባለው ህግ የተፈቀደ ሽልማት ካላገኘ ወይም ስጦታ ወይም መስተንግዶ ለመቀበል የሚያበቃ በቂ ምክንያት ከሌለው በስተቀር ከሥራው ጋር በተገናኘ ከደመወዙ ወይም በህግ ከተፈቀደለት ጥቅም ውጪ ከሌላ ሰው ወይም ተገልጋይ ስጦታ ወይም መስተንግዶ መጠየቅ ወይም መቀበል የለበትም ከላይ የተጠቀሱትን መርሆች ወይም በመርሆዎቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተላለፍ ሰነድ መሰረዝና መደለዝ ወይም የመቤቱን አርማና ማህተም ለሕገወጥ ድርጊት መጠቀም ሀሰተኛ ወይም ተገቢ ያልሆነ የአበል ክፍያ ጥያቄ ማቅረብ ወይም አበል መቀበል ሆን ብሎ የመንግስትን መመሪያ ተግባራዊ አለማድረግ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ወይም የስራ ልምድ ማቅረብ ከሥራው ጋር በተያያዘ በህግ ያልተፈቀደ ሥጦታ ወይም መስተንግዶ መቀበል ያስቀጣል አንቀጽ አስር ግልፅነት ጴበሀከሃ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ ውሳኔዎችን በተቻለ መጠን በግልጽ መስጠት የውሳኔ አሰጣጥ ሂደትን ግልጽ ማድረግና ለሟሰጣቸው ውሳኔዎች ምክንያታዊ መሆን ይኖርበታል ሥራውን ለህዝብ ግልጽ በሆነ አኳኋን ማከናወን ይኖርበታል ተገልጋዮች ፍትሐዊ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች የማሳወቅ የሚሰጡ መረጃዎች ትክክለኛ ተደራሽና ወቅታዊ መሆናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት የሚሰጠውን አገልግሎት የሚፈጀውን ጊዜ እንዲሁም ሌላ አስፈላጊ መረጃን በተገልጋዩ በተጠየቀ ጊዜ በግልጽ ማስታወቅ አአለበት በተሰጠው አገልግሎት ላይ ቅሬታ ያለው ተገልጋይ ወደሚቀጥለው አካል ሄዶ ቅሬታውን ማቅረብ እንደሚችል ማሳወቅ አለበት በሥራ ክፍሉ በር ጠረጴዛና በደረቱ ላይ መለያ ወይም ባጅ በማድረግ ለተገልጋዮች እራሱን ግልጽ ማድረግ አለበት የተፈፀሙ ስህተቶችን በማረም ፈጣን ማስተካከያና እርምጃዎችን በመውሰድ ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ግዴታ አለበት ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብና ሲጠየቅ ማብራሪያ የመስጠት ግዴታ አለበት መርሆዎቹንና በመርሆዎቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተላለፍ ለሕዝብ ግልጽ መሆን ያለበትን መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ለሚያስተላልፈው ውሣኔ ተገቢውን ማብራሪያ ወይም ምክንያት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ለስራ ወይም ለግምገማ የሚያስፈልግ መረጃ አግባብ ባለው አካል ሲጠየቅ በወቅቱ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ባጅ ወይም መለያ ባለማድረግ ለተገልጋዮች ግልጽ አለመሆን ያስቀጣል አንቀጽ አስራ አንድ ምስጢር ጠባቂነት ርከቨፀልበከ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ አንድ መረጃ በምስጢር ሊጠበቅ የሚገባው አግባብ ባለው ህግ ደንብ ወይም መመሪያ መሠረት ምስጢር ከሆነ ብቻ መሆኑን አውቆ ወይም ኣገርን የሚጎዳ መሆኑን ተገንዝቦ ከእዚህ ባሻገር ባሉ ሌሎች ጉዳዮች ላይ የግልጽነት መርህን ይከተላል የሥራ ግዴታውን ሲወጣ በሥራው አጋጣሚ ያወቃቸውን የጉባኤውን ጽህፈት ቤት ወይም ግላዊ የሆኑ ምስጢራዊ መረጃዎችን አይገልጽም የመንግሥትን ሥራ ከለቀቀ ወይም ወደ ሌላ ሥራ ከተዛወረ በኋላም በሥራው አጋጣሚ ያወቃቸውን ሚስጢራዊ መረጃዎች የመጠበቅ ግዴታ ይኖርበታል መርሆዎቹንና በመርሆዎቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተላለፍ ሁኔታ ሆን ብሎ ኢት ያልተፈቀደን ወይም ሚስጥራዊ መረጃን በማናቸውም መግለፅ ያልተፈቀደን ወይም ሚስጥራዊ መረጃን በማናቸውም ሁኔታ በቸልተኝነት መግለፅ በሥራ አጋጣሚ እጁ የገባውን የጽህፈት ቤቱን ሰነድ ወይም ምሥጥር ለሊላ አካል አሳልፎ መስጠት ከፍተኛ ሚስጢራዊ መረጃን ለግል ወይም ለሌላ ጥቅም ማዋል ሚስጢር ያልሆነን ነገር ሚስጢር ነው በሚል ሽፋን መረጃዎችን ግልጽ አለማድረግ ያስቀጣል አንቀጽ አስራ ሁለት ተጠያቂነትልርርዐህበልከክ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ የሚሰጣቸውን ውሳኔዎችና የሚሜያከናውናቸውን የእለት ተዕለት ሥራዎች በተጠያቂነት መንፈስ ማከናወን ይኖርበታል በውሳኔውና ባከናወነው ሥራ ምክንያት ለሚቀርብለት ተገቢ ለሆነ ማጣራት ራሱን ዝግጁ ማድረግና በተፈለገ ጊዜ የመቅረብ ወይም የመገኘት ግዴታ አለበት አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ሁሉ ለተግባራዊነቱ ፈጣን ምላሽ የመስጠት ግዴታም ይኖርበታል የተቋሙን የአለባበስ ስርዓት የሚቃረን አለባበስ በስራ ቦታ መጠቀም የተከለከለ ነው ስላከናወናቸው ሥራዎች ሪፖርት ያቀርባል ይጠየቃል ይገመገማል ግዴታውን በአግባቡ ስለመወጣቱ ጥያቄ ሲቀርብለት አስፈላጊውን ማብራሪያ ይሰጣል መርሆዎቹና በመርሆዎቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተላለፍ ስላከናወናቸው ሥራዎች ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ሪፖርት አለማቅረብ ለሚመለከተው አካል ሆነ ብሎ የሚያሳስት ወይም ትክክል ያልሆነ ሪፖርት ወይም መረጃ ማቅረብ ስላከናወናቸው ሥራዎች ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ በቸልተኝነት የሚያሳስት ወይም ትክክል ያልሆነ ሪፖርት ማቅረብ የተሰጠውን ሥራ ያለበቂ ምክንያት በወቅቱ አለማከናወን ያለፈቃድ ወይም ሥልጣን ሳይኖረው በኮምፒዩተር የተያዘ ዳታን ማጥፋት ወይም መለወጥ ወይም የተሳሳተ መረጃ በኮምፒዩተር ዳታ ውስጥ ማስገባት መመሪያ ባለማክበር በቸልተኝነት በመለገም ወይም ሆን ብሎ የኣሰራረ ስርዓት ወይም የመንግስት ፖሊሲን ባለመከተል በስራ ላይ በደል ማድረስ ኻ ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያላቸው መረጃዎችን ሲጠየቅ ያለበቂ ምክንያት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ወይም በወቅቱ አለመስጠት ያስቀጣል አንቀጽ አስራ ሶስት የሕዝብን ጥቅም ማስቀደም ከዘከ ከ ኮህከሀ በ። ሆ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ በሚያከናውነው ተግባርና በሚሰጠው ውሣኔ የህዝቡን ጥቅም ብቻ እንጂ የግሉን የቤተሰቡን ወይም የቅርብ ዘመዱን ወይም የሌላ ሰውን ጥቅም ማስጠበቅ የለበትም የመንግሥትን የሥራ ጊዜ ለግል ጥቅሙ ማዋል የለበትም ከመደበኛ ሥራው ጋር የጥቅም ግጭት ሊፈጥር የሚችል ሁኔታ ሲገጥመው የማሳወቅ ግዴታ አለበት ከመደበኛ ሥራው ጋር ሊጋጭ የሚችል የውጭ ሥራ መስራት የለበትም በህግ ግዴታ ያለበት ማንኛውም ሃላፊና ሠራተኛ በራሱና በቤተሰቡ ባለቤትነት የተገኘ ገቢን ሃብትና ንብረቱን የማሳወቅና የማስመዝገብ ግዴታ አለበት መርሆዎቹንና በመርሆዎቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተላለፍ የራሱን ወይም የቤተሰቡን ወይም የስጋ ዘመዱን ወይም የሌላ ሰውን ጥቅም አላግባብ ማስቀደም በሕግ ግዴታ እያለበት ጥቅምን በቸልተኝነት አለማሳወቅ በሕግ ግዴታ እያለበት የራሱንና የቤተሰቡን ሃብት ለማስመዝገብ ፈቃደኛ አለመሆን ፓች ኣጣሪ ሥእ በሕግ ግዴታ እያለበት ሆን ብሎ ያልተሟላ ወይም ሃሰተኛ የሀብት ምዝገባ ማድረግ በህግ ግዴታ እያለበት በቸልተኝነት ያልተሟላ ወይም ሃሰተኛ የሃብት ምዝገባ ማድረግ ያስቀጣል አንቀጽ አስራ አራት ሕጋዊ በሆነ ሥልጣን በአግባቡ መገልገልጅፎእርኮ ወዐቨ ከ ልሀከዕቨቨ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ በሥልጣን አላግባብ መገልገል የለበትም ተግባሩን ሲያከናውንና ውሣኔ ሲሰጥ ህግንና ስርዓትን ብቻ መሠረት በማድረግ ይሆናል የተሰጠውን ሥራ በሚያከናውንበት ጊዜ የማይገባውን ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት ወይም በሌላ ሰው መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ወይም ቸልተኛ በመሆን በግልጽ በህግ ከተሰጠው ሥልጣን አልፎ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት መፈፀም የለበትም ከህግ ውጪ በማስገደድ ወይም ተጽእኖ በማድረግ የሌላን ሰው መብት መጋፋት ወይም ከሌላ ሰው ምንም ዓይነት ጥቅም እንዲሰጠው መጠየቅ የለበትም ኃላፊነቱን ወይም ሥራውን ምክንያት በማድረግ የማይገባውን ለማድረግ ወይም ማድረግ የሚገባውን ተግባር ሳለማከናወን ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር ለመፍቀድ አንድን ህገወጥ ድርጊት ለመደበቅ በማሰብ አገልግሎት ከሚጠይቁ ሰዎች ስጦታ ወይም መስተንግዶ መጠየቅ ወይም መቀበል የለበትም ውሣኔን አላግባብ ማዘግየት ወይም ህጋዊ ውሣኔ እንዳይፈፀም እንቅፋት መፍጠር የለበትም መርሆዎቹንና በመርሆቹ ሥራ የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተላለፍ ስልጣኑ ከሚፈቅድለት በላይ መሥራት ወይም በስልጣን አላግባብ መገልገል ዴሪ የ በጽቤቱ ሰራተኞች ላይ ከህግ ውጭ ተገቢ ያልሆነ ጫና መፍጠር ወይም ከሚገባው በላይ እንዲሰሩ ማስገደድ ሥራን በተገቢው ጥንቃቄ አለማከናወን ያስቀጣል አንቀጽ አስራ አምስት አድሎ አለመፈፀምጠፀሀከ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ ህግና መመሪያን መሠረት በማድረግ በቀረበለት ጉዳይ ሳይ ተገቢና ፍትሐዊ የሆነ ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል ውሳኔ በሚሰጥበት ወይም ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት በዝምድና በጓደኝነት በቀለም በዘር በብሔርብሔረሰብ በጸታ በቋንቋ በሀይማኖት በፖለቲካ አመለካከት በግል ስሜት በውለታ በጥላቻ ወይም በሌላ በማናቸውም አቋም በተገልጋዮች ላይ ልዩነት ማድረግ የለበትም ለሀሊናው ተገዥ በመሆን ተገልጋዮችን አድሎ በሌለበት ሁኔታ በማስተናገድ ለጥያቄዎቻቸው ተገቢ መልስ መስጠት ይኖርበታል ህግን ደንብንና መመሪያን መሠረት በማድረግ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የሆነ ውሣኔ መስጠት አለበት ከላይ የተመለከቱትን መርሆዎችና በመርሆቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተላለፍ ከህግና ከመመሪያ ውጭ የሆነ ቅጥር ዝውውር ዕፅድገት ሥልጠና ወይም የትምህርት ዕድል ወይም ጥቅማጥቅም መስጠት አድሎአዊ ተግባራትን መፈጸምመተባበር ወይም ማነሳሳት ያስቀጣል አንቀጽ አስራ ስድስት ሕግ ማክበርርከበ ከ ጸህ ማንኛውም የምቤቱ ጽቤት ሠራተኛ ህገመንግሥትን የመንግስትን ፖሊሲ ህግና መመሪያን የማክበር የመፈፀምና የማስፈፀም ግዴታ አለበት በኃላፊው ወይም በስራ መሪው የተሰጠውን ህጋዊ ትዕዛዝ ማክበር አለበት በጉባኤው ቅጥር ግቢ ውስጥ የህብረት አምልኮ መፈጸም ወይም ሌሎች ህገወጥ ተግባራት እንዲፈፅሙ መፍቀድ ማነሳሳት ማዘዝ ወይም መሳተፍ የለበትም የሌላውን ሰው መብት ወይም ጥቅም ለመጉዳት በማሰብ ሐሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት እውነተኛ ጽሑፍን ወደ ሀሰተኛ መለወጥ ሰነድ ወይም ማህደር ማጥፋት የለበትም በሌላ ሰው ፊርማ ወይም ማህተም ወይም በሃሰተኛ ፊርማና ማህተም መጠቀም የአንድን ሰነድ ይዘት በማሳሳት ሌላ ሰው እንዲፈርም ማስደረግ ሰነድ ወይም ማህደር ማጥፋት የለበትም ደረሰኝን በማበላለጥ ወይም በማቀናነስ ማጭበርበር የለበትም በጽሑፍ በምስል ወይም በሌላ በማናቸውም ዘዴ በመጠቀም ስም ማጥፋት የለበትም መርሆዎቹንና በመርሆቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተሳላለፍ ሕጎችን ወይም የአሠራር ስርዓቶችን በመጣስ መሥራት ወይም ሕጋዊ የሆኑ ትዕዛዞችን አለማክበር ወይም ሌሎች ሠራተኞች እንዳያከብሩ መገፋፋት ወይም ከህግ ውጭ እንዲሰሩ መገፋፋት ወይም ማበረታታት የቅርብ የሥራ ኃሳፊን ፈቃድ ሳያገኝ ወይም ከሥራ ለመቅረት በቂ ምክንያት ሳይኖረው ከስራ መቅረት መቅረቱ በሥራው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ እያወቀ ያለ ፈቃድ ከሥራ መቅረት በሥራ አካባቢ አምባጓሮ ወይም ጠብ መፍጠር ባለጉዳይን የሥራ ኃላፊን ወይም የስራ ባልደረባን መስደብ ወይም መደባደብ ሕግን ሕጋዊ ትዕዛዝን ወይም የአሠራር ሥርዓትን ወይም የመንግሥትን ፖሊሲ በመጣስ ሆነ ብሎ በሥራ ላይ በደል ማድረስ የሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓትን አለማክበር ወይም ያለፈቃድ ቢር ገብቶ መውጣት በጉባኤው ቅጥር ግቢ ውስጥ የህብረት አምልኮ ፕሮግራም መጥራት ወይም መተግበር በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የሌላን ሰው መብት በሚነካ ወይም ስራን በሚበድል ሁኔታ የሃይማኖት ተግባራትን መፈጸም በጉባኤው ቅጥር ግቢ ውስጥ ወይም አካባቢ ማንኛውንም አድማ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት ወይም ማድረግ ማናቸውንም ህገ ወጥ ተግባራት እንዲፈጸሙ መፍቀድማነሳሳትማዘዝ ወይም መሳተፍ ያስቀጣል አንቀጽ አስራ ሰባት ለሕዝብ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ መስጠትከሸሀበከበ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ ባለጉዳዮችን በአክብሮትና በትህትና መቀበል በጥሞና በማዳመጥ ለጥያቄዎቻቸው ተገቢውን ምላሽ ወይም መፍትሔ በወቅቱ መስጠት ይኖርበታል ለባለጉዳዮች ወይም ለጉባኤው አባላትና ሠራተኞች ስለመብታቸው ወይም ስለአሠራር ስርዓቱ ያልተዛባና ትክክለኛ መረጃ በመስጠት በአግባቡ የማስተናገድ ግዴታ አለበት በሌሎች የመንግሥት የተለያዩ ህጎች ስለ ሙያ ሥነምግባር በተደነገገው መሠረት የሙያ ሥነምግባሩን በመጠበቅ ሥራውን ማከናወን አለበት መርሆዎቹንና በመርሆቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተሳላለፍ ለጉባኤው አባላትና ለባለጉዳዮች ተገቢውን ትህትና አለማሳየት ወይም እገዛ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን ባለጉዳዮች ለሚያቀርቡት ጥያቄ ወቅታዊና ተገቢውን ምላሽ አለመስጠት ወይም ማጉላላት ያለበቂና ህጋዊ ምክንያት ጉዳዮችን ወይም አቤቱታዎችን ማዘግየት ያስቀጣል አንቀጽ አስራ ስምንት አርአያ መሆን ፎአእ ከሠ ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሠራተኛ ከሚያምንበት ሃሳብና እምነት የተለየ አስተያየት ያለውን ሰው መብት በማክበር የተለያዩ አስተያየቶች እንዲቀርቡ በማደፋፈር ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ ውይይት በመፍታትና ስህተቱ ሲነገረው በመቀበል ለሌሎች አርአያ መሆን አለበት ማሩ ድች አጣረ የኃላፊነት ስሜት የሚሰማው በመሆን የተሻለ ለውጥን በመደገፍ የሥራ ቦታንና የግል ንጽሕናን የጉባኤውን መልካም ስም ክብር እና ሞገስ በመጠበቅና የአሠራር ባሕልን በማዳበር ለሌሎች አርአያ መሆን አለበት አመራር ሰጪነቱን የሙያ ብቃቱን ዕውቀቱንና ክህሎቱን በማዳበርና ሥራን በቡድን ተግባብቶና ተቀናጅቶ በመሥራት ለሌሎች አርአያ መሆን አለበት የሥራ ዲሲፕሊንና የሥራ ሰዓትን በማክበር ለሌሎች አርአያ መሆን አለበት ከላይ የተመለከቱትን መርሆዎችንና በመርሆቹ ሥር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመተላለፍ ኃላፊነት እያለበት አግባብነት ያለውን የጉባኤውን አሠራርና የጽቤቱን የሥነምግባር መርሆዎች ለሠራተኞች አለማሳወቅ የጉባኤው አባላትን ወይም ሌሎች ተገልጋዮችን ወይም የሥራ ባልደረቦችን መዝለፍ ማመናጨቅ ወይም መልካም ሥነምግባርን በተላበሰ መልኩ አለማስተናገድ የቡድን ወይም የኮሚቴ ሥራ እንዲሠራ ትዕዛዝ ሲሰጥ ያለበቂ ምክንያት ለመሥራት ፈቃደኛ አለመሆን ያስቀጣል ክፍል ሦስት ከተለያዩ አካላት ጋር ስለሚኖር ግንኙነት አንቀጽ አስራ ዘጠኝ ከዜጎች ጋር መኖር ስለሚገባው ግንኙነት ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሰራተኛ ዜጎች ተገቢ ውጤታማና ክብር የተላበሰ አገልግሎት ማግኘት እንደሚገባቸው ማመንና ተግባራዊ ማድረግ አለበት ለሕዝብ አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት በሕግ ሚስጥር ሆነው እንዲጠበቁ ከተለዩት ጉዳዮች በስተቀር ዜጋው መረጃ የማግኘት መብቱ መከበር ያለበት መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ሕዝብንና ዜጎችን በእኩልነት የማገልገልና የማስተናገድ ግዴታ አለበት ጊሬ ኳሌ ሕዝብና ዜጎች ባገኙት አገልግሎት ላይ ያላቸውን አስተያየት ቅሬታ አቤቱታና ጥቆማ ማቅረብ መቻላቸውን በማመን ላቀረቡት ሀሳብ ህጋዊና ወቅታዊ ምላሽ መስጠት አለበት አንቀጽ ሃያ ከበላይ ኃላፊ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሰራተኛ ጥቅም ለማግኘት በበላይ አመራቱ ላይ ጫና ማሳደር የለበትም እውቀቱንና ክህሎቱን በመጠቀም የመንግስት ፖሊሲዎችንና የልማት ዕቅዶችን በውጤታማነት መፈጸም አለበት የበላይ አመራሩን የሥራ መመሪያና የሚሰጠውን የሥራ አቅጣጫ በቅንነት በመልካም ስነምግባርና በሙያዊ ክብር መቀበልና ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት አለበት ለበላይ አመራሩ ወቅታዊ ተጨባጭ ሐቀኛ ግልፅና ተጠያቂነትን የሚያመሳክቱ ሪፖርቶችን የማቅረብ ግዴታ አለበት ወቅታዊ እና ተአማኒነት ያለው መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት ለበላይቨአመራሩ የሚያቀርበው ሀሣብና ውሳኔ የተለየ ዝና ወይም ጥቅም ለማግኘት አለመሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት ለተፈፀመ ጉድለትና ግድፈት ተገቢ እና እውነተኛ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ምላሽ መስጠት አለበት አንቀጽ ሃያ አንድ ከቅርብ ኃላፊ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሰራተኛ ሥራውን በድርጊት መርሀግብር መሰረት በተቀመጠው የአፈጻጸም ደረጃ እያከናወነ መሆኑን ለማወቅ የቅርብ ኃላፊው የሚያደርገውን ክትትልና ድጋፍ በአግባቡ መቀበል አለበት ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ችግር ካጋጠመው የቅርብ ኃላፊውን በማማከር የተሻለ መፍትሔ የሚያስገኝ ውሳኔ መወሰን አለበት አዲስ አመራሮች ሲመደቡ ተገቢውን መረጃ የመስጠት ኃላፊነት አለበት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከቅርብ ኃላፊው ልዩ ጥቅም እንዲያገኝ ማድረግ የለበትም ከቅርብ ኃላፊ የሚሰጡ ገንቢ አስተያቶችን ተቀብሎ መተግበር አለበት ፈ አንቀጽ ሃያ ሁለት ከስራ ባልደረቦች ጋር ስለሚኖር ግንኙነት ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሰራተኛ የዕለት ተዕለት ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት ከሌላው ሠራተኛ ጋር በመልካም ሥነ ምግባር የታነፀ ትብብርና ግንኙነት የማድረግ ግዴታ አለበት ከሁሉም የሥራ ባልደረቦች ጋር የሚኖረው ግንኙነት በሐቀኝነት በትህትና በመከባበር ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ሂስ ለመቀበልና ለመስጠት ራስንና የሥራ ባልደረባን በቅንነት ለማረም ያለውን ዝግጁነት በተግባር ማሳየት አለበት የቡድን ተልዕኮ የማሳካት እውቀትና ክህሎትን ለስራ ባልደረቦች የማካፈል ኃላፊነት አለበት በቡድን ውይይት ወቅት ለሚቀርቡ አስተያየቶች ክብር መስጠትና ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ አለበት አንቀጽ ሃያ ሶስት ከተቋማት ጋር ስለሚኖር ግንኙነት ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሰራተኛ ማንኛውንም ግንኙነቶች በሕግና ደንብ መሠረት መፈፀም አለበት ሕጋዊ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሜደረግ ጥረትን ማስወገድ እና የሚሳተፉትን የማጋለጥ ግዴታ አለበት የተቋማትን የእርስ በእርስ ግንኙነት ሊያጐለብት የሚችል ቀና ትብብር የማድረግ ኃላፊነት አለበት አንቀጽ ሃያ አራት ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ስለሚኖር ግንኙነት ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሰራተኛ በከፍተኛ አመራሩ ወይም ጉዳዩ በሚመለከተው የስራ ክፍል ሊገለጽየሚገባው መረጃ መስጠት የለበትም በኮሙኒኬሽን ክፍል ወይም በበላይ አመራሩ ሊገለጽ የሚገባውን መረጃ መስጠት የለበትም ኃላ ምስጢራዊ ወይም በሕግና በመመሪያ እንዳይገለጽ የተከለከሉ መረጃዎችን ማስተላለፍ የለበትም ከተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት አንጻር በቅንነት በታማኝነት ተገቢና ወቅታዊ መረጃ የመስጠት ኃላፊነት አለበት በመገናኛ ብዙሃን መረጃ ሲሰጥ የሀገር የሕዝብ የተቋም የአመራሮች የግለሰቦች መብት መልካም ስምና ዝና ማክበር አለበት አንቀጽ ሃያ አምስት ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ማንኛውም የጉባኤው ጽቤት ሰራተኛ ተቋሙን በመወከል በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ስብሰባዎችና በመሳሰሉ ኩነቶች ላይ ሲካፈል የሀገርን አቋምና ክብር መፀበቅ አለበት በጠበቀ መንገድ በታማኝነት ሃሳቡን መግለጽና ማቅረብ አለበት በአገር አቀፍ ወይም ዓለም አቀፋዊ ስብሰባዎች ወይም ውይይቶች ላይ የመንግሥት ፖሊሲዎችና የሴክተሩን ብሔራዊ ፖሊሲ በማብራራት ማቅረብ አለበት ከተሰጠው የውጭ ሀገር ተልዕኮ ወደ ሀገር እንደተመለሰ በአግባቡ የተደራጀ ሪፖርት ለላከው አካል የማቅረብ ግዴታ አለበት በዓለም ዓቀፍና አህጉራዊ ስብሰባዎች ላይ ከድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በሚደረግ ግንኙነት የሀገርን የመንግሥትን የዜጎችን ክብርና መብት የሚነኩ ሃሳቦችን ማራመድና ይህን የሚደግፉ ጉዳዮችን መፈጸም የለበትም የሚፈፅሙ ወገኖችንም በጥብቅ መቃወም አለበት አንቀጽ ሃያ ስድስት የስራ ሃላፊዎች ከፈጻሚዎች ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት ማንኛውም የሥራ ኃላፊ ለፈጻሚዎች ግልፅ ተጨባጭነት ያለው ተልእኮ መስጠት አለበት ፈፃሚዎች የተሰጣቸውን ተግባር በውጤታማነት በቅልጥፍናና በመልካም ስነ ምግባር እንዲፈፅሙ ተገቢውን አመራር መስጠት አለበት በአፈፃፀም ለሚከሰቱ ችግሮች ፈፃሚ ሠራተኞችን ከመውቀስ አስቀድሞ ኃላፊነቱን በመውሰድ ለማረምና ለማስተካከል ጥረት ማድረግ አለበት ጥሩ የሥነምግባር ባሕሪ በማሳየት ለሌሎች ሠራተኞች አርአያ መሆን አለበት ለፈፃሚዎች ስብዕናና አስተሳሰቦች ክብር መስጠት አለበት በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ተጠያቂነትን መውሰድ አለበት መራተኞች መብታቸውንና ግዴታቸውን እንዲያውቁ የማድረግ ኃላፊነት ኣለበት መራተኞች የሥራ ተግባራቸውን በቅንነት በሥነ ምግባርና በውጤታማነት መፈፀማቸውን በተጨበጠ መረጃ ላይ ተመስርቶ የመገምገም ኃላፊነት አለበት ሠራተኞችን በእኩል ዓይን ማየት ለተቋሙ ተልእኮና ስኬት ድርሻ ማንኛውም እንዳላቸው መገንዘብ አለበት ማንኛውም ፈፃሚ ሠራተኛ የተለየ ጥቅም እንዲያገኝ ከሦስተኛ ወገን የሚመጡ አስተያየቶችን መቀበል የለበትም ማንኛውም የሥራ ኃላፊ በየትኛውም ጊዜ ከፈጻሚ እና ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ጋር የሚያደርገው የሥራ ግንኙነት ከግል ጥቅም ጋር የተያያዘ መሆን የለበትም አንቀጽ ሃያ ሰባት የሴቶችን መብት ማክበር የጉባኤው ጽቤት ሰራተኛ የልማትና ዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውጤታማነትና ዘላቂነት እንዲረጋገጥ የሴቶችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን የማክበር ግዴታ አለበት ሴቶች በልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝና የማይተካ ድርሻ እንዳላቸው አምኖ መቀበልና ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት አለበት በየደረጃው የሚገኙ ሴቶችን ለማብቃት መንግስት ያስቀመጠውን የሴቶች ፓኬጅና ፖሊሲ የመፈፀምና የማስፈጸም ኃላፊነት አለበት በማንኛውም ጉዳይ የሴቶችን ተሳትፎ ማመጣጠን የሴቶችን መብት ማክበር መሆኑን በመረዳት ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት በማናቸውም ጊዜ ፆታዊ ጥቃቶችን ማውገዝ አለመፈፀም እና ተፈፅሞ ሲገኝም የማጋለጥ ግዴታ አለበት ከቤተሰብ ከሚኖርበት አካባቢ ከትምህርት ቤቶችና ከሥራ አካባቢዎች ጀምሮ የሴቶችን እኩልነት ሁልጊዜ ማክበር መከበሩን ማረጋገጥ የሴቶች እኩልነትን የሚፃረሩ ድርጊቶች አስተሳሰቦችና አመለካከቶችን መታገል ለሚመለከታቸው የመንግስት አስፈፃሚ አካላት የማሳወቅና የማጋለጥ ግዴታ አለበት በሴቶች ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችና ፀረ ዲሞክራሲያዊ ድርጊቶች ላይ የፍትህ አካላት ተገቢና ወቅታዊ እርምጃ የማይወስዱ ከሆነ የመቃወምና የማጋለጥ ግዴታ አለበት ክፍል አራት ስለዲሲፕሊን ጥፋት እና እርምጃ አንቀጽ ሃያ ስምንት የዲሲፕሊን ቅጣት እርምጃ ዓላማ የዲስፕሊን ቅጣት ወይም እርምጃ ዓላማ በሥነምግባር የታነፀ ሠራተኛ ለማፍራት ሠራተኛው በፈፀመው የዲሲፕሊን ጥፋት ተፀፅቶ እንዲታረምና ብቁ ሠራተኛ እንዲሆን ለማስቻል ሰራተኛው ከጥፋቱ የማይታረም ሆኖ ሲገኝም ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ለማሰናበት ነው አንቀጽ ሃያ ዘጠኝ የዲሲፕሊን ቅጣት እርምጃ አፈፃፀም ሠራተኞች ለፈፀሙት የሥነምግባር ግድፈት ወይም የዲሲፕሊን ጉድለት በፍብሔር በወንጀል ወይም በሁለቱም ህጎች ተጠያቂነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለደረሰው ጥፋት ወይም የዲሲፒሊን ጉድለት በእዚህ የሥነምግባር መመሪያ መሠረት ተገቢው አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል በዲሲፕሊን ግድፈት የሚወሰነው ቅጣት ማናቸውም ፍቤት የሚሰጠውን ውሣኔ ሳይጠብቅ ሊፈፀም ይችላል አንቀጽ ሰላሳ የዲሲፕሊን ቅጣት ዓይነቶችና አመዳደብ የጉባኤው ጽቤት በዚህ አንቀጽ መሠረት የተወሰነውን የመቀሥ ገንዘብ ከተቀጣው ሠራተኛ ደመወዝ ላይ በተሰጠው ውሣኔ መሠረት እየቀነሰ በየወሩ መጨረሻ ለገንዘብ ሚኒስቴር ገቢ ማድረግ ይኖርበታል ፓ ያለአግባብ የተወሰደ የጉባኤው ጽቤት ንብረት ወይም የተከፈ ንዘብ ተመላሽ ይደረጋል ነ ኣኒ ካኻ ኣ አንቀጽ ሰላሳ አንድ ቀላል የዲሲፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች በእዚህ መመሪያ በክፍል ሦስት አንቀጽ እና እና እና እና የተመለከቱትን ጥፋቶች መፈፀም ቀላል የዲሲፕሊን ቅጣት ያስቀጣል አንቀጽ ሰላሳ ሁለት ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች በዚህ መመሪያ በክፍል ሦስት አንቀጽ የተመለከቱትን ጥፋቶች መፈፀም ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት ያስቀጣል አንቀጽ ሰላሳ ሶስት የጉባኤው ጽቤት ኃላፊ ውሳኔ የዚህ መመሪያ አንቀጽ ስድስት እንደተጠበቀ ሆኖ የጉባኤው ጽቤት ኃላፊ የዲስፕሊን አፈጻጸምና ቅሬታ አቀራረብ ሥነስርዓት ደንብ ቁጥር መሰረት የተሰጠው ሥልጣን ይኖረዋል ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች አንቀጽ ሰላሳ አራት ጥቆማን ስለማሳወቅ በዚህ መመሪያ ውስጥ የተመለከቱ መርሆዎችና አሠራሮችን የሚፃረር የሥነምግባር ጉድለት መፈፀሙን ያወቀ የስራ ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ጉዳዩን ለጽቤት የበላይ ሃላፊ ወይም ለሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ከበድ ያለ ከሆነም ለበላይ አመራር ወይም ለሥነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ጭምር የማሳወቅ ግዴታ አለበት ማንኛውም የሚቀርብ ጥቆማ እውነተኛ ያልተዛባ ከበቀል የፀዳ አሳሳች ያልሆነና ምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል ጥቆማ አቅራቢው ከማንኛውም በቀል የመጠበቅ መብት እንዲሁም ማንነቱ እንዳይገለፅ ከፈለገ በሚስጥር የመያዝ መብት አለው አንቀጽ ሰላሳ አምስት ስለመመሪያው አፈፃፀም የጉባኤው ጽቤት የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ይህንን መመሪያ የማስፈፀም ኃላፊነት ተሰጥቶታል ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች የስነ ምግባር መመሪያውን በእምነት በመቀበል የቃል ኪዳን ሰነድ አድርጎ በመውሰድ በዕለት ተዕለት ስራው ውስጥ እንዲተገበር ማድረግ ይኖርበታል አንቀፅ ሰላሳ ስድስት የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሠራተኛ ወይም ዳይሬክተር ለዚህ መመሪያ አፈፃፀም አስፈሳጊውን ትብብርና ድጋፍ የማድረግ ግዴታ አለበት አንቀጽ ሰላሳ ሰባት ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ህጎች ይህን መመሪያ የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሠራር በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ ጉዳዩች ላይ ተፈፃሚነት የለውም አንቀጽ ሰላሳ ስምንት መመሪያውን ስለማሻሻል ይህ መመሪያ አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት በማናቸውም ጊዜ በጽህፈት ቤቱ አቅራቢነት ሊሻሻል ይችላል አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ ይህ መመሪያ ከ ቀን ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact