Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

የ እምነቴ ፈተና(ደበበ እሸቱ)trial-1.pdf


  • word cloud

የ እምነቴ ፈተና(ደበበ እሸቱ)trial-1.pdf
  • Extraction Summary

አንዳርጋቸው ጽጌ በምርጫ ወቅት የነበረው ሰላም መሰል አካፄድ በምርጫው መሃፃል ላይ በተፈጠረው የኢህአዴግ ወከባና ማስፈራራት ተበላሸ ሕዝቡ በነቂስና በሌሊት ወጥቶ ድምፁን እንደሰጠው ሁሉ ለማስከበርም ዘብ ቢቆም በኢህአዴግ ካድሬዎች በሚካሄደው አጉል ሥነስርአት ያጣ እሥር አፈና ወከባ የተነሳ ያ የተጀመረው መልካም አካፄድ በምርጫ ሽንፈቱ ምክንያት መጥፋቱንና ነጻ ፍትሓዊና ሰላማዊ እንዳልነበረ ዓለም በመላ ሰማው አወቀው ማስረጃውም ይህንኑ አረጋገጠ ወያኔኢህአዴግ ድጋፍ አገኝበታለሁ ያለውም የካርተር ማእከል ገዢው ፓርቲ አሁን በስልጣን ላይ ነውና አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ አይነት ሂደት ሲያከናውን ስብሰባ ያለምንም ችግር በየቦታው ሲጠራ የምረጡኝ ካናቴራውን አስለብሶ በየቤተክርስቲያት ካድሬዎቹን ሲያሰማራየተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅስቀሳ እንዳይደረግ በየመንገዱና መንደሩ ውስጥ በመንግሥት መኪና የተቃዋሚዎችን የኪራይ መኪና በመከተል ሲያደናቅፉ የምረጡኝ ወረቀት የሚለጥፉትን ሲያሳድድ የሚጠይቀው አለመኖሩና እንደልቡ እንከን የለሽ ያለውን እንከን በእንከን ሲያደርግ ውሎ ማታ በመገናኛ ብዙነኑ ኻንከን የለሽ ማለቱ ማንን ለማታለል ነው። እንዲህ አይነቱን ኑሮ ታዲያ ኑሮ ብለን ልንኖርበት የሚገባን ነው።

  • Cosine Similarity

በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ይህን ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት ቀደምት እርምጃቸውን ወስደዋል የኮንግሬሰ አባላትን በማሳወቅ የተለያዩ ፃገራት ፓርላማዎችን በመቅረብና አውነታውን በማስረዳት በውርጭና በሀሩር በመንገድ ላይ ለሰላምና ለነጻነት ሰልፍ በመውጣት ከጉልበተኛ አምባገነናዊ አገዛዝ ታደጉን በማለት ተንቃቅተዋል ጩኸታቸውም ተሰምቷል የተሰማው እሪታና አቤቱታ በከንቱ አልቀረምየአሜሪካ ኮንግሬስ አባላት ጠንካራ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል የአውሮፓ ሕብረት ያስተላለፈው የምርጫ መዛባትና በምርጫ ወቅት የነበረው ሰላም መሰል አካፄድ በምርጫው መሃፃል ላይ በተፈጠረው የኢህአዴግ ወከባና ማስፈራራት ተበላሸ ሕዝቡ በነቂስና በሌሊት ወጥቶ ድምፁን እንደሰጠው ሁሉ ለማስከበርም ዘብ ቢቆም በኢህአዴግ ካድሬዎች በሚካሄደው አጉል ሥነስርአት ያጣ እሥር አፈና ወከባ የተነሳ ያ የተጀመረው መልካም አካፄድ በምርጫ ሽንፈቱ ምክንያት መጥፋቱንና ነጻ ፍትሓዊና ሰላማዊ እንዳልነበረ ዓለም በመላ ሰማው አወቀው ማስረጃውም ይህንኑ አረጋገጠ ወያኔኢህአዴግ ድጋፍ አገኝበታለሁ ያለውም የካርተር ማእከል ገዢው ፓርቲ ከሪፖርቱ መርጦ የሚጠቅም የሚጠቅመውን ብቻ ቢያቀርብም ሙሉ ሪፖርቱ ግን ከአውሮፓ ሕብረት ሪፖርት ያላነሰ እንጂ እንደተባለው አልሆነም የማንም አምባገነንና ሥልጣን ፈላጊ ጠባይ አንድና ተመሳሳይ ነው ሳዳም ሁሴንም ከነዚህ አይነቶች መሪዎች የተለየ አልነበረም ልዩነት ቢኖር በሳዳም ላይ ጦርነት መታወጁና በሌሎቹ ተመሳሳይ እርምጃ አለመወሰዱ ነው እርግጥ ቀናቸው ሲደርስ ጓዛቸውን ጠቅልለው እብስ ብለው ከፃዛገር መጥፋታቸው አይቀርም ገዢው ፓርቲ ልዩ ጦር ፈጥሮአግአዚ ብሎ ስም ሰጥቶ ከሕዝብ በታክስ የሰበሰበውን ገንዘብ ለሕዝብ ማዋከቢያና መግደያነት እያዋለው ነውእነዚህ ታክሶች ቢቆሙ የአግአዚም ገቢ አብሮ ይደርቃል በዚህም አባላቱ አራሳቸውን በማጥፋት ከሕዝብ ጫንቃ ላይ ይነሳሉ ካልተሳሳትኩ በመቶ የሚሆነው የመንግሥት በጀት ከውጭ እርዳታ የሚገኝ ቀሪው ከሕዝብ በሚሰበሰብ ግብርና ታክስ የሚገኝ ነው ከዚህ ውጪ ገዢው መንግሥት በምንም መልኩ አገዛዙን ሊቀጥል አይችልም ገንዘብ እንኳን ቢያትም ዋጋ የሌለው ስለሚሆን እርባና አይኖረውም ብድርም ለማግኘት ተአማኒነትና የፃገር ሰላም ወሳኝ በመሆኑ ማንም ባንክ አንዲህ ያለውን መንግሥት አምኖ አያበድርምውክልና ሳይኖርም ቀረጥ መሰብሰብ አይቻልም አሁን ካለው ሁኔታና ከምርጫው ውጤት አኳያ ኢህአዴግ የሕዝብ ውክልና የለውም የሕዝብ ውክልና የሌለው ኃይል ደግሞ ልግዛ ሥልጣን ወይ ሞት ካለ አግባብነት ያለው ሊሆን አይችልም የሚሆነው ወራሪና ቅኝ ገዢ ነውር ምርጫውን ያሸነፈው የሕዝብ ድምጽና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጦር ኃይል የላቸውም ኃይላቸው የሕዝብ ድምጽ ብቻ ነው አንድ የሕዝብ ድጋፍ ያለው መንግሥት በምንም መልኩ ከሕዝብ የወጣውናና በሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደረውን የደህንነት ሰራዊት መልሶ በሕዝቡ ላይ አያሰልፍም ምክንያቱም ሕዝብ ይወደዋላ። ዕድሜዬን በሙሉ ያሳለፍኩት በቴያትር ሙያ ነውየተራዘመልኝ ጡረታ ተቋርጦ ጡረታዬ አንዲከበርልኝ ማመልከቻ እስካስገባሁበትና ተቀባይነት አግኝቶ ከቴያትር ቤት ቋሚ ሠራተኛነት እራሴን እስካገለልኩ ድረስ ሌላ ሙያም ሌላ ሥራም የተፈጠረ አይመስለኝም ነበር የጡረታዬን መራዘም እንድተው ያደረገኝ ምክንያት ከራሴ ጥቅም ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከሙያዬና ከሃገር ጋር በተገናኘ ጉዳይ በወቅቱ በሥልጣን ላይ ከነበረ የሐገር ፍቅር ኃላፊ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሻአቢያ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት የአርዳታ ማሰባሰብ ተግባር በየአቅጣጫው ይደረግ ነበር በነጋዴዎች ምክር ቤት ያዋቀረውን የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ቢሮ በማደራጀትና በማስተባበር እኔ እንድሠራ የክልል ባህልና ስፖርት ቢሮን ጠይቆ ቢሮውም በመስማማት ለሐገር ፍቅር ደብዳቤ ጽፎ ወደተጠቀሰው ቦታ ሄፄጄ ሥራዬን ቀጠልኩ ኮሚቴው የጉዳዩን አጣዳፊነት በመመልከት ሥራው ቀን ተሌት አእንዲሠራ አዳዲስ የአርዳታ ማሰብሰቢያ ዘዴዎች አንዲቀየሱ በሚል ሥራውን አስረክቦኝ በርካታ እቅዶች ወጥተው በኮሚቴው ከጸደቁ በኋላ በረጂምና በአጭር የሚከናወኑት ተለይተው በአዲስ አበባና በክልልም ሂደቱ ቀጠሰለ በመጀመሪያው አቅድ በኮሚቴው አባላት አማካኝነት በሚዘጋጀው በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የንግዱ ሕብተሰብ አባላት ማለትም በእራት ግብዣ በጨረታ በእንኳን ያደረሳችሁ መግለጫ ከቤት ቤት በመዞር የቃል ኪዳን ሰነድ ማስፈረም በኤግዚቢሽን ማእከል ባዛር ሲዘጋጅ ማስተባበሩን እኔው ነበርኩ የምሠራው በተጓዳኝ ደግሞ ከተገኘው ገንዘብ ላይ አስቸኳይ አርዳታ ለጦሩ ለማድረስ ኮሚቴው ሲያዝዝ ፕሮግራም ማውጣትና ማከናወንም የኔው ነበር በየክልሉም ይህንኑ መሰል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሲኖርም በክልሉ ያለው የንግድ ምክር ቤት ቢሮ እየጠየቀ የአዲስ አበባው የነጋዴው ሕብረተሰብ ኮሚቴ እያዘዘኝ መፄዴ አልቀረም ሥራው በጣም የተዋጣና ግንባር ቀደም የነጋዴው ስኬታማ ተሳትፎ የታየበት ሆነ እኔንም ቀንም ማታም ያሰራኝ ነበር በዚህ ጊዜ ነበር እኔ በድብቅ ከሁለት ቦታ ደመወዝ እንደምበላ ተደርጎ ሪፖርት የቀረበውሪፖርቱ የደረሰውም የነጋዴው ሕብረተሰብ ኮሚቴ በጉዳዩ በጣም በማዘን የሚከፈለው የነዳጅ ወጪ ሆኖ ሳለ ለሚያደርገው አስተዋጽኦ ደመወዝ እንደሚከፈለው ሆኖ የቀረበው ክስ አሉባልታ እንጂ አንድም እውነታ የሌለው መሆት እንዲታወቅ» የሜል ምላሽ ሰጠበትኮሚቴው ይህንን እንዳልሰማ ጥረት ቢያደርግም ሰማሁት የተሰጠውንም መልስ ተረዳሁ መስማቴ እንዳይታወቅ በመጠንቀቅ ለኮሚቴው ወደ ምድብ ቦታዬ እንድመለስ እንዲፈቅድልኝና የሚረከብ ሰው እንዲመድቡልኝ ጠየቅሁ የኮሚቴው አባላት በግንባር ጉዳዩን በማስረዳታቸው ሥራውን ቀጥል» የሚል ትእዛዝ ከባህል ቢሮው ደረሰኝትእዛዙ በቀጥታ ከቢሮው ለኔ መጻፉ የዛገር ፍቅር አለቃዬን አበሳጨው መሰለኝ አንድ ደብዳቤ ጻፈልኝ ደብዳቤው «የእርዳታ ማሰባሰብ በሚል ሰበብ ወደ ክልልና ከሀገርም ውጪ በመሄድ የመስሪያ ቤቱን ሥራ የበደሉ ስለሆነ በአስቸኳይ ወደ ሥራ ገበታዎ እንዲመለሱ» ይላል ደብዳቤው እንደደረሰኝ ክአለቃዬ ቢሮ በመገኘት በጨዋነት ሥራውን እንድቀጥል ከባህል ቢሮው እንደተጻፈልኝና ከአሳቸው የተጻፈው ደብዳቤ አለአግባብ ስለሆነ እንዲነሳልኝ ብጠይቅ አንድ ጊዜ የተጻፈና በፋይል የተቀመጠ ስለሆነ አይነሳም» ተባልኩይህም ማለት ውሳኔው ይጸናል ማለት ነውስለዚህም ለባሕል ቢሮው «ለኔ ሲጻፍ ለመስሪያ ቤቴ ግልባጭ አለመደረጉ አግባብነት የሌለው ነው በሚል የደብዳቤውን ግልባጭ አያይዢፔ ሰቢሮ ዛለፊው አቀረብኩ ለፃገር ፍቅር አለቃዬ ማዘዣ ደርሶት ደብዳቤው ከግል ማሕደሬ የተነሳ መሆኑ ተገልጾ ተጻፈልኝ እኔም ሥራዬን ከነጋዴው ሕብረተሰብ ጋር ቀጠልኩ ከዚሁ ሥራ ጋር በተገናኘ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተዘጋጀው የውጭ ዛገር የኢትዮጵያውያን የአርዳታ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እንድሳተፍ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተጠየቅሁትና ከ ከነጋዴው ሕብረተሰብም በተሰጠኝ ትእዛዝ መሰረት ይህንኑ ኮሚቴው ለቢሮው አሳወቀ ወደ አውሮፓና እስካንዲኔቪያ ሃገሮች አንድ የሙዚቃ ቡድን ይዢ እንድፄድ ተደርጐ የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋቾቹንና ድምጻውያንን ለማካተት በሚደረገው ምርጫ አኔው እንድወስን ሆነ ይህንን በሚገባ አስተካክዬ ቡድኑ ጉዞ አደረገ ይህም የፃገር ፍቅር አለቃዬን አላስደሰተምይህ ሁሉ ከተከናወነና የድሉ ደስታም በኤግዚቢሽን ማእክል ከተከበረ በኋላ ወደ ዛገር ፍቅር ተመልሼ መደበኛ ስራዩን ቀጠልኩ አዲስ አበባ ቢሮ ያለው አንድ የጃፓን እርዳታ ድርጅት አንድ ቀና ዛሳብ ይዞ ደወለልኝና ከፃላፊዎቹ ጋር እንድነጋገር ጠየቀኝማነጋገር ያለብኝ እኔ ሳልሆን የቴያትር ቤቱ ፃዛላፊዎች መሆናቸውን ነግሬ በቀጠሮ ስዎቹን ይዢ አለቃዬ ቢሮ ገባሁ ሰዎቹ ሁለት ፎቅ ያለው ክብ ቤት ለመስራት መወሰናቸውን የምድር ቤቱ ከተቻለ አርቲስቶቹ ለሱቅ ለላውንድሪ ለጸጉር ቤትና ለመሳሰሉት አገልግሎቶች የሚጠቀሙበት ካልሆነም ቴያትር ቤቱ በማከራየት ጥቅም የሚያገኝበት እንደሚሆንሁለተኛው ፎቅ ምግብ ቤትና የቤት ውስጥ ጨዋታ እንደ ኮረንቦላ ኙል የጠረጴዛ ኳስ የሚካሄድበት ሲሆን ሶስተኛው ፎቅ ደሞ በአንድ ጎን ከ እስከ ሰው የሚይዝ አዳራሽና በሌላ በኩል ከፀ እስከ ሰው የሚይዝ መለስተኝ አዳራሽ ሁለት የመለማመጃ ቦታዎች የሚኖሩት የመሥራት እቅድ ስላለን ፎርሙን ሞልታችሁ ለአዲስ አበባ ቢሮ በቶሎ ዓመቱ ሳያልቅ ስጡ በሚል ስምምነት ተለያየን ወደ ፈረንሳይ ፃገር ለስብሰባ ፄጄ ስመለስ በስምምነቱ መሰረት ፎርሙ የተላክ መሆኑን አምጌ እንዳለሁ ከኦሳካ ጃፓን ስልክ ተደወለልኝ ስለ ሚሰራው የቴያትር ቤት ጥሩ ቬና ነው ብዬ ደስ አለኝ ግን አልነበረምራ የደወሉልኝ ጃፓናዊ «ፎርሙ አልደረስሰንም ደጋግመን ጠይቀን አልመጣልንም ምነው። » የሚል ጥያቄ ያነሳሁበትን ሁኔታ አኔው አኔን ታዘብኩህ አልኩና ሰዎች ፍላጎታቸውን በሰው ስም አስታከው መፈጸም ወይም እወደድ ብለው ሊያከናውኑት እንደሚችሉ ተረዳሁ እፒህ ሴትዮ ካጥፊካስወቃሽከራስ ወዳድና ከአልኩ ባይ ካድሬዎች ወገን የሚሰለፉ ናቸው አቶ ጁነዲን የቅንጅት አባል መሆኔን ያውቃሉ በቴሌቪዥን አይተዋል ያም ሆኖ አንዳችም ለውጥ አላየሁባቸውምና ስጋቴ በጣም ቀነሰ ሴትዮዋ ያልተባሉትን «ተባልኩ» ያሉበት ምክንያት እስካሁን ምን እንደሆነ ባላውቀውም በግምት ግን እንዳሰቡት ቢሳካለቸው ኖሮ ለባለስልጣናቱሸ እፄ የተቃዋሚ ድርጅት አባል በመሆኔ ያባረሩኝ መሆኑን በምሽቱ በሚያገኙት አጋጣሚ በመንገር ቆራጥ የማህበር መሪ በሚል ከበሬታ ሊያገኙ አስበው የነበር ይመስለኛል አንዳንድ ትናንሽ ባለስልጣናት ትልቅ የሚባሉት ባለስልጣኖች ፊት ያላሰቡትን በመከወን ለራሳቸው ዝና ለማግኘት ታማኝ ለመባል በሚያደርጉት የራስ ወዳድነት ሂደት በሚመሩት ድርጅት ላይ ምን ያህል ጉዳት እንደሚያደርሱ ይህ አንዱና በጣም ትንሹ ምሳሌ ሆኖ አግኝቼዋለሁ የሕዝባዊ ስብሰባ በይፋ የተጀመረው ምርጫው ጥቂት ወራት ሲቀሩት ቢሆንም ገዢው ፓርቲ ግን በሚያዝዛቸው መገናኛ ብዙዛን በተለያየ ርፅስ ኢህአዴግ ያደረጋቸውን የልማት ውጤቶችን ማስተዋወቅንና ለምርጫው የሚረዱትን ጉዳዮች ሁሉ ለሕዝብ ማቅረቡን በጣም ቀደም ብሎ ነበር የጀመረው በጣም ያስገረመኝ ጉዳይ ገዢው ፓርቲ በመንግሥትነቱ ባአለበት ግዴታ ያደረገውን ሁሉ ኢህአዴግ ልዩ ሕዝባዊ ዛገራዊ እንደፃነ ተደርጐ እንደአስተዋጽኦ አእንዲቆጠርለት ሲያቀርብ የተቃዋሚዎችን ፃገራዊና ሕዝባዊ አስተዋጽኦም በሙሉ በመንጠቅ ነበር ቀደም ብሎ አቶ በረከት ገዢው ፓርቲ እንደሚመረጥ እርግጠኛ በመሆንና በተኩራራ ስሜት ለአንድ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዲህ ነበር ያሉት ምሞማ ፎሮሏሀጓዴ። ለቴሌቪዥን ደብዳቤ ተፅፎ ሲጠየቅ በደቂቃ ብር ተጠየቀየምንፈልገውን ሁሉ በዚህ ዋጋ እንግዛ ብንል በሌለ ገንዘብ የማይቻል ነውና ሊገኝ ከሚችልበት ሁሉበግለሰብ አጅ ያለውን ማጠያየቅ ስንጀምር በርካታ ዶኩሜንቶች ተገኙቋያንን አሰባሰብንአንዳንድ የኢህአዴግ ባለስልጣኖችም በጃቸው የሚገኘውን የቪድዮ ዶኩሜንት በተዘዋዋሪ ላኩልን በዚህ መልክ የተቻለው ሁሉ ተሰባሰበገዢው ፓርቲ የዚህ ሁሉ ችግር የለበትም ቴሌቪዥን ጣቢያው በ ስለሆነ የሚፈልገውን ፊልም ብቻ ሳይሆን ባለሙያና ስቱድዮ ጭምር በነጻ መንግስት በሚከፍለው ዋጋና ደመወዝ እያንደፋደፈ ያሰራቸዋል ሕጋዊው የምረጡኝ ቅስቀሳ በይፋ ሲጀመር ተቃዋሚ ዛይሎች በየቦታው ስብሰባ ሲጠሩ የሕዝቡ ተሳታፊነት ቁጥርፍቅሩተባባሪነቱና ከጎናችሁ ነን ማለቱ እየተጠናከረ መጣ ያ ደሞ ለጊዜው ወያኔ ኢህአዴግን ምንም አልመሰለውም ነበር ጊዜያዊ ፍቅር መጨረሻው የማያምር ነበር የተባለው በሕወሃት መንደር ካድሬዎችና የሕዋፃት ሹማምንት ቁንጮዎቹን ጨምሮ ለበላይ አካላቸው የሚያቀርቡት ዘገባ ብባተጠራው ስብሰባ ሕዝቡ እንዳይሳተፍ ቢሳተፍም የኛ ካድሬዎች ፈታኝ ጥያቄ እንዲያነሱና ተቃዋሚዎቹን መልስ በማሳጣት እንዲዋረዱ አድርገናል የሚል ፃሰትና መሰረት የሌለው ሪፖርት ስለነበር አመራሩ ተዝናንቶና ተዘናግቶ በአርገጥኝነት እንዲቀመጥ አደረገው ከአንዳንድ ስብሰባዎች ናሙናዊ ፅይታ በሥልክ ትምህርት ቤት በተደረገ የመጀመሪያ ሕዘባዊ ስብሰባ ላይ ሕዝብ አንዳይመጣ በቀበሌ የቤት ሥራ ማህበራትና ሌሎችም ስብሰባዎች ቢጠሩም ሕዝብ ግን አሻፈረኝ በማለት ወደ ምኒልክ ትምህርት ቤት ከስብሰባው እጅጉን ቀድሞ ነበር የመጣውበስብሰባው ላይ የተገኙት የወያኔ ካድሬዎች ያነሱት ጥያቄ ለመልስ የቅንጅቱን አመራር ሳያስጨንቅ በቀላሉ በተሰብሳቢው ሕዝብ መልስ እየተሰጠበት ጠያቂችዎን ያጋለጠና ካድሬም አዳራሹን ጥሎ የወጣበት ሁኔታ ነበር የታየው ይህም ለወያኔ ኢህአዴግ አመራር ሲዘገብ ሕዝብ አንዳልተሳተፈና ጥቂት ሰዎች የተገኙበት የማያሳስብ ስብሰባ እንደነበር ሆኖ ነውና አመራሩ ዛሳቡን ጣለ በደብረዘይት በተደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ በቅድሚያ የአዳራሹ ኪራይ ተከፍሎ ለሕዝብ ጥሪ ተደርጎ አኛም በሰአቱ ስንደርስቀድሞን ፄዶ የነበረው ዶብርፃኑ ደብረዘይት ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ከጣቢያው ፃዛላፊ ጋር ይነጋገራል ምክንያቱ አልገባንምና ምን ተፈጠረ። አልፈረድንበትም ዶር ብርፃኑ ችግሩን ለአቶ በረከት በመደወል ቢያሳውቅም አስተዳዳሪው በስልክ ሊገኝ ባለመቻሉ መፍትሔ አልተገኘም በአዳራሹ የተሰበስበው ሕዝብ ያቀረበው አማራጭ ሜዳ ላይ እንሰብሰብ ነበር ያ ደግሞ የተለያየ የራሱ ችግር አለው በቅድሚያ አስተዳዳሪው ከደብረዘይት ከተማ ውጪ ያመጡት የፖሊስ ፃይል ከከተማው ፖሊስ ጋር ግጭት ሊፈጥር ይችላል ይህ ደግሞ አጉል ነውሱ በሌላ በኩል የከተማው አስተዳዳሪ የከለከሉትን የአዳራሽ ስብሰባ በሚያስተዳድሩት የከተማ ሜዳ ላይ ማድረግ አይቻልም ስለዚህም ያለው አማራጭ ሌላ ፕሮግራም መያዝ ብቻ ነው ስለዚህ በቦታው ለተገኙት የመገናኛ ብዙሃን ዘጋቢዎች ሁኔታውን አሳውቀንና እነሱም የሚመለከታቸውን አነጋገረው የዕለቱ ስብሰባ ተሰርዞ ሕዝቡም አኛም ተበሳጭተን ተለያየን ይህ አይነቱ የስብሰባ ክልከላ ሕብረተሰቡን ለምን የሚል ጥያቄ እንዲያነሳጥርጣሬ አእንዲኖረውከወያኔ ኢህአዴግ ጋር እንዲራራቅ አድርጎታል ይልቁንም ለቅንጅት ተጨማሪ ሃይል በማስታወቂያነትም በኩል ቢለካ በጣም ከፍተኛ ትርፍ ያስገኘ ነው ሕብረተሰቡ ለዴሞክራሲያዊ ሥርአት ግንባታ ቆርጦ ከመነሳቱ አኳያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሰፊ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እየፈጠሩ ናቸውተቃዋሚ ድርጅቶች ያሏቸው ድክመቶች እንደተጠበቁ ሆነው በአጭር ጊዜና ባነስተኛ አቅም የፈጠሩት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተይቶ የማይታወቅ ድል ነበርሱ በኔ አመለካከት ለዚህ ድል ደግሞ የወያኔ ኢህአዴግም ያላዋቂ አስተዋፅኦ አለበትፁ ይህን ለማለት ያበቃኝም የደብረዘይቱ ስብሰባ መከልከል ያስከተለውን ሕዝባዊ ስሜት በማየት ነው የረ ዘይት ስብሰባ መከልከል ማታውኑ በሬድዮም በቴሌቪዥንም ቀረበይህንን ያዳመጡት አቶ ጁነዲን ሳዶ ለቅንጅት አመራር ደውለው በሁኔታው ማዘናቸውንና በአስተዳዳሪውም ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ገለጡይህ ይባል እንጂ አስተዳዳሪው ከቢሮው ንቅንቅ አላለም ነበር ማስተዳደሩንም ቀጥሏል ከ ቀናት በኋላ የደብረዘይት ስብሰባ አንደገና ሲጠራ ባለፈው ከመጣው ቁጥር በአጥፍ የጨመረ ሕዝብ ነቅሎ መጣ ቦታም ጠበበ የድምፅ ማጉያ በመጨመር ውጪ ያለውም ሕዝብ እንዲሳተፍ ተደረገ በውይይቱ ላይ የተነሱት ጥያቄዎች የትምሕርት የጤናየመሬት ፖሊሲን የሚመለከቱና ስለሃገር ሉአላዊነት ስለአንድነትስለልማት ነበሩ በየአንዳንዱ ነጥብ ላይ ፖሊሲያችን ላይ በሰፈረው መሰረት ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይት ተደርጎበት ስብሰባው በሚያስደስት ሁኔታ ተፈፀመ የትም ቦታ ቢሆን ካድሬዎች በሕዝቡ መፃል ያሉና ጥሩም ይሁን መጥፎ ተግባራቸውን የሚያከናውኑት በሕዝብ መፃል ሆነው ነውበሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ሲገኙ ሕዝቡ ያውቃቸዋልጥያቄም ጠየቁ አስተያየት ሰጡ ሕብረተሰቡ ከቆሙለት ፓርቲ ጋር ፈርጆ ነው የሚያዳምጣቸውአነሱም ለመናገር ሲነሱ በጥላቻ በንቀትና በማንአለብኝነት ስለሆነ ብዙ ጊዜ ተቀባይነት የላቸውም እፄ ይህን እንደ ወያኔ ኢህአዴግ ድክመት አይቸዋለሁ የሕበረተሰቡን አዝማሚያ ካዩ በኋላ አእንኳን በደብረዘይት ለሚደረግ ስብሰባ ከአዲስ አበባ በናዝሬት ለሚደረግ ስብሰባ ደሞ ከሞጆ በማምጣት ማንነታቸውን ሰውሮ የሚፈለገውን መልእክት እንደ ነጻ ተሳታፊ ግለሰብ ማቅረብ ያስችል ነበር ሌላው ያየሁት ድክመት የትም ይሁን የት የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ቅደም ተከተላቸው እንኳን አይለወጥም ም። ለብዙ ጊዜ ተሞክሮ እሩብ መንገድ እንኳን ሳይራመድ መቋጫው መበተን ይሆን የነበረውን ጉዳይ ፈር ለማስያዝ የሚደረግ ስብሰባ ነው ከእነዚህ ፓርቲዎች መፃል በጣም ለጋ ዕድሜ ያለው ቀስተደመና ቢሆንም በአመራር ላይ ያሉት ሁሉ በተለያየ መልኩ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውና ስር ነቀል ለውጥዴሞክራሲያዊ ስርአትነፃነት ለማምጣት የተዘጋጁ ናቸው በቀስተደመና ያለው አንድ አዲስ አካፄድ በጣም ግልጽና ዴሞክራሲያዊ መሆኑ ነው ለማንኛውም ጉዳይ ዴሞክራሲያዊ ውይይት ዋነኛው መመሪያ ሆኖ ተቀምጧል የቀስተደመና ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት የፓርቲያችን ሊቀመንበር ዶር ብርፃኑ ነጋ ያቀረቡት ፅሁፍ ይህንን በግልጥ ያሳያልና አቀርበዋለሁ ዶር ብርፃኑ ያቀረቡት የመቀናጀት ቅድመ ዘገባ ቀስተ ደመና ኢትዮጵያ በጣም አጭርግን በጣም በሁኔታዎች ያሸበረቀና የጣፈጠ ታሪክ ያለው ለጋ ድርጅት ነው በዚህ በመጀመሪያው ጉባኤው ከሚወስናቸው ጉዳዮች አንዱ የቅንጅቱን ውህደት መሆኑና ይህም የሚያስከተለውን የቀስተ ደመናን መክሰም ከግምት ውስጥ ስናስገባ ሊሰማን የሚገባው ስሜት በእድሜው ማጠር ማዘን ሳይሆን በአጭር እድሜው ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎችና ያስመዘገባቸው ውጤቶች «ለካ በአጭር አድሜ ብዙ ነገር መስራት ይቻላል» ብለን የምንኮራበት ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታና በፓለቲካውም መዘበራረቅ ምክንያት አገሪቱ ሊገጥማት የሚችሉ ችግሮችን በሚመለከት በቅርብ የምንተዋወቅ አንድ ስምንት የምንሆን ሰዎች ተከታታይ የሆኑና አንዳንድ ጊዜ በየሳምንቱ አልመች ሲልም በወር አካባቢሲመች በአንድ ላይ ለምሳ እየተገናኘን ስንወያይ አለበለዚያም በተናጠል ጥቂት ሆነን ስንገናኝ ምናልባት አንድ ሁለት አመት አጥፍተናል እነፒህ ውይይቶች በመሰረቱ የአገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ በመገምገም ላይ ያተኮሩ የሀሳብ መለዋወጦች ሆነው ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል ስብስቡም ወደ ተቀናጀ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያመራል ተብሎ አልተጀመረም በነሂህ ውይይቶች መቋጫ ኢህአዴግ የአገሪቱን ፖለቲካ እያበላሸው እንደሆነበዚህ ከቀጠለአገሪቱ ምናልባትም በቀላሉ ልትወጣው ወደማትችለው ቀውስ የምትገባ መሆኑን በተለይ በአዋሳ በጋምቤላ በቴፒ ወዘተ ያየናቸውና እያደር እየባሱ የሄዱ ግጭቶች አካፄዳቸው አጉል እንደሆነና ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉና ይህንን የሚያበርድ የፖለቲካ ሁኔታ ካልተመቻቸየአገሪቱ አንድነትና የህዝቡም ሰላማዊ ትሮ ክፉኛ ሊናጋ እንደሚችል በትንተና ደረጃ ስምምነት ነበረን ከዚህ በተጨማሪም ለዚህ አጠቃላይ የፖለቲካ ችግር ምክንያቱ ኢህአዴግ የሙጢኝ ብሎ የያዘው ዘርን ከዜግነት የሚያስቀድም ፖለቲካ ወይም በአገሪቱ ያሉትን ባህለዊ ስብስቦች ርህህ ርዕብበህቨቨር በጠንካራ የዜግነት እኩልነት ሀረግ ከማስተሳሰርና ባህላዊ ልዩነቶችን እንደ አገራዊ ውበት ከመመልከት ይልቅ ልዩነቶችን ለመከፋፈያና ለጊዜያዊ ፖለቲካ ጥቅም ማግፒያ መሳሪያ አድርጎ የመጠቀም ጠባብና አደገኛ አካሄድ መሆኑን ተቀበልን ከዚህ ቀጥሎ አሁንም በመርህና በአስተሳሰብ ደረጃ መፍትሄውን በሚመለከት በጥቅሉ ባደረግናቸው ውይይቶች በአገራችን የፖለቲካ ደህንነትና እንደአገር ወደፊት ሊወስደን የሚችለው በዜግነት እኩልነት ላይ የተመሰረተ የባህላዊ ስብስቦችና የጋራ መብቶች ሙሉ ለሙሉ የሚያከብር ብቻ ሳይሆን እንዲበለጽጉ የሚንከባከብ የይስሙላ ሳይሆን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት አና በዚህም ዙሪያ የአገሪቱን ልሂቃን ብሎም አጠቃላይ ህዝቡን አሳምኖ ማሰባሰብ ርዕበ«ኢከ መፍጠር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አመንን ብዙ ጊዜ ፈጅተን የችግሩን አይነቶች ምንጮቹንና መፍትፄ ይሆናሉ ብለን ባልናቸው ሀሳቦች ላይ በአብዛኛው ከተስማማን በኋላ ጉዳዩ የግድ ከወሬ ደረጃ አልፎ ተግባራዊ አርምጃ ወደ መውሰድና በግለሰብ ደረጃ የእያንዳንዳችን ሚና ምን መሆን አለበት ወደሚለው ጉዳይ ውይይት ሲሸጋገር ለአገር በማሰብ ከተነሳ ግን ሌላ ጭብጥ ተግባር ካልነበረው ምሁራዊ ውይይት ምናልባትም ተግባር ውስጥ ሊገባ የሚችል እንቅስቃሴ ሊሆን አንደሚችል ፍንጮች መታየት ሲጀምሩ ለዚህ ተግባራዊ አንቅስቃሴ ዝግጁ ያልነበሩት ከውይይቶቹ ቀስ አያሉ መቅረት ይጀምራሉ በውይይቱ ዙሪያ የተሰባሰብነው ሰዎች ይህንን ጥያቄ ያነሳነው በዙሪያ ጥምጥም ሳይሆን በቀጥታ ነበር። የሚሉት ጉዳዩች ነበሩ በአነኝህ ጉዳዩች ላይ ረዘም ያሉና አንዳንድ ጊዜ ግማሸ ምሽቶችን የሚወስዱ ጥልቅ ውይይቶች አድርገናል የውይይታችንን አጠቃላይ ጠገግ የሚወስነው መጪውን የግንቦት ምርጫ በሚመለከት የነበረን አጠቃላይ ስምምነት ነበር ይህም ግንቦት ምርጫ ከዚህ በፊት የነበሩት አይነት ምርጫዎች ሊሆን አይችልም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በሰውና በንቃት ተሳትፈው አሁን ያለውን የኢህአዴግ ፍፁም የፖለቲካ ሞኖፓል ሙሉ ለሙሉ እንኳን መስበር ባይቻል በጣም በጣም ሊያዳክሙት ይገባል ይህ እንዲሆን ደግሞ በተቃዋሚው ጎራ ያሉትንና በዋና ዋና መሰረታዊ መስመሮች ላይ ቢያንስ በፕሮግራም ደረጃ ብዙ ልዩነት የሌላቸው ኃይሎች በቅንጅት የሚሰሩበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ለዚህም ማድረግ ከሚገባን ነገሮች አንዱ የአነፒህን የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ፕሮግራሞች በዝርዝር ማጥናት በፕሮግራም ደረጃ ብዙ ተቀራራቢ የሆኑት እስከአሁን አብሮ ለመስራት ያልቻሉበትን ምክንያት ማጥናትና ማወቅ ያስፈልገናል በሚል ጊዜያችንን ወስደን እነፒህን ፕሮግራሞችና በተግባር ደግሞ በጋራ አብሮ ለመስራት እንቅፋት የሆኑትን ምክንያቶች በዝርዝር ተመልክተናል እነሺሂህን ጉዳዮች በሚመለከት የደረስንበት ድምዳሜ በአጭሩ በእርግጥ ብዙዎቹ በተለይ ሕብረ ብሔራዊ የሆኑት ድርጅቶች ለመዋሀድ ከደረሱ በኋላ በፕሮግራም ላይ ባልተመሰረቱ ልዩነቶች ውህደታቸውን ማሳካት እንዳልቻሉ ከዚህ በፊት ተቃዋሚች በጋራ ለመስራት ችግር የሆነባቸው በአብዛኛው በውስጥ አሰራራቸው በአመራሮቻቸው አካባቢ ባሉ የግለሰብ ሰብዕና ልዩነቶች በአገሪቱ የወደፊት የፖለቲካ ሂደትና የትግል አካሄዴ ላይ ግልፅነት ማጣት እያንዳንዳቸው ድርጅቶች ከምስረታ ታሪካቸው ጋር የተያያዙ የውስጥ ድርጅት ባህሎችና ከዚህም የተነሳ አዳዲስ አሰራሮችንና ለውጦችን ለመቀበል ክፍት ፈቃደኝነት አለመናር ወዘተ መሆናቸውን ነው ይህም ማለት በእነፒህ ከመርህ መለስ ያሉ ልዩነቶች ላይ ስልታዊ አካሄድ ከተካፄደ ብዙዎቹን ድርጅቶች ማቀራረብና በተለይ ለምርጫው በጋራ እንዲሰሩ ማድረግ ይቻላል የሚል ግንዛቤ ላይ ነው የተደረሰው አዚህ ላይ በተለይ ጥንቃቄ ሊወሰድበት የሚገባ ተብሎ የታመነበት በሕብረ ብሔራዊና በብሔር ላይ በተመሰረቱ ድርጅቶች መሐክል ከአጠቃላይ የዴሞክራሲ ሥርዓት ምስረታ አንፃር ተባብሮ መስራት አስፈላጊነቱ ላይ ክርክር ባይኖርም እንደነዚህ አይነት ድርጅቶችን መፍጠር ከተቻለ እነፒህን ሁለቱን አለመቀላቀል የተሻለ አማራጭ አእንደሚሆን በአኛ በኩል መገፋት ያለበት አቋም ነው በቅንጅት ደረጃ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ክፍት የሆኑ ድርጅቶች ቢቀናጁ በብሔር ላይ የተመሰረቱ ድርጅቶች ጋር ግን በስልት ደረጃ አብሮ መስራት ቢሞከር ይሻላል የሚለው ነውፎ በሌላ በኩል በድርጅቶች ደረጃ አብሮ ለመስራት እስካአሁን ችግር ከፈጠሩት ጉዳዮች አንዱ የፖለቲካው ሂደት በምርጫው ላይ ያተኮረ እንደመሆኑ የሚፈጠሩ የድርጅት ቅንጅቶች በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱና ሕጋዊ አውቅና ያላቸው ብቻ መሆን አለባቸው የሚለው ሁለተኛው መርህ ነው ከአገር ውጭ ባሉና በሕጋዊ መንገድ በተናጠል ወይንም ተቀናጅተው እንዲታገሉ ሁኔታው መመቻቸት አለበት ለዚህ ምርጫ የሚቀናጁ ድርጅቶች ባገር ውስጥ ያሉና በምርጫው የሚሳተፉ ቢሆኑ የሚመረጥ ነው እንግዲህ በእነሂፒህ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ አቋም ከተወሰደ በኋላ ከላይ ከ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ነው ውይይቱ የቀጠለው በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ተቁ በተቀመጠው ማለትም ያሉትን መቀላቀል ከአንዱ ጋር በግልጽ መወገንን ስሚያስከትል በዚህም ምክንያት ድርጅቶችን ለማቀራረብ የሚደረገውን ሙከራ ሊያደናቅፍ እንደሚችልከዚያም በላይ ግን የራስን ድርጅት መመስረት ቢያንስ እኛ የምናምንባቸውን መሰረታዊ እምነቶቻችንን በሚቀናጀው ድርጅት መፍጠር ትክክለኛ መሆኑንነገር ግን ዋና እንቅስቃሴያችን የድርጅቱን መመስረት እውን ማድረግ ተቀዳሚ ተግባራችን መሆን እንዳለበት አምነንበታል የራሳችንን ድርጅት ለመፍጠር ከተስማማን በኋላ የሚቀጥለው ተግባር የድርጅቱን መለስተኛ ፕሮግራም ማዘጋጀት ሌሎች ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች መቅረብና እንዲቀላቀሉን መጠየቅ ቀጣይ እርምጃዎቻችን ነበሩ በዚህም መሰረት ቀደም ብለን ካደረግናቸው ዝርዝር ውይይቶች በመነሳት አጠቃላይ ርፅዮተ ዓለማችን ማሀበራዊ ዴሞክራሲ ር ሀበባዕርየርሃነ አንደሚሆን ይህንን አጠቃላይ ርዕዮተ ዓለም ግን በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በመተርጎምና ከዚህ ጋር በተጣጣመ መልኩ በተቻለ መጠን በአጭሩአሁን ያለውን የቀስተ ደመና ፕሮግራም መጻፍ ይህም ሲሆን በተቻለ መጠን በጣም በቀላሉና ለሁሉም በሚገባ መልኩ ግን ደግሞ በቋንቋ አጠቃቀም ደረጃ የተምታታ ትርጓሜ እንዳይሰጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ መሥራት አንዳንዴም ብዙዎቻችን ካለን የአካዳሚ ልምድ የተነሳ ጸጉር ስንጠቃ እስከሚመስል ድረስ ተፋጭተን አሁን የቀስተ ደመና ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ የሆነውን ሰነድ አዘጋጀን ከዚያ በኋላ የነበረው ከባዱ ተግባራዊ ስራ ስለነበር በአንድ በኩል ከኛ በተጨማሪ ሰዎችን ማፈላለግ በእውነቱ እኛም የማናውቅበት አታካች ሥራ ነበር በሌላ በኩል ግን የድርጅቱን መሰረት ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብሮ ከመስራት ጋር አያይዘነው ስለነበር እኛ ባሰብነው መሠረት ቅንጅት ሊፈጥሩ ይችላሉ ያልናቸውን ድርጅቶች አመራሮች አንድ በአንድ ማነጋገርና እነሱን ማሳመን ነበረብን በአውነት ለመናገር ይህንን ስራ ስንጀምር በጣም የፈራነው ግን በጣም ቀላል ሆኖ ያገኘው ሥራ ይህ ነበር በመጀመሪያ ጊዜውም ሊሆን ይችላል ያናገርናቸው ድርጅቶች በሀሳቡ ላይ ምንም ማንገራገር አላሳዩም በአንድ በኩል የአኛን ወደ ፖለቲካው መድረክ መምጣት ብዘሥች በደስታ ነበር የተቀበሉት ይህ ሁሉ ሲሆን ፕሮግራሙን በመቅረጽ የጠፋው ጊዜና የነበረው ዝርዝር ክርክር እንዲህ ቀላል አልነበረም ርዑ ዐጠዕዌርሸፎጋርሃ የሚለውን የተስማማንበትን የእንግሊዝኛ ቃል በአማርኛ ለመተርጎም በተለይም ማህበረሰባዊ ፍትህ ወይንስ ማሕበራዊ ፍትህ በሚል ያጠፋነው ጊዜ እንኳን በፍፁም ቀላል አልነበረም የመኢአድ ልምድና ቆራጥነት እስከ ወረዳና ምክትል ወረዳ በየመንደሩ በከተማም በክልልም ዘልቆ መግባቱየኢዴአፓ መድህን ረጂም ልምድ የኢዴሊ የወጣቶች ፃዛይልና ጥንካሬ በአንድነት ተቀናጅቶ ታላቅ ፖለቲካዊ ለውጥ በማምጣት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ መከራውን ከሚያበላው ችጋር እንደሚያላቅቀው ምንም ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው ያም ሆኖ ከታሰበበት ግብ ለመድረስ ረጂም ውጣ ውረድ ብዙ መሰናክል ቁጥር የበዛበት አሰጥ አገባ እንደሚኖር ከጅምሩ ይታወቅ ስለነበርአንዱ ሲግል አንዱ ሲያበርድ ደሞ ሲጠም ማቃናት ደህና መንገድ በማስያዝ በኩል እድሜ ከልምድ የሰጣቸውና በለጋ ፅድሜ ወደ ትግል ገብተው የበሰሉት ተሰብሳቢዎች እንደሚሆን እንደሚሆን እያደረጉት ወደ መግባባቱ ለጥቆ ወደመተማመኑ አልፎም ወደ ስምምነት እየተደረሰ መጣ የስብሰባው ዓላማ በአንድ ተሰባስቦ ለመቀናጀትና የፃሳብ የተግባር የፖለቲካ የኢኮኖሚ የአባላት ጉልበት ለማግኘት ነውቅንጅችን ለመፍጠርነ በተናጠል ለገዢው ፓርቲ ኢላማነት ከመጋለጥ በቅንጅት ተጠናክሮ መፈርጠም ጠቃሚነቱ ታምኖበት ተግባራዊ ለማድረግ ነውይህ ደግሞ በአንድ ጀምበር ተጀምሮ የሚዘጋ ሂደት ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ ክርክር የሚያስነሳ ጉዳይ ነውስልጣንን ያሳጣልደረጃን ዝቅ ያደርጋልስነስርአት የተጠናከረ ይሆናል ተጠያቂነት ያለበት ቢሆንም የበለጠ ይጠነክራልግለሰቦች እኔ የሚሉት ይጠፋልየያንዳንዱ ፓርቲ አመራር ቦታውን ይለቃል በተናጠል ይቀርና በድምር ይሆናልታዲያ ይህ ፅድገትና ጥንካሬ ቢሆንም ከግለሰቦች አመለካከት የተነሳ ችግር አለውግን በጥቅሙ ለፃሃገርና ለወገን ተብሎ ስለሆነ ግልን በመተው በተናጠል ወደ ቅንጅት በመለወጥሁሉንም ለሃገርና ለሕዝብ በሚል ቅድሚያውን በማድረግ ሁሉም ለቅንጅት መፈጠር ቆሙ የሚል ነበር ሪፖርቱ ስለዚህ ሁኔታና እንቅስቃሴ የሰሙ ሁሉ ገሚሱ ያድርገው ሲል ሌላው አይይ የማይሆን ነገር። ለዚህ መች ታደሉናዕድሜ የሌለው ቅንጅት ነው ከኛ ጋር ካላቸው ልዩነት ይበልጥ የርስ በርሳቸው አለመግባባት ይበታትናቸዋልና ከቁምነገር አታስገቡት» ነበር የተባለው ለዚህም የተሰጠው የዕድሜ ገደብ ቢበዛ ስድስት ወራት ነበር እንዲያውም በሙጫ የተጣበቀ ቅንደት ነው ተብሎም ለመዘባበቻነት ውሎ ነበርሳይሆን ቀረ እንጂ የተወሰነለት የስድስት ወር ጊዜም አለፈ የቅንጅቱ መሰረትም ሙጫ መሆኑ ቀረና ድርጅቶቹን በይበልጥ በማጠናከር የሕዝቡ እየሆነ መጣመንገዶች ሁሉ ወደ ቅንጅት ቢሮወሬው ሁሉ ቅንጅት መሆን ጀመረ ገዢው ፓርቲና የምርጫ ሥልቱ ምላሽ ኢህአዴግ በምንም መልኩ ይህን ምርጫ እሸነፋለሁ የሚል ሃሳብም ግምትም አልነበረውምይህ ማንአለብኝነት የተፈጠረው ደሞ የሕዝብ ፍቅር አለኝ ብሎ ከማመን የመነጨ ሳይሆን ገዢው ፓርቲ ለምርጫው በማለት ያለ የሌለውን ገንዘብ አንጠፍጥፎ ባሰራው ካናቴራና በረጨው ገንዘብ በካድሬዎቹ ቅስቀሳ በየቀበሌ ባሉት አባሎቹ በመተማመን ነበር በዚህ መስል የምርጫ ወቅት አስቀድሞ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ግን ተዘንግቷል ብዬ አስባለሁ ምርጫን ለማሸነፍ በቅድሚያ የሕዝብን ልብ ማሸነፍ ያስፈልጋልየሕዝብን ልብ ለማሸነፍ ደግሞ ታማኝ ሆኖ መገኘትን ይጠይቃልለሕዝብ ታማኝ ለመሆን ደሞ ለሃገር ተቆርቋሪነትን የሕዝብ ወገናዊነትን ማረጋገጥ ይጠይቃልእርግጥ ቅንጅትም ይህን ሁሉ የሚያሟላ መሆኑ ገና ያልተፈተነበት ጉዳይ ነው ወያኔኢህአዴግ ደሞ ባለፉት ዓመታት የግዛት ዘመኑ በነዚህ ነጥቦች ላይ ከሕዝብ ጋር አልተግባባምሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህን ከግንዛቤ በማስገባት ነበር ወደ ቅስቀሳው መግባት ያለባቸው ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓላማቸውን ለማሳወቅ እንቅስቃሴ ጀመሩፁየቅስቀሳው ሂደት ልዩነት ነበረውየገዢው መንግሥት ቅስቀሳውን የሚያካሂደው በመንግስት የሥራ ሰአት ሰራተኛውን በልዩ ልዩ ዘዴ በመሰብሰብ አጀንዳው ለየት ባለ መልኩ ተቀርጾ ሥራን በተመለከተ ይጀመርና አንደኛው አጀንዳ በዚህ መልኩ ተጠናቆ ድንገት ወደ ምርጫ በመግባት ኢህአዴግን መምረጥ ማለት የሥራ ማረጋገጫ የደምወዝ አድገት የስራ አጡ ወደ ስራ መግባት እንደሆነ ተደርጎ ሠራተኛው ምንም ለመናገር እድል ሳያገኝ የስብሰባው መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ብቻ በሚሰጡት ዛፃሳብ ላይ ተከናውኖ ኢህአዴግን ለመምረጣችሁ መተማመኛ ማሉልን ፈርሙልን በሚል ሰራተኛው ሕዝብ የቁም ስቅሉን የሚያይበት ነበርይህ ሁኔታ ደሞ ለቅንጅት ወዲያው ያውም በአብዛኛው ጊዜ ስብሰባው ሳይበተን ስለሚደርስ ለቅስቀሳችን ጥሩ መሳሪያ ሆኗል ጥንቃቄም እንድናደርግና ለተዘረጋው ዕቅድ ማፍረሻ እንድናዘጋጅ አልፎም ለሕብረተሰቡ በስፋት በማሳወቅ ከዚህ ስህተትና አደጋ እንዲጠነቀቅ ምቹ ሆኗል በሌላ ጎኑ ደሞ በቅድሚያ ምልክት የተደረገበት የንቦችን መምረጫ በማዘጋጀት ይህን ካርድ ይዛችሁ በመግባት ከምርጫ ጣቢያ የሚሰጣችሁን በመተው ይህን በኮሮጆው አስገብታችሁ የቀበሌውን መልሳችሁ ስታመጡልን ከ ብር ይከፈላችኋል ተብለውም የምርጫ ካርድ የተሰጣቸው ነበሩ ለዚህም መራጩ ሕዝብ የወሰደው አቋም ወደ ምርጫ ጣቢያ በሚሄድበት ወቅት በር ላይ ያለው ጠባቂ የግድ እንዲፈትሸውና የተሰጠው የምርጫ ካርድ እንዲታይና እንዲወሰድ ማድረግ ነበርና በዚህም ኢህአዴግን ቀጥተው ቅንጅትን መርጠው እንደወጡ ፍተሻ ላይ ተያዘብን ብለው ለሰጣቸው አካል ያመሰከቱ ዘዴኞች ነበሩ የገዢው ፓርቲ ወጣቱን ለመያዝና እንዲመርጠው ለማድረግ ከተጠቀመበት ዘዴ አንዱበማህበር ያደራጃቸውን ወጣቶች በመሰብሰብ ኢህአዴግን ካልመረጣችሁ ድርጅታችሁ ይፈርሳል ሕናንተም አሰብን ለማስመለስ በሚደረግ አላስፈላጊ ጦርነት ውስጥ ትገባላችሁ የሚል ነበር ይህን የማደናገርያ ወጣቱ በዘዴ አከሸፈው ይህ አካድ መታቀዱና በአንዳንድ ኣካባቢ ተግባራዊ የመደረጉ ማስረጃ እንደደረሰን ቅንጅት የወጣቱን ድርጅት የሚያፈርስ ሳይሆን በበለጠ ተጠናክሮ የሚንቀሳቀስበትን መንገድ የሚያመቻች መሆኑንወደ ጦርነትም እንደማይዘምትና ቅንጅት እንቅስቃሴው ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ላይ እንደተመሰረተ ወጣቱ በሁሉም መንግሥታት ዘመን የሚታሰረው የሚሰቃየው የሕብረተሰብ አካል ሆኖ መኖሩንና ቅንጅት ግን መብቱን ጠብቆ እድገቱን እያስተካከለ አምራች ዜጋነቱን በማረጋገጥ ለነገ ፃዛገር ተረካቢነት ያዘጋጀዋል እንጂ እንደሚባለው አለመሆኑን በፕሮግራሙ አስተላለፈ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለመያዝ የተጣለው ዘዴ ደግሞ ከያንዳንዱ ትምህርት ቤት አባላት የሚገኙበት ተወካይ በተማሪዎች እንዲመረጥበምርጫውም ወቅት የአዲስ አበባ ወጣቶች ማሕበር አባላት እንዲሆኑ በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ተማሪዎችን በትምህርት ሥርአቱ ላይ ለማነጋገር እንደሚፈልጉ ተነግሮ ስብሰባው ላይ እንዲገኙ ተባለ በተጨማሪም የኢህአዴግ አባላትና ታማኝ መምህራን ከተለያዩ ቀበሌዎች የወጣት ማሕበር አባሎችን ተሳታፊ በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጥቂት ጊዜ ስለትምህርት ፖሊሲው መሻሻል እንዲናገሩና ወዲያው በተቀየሰው ዘዴ ስለኢህአዴግ እንዲያነሱና ወጣቱ ከኢህአዴግ ጎን እንዲቆም በማግባባት ድጋፋቸውን ማግኘት ነበር እቅዱ በየትምሕርት ቤቱ የተወካዮች ምርጫ ተከናውኖ በፕሮግራሙ መሰረት ሁሉም ወደ ስብሰባው ቦታ ፄዱ። እንደ አማራጭ የቀረበውም«እንግዲያው በፊርማና ማህተም የጋበዛችሁትን ሕዝብ ወጥታችሁ ይቅርታ ጠይቁትና ይመለስ» ቢባሉም ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ይህን ለማድረግ አልፈቀደምየገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ደሞ ቅንጅት ርካሽ ጭብጨባ ፍለጋ ነው ይህን ሰበብ ያመጣው አሉ ቅንጅት ደሞ «አኛ ለሕዝብ ከበሬታ ቅድሚያ እአንሰጣለን ከ በላይ የሆነ ተጋባዥ አትገባም ተብሎ ታግዶ አኛ ፕሮግራሙን መካፈል ማለት የሕዝብ ንቀት ነውና አናደርገውም» በማለት የቅንጅት አባላት ጥለው ወጡ የገዢው ፓርቲ በዚያ ፕሮግራም ላይ እንደማንኛ ውም ፓርቲ ተጋብዞ ተሳታፊ ሆኖ ሳለመመርያ የመስጠትም የአዛዥነትም ስልጣን ሊኖረው አይገባም ነበር ነገሩ ከጅምሩ አንስቶ የተገላቢጦሽ ነበር በክርክሩ ላይ ማን አንዴት መቅረብ እንዳለበት መመሪያ ይሰጥ ነበር ፈላጭ ቆራጭነትም ይቃጣዋል አንዳንድ ጊዜ አንዲያውም ሌሎቻችሁ ዝም ብላችሁ አኔ ብቻ ላውራ ወደ ማለቱም ይዳዳቸዋል የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህን ሁሉ ችለው ነው በድል አድራጊነት የተወጡት ቅንጅት ለሕዝብ ያለውን ከበሬታ አሳይቶና ያንን አቋም ይዞ ከወጣ በኋቷላ ያ የማዘዝ ሱስ ያለበት ወያኔኢህአዴግ አሁንም በማያገባው ገብቶ ቅንጅት ሕዝቡን ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል ካልሆነ በውይይቱ ላይ መገኘት የለበትም የሚል ሆነ አቋሙኔ ምን አገባው። በዚህ በመጨረሻው የሁለት ሰአት ተምናምን ፕሮግራም ላይ ብርፃዛኑና ልደቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ ያለበትን ዕውነታ ሁሉ አዝረከረኩት የወያኔ ኢህአዴግ የንግድ ድርጅቶች አንዲት ብናኝ ጥቅም በማያገኘው የትግራይ ሕዝብ ስም እየነገዱባቸው እንደሆነ ገዢው ፓርቲ ምን ያህል ገበሬውን አንዳደኸየው የንግዱን ሕብረተሰብ አስሮ መንቀሳቀሻ እንዳሳጣው የትምህርቱን የጤናውን በአጠቃላይ ሁሉንም የኢህአዴግ ፖሊሲ ልክ አሳዩትና ወያኔን ባዶ አስቀሩት ሌላ ድል ለቅንጅት ተመዘገበ ኢህአዴግ አካፄዱ ሁሉ እያንሸራተተ ሊጥለው መሆኑን በመገንዘብ ቅንጅትን ጭራቅ አድርጎ ለማቅረብ በልዩ ዘዴ መንቀሳቀሱን አጠናከረለዚህ አንድ ማሰሪያ እንደሚያስፈልገው በማቀድ ቅንጅት በሬዲዮም በቴሌቪዥንም ባለው የምፅዋት ሰአት እውነቱን አጋለጠ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ። ቢሉም በርካታ የሆኑት ግን ይህን አባባል ከምንም ሳይቆጥሩ ጥያቄ አነሱ «ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ይህ ስብሰባ ከምርጫው ቀን ቀደም ብሎ መደረጉ ያለዎትን የእምነት ፍቅር ያሳያል ሆኖም ግን እርስዎ ቀደም ሲል በሰጡት መግለጫ ይህ ምርጫ እንከን የለሽ ነውማንም ማንንም ሊወቅስ የማይችልበት ዴሞክራሲያዊና ነፃ ይሆናል ብለው ለኢትዮጵያም ለዓለምም ሕዝብ የገቡትን ቃል ተቃዋሚዎች እንዳያበላሹትና ተወቃሽ እንዳያደርጉዎት ተቃዋሚዎችም ተገኝተው ውይይቱን በአንድነት ብናደርግ መልካም ይሆናል በእግዚአብሔርም ፊት አያስጠይቅም» በሚል ሀሳብ ቀረበና አብላጫው ተሰብሳቢ ደገፈውነፁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላሰቡት ሁኔታ ስለገጠማቸው «ፃሳቡ ጥሩ ነው ግን ሰፊ ጊዜ ይዘን ሌላ ጊዜ እንነጋገርበታለን በማለት ስብሰባውንም በክብር የጠሯቸውንም አባቶች ረግጠው ወጡ ይህ እቅድ እንደከሸፈ የጦር አቅጣጫው የዞረው ወደ ሴቶች በተለይም በዕድሜ ወደገፉና አቅመ ደካማ ወደሆኑ ሴቶች ነበርአቀራረቡ ለየት ባለና የነዚህን ሴቶች ድክመት አንደመጠቀሚያ ያደረገ ነበር አንዱ መንገድ በየመንደሩ ማህበር በሚጠጣበት በመገኘት ፅዋ በመሳለምና አማኝ በመምሰል ጠበል ቀምሰው አብረው በመቀመጥበድንገት ዓየሩን በመለወጥና ስለምርጫው በማንሳት ገዢውን ፓርቲ እንዲመርጡ በማግባባትና ለማሕበሩም መደገፊያ እንዲሆን ከ እስክ ብር ድጎማ መስጠት ነው ሌላው በየመንደሩ የቡና ሰአትን በመጠበቅ ሳይጋበዙ እየደረሱ «ስለምትወዱን አቦል ላይ ደርሰናል» በማለት ተቀምጠው በዚያው በተለመደ መንገድ ድንገት የቡና ጠጪ ውን ወሬ ወደ ምርጫ በመለወጥ ኢህአዴግን ምረጡ በማለት ለቡና መግዣ ከ አስከ ብር በመቸር ከመንድር መንደር መዘዋወር ነበር በሁለቱም ቅስቀሳ ላይ አንድም ገንዘቡን አልቀበልም ያለ ባለመኖሩ ምድረ ካድሬ ኢህአዴግን እንደሚመረጥ በይበልጥ አረጋግጫለሁ የሚል ሪፖርት ለበላይ አካላት በሙሉ ልብ አስተላለፈ እነዚህ ድጎማ ተቀባዮች ግን ካድሬዎቹ እንደወጡ ሲሳሳቁበት የነበረው «ብሬን በጄ ካርዱን በሆዴይለያል ጉዱ ምርጫ ሲሄዱ» በሚለው ማሳረጊያ ነው ሁሉም ገብቷቸው ነበር ባለፉት «የምርጫ» ወቅቶችም ይሁን አሁንም ስለምርጫ ያለው ግንዛቤ አንዱ ፓርቲ ሌላውን ለማሸነፍና የሕዝብን ድጋፍ በአመቺው መንገድ ለማግኘ ት መጣርና አንዱ ከሌላው ጋር እንደጠላት መተያየትን ነውቅንጅት ይህን አመለካክት ለመለወጥና ሕብረተሰቡም ዘወትር የፖለተካዊ ስብሰባ በሚደረግበት ወቅት በሚደረጉ ንግግሮች አንዱ ፓርቲ ሌላውን መንቀፍና ድክመቱ ላይ ማተኮር የራስን ከፍ ከፍ የሌላውን ድምጥማጡን ማጥፋት ሳይሆን በአውነት ላይ የተመረኮዘ የሰለጠነና ዘመናዊ አካፄድ ለሕብረተሰቡ ማሳየትና ግንዛቤውንም ዘመኑ ወደሚፈቅደው ሰላማዊና የሰለጠነ ሂደት ለማምጣት ጥረት እያደረገ ነው ይህንንም በመገናኛ ብዙፃን ላይ ሲያቀርብ በነበረው የቅስቀሳና የክርክር መድረኮች በትንሹም ቢሆን ለማሳየት ሞክሯል ቅንጅት ይህን ምርጫ ገዢው ፓርቲ እንዳለው ነፃና ዴሞክራሲያዊ ይሆናል የሚል ትንሽም እምነት ባይኖረውም ያም ሆነ ይህ ይህን የምርጫ ወቅት ማወደስ አለብን ሕዝቡን ለምርጫው ማዘጋጀት ተገቢ ነው በማለት «ለዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ እንዘምር» በሚል መርህ ለሚያዝያ በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማዘጋጀት አቀደ ይሁንና አደባባዩ በኤግዚቢሽን ማአከል ስር ነው እዚያ ጠይቁ ተብሎ ሲጠየቅ ተይዛጻል ተባለ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ደግሞ ተይዚኳል ማለት የሚቻለው ሲከፈልበት ነው አስካሁን የከፈለ ስለሌለ አሁን መጥታችሁ ብትከፍሉ ልትይዙት ትችላላችሁ ስላሉ ቅንጅቱ ወዲያው ክፍያውን በመፈጸም ቀኑን ያዘው ይህን ሕዝባዊ ስብሰባ ለዴሞክራሲ ደስታ እንፍጠር እንደሰት በሚል ርአስ ሥር ብናካሂደው ምን ይመስልሃል» አለኝ ዶር ብርፃኑ ሃሳቡን ተቀበልኩትና « ምንም አይነት የፖለቲካ ስብሰባ ስሜት ሳይፈጠር ዝም ብሎ ምርጫው ዴሞክራሲን ሰብአዊ መብትን በአጠቃላይ ነጻነትን በአውነተኛ ገጽታው ለሕዝብ የሚሰጥ ምርጫ እንዲሆን የምንመኝበት ይሁን ተባብለን ተስማማን ብርፃኑ ፃሳቡን ለሥራ አስፈጻሚ በማቅረብ አጸደቀና ያው እንግዲህ ተፈቅዳል አስፈላጊውን በማስተካከል አዲስ ባህል እናሳይ» ብሎ ፃለፊነቱን ጫነብኝ በነገራችን ላይ ዶር ብርፃኑ የምርጫ ዘመቻ ኃላፊ ነበር ደግነቱ የሚያስፈልገውን ኮሚቴ ሁሉ አዋቅሮ ስለነበር የኔ ድርሻ ያ በአግባቡ መከናወኑን መከታተል ነበር የሙዚቃ ባንድ ያስፈልጋል መድረክ ያስፈልጋል የድምጽ ማጉያ ያስፈልጋል አለቱ ተወስኖ ለሕብረተሰቡ ጥሪ ማድረግ ያስፈልጋል ለመብራት ሓይል ማሳወቅ ያስፈልጋል ለፖሊስ ማሳወቅ ያስፈልጋል ብዙ ያስፈልጋሎች ነበሩ ለሁሉም የሚያስፈልገው በጽሁፍ ደረሰ ሕዝቡ ገና ስለሁኔታው ሲሰማ ወሬው ሁሉ አሱ ሆነ ቀኑ ተያን በሚዲያ ሚያዝያ ፀ የሕዝባዊ ስብሰባ ጥሪ ገ ይህን የሰማው ኢህአዴግ የቅንጅትን ሰልፍ ለማክሸፍ በሚል አቅድ ሕዝቡን ለሚያዝያ ሰልፍ ጠራ የተጠራውም ሰልፍ በፍቃደኝነት ውጣ ሳይሆን ነጋዴው ሱቁን ዘግቶ አንዲወጣ ካልወጣ የንግድ ፈቃዱ እንደሚነጠቅ የመንግሥት ሰራተኛው ሰልፍ እንዲወጣና ቁጥጥርም በሰልፉ ቦታ እንደሚደረግ ለመመላለሻ አውቶቡስና ሊዎንቺና አንደሚዘጋጅ ወጣቱን ሰልፍ ካልወጣህ አደገኛ ቦዘኔ ብለን እናስገባሃለን በሚል የአዲስ አበባ የወጣቶች ማህበር አባላቱን ካናቴራ አልብሶ እንዲያወጣየሴቶች ማሕበርም እንዲሁ ሆነና ከአዲስ አበባ እስከ ኑ ድ ማዓ ት ጐ። የሚለው ፃሳብ ወዘወዘኝ አዲስ አበባ ገብተን ብርፃኑ ቤት ስንደርስ የሰልፉ ሪፖርት በቴሌቪዥን ይታያል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደስታ ራሳቸውን ስተዋል የታዘዙትና ግዴታ የተጣለባቸው ሰልፈኞች ሳያምኑበት ስለወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር «ይህን ማዕበል የሆነ ድጋፍ ማንም ምንም ሊያደርገው አይችልም» ነበር ንግግራቸው እውነትም ብዙ ሰው ነበር በግዴታም በቀን ወጪም በማስፈራራትም የወጣ ቤቴ ገብቼ ስለሁኔታው ከባለቤቴ ጋር ስንነጋገር ባለቤቴ «ምንም አታስብ ማስታወቂያውን መንግሥት ሰርቶላችኋል ሕዝቡ በግዴታ ነው የወጣው ያንን ብድር ለመመለስ ነገ ተነቅሎ ይወጣል» አለችኝ ሁልጊዜ ግምቷ ልክ ስለሆነ አመንኳትነ ግን ቢደክመኝም እንቅልፍ አልወሰደኝም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ ስለቀኑ ውሎ ባለስልጣናት አስተያየት ይሰጣሉ አቶ ሕላዊ ዮሴፍ በቢሯቸው ውስጥ ሕዝቡ ለኢህአዴግ ስላለው ፍቅርና ስለወጣው ሕዝብ ብዛት በደስታ ፈንድቀው ነው የሚናገሩት እንደአባባላቸው ነገ በቅንጅት ሰልፍ ላይ ፀም ሰው አይገኝም የንግግራቸው ጥንካሬ አሳሰበኝ እንደፈርዖን ጦር የወያኔ ድጋፍ ሰልፍ በቅንጅት ሱናሚ ተዋጠ ሚያዝያ አይነጋ የለም ነጋ ከቤቴ ሁለት ሰአት ላይ ወጣሁ ወደ ቢሮ ቢሮ አካባቢ ብዙ ሰው አለ ካናቴራ እንግዛ ባንዲራ ስጡን መፈክር እንያዝ የሚል እኛ ደግሞ ካናቴራ የለንምና እንደደረስኩ ያገኘ ሁት መፍትሔ የምርጫ ምልክታችንን ጣት በፎቶ ኮፒ አባዝቶ ማደል ነበር ሕዝቡ ደግሞ በቡድን አንዳንድ ስጡንና እናባዛዋለን በሚል ቀና ትብብር አፋጠነልን በሰአት ከፀ መስቀል አደባባይ ስደርስ ሕዝቡ መግባት ጀምሯል ይደረግ እንደነበረው የመስቀል አደባባይ ለትራፊክ አልተዘጋምየቀይ መስቀል በዓልም ነበርና ሲያልቅ መብራቱ ጠፋመብራት ፃይል ለመደወልና ትራፊክ ለማዘጋት ወዲያ ወዲህ ስል ሆነ አደባባዩ ሞልቶ መንገዱን ያለትራፊክ ትፅዛዝ የሕዝብ ናዳ ዘጋው ትላንት ጎርፍ የተባለው ወደ ጅረትነት ተለውጦ የዛሬው ሰልፍ የሱናሚ ማዕበል ሆነያውም ስነስርአት የሞላው መብራቶች እንዳይሰበሩ ስርአት እንዳይጣስ ሕዝቡ እርስ በርሱ ኮሚቴ ፈጥሮ ተደላድሏል ተሰላፊም ጠባቂም ሆኗል መስቀል አደባባይ ስንቱን ሕዝባዊ ስብሰባ በኩራት ያላስተናገደውን ያህል ዛሬ ምጥ ያዘው ጠጠር መጣያ ጠፋ ሰአቱ ሰአት ነው ገና ስብሰባው ለ ሰአት ነው የተጠራው ቦታው ከአሁኑ ሞልቷል ለጥበቃ የተመደቡት የፖሊስ አባላት የሕዝቡን ስነ ስርአት ጠባቂነት ሲያዩ ዘወር አሉ ሕዝቡ አንደጎርፍ ገና መንገድ ላይ ነው ሰልፉ ሜክሲኮ ቆሟልባምቢስ ከትሟል ከቦሌ አቅጣጫ የሚመጣው ከሳይ ኬክ ቤት ማለፍ አልቻለም ከደብረዘይት መንገድ የተመመው ገቢዎች ሚኒስቴርን አላለፈም መንገዱ ሁሉ ሕዝብ ነው ከሱሉልታ የነቀለው ከ በላይ ፈረሰኛ አዲስ አበባ መግቢያ ላይ በካድሬዎች እንዳይገባ ታግዶ ቆሟል የዩኣቨርሊቲ ተማሪዎች በጉጉት ሲጠብቁትና የሕዝብ አካል መሆናቸውንና ኢህአዴግ የኔ ናቸው በማለት የነዛው የፃሰት ፕሮፓጋንዳ የፈጠራ ወሬ መሆኑን ለራሱ ለኢህአዴግም የሚያረጋግጡበት ስለነበር ዝግጅታቸውን ጨርሰው መንገድ ሲጀምሩ ከግቢው እንዳይወጡ በሆድ አዳሪዎችና አሾክሻኪዎች በጆሮ ጠቢ ካድሬ ተማሪዎች ጥቆማ ወድሮ ይጠብቅ በነበረ የስለላ ቡድን ታገዱ ተማሪዎቹ ቆራጥ ናቸውና ለዓላማቸው በመቆም የልቀቁን ክርክራቸውን ትግል ቀጠሉ ሁኔታው አላምር ያላቸው የስለላ ቡድን አባላት ጉዳዩን ለበላዮቻቸው በማስረዳት የልቀቁ ትፅዛዝ በመሰጠቱ በትግላቸው አግዱን አስነስተው አራሳቸው ያዘጋጁትን የቅንጅት ደጋፊዎች የአዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች» የሚል ቅስት ይዘው ከዩኒቨርሲቲ አስከ መስቀል አደባባይ ሆ አያሉ በሕዝብ ታጅበው ወደ አደባባዩ ሲገቡ ያጋጠማቸውን የጉልበተኛነት እገዳ ሕዝቡ ሰምቶ ስለነበር የጀግና አቀባበል አደረገላቸውእውነትም ቆራጥ የሕዝብ ወገኖች። ና ኬ ውጪ ሄዶ እንዲታከም ፃኪሞች ቢነግሩትም ይህን ሳላይና ምርጫ ሳልመርጥ ንቅንቅ አልልም አሻፈረኝ ብሎ ነበር የቆየው የምርጫው እለት የዘኪምም ትእዛዝ ጥሶ የቤተሰብ ምክርም አምቢ ብሎ የጓደኞቹን ልመናም አልሰማም ብሎ አንዲት ድምፅ ብዙ ዋጋ አላት በሚል ቁርጠኝነት እውነትም ሰልፉ ፈውስ አስገኘለት መሰል በሌሊት ፄዶ መርጦ እፎይ አለ የቅንጅት አመራር አባላት ያንተ ደህንነት ነው አንጂ የሚጠቅመን በመታመምና ከዚያም ላለፈ ሁኔታ መዳረግ ይጎዳናል እባክህ ሂድና ታከም ብለው ቢማጸኑትም አልሰማም ብሎ አምቢ አለ አሁን ድምጽም ሰጠ ሰልፉንም አየ ውጤቱንም አወቀና ለመሄድ ተዘጋጀ የቅንጅቱ አመራር አባላት በደህና ጤናውን ይዞ እንዲመለስ ተመኙለት ድጋፉ ብዙ ነውና ብዙ ዕድሜ ይስጠው እያልን ነው ኬ ያደረግኸው ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነውና አንመካብፃለን አልነው ሕዝብ ያላንዳች ተፅአኖና ግዴታ ባመነበትና በቆመለትየኔ ብሎ በተቀበለው የነገና የዘላቂ ሕይወቱ ነፃነት ሰብአዊና የዴሞክራሲያዊ መብቱ ማረጋገጫ ቀን ብሎ ያን በመሰለ በሰከነ አካፄድ የሰለጠነ ስነ ስርአትበኢህአዴግ ካምፕ በማይታወቅ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትማንነቱንና ምንነቱን አሳየለዓለም ሕዝብ አስመሰከረ ኢህአዴግ ምንም ይበል ምንም ስለ ቁጥሩም ያሻውን ቁጥር ይጥቀስ ይህ ሕዝባዊ ስብሰባ ግን የያ ኙን ሰልፍ እንደፈርዖን ሠራዊት የዋጠ የቅንጅት አመራሮች ቅስቀሳ በወጡበትና ከሕዝብ ጋር ባደረጉዋቸው ስብሰባዎች ሁሉ ሕዝቡን ሲሉት የነበረው ኢህአዴግ ገንዘቡን ሲሰጣችሁ የናንተው ነውና ተቀበሉት በምርጫው ወቅት ግን ካርዳችሁን የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ ለማን እንደምትሰጡ አስቡ ይበጀናል የተሻለ አስተዳደር ያሰፍናል ቃሉን ቢያጥፍ ውረድ እንለዋለን የምትሉትን ፓርቲ ምረጡ እኛን ብቻ ምረጡ አንልም ካመናችሁበት ኢህአዴግንም ቢሆን በነጻ ያለፍርሃት ከሆነ ምረጡትበፍርፃት ግን ማንኛውንም ፓርቲ አትምረጡ ሲሉ ስለነበር ሕዝቡ አመዛዝኖ ሁኔታውን ከህልውናው ጋር መክሮበት የሚበጀውን ለመምረጥ ወሰነ በምርጫው ቀን ደሞ በዚያች ቅንጅት ከስከድ ሚሳይል የበለጠ ዛሣይል አላት በሚላት የምርጫ ካርድ ሊቀጣው ተዘጋጅቶ ቀኑን በጉጉት መጠባበቅ ያዘዝ የፓርቲናየመንግሥትመገናኛ ብዙሃን አበው ሲተርቱ «ቀበጡን ጅብ በላት መዝጊያዋን አውሳ» ወይም «የቀበጡ ፅለት ሞት አይገኝም» ይላሉ ለወያኔ ኢህአዴግ ሲስተካከል ግን «አይቀብጡ ቅብጠት ለመዘረር በቅንጅት» ተብሏል ቅንጅት የመገናኛ ብዙፃንን በሚገባ ለመጠቀም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በቴሌቪዥን በተሰጠን ደቂቃ በሬዲዮም ላለን ደቂቃ ዕቅድ አውጥተን ተያያዝነው ኢህአዴግ ሚዲያው በጁ ነውዋልታ ሪፖርት ይሰራልፋና ሙሉ ጊዝውን መድቧልአዲስ ዘመንና ፄራልድም ገፆቻቸውን አዘጋጅተዋል እኛም ያለችንን የምጽዋት ሰአት ይዘናል ወያኔ ኢህአዴግ የመገናኛ ብዙፃን ቅስቀሳውን ሲጀምር በክስ ግለሰቦችን በመጥቀስ የስም ማጥፋት ዘመቻ በማካፄድ ነበር መነሻ ያደረገው ሕዝቡ ይሰማዋል እንጂ ከቁጥር አላስገባውም የሚባለው ሁሉ አልጥምህ ያለው ገና ከጅምሩ ነው እኛና ሕዝቡ ደሞ በጣሙን ተግባብተናል ከአኛ ምን እንደሚጠበቅ አውቀናል የሚፈልገውን ብቻ ሳይሆን የሕዝቡን ሰቆቃና ችግርብሶቱን በሚገባ አጢነን ነበር ያመቻቸንለት አንዱን ለምሳሌ ያህል እንመልከት በየክልሉ ለወያፄ ኢህአዴግ ባላቸው ታማኝነትና ትዕዛዝ ተቀባይነት የአመራሩን ቦታ የያዙት የወያኔ ኢህአዴግ ካድሬዎች ከላይ ከአለቆቻቸው በወረደላቸው መመሪያ መሰረት እንከን የሌለው ተብሎ ቃል የተገባለትን ምርጫ በተለመደው የወያኔ በሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳ በቅንጅታችን ላይ ዘመቻ ለማካፄድ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል አንድ ቀን በደሴ ከተማ በከንቲባው ፅቤት በተካፄደው ስብሰባ በቅንጅቱ ላይ መጥፎ ፕሮፓጋንዳ የሚያናፍሱ ታማኞች ተሰብስበው መመሪያ እንደተሰጣቸውና የመንቀሳቀሻ በጀትም ከሕዝብ ከተሰበሰበው ገንዘብ አንደተመደበላቸው በስብሰባው ከነበሩ ደጋፊያችን ተነግሮናል በዚያው ጊዜ በድሬዳዋ ካውንስል መሰብሰቢያ አዳራሽ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናትና የቀበሌ ሹማምንት ተመሳሳይ የሆነ ስብሰባ አካሂደው የሚከተለው ውሳኔ ተላልፏል የትኩረት አቅጣጫዎች ለወጣትና ለሴቶች ማሕበራት ቁጠባና ብድር ለወሰዱ ሰዎችና አዲስ ለሚሰጣቸው ለሃይማኖት መሪዎች ለችግረኞች ድጎማ መስጠት ለመምህራንና ለምድር ባቡር ሠራኞችና መሪዎች ለድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኛ ማሕበር መሪዎች በተለይ ያኮረፉ ሰዎች ማለትም የቀድሞው መንግሥት ሠራተኞች በሚኖሩባቸውና በብዛት በሚገኙባቸው ቀበሌዎች ፀፀ ዐ ፀ ዐ በካቢኔ አባላት አማካይነት ጭምር ቅስቀሳ ማድረግቡ በፀ ሳቢያን ከሥራ የተባረሩ የቀድሞ ጦር አባላት ያሉበት ስለሆነ ጥንቃቄ የተሞላበት የፖለቲካ ሥራ መሥራት ከመፃከላቸውም «ተመልምለን የምንጠብቅ የቅንጅት ወታደሮች ነን የሚሉ መመልመልና ለፕሮፓጋንዳ ሥራ መጠቀም በፀዐ የምድር ባቡር ሠራተኞች ያሉበት ስለሆነ ችግራቸው እንደሚፈታ በመግለፅ ከፍተኛ የፖለቲካ ስራ መስራት በ ከዚራ የቅንጅት አባሎችና ደጋፊዎቻቸው በስፋት የሚንቀሳቀሱበት ስለሆነ የደህንነት ሄፃሃይሎች ጥብቅ ክትትል እንዲያደርጉባቸው የየፃልማቱም ሆነ የቁጠባና ብድር አሁን መጀመሩ የሕብረተሰቡን ችግር የሚፈታ አይደለም የምረጡኝ ዘመቻ መደለያ ነው በማለት የቅንጅት አባሎች ደጋፊ ለማሰባሰብ ቤት ለቤት የቅስቀሳ ሥራውን ተያይዘውታል እኛን በእርግጥ ቀድመውናል ይህን ለመምታትም ከፍተኛ ሥራ ያስፈልጋል ለዚህ አንዱ መሳሪያ ቅንጅት ለውድድር ያቀረበው ሰው ጡረታ የወጣ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ማጥላላት ነው የድሬዳዋ ተማሪዎች ድጋፋቸውን ለቅንጅት እየሰጡ እንደሆን ታይቷል ስለዚህ ተማሪዎችን ለመያዝ አስተማሪዎችን በመሰብሰብ የቅንጅት አቅጣጫ ጥሩ እንዳልሆነ በማሳመን በጥብቅ መንገር ነው በአጠቃላይ ድሬዳዋ የሚገኘው የመንግሥት ሰራተኛ ደመወዝ ከመንግስት እየበላ ልቡን ለቅንጅት ያደረገበት ጉዳይ የሚያሳስብ ነውና መፈተሸ አለበት ጎበዝ። በመጨረሻው ከምንም በላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ቅንጅት ቢያሸንፍ ለእኛ ለአመራሮች ከፍተኛ ችግር መሆኑ ነው ቅንጅት ሲያሸንፍ የራሱን አባሎችና ደጋፊዎችን በኛ ቦታ ስለሚያስቀምጥ አሁን የምናገኘውን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ከየትም አናመጣውም ስለዚህ ለራሳችን ህልውና መታገል አለብን ለገጠር ቀበሌዎች ስኳር ስንዴ በግ ማሰራጨቱ ይቀጥል የአድር ማሕበራት ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስመዘግቡ ተማሪዎች ኢህአዴግን ከመረጡ የስኮላርሽፕ አድል የሚሰጥ መሆኑን መንገርና ማሳመን ፎርም ማስሞላት የስንዴ አርዳታ የቅስቀሳ መጠቀሚያችን ይሁኑ የሚሉ ናችው ይህ የቅስቀሳ ዘመቻ ከ ጀምሮ በካድሬዎ ችና በድርጅቱ አባላት ከ ጀምሮ ተመሳሳይ ስብሰባ በሐረር በጅጅጋና በሂርና እንዲካሄድ ተወስኖ ስብሰባው ተጠናቋል ይህ ነው እንክን የለሽ ይሆናል ተብሎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቃል የተገባው የምርጫ ሂደት ወያኔ ኢህአዴግን የሚመሩት ግለሰቦችና በከፍተኛ የመንግስት ስልጣን በፃላፊነት ደረጃ ያስቀመጧቸው ጀሌዎቻቸው ሺህ ጊዜ ቢፍጨረጨሩ ቅንጅቱ በዝርዝር ያስቀመጣቸውን አማራጭ ፖሊሲዎች በጥልቀትና በብቃት መመከት የሚችል አማራጭ ፖሊሲ ማቅረብ አንደማይቸሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልፅ ሆነ ፖሊሲዎቻችንም በከተማውና በገጠሩ ሕዝብ ድጋፍ እያገኙ ሲመጡ ቅንጅት አማራጭ የለውም በማለት ብዙ የቀባጠረው ወያኔኢህአዴግ ማጣፊያው አጠረበት ፖሊሲን በፖሊሲ አሸንፎ ሕዝብ ፊት ተቀባይነት አግኝቶ በምርጫ ውድድር እንደማያሸንፍ ሲያውቀው አራሱ ተሸብሮ ሕዝብን ማሸበር ዋነኛው ዓላማ አድርጎ መንቀሳቀስ ጀምሯል ቅንጅት ስለወታደሩ በሃገራችን ውስጥ የሕዝብ ደም በከንቱ የፈሰሰባቸው የሰቆቃ ታሪኮች በፊልም መረጃ ተቀርፀው በማስታወቂያ ሚኒስቴር እጅ የሌሉ ይመስል ሩዋንዳ ድረስ ተጉዞ በየመንገዱ የወደቀ የሰው አሬሳ ክምር እያሳየ ተቃዋሚዎች ቢያሸንፉ ይህ ነው የሚጠብቃችሁ እያለ ተሸብሮ ሊያሸብረን ጣረ የወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት በቴሌቪዥን እየደጋገመ የሚያሳየንን የሩዋንዳን እልቂት የፈፀሙት ስልጣናችሁን አካፍሉ የሚል ፈተና የገጠማቸው የመንግሥት ባለስልጣናት ናቸው በሚያዙት የጦር ሃይልና በዘረኛ ቅስቀሳ ተነሳስተው ምንም መከላከያ በሌላቸው ንፁሣን የፃገሪቱ ዜጎች ላይ የዘመቱት እነዚህ የመንግሥት ባለስልጣናት ናቸው ወያኔ ኢህአዴግ ህዝብን ማሸበር እንኳን ቢፈልግ ለምን እንዲህ ዓይነቱን የሽብር ፕሮፓጋንዳ እንደሚያሰራጭ ለእኛ ለሃገሬው ህዝቦች ብቻ ሳይሆን ለውጭ ታዛቢዎችም ግራ አጋቢ ስልጣኔን ከተፈታተናችሁ የሩዋንዳ አረመኔ ገዢዎች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ አንደዘመቱትአዘምትባችኋለሁየሚል ካልሆነሌላ ምን ትርጉም ይኖረዋል። ጠንካራ ተቃዋሚ የለም ሲባል የነበረው አሁን ደሞ ተለውጦ ጥሩ ተቃዋሚ የለም ማለት ተይዛል ጠንካራው ሲመጣ ጥሩ የማይሆንበትሕዝብን ወክሎ የሕዝብ ወገን ሆኖ የሕዝብን ምሬትና ሰቆቃ ለማስወገድ በመንቀሳቀሱና አቋመ ጠንካራ አይበገሬ በመሆኑ ነው ጥሩ የማይሆንበትም በኢህአዴግ አምሳል ተቀርፆ በስመ ተቃዋሚ ዝም ብሎ የሚንቀሳቀስና አቋሙ የኢህአዴግ ዓላማው የኢህአዴግ ሁለንተናው ኢህአዴጋዊ አለመሆኑ ነው በሃይማኖት ውስጥ መንግሥት አይገባም የሚለውን የሚያፈርሰው ደሞ ባለፈው ዕሁድ የሙስሊሙን ሕብረተሰብ አባላት የትንሳኤ እለት በስብሰባ ማዕክል የጥሪው ወረቀት እንዳይለይ በሚል የቁጥጥር መሳሪያ ስብሰባ ተጠርተው ኢህአዴግን ምረጡ የሚል ተማፅኖና ምክር ሲሰጥ ነበር ሌላው እንከን የለሸ ሂደት ጠቅላላው የአዲስ አበባ ነዋሪ በቀበሌዎች አስገዳጅ ጥሪ እንዲወጣና ተቃዋሚዎችን እንዲቃወም መመሪያና ትዕዛዝ በመስጠት «ባትወጣ ወየውልህ እየተባለ ጥሪ ተደርጎለት በማያምንበት እንዲወጣ እየታመስ ነው ይህም እንከን የለሽ የተባለው ምርጫ ሂደት ነው አቃቂ ቁጥራቸው ከ የማያንሱ የጋሪ ባለንብረቶችና አሸከርካሪዎችም በሐሙሱ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጡ ባይወጡ እያንዳንዱ የ ብር መቀጫ እንደሚጣልበት ማስጠንቀቂያ ደርሶታል ደሞ ሌላው እንከን የለሽ ሂደት ደርግ የሕዝብ ድጋፍ ኖሮት አያውቅም። ይህን ሁሉ ሕዝቡ ያያል ይታዘባል በየክልሉ ያሉት የገዢው ፓርቲ ተሹዋሚዎች ሕዝቡን የግድያለፍላጎቱና በማያምንበት ሁፄታ ተቃወም ካልተቃወምክ መከራህን ትበላለህ ነጋዴው የንግድ ፈቃድህን ሠራተኛው ሥራህን ሥራ የሌለውና ጡረታ ላይ ያለው ኑሮህን ወጣቱ በቦዘኔ ስም ነፃነትህን እየተባለ ሁሉም በየፈርጁ የማስፈራርያው ናዳ እየወረደበት ነው ይፄም የእንከን የለሽ አንዱ ገፅታ ነው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫውን እንንክን የለሽ በሆነ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት ተብሎ ለሕዝብ የተገባውን ቃል በማመን ለምርጫ ቢዘጋጁም ገዢው ፓርቲ የሚደርስባቸው እንከን በእንክን የሆነ ሂደት ተሰላችተውና ተመርረው ከምርጫው አራሳቸውን ያገላሉ በሚል እምነት ጫና ቢያበዛባቸውም እነሱ ግን የሕዝብን ድጋፍ አበረታችና ቆራጥ አቋም ጋሻና መከታቸው አድርገው ዘመቻውን በጀመሩት በሰለጠነው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት ቀጥለውበታል ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ከጎኑ በቆራጥነት የተሰለፉትን ኢትዮጵያውያን ሁሉ በቀረበላቸው ድጎማ ሳይሸነፉ ገንዘቡን በኪሳቸው ምርጫውን በሆዳቸው የያዙትን የሚደርስባቸውን መከራ ችለው ለቅንጅት ድል አድራጊነት በተለያየ የቅስቀሳ ሥራ ላይ የተባበሩትን ቅንጅት ሥራ ነውቅንጅት ፍቅር ነው ቅንጅት አንድነት ነው ቅንጅት ኢትዮጵያዊነት ነው በማለት የሚዘምሩትን የነገ ተተኪዎች ላደረጉለት ድጋፍና ትብብር ከልብ እያመሰገነ እንከኑን ሁሉ ችሎ ለድል አንደሚበቃና ለዚህም ብርታቱና ጥንካሬው ላለፉት ዓመታት ግፍና መከራ የተጫነበት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ እምነቱ ጠንካራ ነው ገዢው መንግሥት ያልገባውና ያልተረዳው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቻይ ቢሆንምበቃኝ ሲል ደሞ ለውሳኔው ጠንካራነት ማረጋገጫው ለማድረግ የወሰነውን እንደማይቀለብስና በውሳኔው ጸንቶ እንደሚቆም ነው ለ ዓመታት መከራና ስቃዩን ውጣ ውረዱን ተሸክመን አብረን ኖረን ሰብአዊነታችን ሲረገጥ ከዛሬ ነገ ይሻል ይሆናል በሚል ተስፋ በደርግ ስርአት ሲጨፍርብን የነበረውን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ይለወጥ ይሆናል በሚል ቀቢጸ ተስፋ ስንናፍቅእርስ በርስ የመናቆርን አባዜ ይቅር ስንል ሰሚ ማጣትን በስህተት እንኳን ለኢትዮጵያ ማሰብ ይጀመር ስንል ሁሉ ችለን ኖርን አሁን ግን መሸከም ሲያቅተን ሌላ አማራጭ ያስፈልገናል በማለት የተነሳንና የቆረጠን ሕዝብየነፃነትን ጣዕም በመጠኑም ቢሆን የቀመሰን ሕዝብ ወደ ነበረበት መልሶ በሰለቸው መንገድ መግዛት አይቻልም ገዢው ፓርቲ ወያኔኢህአዴግ ደግሞ ደጋግሞ ማስፈራሪያ አድርጎ ሊጠቀምበት በስሙ የሚነግደው በኢትዮጵያ የመከላከያ ዛይላችን በፖሊስ ሰራዊታችን በደህንነት ተቋማችን ነው እነሱ ደሞ በህገመንግሥቱ ላይ በግልፅ በሰፈረው መሰረት ሕብረብሔራዊ ሆነው ሃገርና ሕዝብን ለመጠበቅ ተቋቋሙ እንጂ ግለሰብን ወይም አንድ ድርጅትን ዘለዓለማዊ ገዢ አድርገው ሊያስቀምጡ አለመቋቋማቸውን የማያውቁት ይመስል በስማቸው መጠቀም አግባብነት የለውም ቅንጅት ተቋማቱ ለምን አንደቆሙ ለማወቃቸውና የሕዝብን ውሳኔም ተግባራዊ ለማድረግ ምርጫውንም ነፃዛ ፍትፃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የገቡትን ቃል እንደሚጠብቁ ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለውም ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የመከላከያ የፖሊስና የደህንነት ተቋማትን በሚመለከት በማኒፌስቶው ላይ በግልፅ ያስቀመጠው ማኒፌስቶ ገጽ ይህ ነው ትክክለኛው አሠራር ይህንንም ምርጫ እንከን የለሸ ለማድረግ ገዢው ፓርቲ ሊከተለው የሚገባ አካፄድ ይህ መሆን አለበት ሕዝባዊ ስብሰባዎች አዲስ አበባ የመጀመርያው ስብሰባ በአዲስ አበባ የተካሄደው በብሔራዊ ሉተሪ አዳራሽ ውስጥ ነበር ተሰብሳቢው ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ሃይማኖቶች የተውጣጡ አባላት የተሳተፉበት ነበር ለቅንጅት ደሞ ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ፃገር መሆኗ ውበታችን ድምቀታችን የአንድነታችን ሣይል የሉአላዊነታችን ማረጋገጫ ነውና ይህንኑ በተሻለ መንግሥታዊ አስተዳደር እናስተካክለው ለማለት የቅንጅትን ዓላማ ለማወቅ የመጣ ነው የቀስተደመናም አርማ ይህንኑ ያመለክታል በዕለቱ ስብሰባውን በመዛል ወንበርነት የመራሁት እኔ ስለ ነበርኩ የመጀመርያውን ምሬት የሞላበትን ንግግር አቀረብኩ «መኖር ለምን አስፈለገን።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact