Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ይህ ከሆነማ አባባሉ ከእሱ በላይ ስለእሱ አውቃለሁ ማለትም ትክክለኛ ዕውቀት አይሆንም ፍጥረተ ዓለምና ምሥጢረ ተፈጥሮ ሥነ ፍጥረትን ክሥተት ያህል የማያስደንቅ ተአምራዊ ኑሮ ነው ከሚከተለው ጥቅስ ስለፈጣሪው ሠራዒ መጋቢነት እንዲፈጸም ከመደረጉ በቀር የተቀነሰ ወይም የተጨመረ ነገረ ሃይማኖት ትምህርታችን ይህ ምሥጢር ትንሣኤ ሙታን ይባላል ሰው ከፈረሰና ከበሰበሰ በኋላ ይነሣል ስንል እንዲያው በማናውቀው አይደለም። እኛ ግን ፈጣሪያችን ክርስቶስ በሞቱ ሞትን ድል አድርጐ ስለተነሣ ስለ ትንሣኤ የምንሰጠው ትምህርት እውነተኛ ነው የሃይማኖታችንም ቀኖና ፍጻሜው «የሙታንን ትንሣኤ እንጠባበቃለን» የሜል ነው ክርስቲያኖች የሥጋን ሞት እንዳይፈሩ ታዘዋል ነገር ግን ነፍስና ሥጋ በትንሣኤ ከተዋሓዱ በኋላ የሚመጣውን ሁለተኛውን ሞት ፍሩ ተብለዋል ይህ ሞት የመጨረሻው ነው «የሙታን ትንሣኤ በትርጓሜ ቤት ዘይቤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ተብሎ ሲጠራ የጻድቃንና የኃጥአን ትንሣኤ ደግሞ ትንሣኤ ዘለክብር እና ትንሣኤ ዘለኅሳር በመባል ይታወቃል «ያንጊዜ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ይህ የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ ሞት ድል በመነሣት ይዋጣል መቃብርም እንዲሁ» ኢሳ ዳን ሆሴ ቆሮ ከዚህም ጋር ቤተ ክርስቲያን «መድኃኒቴ» ብላ የምትጠራውና የምታመልከው ክርስቶስ ወይም መሚሕ እርሱ ነው።
ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት ክፍል በየሰንበት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስተማሪያ የተዘጋጀ መስከረም ዓም ርእስ መግቢያ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት መግቢያ የክርስትና እምነት መሠረተ ትምህርት ምሥጢረ ኩነት አምላካዊ ፍጥረተ ዓለምና የፈጣሪ ሠራዒ መጋቢነት የሰው ልጅ ተፈጥሮና ኑሮው ተስፋ ድኅነት ድኅነት ምሥጢረ ድኅነት ምክንያተ ድኅነት ድኅነት በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ የእምነትና የአምልኮ ቀኖና አፈጻጸም በብሉይና በሐዲስ ኪዳን አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስትና እምነት የተከፈለ መሥዋዕትነት በዘመነ ሐዋርያት በዘመነ ሰማዕታት በዘመነ ሊቃውንት ነገረ ማርያምና ነገረ ቅዱሳን ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ጥምቀት ምሥጢረ ሜሮን ምሥጢረ ቁርባን ምሥጢረ ክህነት ምሥጢረ ንስሐ ምሥጢረ ቀንዲል ምሥጢረ ተክሊል የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት ዘመነ መናፍቃን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን አተካከልና አሠራር ሥርዓተ ጥምቀት ሥርዓተ ሜሮን ሥርዓተ ቁርባን ሥርዓተ ንስሐ ሥርዓተ ክህነት ሥርዓተ ተክሊል የስብከት ዘዴ ለሰባኪው የሚያስፈልገው የስብከት ዓይነቶች ስብከት የሚሰጥባቸው ቦታዎች ለተለያዩ ምእመናን የሚሰጡ ስብከቶች ስብከትና ፖለቲካ ስብከትና ኦርቶዶክሳዊ ጠባዩ በዕድሜ ደረጃ ከፋፍሎ ማስተማር በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምሳክ አሜን መግቢያ ለመንፈሳዊም ሆነ ለሥጋዊው ጥበብ መጻሕፍት ከፍ ያለ ድርሻ ያበረክታሉ ሰዎች ከበጎው የሚተባበሩበትን ከክፉው የሚርቁበትን የዕለት ተግቦራቸውን የሚያከናውኑበትን ምሥጢር ይገልጣሉ ያስረዳሉራ በመሆኑም አንዳንድ የነገረ ሃይማኖት ሊቃውንት መጻሕፍትን «መንገድ አመልካቾች» በማለት ይጠሯቸዋል የጥንት አባቶቻችንም ይህን በመረዳት መንፈሳዊና ሥጋዊ ጥበብ የሚያስጨብጡ መጻሕፍትን በብዙ ድካም ብራና ፍቀውቀለም በጥብጠው ጽፈው አቆይተውልናል ይህም አባቶቻችን ከእግዚአብሔር ያገኙትን ሃይማኖት ጥበብ እንድንይዝ አድርጎናል ቅደስት ቤተ ክርስቲያናችንንም የመጻሕፍት ማኅደር ለመሆን አስችሏታል መጽሐፍ ማዘጋጀት ብዙ ድካምና ውጣ ውረድ ያለበት ቢሆንም «በቃል ያለ ይረሳል በመጽሐፍ ያለ ይወረሳል» እንዲሉ ሊቃውንት በጉባኤያቸው ያስተማሩት ትምርት ሳይጠፋ ሳይቆነጸል ለልጆቻቸው እንዲደርስ በማሰብ ጸሐፊ አዘጋጅተው አስጽፈው ለዛሬው ትውልድ አቆይተዋል አሁን ያሉ አባቶቻችንም ይህንኑ ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛሉ ማኅበረ ቅዱሳንም በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያናችን ያሏት ሊቃውንት በተለያዩ ጊዜያት የሚያስተምሩት ትምህርት ለምእመናን እንዲዳረስ ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፍ በማለት መምህራን በቃል ያስተማሩትን በአንዳንድ ሽቶች ያሰፈሩትን በማሰባሰብ በመጻሕፍት መልክ እንዲቀርብ በማድረግ ላይ ይገኛል ይህ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት የተባለው መጽሐፍ ከላይ እንደተጠቀሰው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በካህናት ማሰልጠኛዎች በሰንበት ትቤቶች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መንፈሳዊ ጉባኤያት ያስተማሩት ትምህርት ውጤት ነው በዚህ መጽሐፍ የተካተቱት ትምህርቶች አብዛኞዎቹ በተለያዩ መምህራን በሽት መልክ የቀረቡ ነበሩ በመሆኑም ለአያያዝ የማይመቹ ለጉዳት የተጋለጡና ረጅም ጊዜ ለማቆየትና ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ የማይመቹ ናቸው ሽቶቹንም በጊዜው እያባዙ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረጉ ለከፍተኛ የገንዘብ የጊዜና የጉልበት መባከን የሚዳርጉ ናቸው እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የሊቃውንቱ ትምህርት በትምህርታቸው እንዲተላለፍና መጪው ትውልድ ቀደምት አባቶቹን በትምህርታቸው እንዲያውቅ ለማድረግ ትምህርቶቹን በጽሑፍ መልክ ማቅረቡ ታላቅ አስተዋጽዖ አለው ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ አድርጎ የተነሳው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ነገረ ሃይማኖትንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናቸውን ከማሳወቅ አንፃር ይህ መጽሐፍ ለተቋማቱ በማስተማርያነት መልክ የቀረበ ነው በመሆኑም በሁሉም ተቋማት በሚገኙ መንፈሳዋ ጉባኤያት መስጠት ያለበቸውን ትምህርቶች የካተተ በመሆኑ ተማሪዎቹ ተመርቀው ሲወጡ ስለ ነገረ ሃይማኖታቸው አንድ ዓይነት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል መጽሐፉ ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና የስብከት ዘዴ የሚሉ ትምህርቶችን በውስጡ ያካተተ ነው በመጽሐፉ ውስጥ ከተካተቱ ትምህርቶች መካከል አንዳንዶቹ በሌሎች ሊቃውንት በመጽሐፍ መልክ የቀረቡ ቢሆንም በሁሉም ቦታ ያሉ ተማሪዎች የሚያገጃቸው በመሆኑና ለማስተማርያነትም ጉልህ ድርሻ ያሳቸው በመሆኑ በከፊል በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ሥልጠናዎች ተገኝተው በማሰልጠን ከመጻሕፍቶቻቸውም በከፊል ወስደን በዚህ መጽሐፍ አካተን እንድናሳትም የተባበሩንን መልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን የጠቤተ ክህነት ምዋና ሥራ አሥኪያጅ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ቀዳማዊ ሊቀካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየን በልዑል እግዚአብሔር ስም እናመሰግናቸዋለን በተለያዩ ቦታ የምትገኙ የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ውድና ብርቅ የሆኑ አባቶቻችን በብዙ ጥረትና ድካም አዘጋጅተዋቸው የቀሩትን ትምርቶች በማሰባሰብ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር የሚታተምበትንና ለትውልዱ አገልግሎት የሚሰጡበትን መንገድ እንድታመቻቹ አደራ እንላለን ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት በመልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን የጠቤተ ክርህነት ምዋና ሥራ አሥኪያጅ መግቢያ «ወዘእንበለ ተአምኖሰ ኢይትከሃል ያሥምርዎ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት አይቻልም» ዕብ በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረው የሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር ያለው ግንኙነት የአባትና ልጅ ያህል ወይም ከዚያ በላይ ቅርበት ያለው ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖርና እግዚአብሔርን ለማስደሰት የሚቻለውም በእምነት እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል ከዚያም በምን ዓይነት እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት እንደሚቻል ከራሱ ከቅዱስ መጽሐፍ ቃልና እንዲሁም ከዘመነ ብሉይና ከዘመነ ሐዲስ ቅዱሳን ምእመናን ሕይወት ሁሉንም ዓይነት ትምህርት ማግኘት ይቻላል የክርስትና እምነት የእግዚአብሔር ወዳጅነቱ ከተመሰከረለት ከአብርሃም እምነት የቀጠለ ትክክለኛ ሃይማኖት ስለሆነ በእምነትና በምግባር አብርሃምን መስሎና አህሎ በመኖር እግዚአብሔርን ማስደሰት የሚቻለው በዚህ እምነት ነው ለዚህ እምነት መሠረቱ ብሉይ ኪዳን ስለሆነ ትምህርተ «ክርስትናን» ከሥር መሠረቱ ጀምሮ መማር የሚቻለው ከብሉይ ኪዳን መነሣት ሲቻል ነው የክርስትና እምነት መሠረተ ትምህርት የሰው ልጅ ስለ እግዚአብሔር ኑባሬ ያለው ዕውቀት ፍጹምነት በመሠረቱ ዓለም በራሱ የተገኘና በራሱ የሚኖር ወይም ያለ አስገኝ በራሱ የተገኘና ያለሠራዒና መጋቢ በራሱ የሚኖር ሥነ ፍጥረት አይደለም ለተፈጥሮው አስገኝ ለኑሮው ሠራዒ መጋቢ ለጉዞው መነሻና መድረሻ አለው ከባሕር ወለል በላይ በተን መልክ ወደ አየር የወጣ ውኃ በዝናም መልክ ተመልሶ ወደ ምድር እንደሚወርድና ከዚያም ወንዝ ፈጥሮ ወደ ባሕር ወለል እንደሚጓዝ የሰው ልጅም እንዲሁ መነሻው መድረሻው የሆነ ተጓዥ እንደሆነ በቃለ እግዚአብሔር ምስክርነትና በእምነት ማወቅ ይቻላል የማያውቅም ይህን ሊያውቅ ይገባል ለዚህ ዕውቀትና እምነት ታዲያ ሥር መሠረቱ በቅድሚያ ለሚያየውም ሆነ የማይታየው ዓለም ፈጣሪና ሠራዒ መጋቢ እንደ አለው ማወቅና ማመን ነው የዕውቀት ምንጭ ሥነ ፍጥርት ስለ ሥነፍጥረት የሃይማኖት ትምህርት ቤትነት ማስረጃ ጥቅስ «ወዘሰ ኢያስተርኢ እግዚአብሔር እምፍጥረተ ዓለም ይትዐወቅ በፍጥረቱ ለፍጥረቱ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ እግዚአብሔር በፍጥረቱ ለፍጥረቱ ይታወቃል» ሮሜ «እንስሶችን ጠይቅ ያስተምሩሃል የሰማይንም ወፎች ጠይቅ ይነግሩሃል ወይም ለምድር ተናገር እስዋም ታስተምርሃለች የባሕርም ዓሦች ይነግሩሃል የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንደ አደረገ ከእነዚህ ሁሉ የማያውቅ ማነው። ይህ ከሆነማ አባባሉ ከእሱ በላይ ስለእሱ አውቃለሁ ማለት ሊሆን ነው በሌላ አንጻር በእርግጥ ለሰው የሚነገር ቃል ሁሉ ለፈጣሪ ሲነገር የፈጣሪን ባሕርይና ግብር ለመግለጽ በቂ ቋንቋ ላይሆን ይችላልር ለምሳሌ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ምሉዕ ሲሆን ቅዱስ መጽሐፍ ግን እንደውሱን ፍጡር «መጣ ሄደ ወጣ ወረደ» ወዘተ ሲል ይገኛል ይህ ዓይነቱ ቋንቋ ታዲይ ሰውኛ እንጂ እግዚአብሔርኛ አይደለም ለምሳሌ ወንጌላዊው ዮሐንስ ስለ ቃል ሥጋ መሆን ሲመሰክር «ብርሃን ወደ ዓለም መጣ» ካለ በኋላ «በዓለም ነበረ» ይላል ዮሐ ወንጌላዊው በዓለም ላይ ያለውን አምላክ «መጣ» ሲል የተናገረውና «መጣ» ያለውን ደግሞ እንደገና መልሶ «በዓለም ነበረ» ያለው በመሳሳት አይደለምኗ ወንጌል የተሰበከው በሰውኛ ቋንቋ ስለሆነ መጀመሪያ በዓለም ላይ ያለውን አምላክ እንደውሱን ፍጡር «መጣ» አለ በዓለም ላይ ምሉዕ እንደገና «በዓለም ነበረ» የሚል እግዚአብሔርኛ ቃል መልሶ አዳነው «ንባብ ይገድላል ትርጓሜ ግን ያድናል» ቆሮ ተብሎ እንደተጻፈ ገድሎ ማዳንም ልማደ መጽሐፍ ስለሆነ አያስተችም አሁንም ይህን የሞተ ንባብ ሕያው ለማድረግ ሲያስፈልግ «መጣ» የሚለውን ቃል «ታየ ተገለጠ» ብሎ በመተርጎም ማዳን ያስፈልጋል እግዚአብሔር በየትኛውም ዓለም ምሉዕ ስለሆነ «መጤ» ሊባል ከቶ አይገባውምና ከዚህ በተረፈ እግዚአብሔር የሚጠራበት ስያሜ እሱን እንደ እሱነቱ ለመጥራት በቂ አይደለም ማለት ለስሙ የሚሰጠውን ክብር ለሰው ልጅ በስም ያስተዋወቀው ራሱ እግዚአብሔር ስለሆነ ስለስሙ ብቃትና ፍጹምነት አዋቁቂው ራሱ ባለቤቱ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም ከእሱ በላይ ስለእሱ አውቃለሁ ማለትም ትክክለኛ ዕውቀት አይሆንም ፍጥረተ ዓለምና ምሥጢረ ተፈጥሮ ፍጥረተ ዓለም «ፍጥረተ ዓለም» የሚለው ቃል ራሱ የፈጣሪን መኖር የማያመለክት ዓለም አቀፍ ቋንቋ ነው በእርግጥ ዓለም የአንድ ብቸኛ ፈጣሪ ግሩም ድንቅ ሥራ መሆኑ ለሰው ልጅ ግልጽ የሆነው ከተፈጥሮ ጋር ስለሆነ የዚህ ትምህርት ዋና ዓላማም የዚህን አምላካዊ ተግባር አፈጻጸም ለማዘከር እንጂ የአዲስ ዕውቀት ግኝት ለማስተዋወቅ አይደለም ዓለም የተፈጠረው በተለያየ መልክና ጠባይ መጠንና ቅርጽ እንደመሆኑ ሥነ ፍጥረት የፈጣሪን መኖር ብቻ ሳይሆን ከሃሊነቱን ጭምር የሚገልጽ ተአምራዊ ተግባር ነው ይህንም በዓይን አይቶ መረዳት ስለሚቻል ብዙ ትውውቅ የሚያስፈልገው አይሆንም በዚህ ዓይነት ኅብረ ተፈጥሮ የተገኘውን ዓለም በዝርዝር ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ «ሕያውና ግዑዝ ረቂቅና ግዙፍ ሰማያዊና ምድራዊ ጊዜያዊና ዘለዓለማዊ» በሚል የጥቅል ስም ማስተዋወቅ የዓይነቱን ወይም የኅብሩን ብዛትና ምንነት በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችል ይሆናል ምሥጢረ ተፈጥሮ ሥነ ፍጥረት አሁን ያለውን ህልውና ያገኘው በሁለት መንገድ ሲሆን ይህም በትርጓሜ ቤት ዘይቤ እምኅበ አልቦ ኅበ ቦ ግብር እምግብር በመባል ይታወቃል «እምኀበ አልቦ ኅበ ቦ» ማለት ካለመኖር ወደ መኖር ወይም «ከኢምንት ወደምንት» ወይም አስቀድሞ ካልተገኘ ነገር የተገኘ ማለት ነው ይህ ዓለም እንዴት እንደተገኘ በዝርዝር ለመረዳትም የኦሪት ዘፍጥረትን የመጀመሪያ ምዕራፍ መመልከት ይጠቅማል በተጨማሪም «ዓስሞች በክግዚክብሔር ቃስ ክገደተዘጋዱ ፀህ የሚታየውም ከሚታፀ ሸገዳስሆነ በክምነት ክገናገራስገ ሰብ «ሸሱ ተናግሯስና ተፈጠሩ ሽሱ ክዘዘ ጸኑም» መዝ ዩሚሰውንገና ዩየመሳሰሰጡገ ቃስ መጽሐፍ በመመስከት በዚህ በኩፅ ፀሰውገ የሰውዋት ሸደማስ ማስፋት ቻሳፅ ግብር ክም ግብር ማስት ደግሞ ጸስቀድሞ ከተፈጠረ ነገር የተገኘ ማስት ነው የተፈጥሮ ስለምን ዓለም እንዴት እንደተፈጠረ ለማዘከር ያህል ይህን ሐተታ ማድረግ እንዳስፈለገ ሁሉ ስለ ምንነቱም አዘክሮ ማለፍ እንዲሁ አስፈላጊ ይሆናል እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረው ለክብሩ መግለጫ እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል ኢሳ «ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይገልጣሉ» መዝ የሚለው ቃል የሚያረጋግጠው የዚህን ምሥጢር እውነትን ነው ቅዱስ ኤኢፋንዮስ «አክሲማሮስ» በተባለው መጽሐፉ «ብቸኛ የሆነው ቅድምናዬ በኃያልነቴና በከሃሊነቴ ይታወቅ ዘንድ ዓለምን ለመፍጠር እፈቅዳለሁ አልኩ» ሲል እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረው በእርግጥ ለክብሩ መግለጫ እንጂ ለመገልገያ እንዳልሆነ ማረጋገጥ የሚቻለውም እንደ አምላክነቱና ፈጣሪነቱ መጠን እሱ የሁሉ ነገር ምንጭ ስለሆነ የፍጥረቱ የሚፈልገው ምንም ዓይነት ጥቅም ስለሌለ ነው ንብረተ ዓለምና የፈጣሪ ሠራዒ መጋቢነት ንብረተ ዓለም «ንብረተ ዓለም» ማለት «የዓለም ኑሮ መጀመያ ስለሆነ ያልነበረው ዓለም ሲፈጠር ኑሮ በጊዜ ተቀመረ በዘመን ተሰፈረ ወይም መኖር» ማለት ነው ተፈጥሮ የኑሮ ያልነበረው ኑሮም ተጀመረጾ የተጀመረው የፈጣሪ ሠራዒ መጋቢነት ፈጣሪነትን ከእናትና አባትነት ሓላፊነት ጋር ማነጻጸር ይቻላል እናትነትና አባትነት ያሳዳጊነት ግዴታንም የሚያጠቃልል እንደሆነ ሁሉ የተፈጠረውም ዓለም እንዲሁ ያለ ሠራዒ መጋቢ ለራሱ የተተወ አይደለምፁ ሁሉም እንደየተፈጥሮ ደረጃው የየራሱን ኑሮ እንዲኖር ከተፈጥሮ ተአምር ያነሰ አይደለም ፈጣሪ በሠራዒ መጋቢነቱ ለተፈጠረው ዓለም ኑሮና ለአዲስ ተፈጥሮ ክስተት ምክንያት የሆኑ ነገሮች ሁሉ ምክንያትነት ሳይጓደል «በኃይለ ዘርና ምሥጢረ አዝዋግ» የልደትና ሥርፀት የተፈጥሮና ኑሮ ሂደት ሳይቋረጥ የነፋሳት መንፈስ የውኃዎች መፍሰስ የብርሃናት መመላለስ የመዓልትና ሌሊት የክረምትና በጋ መፈራረቅ ሳይታጎል ሁሉም እንደ ተፈጥሮውና የኑሮ ደረጃው የሕገ ተፈጥሮ ተገዥ የሆነው ሥርዓት ሳይፋለስ የየራሱን ዘለዓለም መቻሉ በእርግጥ የሥነ ፍጥረትን ክሥተት ያህል የማያስደንቅ ተአምራዊ ኑሮ ነው ከሚከተለው ጥቅስ ስለፈጣሪው ሠራዒ መጋቢነት በቂ ዕውቀትንና ግንዛቤን ማግኘት ይቻላል ለመኖር ቅጥስ «መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም» መዝ ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖራለንም» የሐዋ «በእሱ ሕያዋን «ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራን እየሠራ ዝናምን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ልባችንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም» የሐዋ «ከእርሱ ልቡን ወደራሱ ቢመልስ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል» ኢዮ «በፊትህ ሕይወትንና መልካምነትን ሞትንና ክፋትን በረከትንና መርገምን አስቀምጣለሁ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ምረጥ» ዘዳ ዘንድ መልካምን «ባይናቼ ነፋሳት በዚህ ዓሰም ሳይ ተመጥነው ክከገዲ ነዜኳሱ የሚፀደርግበትኘ ቦታ ምሥጢር ጸሮዩ ዛናክ የሰው ልጅ ተፈጥሮና ኑሮ የሰው ልጅ በፈጣሪው አርአያና አምሳል የተፈጠረ ሕያዊት ለባዊት ነባቢት ነፍስ ያለችው ንጽሐ ሥጋ ንሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና የተሰጠው መቅድመ ወንጌል መንፈሰ አእምሬ መንፈሰ ለብዎ መንፈሰ ጥበብ መንፈሰ ምክር ማንፈሰ ኃይል መንፈሰ ረድኤት መንፈሰ ፈሪሃ እግዚአብሔር ጸጋን በስፋት የታደለ ኢሳ ታላቅ ፍጡር ነው በዚህ ዓይነት ተፈጥሮ «አድርግ አታድርግ» ከሚል አምላካዊ ሕግና ትእዛዝ ጋር ኑሮውን የጀመረ ፍጡር የሰው ልጅ ብቻ ነው ሆኖም በዚህ ዓይነት ኑሮውን የጀመረው የሰው ልጅ ከጊዜ በኋላ እንዳኖሩት አልተገኘም ድቀተ ኃጢአት ድቀተ አዳም ቀደም ብሎ የተገለጸው ዓይነት ተፈጥሮና ኑሮ የነበረው የሰው ልጅ «አታድርግ» የተባለውን በማድረጉና በክፉ ምኞቱ የዲያብሎስን ዓይነት ስሕተት ስለተሳሳተ የዲያብሎስን ዓይነት አወዳደቅ ወደቀ በዚህ ስሕተቱና ድቀቱም ሁሉንም ዓይነት ሞት ሞተ ሞተ ኅሊና ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ ዘፍ ሮሜ ስሕተት «አድርግ አታድርግ» የሚለውን አምላካዊ ሕግና ትእዛዝ መተላለፍ ድቀት ከልዕልና ወደ ትኅትና ከክብር ወደ ኃሣር ከሕይወት ወደ ሞት አዘቅት መውረድ ሞተ ኅሊና የንጽሐ ልቡና እጦት የክፉ አሳብ ተገዥ መሆን ሞተ ሥጋ የነፍስ ከሥጋ መለየትና ወደ አፈርነት መመለስ ሞተ ነፍስ የነፍስ ወደ ሲኦልና ገሃነም መውረድ ከዘለዓለማዊ ኩነኔ ፍርድ ሳይ መውደቅ ምክንያተ ስሕተት ምክረ ሰይጣን ሰይጣናዊ ምኞት እከብር ባይ ልቡና የምክንያት ምክንያት የአንድን ድርጊት ውጤት አስቀድሞ ለማወቅ ያለመቻል ድክመት ሰብአዊ ድክመት ተስፋ ድኅነት ድኅነት ምሥጢረ ድኅነት ምክንያተ ድኅነት ተስፋ ድኅነት የሰው ልጅ ስለፈጸመው ጥንተ አብሶ ከዲያብሎስ ያላነሰ በደል በመፈጸም የዲያብሎስን ዓይነት አወዳደቅ ቢወድቅም እንደ ዲያብሎስ ዕሩቅ ውዱቅ ሆኖ አልቀረም ማለትም በተፈጥሮ የታደለውን ጸጋ ክብር እንደተገፈፈና የዲያብሎስን አወዳደቅ እንደወደቀ አልቀረም አውቆ በድፍረት ሳያውቅ በስሕተት በሠራው ኃጢአት ክፉኛ ስለተጸጸተ በቃል ኪዳን የተደገፈ ተስፋ ድኅነት ተሰጠው። ኪዳነ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት ኪዳነ በረከት ማለት ነው ኪዳነ አዳም የሐዋ ገላ ኪዳነ አብርሃም የሐዋ ኪዳነ ኖኅ ዘፍ ዘመነ ተስፋ ከድቀተ አዳም እስከ ክርስቶስ ድረስ ያለው ዘመን የተስፋ ዘመን ይባላል ዘመነ ክርስትና ራሱ የትንሣኤ ሙታንና የመንግሥተ ሰማያት ተስፈኞች ዘመን እንደመሆኑ መጠን በእርግጥ የተስፋ ዘመን ሊባል ይችላል ሆኖም የአዲስ ኪዳን ሕዝብ የመንግሥተ ሰማያት ተስፈኛ ለመሆን የበቃው በክርስቶስ በተፈጸመው የድኅነተ ዓለም ተግባር ስለሆነ ዘመነ ተስፋ የሚለው ቃል ትክክለኛ መጠሪያ ሊሆን የሚችለው ከአዳም እስከ ክርስቶስ ለነበረው ዘመን ነው ኢትዮጵያዊው ደራሲ «ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል» ሲል የተናገረው ቃል የሚያረጋግጠውም ይህንኑ ሐቅ ነው ለዚህም የምስክርነት ቃል ምንጩ ቅዱስ መጽሐፍ መሆኑ ግልጽ ነው የሐዋ ገላ ወዘተ ዘመነ ተስፋና የዘመነ ተስፋ ኑሮ የተስፋ ዘመን «ዘመነ አበውና ዘመነ ኦሪት» በሚል ሁለት ክፍለ ዘመን ይከፈላል ሃይማኖተ አበውና ተስፋ አበው በጽኑዕ እምነት ላይ የተመሠረተ ሃይማኖትና ተስፋ ስለሆነ አምልኮተ እግዚአብሔር በሕገ ልቡና ይፈጸም በነበረበት በዚያ ዘመን እንኳ በዘመኑ ነዋሪዎች ላይ ይታይ የነበረው የእምነትና አምልኮ ጽናትና የምግባር ሥምረት ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ እለተ ምጽአት ለሚነ ምእመናን ሁሉ አብነትነት ያለው ሆኖ የሚኖር ነው ለምሳሌ የአቤል ምሥዋዕት ሥሙርነት ዘፍ ዕብ የሄኖክ እምነት አስደሳችነት ዘፍ ፅብ የኖኅ እምነት ተስፋ ፍጹምነት ዘፍ ዕብ ዕብ ያዕ ዘፍ የኢዮብ ትዕግሥት ዕፁብ ድንቅነት ያዕ የአብርሃም እምነትና ምግባር ፍጹምነት ዕብ ዘፍ የመልከ ጸዴቅ ክህነት አብነትነት ዘፍ ዕብ መዝ የሣራ ደግነት ዘፍ ጴጥ የርብቃ ትዳር ፈላጊነት ዘፍ በዘመነ ኦሪት ይፈጸም የነበረው የእምነትና አምልኮ ተግባር ከዘመነ አበው ጋር ሲነጻጸር በሕገ ልቡና ይፈጸም የነበረው ሥርዓተ አምልኮ በሕግ መጽሐፋዊና በሥዩማን ካህናት ሠራዒ መጋቢነት እንዲፈጸም ከመደረጉ በቀር የተቀነሰ ወይም የተጨመረ ነገረ ሃይማኖት የለም ድኅነትና ምሥጢረ ድኅነት «ድኅነት» የሚለው ቃል በአጭሩ የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ያጣውን የተፈጥሮ ጸጋ ክብር በአዲስ ተፈጥሮ እንደገና ለመታደል መብቃቱን ለመግለጽ የሚነገር ልዑል ቃል ነው በሌላም አገላለጽ ድኅነት የሚለው ቃል አዳም በክርስቶስ የታደለውን የሕይወተ ሥጋና ሕይወተ ነፍስ በረከተ ሥጋና በረከተ ነፍስ ጸጋ ሉቃ ሮሜ ወይም በሌላ አነጋገር የሞተ ሥጋና የሞተ ነፍስ ድቀት የደረሰበት አዳም በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘው የሐ ትንሣኤና ሕይወት የሚገለጽበት ሕያው ቃል ነው ዮሐ። በቀረበው ትንተና ላይ እንደሚታየው ይህ ምሥጢር በብዙ ዓይነት ገጸ ንባብ የተገለጠው የተለያየ ትርጉም ስላለው አይደለም ሁሉም ዓይነት ገጸ ንባብ ሲተረጐምና ሲመሠጠር የሚያስተላልፈው መልእክት አንድ ነው በሐዲስ ተፈጥሮ ወደ ጥንተ ተፈጥሮ ደረጃ መመለስ ከብልየት መታደስ በአዲስ ሕይወት የተፈጥሮ ጸጋን መልበስ ወዘተ ነው የድኅነተ ዓለም ተግባ ጸም እግዚአብሔር በኪዳነ አዳምና በኪዳነ አብርሃም ለሰው ልጅ የገባው ተስፋ ድኅነት የተፈጸመው በአንድ ልጁ ምሥጢረ ሥጋዌ ሲሆን ወልደ አብ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን የድኅነተ ዓለም ማቴ ተግባር የዲያብሎስና የፈጸመውም ሕማሙንና የሞት ድል መንሻ የኃጢአት መደምሰሻ ቆሮ ሞቱን ኢሳ የመንግሥተ ሰማያትና የዘለዓለማዊ ሕይወት መውረሻ ዮሐ ዕብ በማድረግ ነው የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን የፈቀደው ሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ ሕይወትነት ሞተ ሥጋ በትንሣኤ ሥጋ ሞተ ነፍስ በሕይወተ ነፍስ ተደምስሷል የዚህ ድኅነት ባለቤት ለመሆን የሚቻለውም በትምህርተ ድኅነት ለሰው ልጅ ሊታደል የሚችልበትን ምሥጢር በመፈጸም የመድኃኒት ቤትነቷን በተግባር በመተርጎም ላይ ትገኛለች እግዚአብሔር «የድኅነት አምላክ» ተብሎ የሚጠራው በልጁ ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ በፈጸመው የድኅነተ ዓለም ተግባር ብቻ አይደለም በኪዳነ ኖኅ ዘፍ እንደተገለጠው ከዚያም በፊት ለሰው ልጅ ኑሮ ደኅንነት ይፈጽመው በነበረ የትድግና ተግባር የድኅነት አምላክ መሆኑን ለሰው ልጅ በተግባር ገልዷጂል ይህንንም ከሚከተለው ትንተና መረዳት ይቻላል ድኅነት ምሥጢረ ድኅነትና ምክንያተ ድኅነት በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ የዘመነ ብሉይ ድኅነትና ምክንያተ ድኅነት ድኅነት ምክንያተ ደኀነት በዚህ ዓለም ላይ ለመኖር የሚቻልበትን ምክንያት ሁሉ ከሚያሳጣ አባር ቸነፈር ኢዮ ስደትና ምርኮ ኤር የነፃነት እጦትና የባዕድ ተገዥነት በጸምነትዛ ክምስኮ ጸክካሄዶገ ከክግዚክብሔር ጋር ማቋረግ ስብ ዩክምነትና ክምስኮ መሥዋስሰት ጸቅርቦት ዘፍ ኪዮ ጸሎትና ጾም ሻ ነገ ዮና ዚ ምጽዋት ጻገ ክገግዳ ተቀባፀነት ዘፍ ሸግዚጸብሔር ክገደፈጣዕነተቱና ክምሳክነቱ የሚፀደርገው ኤር ዘፀ ወዘተ አደጋ በእግዚአብሔር ረድኤት በመጠበቅ የሕይወት ኑሮ መኖር ቸርነት መዝ የዘመነ ሐዲስ ድኅነትና ምክንያተ ድኅነት ድኅነት ምክንያተ ድኅነት በአዲስ ተፈጥሮ ወደ ጥንተ ተፈጥሮ ደረጃ መመለስ ቆቁሮ ኤፌ በጥምቀት እንደገና መወለድ ዮሐ « ከኃጢአት ባርነት ነፃ መውጣት ዮሐ ከማዕሰረ ኃጢአት መፈታት ዮሐ ሞተ ሥጋንና ሞተ ነፍስን በትንሣኤና ሕይወት ድል መንሣት ዮሐ ቆሮ « ከኃጢአት እድፈት መንጻት ዕብ ራፅዕ በምድራዊና ሰማያዊ በረከት መባረክ ዮሐ የክርስትና ክምነትና ጥምቀት ማር ምግባር ስ ማቴ ምሥጢረ ቁዌቁርባኘን መኗጸም ዮጠ ኳቅር ጸጥ ጾም ጸሱትና ገስሐ የሐዋ የሐዋ ፎወቅርታ ማድረግ ማቴ ምጽዋት ማቴ ዩቅዱሳገ ስማሳጅነትና በስማቸው የሚፈጸም ምግባረ ሠባ ማቴ የሸግዚስብሔር ቸርነት ርሜፋ ራ የክርስቶስ ማንነት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ለክርስትና እምነት መሠረቱ ይህ ዕውቀት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር እንደሆነ ማወቅ ሕይወት ያለው ዕውቀት ነው ዮሐ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችውም በዚህ እምነት ላይ ነው ማቴ ያለዚህ እምነት በኑዕ ዐለት ላይ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን ባለቤት መሆን አይቻልም የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው በዚህ ሥጋዌ ኃጢአተኛውን ዓለም ለማዳን አስቀድሞ በገባው ቃል መሠረት ነው ኤፌ ፅዝራ ሱቱኤል ከእግዚአብሔር ጋር ቃል በቃል ለመነጋገር በበቃበት የራእይ ወቅት እግዚአብሔር ዓለምን በማን ሊጎበኝ እንዳሰበ ለመጠየቅ መቻሉንና ከዚያም በመልሱ ጎብኙ ራሱ መሆኑንና ይህን ጉብኝት ለማድረግ ፈቃዱ የሆነውም ከፍጥረተ ዓለም በፊት ጀምሮ እንደነበር ለመረዳት እንደቻለ በስሙ የተጻፈው መጽሐፍ ቃል ያረጋግጣል ዕዝራሱቱኤል ይህም የሚያመለክተው የክርስቶስ ምጽአት ከጊዜ በኋላ ታስቦ የተፈጸመ ድርጊት አለመሆኑን ነው ወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ ምሥጢረ ምጽአቱን አስቀድሞ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለአባት ተፀነሰ ተወለደ ቀስ በቀስ አደገ በሠላሳ ዘመኑ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ በመጠመቅ የእኛን ጥምቀት ባረከ ከዚያም በምድር ላይ በመመላለስ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ሰበከ አስተማረ ስለእኛ ስለሰዎችና ስለመዳናችን በመስቀል ላይ ተሰቀለ ሞተ በሦሰተኛው ቀን ተነሣ በአርባኛው ቀን አረገ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ላከ ዳግመኛ ለፍርድ እንደሚመጣም በሐዲስ ኪዳን ፍጹም ተስፋ ሰጠ የእምነትና አምልኮ ቀኖና አፈጻጸም በብሉይና ሐዲስ ኪዳን በዘመነ ብሉይ በዘመነ አበው በዘመነ ኦሪት ቀደም ብሎ በተጠቀሰው መንገድ ከፈጣሪ ጋር ግንኙነት በማድረግና የሚፈለገውንም መሪ ቃል በመቀበል የአምልኮ ግዴታን በሕገ ልቡና መፈጸም በኪዳነ አብርሃም እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የገባው ቃል ኪዳን የሚጠይቀውን ግዴታ በመፈጸም የአብርሃማዊ በረከት ተጠቃሚ መሆን ዘጸ የቃል ኪዳን ግዴታ ጽድቅና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ መጠበቅ ዘፍ የአማናዊ ጥምቀት ምሳሌ የሆነውን ሥርዓተ ምሳሌ የሆነውን ሥርዓተ ግዝረት መፈጸም ዘፍ የአብርሃምን እምነትና ምግባር ግዴታ በሕግ መጽሐፋዊ መፈጸም ዘሌ ዘጸ ሥርዓተ ግዝረትን መፈጸም ዘሌ የአምልኮ መሥዋዕት በማቅረብ በረከትን የኃጢአት ሥርየትን የአረቦን ድኅነትን ወዘተ ለማግኘት መብቃት ዕብ በጸሎት አቅርቦት አምልኮትን በመግለጽ የራስንም ሆነ የሌላውን ደኅንነት ማስጠበቅ ነገ ዘፀ ዘጉ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከዘመነ አበው ቅዱሳን ምእመን የእነሄኖከን አብርሃምን ይስሐቅንና ያዕቆብን ከዘመነ ኦሪት የእነሙሴን ጌዴዎንን ባርቅን ሶሞሶንን ዮፍታሔን ስም በመጠቃቀስ ስለ የአምልኮ መሥዋዕት በማቅረብና በእምነት እምነታቸው ደግነት በምሳሌነት ያወሳል የእግዚአብሔርን ስም በመጥራት የአብርሃም ዕብ በረከት ተሳታፊ መሆን ዘፍ በጸሎት አቅርቦት አምልኮትን መግለጽ ኢዮብ ኢዮ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሥጢረ ሥላሴ ምሥጢረ ሥላሴ እግዚአብሔር አንድ ነው ነገር ግን ሦስት ገጽ ሦስት አካል አሉት እነዚህም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው። እኛ ግን ፈጣሪያችን ክርስቶስ በሞቱ ሞትን ድል አድርጐ ስለተነሣ ስለ ትንሣኤ የምንሰጠው ትምህርት እውነተኛ ነው የሃይማኖታችንም ቀኖና ፍጻሜው «የሙታንን ትንሣኤ እንጠባበቃለን» የሜል ነው ክርስቲያኖች የሥጋን ሞት እንዳይፈሩ ታዘዋል ነገር ግን ነፍስና ሥጋ በትንሣኤ ከተዋሓዱ በኋላ የሚመጣውን ሁለተኛውን ሞት ፍሩ ተብለዋል ይህ ሞት ትንሣኤ የማይከተለው ነው ይህ ሞት የመጨረሻው ነው «የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲህ ነውበመበስበስ ይዘራልባለመበስበስ ይነሣል በውርደት ይዘራልበክብር ይነሣልበድካም ይዘራልበኃይል ይነሣል»ቆሮ የሙታን ትንሣኤ በትርጓሜ ቤት ዘይቤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ተብሎ ሲጠራ የጻድቃንና የኃጥአን ትንሣኤ ደግሞ ትንሣኤ ዘለክብር እና ትንሣኤ ዘለኅሳር በመባል ይታወቃል «ያንጊዜ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ይህ የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ ሞት ድል በመነሣት ይዋጣል መቃብርም እንዲሁ» ኢሳ ዳን ሆሴ ቆሮ ከዚህም ጋር ያን ጊዜ የሙታን መቀስቀሻ መለከት ሲነፋ በሞት ያንቀላፋው ሁሉ እንደሚነሣ ሌላው ደግሞ ከመቅጽበት ግብር እምግብር እንደሚለወጥ በፍጹም እምነትና ተስፋ ይጠበቃል ቆሮ ተሰ ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ዘቤተ ክርስቲያን ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በቅዱስ ወንጌሉ «በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነው አንዳችስ እንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለም በእሱ ሕይወት ነበረች ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች ብርሃንም በጨለማ ያበራል ጨለማም አላቸነፈውምለሰው ሁሉ የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ በዓለም ነበረ ዓለሙም አላወቀውም ቃል ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀበልን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና»ዮሐ ሲል የተናረገው ስለ ክርስቶስ መሆኑ ግልጽ ነው ቅዱስ ዮሐንስ በመጀመሪያ «ቃል ነበረ» ሲል ቀዳማዊነቱን «ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ» ሲል ከባሕርይ አባቱ ከአብና ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስላለው አንድነት «ቃልም እግዚአብሔር ነው» ሲል አምላክነቱን «ሁሉ በእርሱ ሆነ ያለ እሱ የሆነ አንዳች የለም» ሲል ፈጣሪነቱን «በእሱ ሕይወት ነበረች ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች» ሲል የዓለም መድኃኒትነቱን «ብረሃን በጨለማ ያበራል ጨለማም አላቸነፈውም» ሲል የብርሃንነቱን ኃያልነትና ዘለዓለማዊነት «እውነተኛ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ በዓለም ነበረ ዓለሙም አላወቀውም» ሲል ምሉዕነቱን «ቃል ሥጋ ሆነ» ሲል ሰው መሆኑን «ጸጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ» ሲል ለእኛ ሲል ሰው መሆኑን «እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀበልን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና» ሲል በእሱ ስላገኘው የድኅነተ ሥጋና ድኅነተ ነፍስ ጸጋ ምልዓት መመስከሩ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን አሁንም ስለ ክርስቶስ የምትመሰክረውን ይህን ቃል ነው «ክርስቶስ» ማለት «መሚሕ» «መሚሕ» ማለትም «የተቀባ» ማለት ነው ይህ ቃል በሌላ አንጻር ሥዩማነ እግዚአብሔር ለሆኑ ነቢያትና ካህናት እንዲሁም ነገሥታት ሊነገር የሚችል ቋንቋ ስለሆነ «ክርስቶስ ዘቤተ ክርስቲያን» የሚለው ቃል ሰማያዊውን ከምድራውያኑ ለመለየት የተነገረ ቋንቋ ነው ወልደ እግዚአብሔር ሰው በመሆኑ «መሚሕ ክርስቶስ» ቢባልም ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የዋጀ የመሠረተና ያጸና የባሕርይ አምላክ ስለሆነ እሱ የቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንም የእርሱ ናት እርሱ «ወልድ» ተብሎ እኛን «ውሉድ» እሱ «ክርስቶስ» ተብሎ እኛን «ክርስቲያን» ያሰኘ እርሱ ነው በአሁኑ ጊዜ ቅዱሳን ምእመናን «በወልድ ውሉድ» «በክርስቶስ ክርስቲያን» ተብለው የሚጠሩት በወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ በእርሱ ነው ከዚህም ጋር ቤተ ክርስቲያን በምሥጢራዊ አነጋገር አካሉ ስለሆነች ወይም በእርሱ ራስነት የተገጣጠመች አካል ስለሆነች ኤፌ በእርግጥ እርሱ የቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንም የእርሱ ናት ቤተ ክርስቲያን «መድኃኒቴ» ብላ የምትጠራውና የምታመልከው ክርስቶስ ወይም መሚሕ እርሱ ነው። አባላቱ ወደ ተለያዩ አኅጉር ስለተሰደዱ ኢየሩሳሌም ሳይ አንደ ኩሬ ውኃ በአንድ ቦታ ተገድቦ የነበረው የክርስትና እምነት ትምህርት እንደ መስኖ ውኃ በየአህጉሩ ተሰራጨ በተለይ ወደ አንጾኪያ ተሰድደው የነበሩት ክርስቲያኖች አንድነት እየጠነከረ ስለሄደ «ደቀ መዛሙርት ናዝራውያን» የሐዋ እየተባሉ ይጠሩ የነበሩት ምእመናን «ክርስቲያን» ተብለው ተሰየሙ የሐዋራ የክርስትና እምነት በዓለም ላይ ያደረገውን መስፋፋትና መጠናከር በምሳሌ መግለጽ ቢያስፈልግ ትክክለኛ ተነጻጻሪ ሆኖ የሚገኘው በቅዱስ ወንጌል እንደተገለጠው የሰናፍጭ ዘር ነው የሰናፍጭ ቅንጣት እጅግ በጣም አነስተኛ የሆነች የዘር ዓይነት ናት ሆኖም ከእርሻ ላይ ስትዘራ የወፎች ማረፊያ የሆነች የዘር ዓይነት ናት ሆኖም ከእርሻ ላይ ስትዘራ የወፎች ማረፊያ ለመሆን እስከምትችል ድረስ ታላቅ ዛፍ ትሆናለች ማቴ የቤተ ክርስቲያንም የዕድገት ልክ እንደዚህ ነው የተነሣችበትንና የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ ዝቅታና ከፍታ ያለማብራሪያ ከምሳሌው መረዳት ይቻላል ሆኖም ቤተ ክርስቲያን ይህን ስፋት ያላት ታላቅ የሕይወት ዛፍ የሆነችው በዝናም ውኃ አይደለም የወንጌል ጠለ ትምህርት የማይለያት የክርስቶስ ተክል ስለሆነች ነው ቃለ ወንጌል በተዘራበት ቦታ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ትበቅላለች ዘሪው ጴጥሮስም ይሁን ጳውሎስ ወይም ሌላ የተዘራው ዘር የሚበቅለውና የሚያድገው በእግዚአብሔር አምላካዊ ግብር ነው ቆሮ ማር ምድር እንኳ ጠቃሚ ፍሬን የምትሰጠው ከላይ በእርሷ ላይ የሚወርደው የዝናም ነጠብጣብ ብቻ አይደለም በሁሉም ወራት የምሕረት ዝናምን ከሚለግሳት እግዚአብሔር የተዘራው ለመብቀል የበቀለው ለማደግና ፍሬ ለመስጠት የሚበቃበትን በረከት ስታገኝ ነው ዕብ የተዘራው የሚበቅለው የተተከለው የሚጸድቀው በግብር አምላካዊ እንደሆነ ቢታመንም ለምድራዊው የግብርና ተግባር ትጉህ ገበሬ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለሰማያዊው ግብርናም እንዲሁ ከዚያ የላቀ ትጉህ ታጋሽና ጠንካራ የወንጌል ገበሬ ያስፈልጋል የግብርና ትልቁ ተግባር ደግሞ የተዘራውን ሰብል ከአረምና ከተባይ ተጠ ቂነት መጠበቅ ነው ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ መረዳት የሚቻለውም የወንጌል ገበሬዎችንና የቤተ ክርስቲያን መጋቢዎችን ከፍተኛ ተልዕኮ የጠየቀው ቃለ እግዚአብሔርን ወይም ቃለ ወንጌልን የመዝራቱ ተግባር ብቻ ሳይሆን የተዘራውን ቃለ እግዚአብሔር ከሰው ሠራሽ አረምና ተባይ ኑፋቄ ጥቃት የመጠበቁ ተግባር ነበር በመሆኑም ከውጭና ከውስጥ የሚያጋጥመውን ፈተና ለመቋቋም ብዙ ደም ፈስሷል ብዙ ገድል ተፈጽሟል ብዙ መሥዋዕትነት ተከፍላል ስለ ክርስትና እምነትና ሕይወት የተከፈለ መሥዋዕትነት በዘመነ ሐዋርያት ዘመነ ሰማዕታትና ዘመነ ሊቃውንት ዘመነ ሐዋርያት «የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል እንግዲህ ያላመነበትን እንዴት ይጠሩታል ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደተጻፈ ካልተላኩስ እንዴት ይሰብካሉ» ሮሜ ዘመነ ሐዋርያት የክርስትና እምነት የዓለም ሃይማኖት ለመሆን የበቃበት ሐዋርያዊ ጉዞ በመንፈስ ቅዱስ ተባርኮ የተጀመረበት በጉዞው ውጤታማነት የሐዋርያት የዓለም ጨውነት የዓለም ብርሃንነት የተረጋገጠበት ዓለም በጥበቡ ሊደርስበት ያልቻለው የድኅነተ ዓለም ምሥጢር በስብከተ ወንጌል ሥርጭት ገሃድ የሆነበት ቆሮ የቃለ ወንጌል ዘርና መከር ወቅት ነው ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ከታጠቁ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ሂዱና አስተምሩ ማቴሾ በጨለማ የነገረኳችሁን በብርሃን ተናገሩት በጆሮአችሁ በሹክሹክታ የነገርኋችሁን በሰገነት ላይ ስበኩት ማቴ ሲል የሰጣቸውን ትእዛዝ ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ዓለም ወጡ መልካሙን የምሥራች ዜና አወሩ የሕይወትንም ቃል ለዓለም አሰሙ የዓለምን ጨለማ ለማራቅና አልጫውን ዓለም ለማጣፈጥ የሚቻልበትን የብርሃንነትና የጨውነት ተግባር ፈጸሙ የተኛውን ቀሰቀሱ የሞተውን አስነሠ ኤፌ የነቃውም ዓለም የተነገረውን የምሥራች ቃል ሰማይድንበተ የነበረውነ ስም ተቀብሎ በክርስትና እምነት ተጠራ የሐዋ ቃለ ወንጌል በዚህ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ላይ የተዘራውና ይህ የሕይወት ፍሬ የተመሠረተው እንግዲህ በእነዚህ ሐዋርያት የወንጌል ግብርና ስለሆነ ዘመነ ሐዋርያት ለክርስትና እምነት በእርግጥ ዘመነ ዘርና ዘመነ ፍሬ እንደሆነ በግልጽ ይታያል ይህ እንዲህ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በዚያ የበረከት ዘመን እንደ ሲሞን መሠርይ ያሉ የሐዋ ቢጽ ሐሳውያን ወይም መናፍቃን ከውስጥም ከውጭም በመነሣት የክርስትና እምነትን ለመበረዝ ለማደስና ለመለወጥ ያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ ቀላል ስላልነበረ ዘመኑ የፈተና ዘመን እንደነበረ ማወቅ ይቻላል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ «እኛ ከሰበክንላችሁ ወንግል የሚለይ ትምህርትን ከሰማይ መልአክ እንኳ ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን» ገሳ ሲል በመረረ ቃል ያስጠነቀቀውም ስለዚህ ነበር ዘመነ ሰማዕታት ዘመነ ሰማዕታት የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትነው የእምነታቸውን ደግነት በተግባር ያረጋገጡበት የገድልና ትሩፋት ዘመን ነው ቤተ ክርስቲያን የዚህ ገድል ፈጻሚ መሆን የጀመረችውም ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ መሆኑ አይካድም ለምሳሌ በሐዋርያነት ከተሾሙት ሰባት ዲያቆናት አንዱ የነበረው እስጢፋኖስ በክርስትና እምነት ተቃዋሚዎች በድንጋይ ተደብድቦ የሰማዕትነትን ገድል የፈጸመው በዘመነ ሐዋርያት ነው የሐዋ ሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቀዳሜ ሰማዕት ተብሎ ለመጠራት የበቃውም በዚህ ምክንያት ነው ቀጥሎም ሐዋርያው ያዕቆብ በአረማዊው ሄሮድስ ትእዛዝ በሰይፍ ተሰይፎ የሰማዕትነትን ጽዋ የተቀበለው በዚያ ዘመን መሆኑ ግልጽ ነው የሐዋራ ነገሩ እንዲህ ሲሆን ታዲያ ዘመነ ሰማዕታት ከዘመነ ሐዋርያት የተለየ ክፍለ ዘመን እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድ የቻለው በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ አጠቃላይ ጥፋት አዋጅ ለታወጀበትና አዋጁ ተግባራዊ ለሆነበት ልዩ የሥቃይ ወቅት ይህ ስያሜ እንዲሰጠው ስለተደረገ ነው ለዚህ ኢሰብአዊ አዋጅ የታሪክ ተጠያቂ የሆነውም ሮማዊው ቄሣር ዲዮቅልጥያኖስ ነው ሆኖም ድርጊቱ በሰላም ዘመን ሊፈጠሩ የማይችሉ አያሌ ሰማዕታት መገኘት ምክንያት ከመሆኑ በቀር በክርስትና እምነት ሂደት ላይ የፈጠረው መሰናክል አልነበረም አስቀድሞ እንደተገለጠው ይህ ዕልቂት በይበልጥ ተግባራዊ የሆነው ከ እኤትአ ወይም ከ እኤአ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ስለሆነ ይህ ወቅት ዓመተ ሰማዕታት በመባል ለሚታወቀው የዘመን አቆጣጠር የታወቀ መነሻ ሆኖ ይገኛል ይህ ሁሉ የሚያመለክተው የክርስትና እምነት ምን ያህል መሥዋዕትነት የተከፈለበት ሃይማኖት መሆኑን ነው ዘመነ ሊቃውንት ዘመነ ሊቃውንት በክርስቶስ የተነገረውና በሐዋርያት የተሰበከው ቃለ ወንጌልም ሆነ የድኅነተ ዓለም ተግባር አፈጻጸም በስፋትና በጥልቀት የተመሠጠረበት የነገረ ሃይማኖት ቀኖና በዓለም አቀፍ ጉባኤ የተደነገገበትና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት መልክና ቅርጽ እንዲኖረው የተደረገበት ሌላው የቤተ ክርስቲያን ወርቃማ ዘመን ነው ይህ እንዲህ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ዘመን የመናፍቃን መፍለቂያ ዘመን በመሆኑ ሌላው ዘመነ ሰማዕታት መሆኑ አልቀረም።