Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي
  • قائمة القراءة
  • مختصر
  • كتاب مسموع
  • بحث
  • تحميل
  • myzon
  • تسجيل الدخول
  • تسجيل
English  አማርኛ  Français  العربية
كتاب اليوم

ታቦት (በዲያቆን አግዛቻው ተፈራ).pdf


  • word cloud

ታቦት (በዲያቆን አግዛቻው ተፈራ).pdf
  • Extraction Summary

ነገር ግን ያም ባይሆን ታቦት ፍጹም የሆነው እስኪመጣ ድረስ ጥላና ምሳሌ ሆነው በጊዜያዊነት ከተሰጡት ነገሮች መካከል አንዱ በመሆኑ ብሉይ ኪዳን ታቦት ከባቢሎን ምርኮ ጀምሮ አገልግሎት መስጠቱን እንደማይቀጥል የብሱይ ኪዳን መጻሕፍት መስክረዋል «ዳሩ ግን የአስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለተሻረው ስለፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት አስኪሳናቸው ድረስ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም። እህ ጉኔ ነ በ ነ ማቻ። ለ ላ ክመጀሎ ህዝ ለ ዞ ኳ ሦ ሪሀ ነ ። ዕብ ቴባቴቡታ። ምስጢሩ ቦታነትና ማኅደርነት ነው። ባስቅኔዎች ግኘየ ቤተ ጥሬኔ ነው ይላሰ። ታቦትመኀበር ምሥዋዕ በመንበርላይ የሚቀመጥ ጽላት ። ጸሎት ዕብ ኔዴርስለትብፅዐት። ባማርኛ ግን አንዱ ብቻ ጽላት ይባላል ይኸውም ሥራው በመጽሐፍ አምሳል መኾኑን ያሳያል አንድ ቅጦል ክርታስ ወይም ብራና በ ኹለት ወገን ስለ ተጣፈበት ኹስሰት ገጽ እንዲ ባል ጽላት ማለትም እንደዚህ ነ ነው።

  • Cosine Similarity

ክፍል ታቦት ታቦት በብሉይ ኪዳን ታቦት ከግራር ዕንጨት እንዲሠራ በእግዚአብሔር የታዘዘ ሲሆን ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል ሳሜ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል ሳሜ ሆኖ በሣጥን መልክ የተሠራ ነበር በዚህ መለኪያ መሠረት ከተሠራ በኋላ ውስጣዊና ውጫዊ አካሉ በጥሩ ወርቅ እንዲለበጥ አራት ካህናት ለመሸከም እንዲችሉ አራት የወርቅ ቀለበቶችና በቀለበቶቹ ውስጥ የሚውሉ ከግራር ዕንጨት ተሠርተው በወርቅ የተለበጡ መሸከሚያ መሎጊያዎች እንዲሠሩ እንዲሁም የታቦቱ ክዳን ሆኖ በስርየት መክደኛነትም የሚያገለግል ክዳን በታቦቱ ልክ ከጥሩ ወርቅ ተዘጋጅቶ በላዩ ሁለት ኪሩቤል በትይዩ ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘርግተው የስርየት መክደኛውን በሚሸፍንና ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው እንዲመለከቱ ሆነው እንዲሠሩ የታቦቱን አጠቃላይ ንድፈ ሐሳብ ለሙሴ ነገረው ዘፀ ሙሌም ከእግዚአብሔር ዘንድ በልቡ ጥበብ የተሰጠውን ሰው ባስልኤልን ጠርቶ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ታቦቱ እንዲሠራ አደረገ ወ በዚህ ሁኔታ የተሠራው ታቦት ይቀመጥ የነበረው በቤተ መቅደሱ ውስጠኛው ክፍል ውስጥ ነው ዕብ ዘፀ ታቦቱም በውስጡ ሁለት ጽላት መና የነበረበትን የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትርን ይዞ ነበር ዕብ ዘፀ ዘጐ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ግን ከሁለቱ የድንጋይ ጽላት በቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም ምን እንዳልተገኘ ተጽፎአል ነገ ዜና ዐ ጽላቱን የተመለከትን እንደሆነ በመጀመሪያ የእግዚአብሔር እጅ ሥራ ነበሩ። ነገር ግን ሙሴ ጽላቱን ከእግዚአብሔር ተቀብሎ ከተራራው ሲወርድ በአሮን መሪነት ሕዝቡ የጥጃ ምስል አቁሞ ሊያመልከው በመመልከቱ ተቄጥቶ ጽላቱን ከእጁ ጥሎ ሰበራቸው ከዚህ በኋላ ሙሴ እንደሰበራቸው ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላት ጠርቦ እንዲያመጣና የቀድሞዎቹን ዐሥሩን ቃላት እግዚአብሔር ራሱ እንደሚጽፍባቸው ነግሮት እንዲሁ አደረገ እግዚአብሔርም ጻፈባቸውና ለሙሴ ሰጠው ዘፀ ዘዳ ከዐሥሩ ትእዛዛት ውጪ እግዚአብሔር ኅቡእ የሚባል ስሙንም ሆነ የተገለጸ ስሙን ወይም ሌላ ተጨማሪ ምስልና ሐረግ እንዳልጻፈና እንዳልቀረጸ ግልጽ ነው «እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳትና በደመናው በጨለማውም ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምፅ እነዚህን ቃሎች ዐሥሩን ትእዛዛት ማለት ነው ለጉባኤአችሁ ሁሉ ተናገረ ምንም ምን አልጨመረም በሁለቱም የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው ለእኔም ሰጣቸው ዘዳ አንዲሁም ን ተመልከት በጽላቶቹ ላይ የተጻፉት ዐሥሩ ቃላት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን የሚያሳዩ በመሆናቸው በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ምስክር ሆነው ቆመዋል በፀ ዘዳ በመሆኑም ጽላቶቹ የምስክር ወይም የቃል ኪዳን ጽላት ሲባሉ ታቦቱም የምስክር ወይም የቃል ኪዳን ታቦት ተብሎ ተጠርቷል በዘፀ ዘኀ ኢያ ፅ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት የጽላቶቹ ማስቀመጫ ከመሆኑ ባሻገር የስጠው ዋና አገልግሎት አግዚአብሔር ከአስራኤል መሪዎች ጋር በመገናኘት ትእዛዝና ረድኤትን ለሕዝቡ ለመስጠት እንዲችል የሕዝቡንም ልመናና ጥያቄ መሪዎቻቸው ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርቡ ለማድረግ ነው ፀ ዘጉ መሳ ስለዚህ ታቦቱ አግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል መኖሩን አመልካች ነበር ሳሙ አስራኤላውያን ከምድረ ግብጽ ወጥተው በምድረ በዳ ተጓዝች ሆነው በኖሩበትና ተስፋይቱን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ባለው ጊዜ ታቦቱን ተሸክመው ይጓዙ ነበር የሚሸከሙትም ካህናት ናቸው ዘዲ ኢያ ዜና ፋ ካህናት ታቦቱን የመሸከማቸው ተግባር ቀጣይነት የነበረው ግን እስራኤላውያን በአገራቸው መኖር ሲጀምሩና አንድ ቋሚ ቤተ መቅደስ እስኪታነጽ ድረስ ነበር ይህ ከሆነ በኋላ ግን ታቦቱን ከመሸከም ዐርፈዋል ዜና ታቦቱ በቤተ መቅደስ ስፍራውን ከያዘ በኋላ በእስራኤላውያን ዘንድ ለበዓላትም ሆነ በሌላ ምክንያት በዓለ ንግሥ ተደርጎ በካህናቱ ተሸካሚነት ከመቅደሱ ወጥቶ መቅደሱን ዞሮ ወደ ስፍራው የሚመለስበት ሥርዐት ፈጽሞ አልነበረም እርግጥ አንዳንድ ጊዜ በጦርነት ወቅት ታቦተ ሕጉን ወደ ጦር ሜዳ ይዘውት ይወጡ አንደነበር አይዘነጋም ሌላው ነጥብ ታቦቱ በአግዚአብሔር ስም ብቻ እንጂ በሌላ በማንም ስም አለመጠራቱ ነው ይህን ለሰማረጋገጥ ካስፈለገ ስለ ታቦቱ የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መመልክት ይቻላል ለአብነት ያህል የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ብንመለከት ታቦቱ የእግዚአብሔር ታቦት» ወይም «የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት» ተብሎ ተጠርቷል ኢያ ሳሙ ሳሙ ፅ ኩና ል እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰጠው በስሙ የተጠራውን አንድ ታቦት ብቻ ሲሆን በዘመናቸው ሁሉ የነበረውም ያው አንዱ ታቦት ብቻ ነበርኑ። ፊ ከዚህ ውጪ ያንን አስመስለው ብዙ ታቦታትን እንዲሠሩና እንዲያራቡ አልታዘዙም እነርሱም ቢሆን ይህን አላደረጉም ከብዙ ዘመን በኋላ እስራኤላውያን በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል ምስክርና ቃል ኪዳን ሆኖ እንዲጠበቅ የተሰጠውን ሕግ አፍርሰው በመገኘታቸው እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ሌላ ዐዲስ ቃል ኪዳን እንደሚገባና የታቦቱም ሆነ የጽላቱ አገልግሎት ስለሚያበቃ ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ታቦት ብለው እንደማይጠሩት ልብ እንደማያደርጉት እንደማይሹትና ከእንግዲህ ወዲያ እንደማይደረግ በአጽንዖት ተናገረ ኤር ቃል ኪዳኑን በማፍረሳቸው ምክንያት እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በባቢሎናውያን ሲያስማርክ የታቦቱም ታሪክ እዚሁ ላይ ይደመደማል የባቢሎን ንጉሥ ባሪያ የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ቤተ መቅደሱን በዝብዞ በውስጡ የነበሩትን የወርቅ የብርና የነሐስ የተቀደሱ ዕቃዎች ሁሉ ወደ ባቢሎን ካፈለሰ በኋላ ቤተ መቅደሱን በእሳት አቃጥሎታል ይሁን እንጂ በተማረኩት የተቀደሱ ፅቃዎች ዝርዝር ውስጥ ስለ ታቦቱ የተወሳ ነገር የለም ነገ ዜና ሰባው የምርኮ ዘመን መነ ጹዋዌ አብቅቶ ምርኮኞቹ የይሁዳ ሰዎች ወደ ምድራቸው ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ወደ ባቢሎን ተማርኮ የነበረውን የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ሁሉ ይዘው ተመልሰዋል በተመለሱት የተቀደሱ ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ አሁንም ታቦቱ አልተጠቀሰም ዕዝ ይህም የሆነበት ምክንያት በኤር የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው ስለዚህ ከባቢሎን ምርኮ መልስ ቅሬታዎቹ የእስራኤል ልጆች በምድራቸው ላይ መርባትና መብዛት ሲጀምሩ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ብለው አልጠሩም የዐዲስ ኪዳን ታቦት እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ ስልቶችና መንገዶች ለብሉይ ኪዳን ሰዎች ተናግሮ ነበር ዕብ ከነዚህም መካከል በታቦቱ አማካይነት ራሱን ለእስራኤል መሪዎች ገልጦ ሕዝቡን ያነጋገረበት መንገድ አንዱ ነው ለማለት ይቻላል ታቦት በብሉይ ኪዳን ዘመን የሰጠው ዋና አገልግሎት ይህ ነውና ሆኖም ታቦት እግዚአብሔር እስከ መጨረሻው የሚናገርበት ብቸኛ መንገድ አልነበረም ስለዚህ ከባቢሎን ምርኮ በኋላ በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ስለ አግዚአብሔር ታቦት አለመወሳቱ ሊያስገርመን አይገባም ይሁንና ብሉይ ኪዳን በዐዲስ ኪዳን ለመተካት የተቀጠረለት ጊዜ ገና ሳያበቃ ታቦት አገልግሎት መስጠት ማቋረጡ ጥያቄ ማስነሣቱ አይቀርም ለዚህ ክሥተት ዋና ምክንያት የሚሆነው የአስራኤል ልጆች በጽላቱ ላይ ተጽፎ የተሰጣቸውን ቃል ኪዳኑን አፍርሰው መገኘታቸው ነው ኤር ነገር ግን ያም ባይሆን ታቦት ፍጹም የሆነው እስኪመጣ ድረስ ጥላና ምሳሌ ሆነው በጊዜያዊነት ከተሰጡት ነገሮች መካከል አንዱ በመሆኑ ብሉይ ኪዳን ፍጻሜን ሲያገኝ የታቦትም አገልግሎት ማክተሙ አይቀርም ነበር የብሉይ ኪዳን ታቦት ከባቢሎን ምርኮ ጀምሮ አገልግሎት መስጠቱን እንደማይቀጥል የብሱይ ኪዳን መጻሕፍት ራሳቸው አስረግጠው መስክረዋል ኤር ጊዜው ደርሶ ትንቢቱ መፈጸሙንና በዐዲስ ኪዳን ከተገለጠው የጽድቅ አገልግሎት የተነሣም ታቦት ቀድሞ የነበረውን የአገልግሎት ክብር ማጣቱንና መሻሩን ደግሞ የዐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መስክረዋል «ዳሩ ግን የአስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለተሻረው ስለፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት አስኪሳናቸው ድረስ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም። የኩነኔ አገልግሉት በክብር ከሆነ ይልቅ የጽድቅ አገልግሉት አንዴት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና ያ የከበረ እንኳ አጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን ዐጥቷልና ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኗልና » ቆሮ ከ የታቦት አገልግሎት በዚህ ሁኔታ መሠረት ቢያበቃም እግዚአብሔር ግን ሕዝቡን ማነጋገሩ አልቀረም እንዲያውም በዐዲስ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ሕዝቡን ያነጋገረበት መንገድ በብሉይ ኪዳን ዘመን ካነጋገረበት መንገድ በእጅጉ የተሻለና የበለጠ ነው ይኸውም ለሚመጣው አማናዊ ነገር ምሳሌ በሆኑ በተለያዩ መንገዶችና ስልቶች ሳይሆን የአግዚአብሔር ቃል እንደሚመሰክረው ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለኛ ተናገረን» ዕብ ል የአግዚአብሔር አንድያ ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱን መልእክት ለኛ በመናገሩ የዐዲስ ኪዳን መካከለኛ ወ። ሆኑን ብቻ ሳይሆን የታቦቱን አገልግሎት መተካቱን ጭምር ወይም ደግሞ የዐዲስ ኪዳን አማናዊ ታቦት መሆኑን ተገንዝበናል ዮሐ ዛሬ ታቦት ባለመኖሩ ቀድሞ የነበረው የታቦት አስፈላጊ አገልግሎትና ስፍራ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መተካቱን የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ሳይቀሩ መስክረዋል በምስክርነታቸውም ያ የቀድሞው ታቦት በምሳሌነት ኢየሱስ ክርስቶስን ለማሳየት እስከ ጊዜው የተሰጠ እንጂ ራሱን ችሎ ለራሱ አገልግሎት የቆመ አለመሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል «ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሄፄ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይኔቅዝ ይትሜሰል ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ ዘኮነ ሰብአ ዘእንበለ ፍልጠት ወኢውላጤ» ትርጓሜ «ከማይነቅዝ ዕንጨት ተሠርቶ ሁለንተናው በወርቅ የተለበጠው ታቦት ያለመለያየትና ያለመለወጥ ሰው የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን ይመስልልናል» ውዱ ማርያም ዘእሑድነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታቦት መባሉን ሲገልጽ ደግሞ ሊቁ ቄርሎስ እንዲህ ብሏል «ወእምድኅረዝ ኮነ ሰብአ ተሰምየ ብእሴ ወመሲሐ ወኢየሱስፃ ወታቦተ ወዐራቄ ወበኩረ ለዘሰከቡ ወበኩረ ለዘይትነሣእ እሙታን ወርእሰ ሥጋዛፃ ለቤተ ክርስቲያን» ትርጓሜ «ሰው ከሆነ በኋላም ብእሲ የተቀባ ኢየሱስሩ ታቦት አስታራቂ ለሙታን በኩር ከሙታን ወገን ለሚነሣም በኩር የቤተ ክርስቲያን ራስ ተባለ ሃይ አቤ ምል ክፍ ቀ በሌላም በኩል ነቢዩ ኤርምያስ ሕጉ በቀድሞው ጽላት ላይ ተጽፎ በታቦቱ ውስጥ መቀመጡ ስለሚያበቃ እንደ ገና በሌላ ዐዲስ የድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሕዝቡ ልብ ላይ ሕጉን እንደሚጽፈውና እንደሚያኖረው በተናገረው መሠረት የዐዲስ ኪዳን ጽላት የምእመናን ልብ ሆኗል ኤር መዝ ቆሮ በመሆኑም ሐዋርያትም ሆኑ ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖች እንደ ብሉይ ኪዳን ሰዎች በጽላት የተጻፈን ሕግ አልተቀበሉም ይህንንም ሲያስረዳ ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የዕብራውያንን መልእክት በተረጐመበት ድርሳኑ እንዲህ ብሷል «ወሐዋርያትስ ኢነሥኡ ምንተኒ ወኢተወፈዩ ዘተጽሕፈ በረቅ አላ ተወክፉ በሰሌዳ ልቦሙ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ» «ሐዋርያት ግን በብራና የተጻፈ ሕግ አልተቀበሉም የመንፈስ ቅዱስን ሀብት በልቡናቸው ሰሌዳነት ተቀበሉ እአንጂ» በተ ድርሳን ቁጥር ብ እንዲሁም ኛ ድርሳን ተጥር ዐን ተመልክት ጥላውንም አካሉንም የማይወክል ታቦት የኢኦተቤክ በዓለም ላይ ካሉት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶም ሆነ ክሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት ለየት የሚያደርጋት በክርስትናዋ ውስጥ የኦሪት ነገሮችን ይዛ መገኘቷ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልዷል ይህም ከመጀመሪያው ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኒቱን ኦሪታዊት እያሰኘ የሰላ ትችት ሲያሰነዝርባት መቆየቱን በመቅድሙ ላይ ተመልክተናል ታዲያ የወንጌልን መንፈሳዊ ጣዕም ያልቀመሱት ተከታዮቿ በያዘቻቸው የኦሪት ነገሮች ልባቸው ነሁልሎ ሲኩራሩና ኦሪታዊነቱን ለቤተ ክርስቲያኒቱ ትክክለኛነት እንደ ዋና ነገር ሲጠቃቅሱት የወንጌሉ ብርፃን በልባቸው የበራ ምእመናኖቿ ደግሞ ለእናት ቤተ ክርስቲያን ማፈሪያና አንገት ማስደፊያ በሆነው በዚህ ጉዳይ እያዘኑና እየጸለዩ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሙሉ በሙሉ ከኦሪት ወደ ወንጌል ዘወር የምትልበትን ጊዜ በናፍቆት ይጠባበቃሉ አንዳንድ ጊዜ ግን እንዲያው ለስሙ የኦሪትን ነገሮች ይዛለች ይባላል እንጂ አንዳንዶቹ የያዘቻቸው ነገሮች ከስማቸው በቀር ከኦሪቱ ጋር ምንም መመሳሰል የላቸውም ዛሬ የኢኦተቤክ ይዛ የምትገኘው ታቦት ለዚህ ጥሩ ማስረጃ ነው ታቦት በብሉይ ኪዳን እንደነበር ይታወቃል የዛሬው በቤተ ክርስቲያናችን የሚገኘውና ታቦት» ተብሎ የሚጠራው ከብሉዩ ታቦት ጋር የሚመሳሰልበትን ነጥብ ለማግኘት ያስቸግራል ስለ ብሉይ ኪዳኑ ታቦት በማስረጃ አስደግፈን ካሁን በፊት በስፍራው ስለተመለክትን እዚህ ላይ መድገሙ ወረቀት መፍጀትና አንባቢን ማሰልቸት ስለሚሆን ከዋና ዋና ማነጻጸሪያ ነጥቦች በቀር ብዙውን ዝርዝር ሁኔታና አስረጂ ጥቅሶችን ትተንና የታለፉ ጉዳዮችን አንሥተን በንጽጽር ማየቱ የነገሩን እውነተኛነት ስለሚያረጋግጥልን የብሉይ ኪዳንን ታቦት ከኢኦተቤክ ታቦት ጋር ቀጥሎ በማነጻጸር እንመለከታለን የሁለቱን ልዩነት ለማነጻጸር «የብሉይ ኪዳን ታቦት» በሚለው ሥር የሚገኘውን ተራ ጥር የኢኦተቤክ» ታቦት በሚለው ሥር ካለው ተመሳሳይ ቀጥር ጋር ያነጻጽሩ የብሉይ ኪዳን ታቦት በጐጥር አንድ ብቻ ነበር አራት ካህናት የሚሸከሙት ሆኖ እግዚአብሔር በሰጠው መለኪያ መሠረት በትልቅ ሣጥን መልክ የተሠራ ነው ለሁለቱ የድንጋይ ጽላት ማስቀመጫም ነው ጽላቶቹ ሁለት ብቻ ሲሆኑ ከድንጋይ የተጠረቡና በፊትና በጀርባቸው ዐሥሩ ቃላት ብቻ የተጻፉባቸው ነበሩ የጻፈባቸውም ሙሴ ወይም ሌላ ፍጡር ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው ካህናት የተሸከሙት አስራኤላውያን ተጓኙች በነበሩበት ዘመን ብቻ ነበር ወደ ርስታቸው ገብተው መኖር ከጀመሩ በኋላ ግን ታቦቱ በበዓለ ንግሥ ስም ከስፍራው አልተንቀሳቀሰም በዔሊ ዘመን ግን ካህናቱ ወደ ጦርነት ይዘውት ወጥተው የነበረ ቢሆንም በፍልስጥኤማውያን እንዲማረክ ሆኖ በኋላ በብዙ ክብር ተመልሷል ሳሙ ከዚያም በአሚናዳብ ቤት ለ ዓመታት ሳሙ በአቢዳራ ቤት ደግሞ ለ ወራት ተቀምጧል ሳሙ ዜና ከዚህ በኋላ ዳዊት ድንኳን አስተክሎ በድንኳን ውስጥ እንዲኖር አደረገ ጌቤና በመቀጠልም ሰሎሞን አባቱ ዳዊት ካስተከለለት ድንኳን ውስጥ ታቦቱን አስወጥቶ ወደ አነጸው መቅደስ ውስጥ አስገባው ነገ ዜና ከላይ በተዘረዘሩት የተለያዩ ምክንያቶች ዳዊትና ሰሎሞን ታቦቱ አንድ ስፍራ ይዞ እስኪቀመጥ ድረስ ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር ሲባል ካህናቱ እየተሽከሙ ልዩ በዓል የተደረገ ቢሆንም ከዚያ በኋላ ግን ቀን ተወስኖለትና የታቦቱ በዓለ ንግሥ ተብሎ ሲከበር በእስራኤላውያን ታሪክ ውስጥ ፈጽሞ አልታየም አልተሰማምም ሌላው ቀርቶ እስራኤላውያን እንዲያከብሯቸው በታዘዙት በዓላት ላይ እንኳ ታቦቱን እንዲያነግሥ የተሰጣቸው መመሪያ ባለመኖሩ ታቦቱን አላነገሠም የእግዚአብሔር ቃል እንዲያውም መቅደስ ከተሠራ በኋላ ካህናቱ ታቦቱን ከመሸከም ማረፋቸውን ይናገራል ዜና ታቦቱ የተጠራው በእግዚአብሔር ስም ብቻ ነው የሰጠው ዋና አገልግሎት ሕዝቡን በመሪዎቻቸው በካህናት አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት ነበር ከዚህ በቀር የኅብስት ገበታም ሆነ ሌላ መሠዊያ ሆኖ ያገለገለበት ሁኔታ ፈጽሞ የለም የኢኦተቤክ ታቦት ዮተጥሩ እጅግ ብዙ ነው ይህን ያህል ይሁን ተብሎ የተወስነ ቀጥር ባለመኖሩም ወደፊት ቀጥሩ እየጨመረ እንደሚሄድ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል አንድ ቄስ ብቻውን የሚሸከመው መሆኑ አንድ ልዩነት ሲሆን እንዲሁ በልማድ ጽላት የሚባለው ዝርግ ሰሌዳ ታቦትም ተብሎ ይጠራል እንጂ በታቦት ስም ለመጠራት የሚያበቃ የታቦት መልክና አሠራር ፈጽሞ የለውም ብፁዕ አቡነ መልከ ጹዴቅ በመጽሐፋቸው እንደህ ብለዋል ፌ በአሁኑ ጊዜ የጽላት ማኅደር ታቦት ስለሌለ የጽላት ማኅደር የሆነው መንበር ነው ወይዑዱ ታቦተ» ሲል መንበሩን እንደሆነ ያመለክታልና» ካሉ በኋላ ይህም አገላለጽ ፈራሽ መሆኑን በሌላ አስረጂ ሲገልጹ ሆኖም መንበሩን ለይቶ መንበረ ታቦት ምሥዋዕ ሲለው ይገኛል» ብለዋል በመቀጠልም ልማዳዊውን ስያሜ ሲያስረዱ እንደ ደንቡ ጽላት ወይም ጽሌ መባል ይገባዋል ምክንያቱም ታቦት የሚባለው የጽላቱ ማኅደር ነውና በአሁኑ ጊዜ ግን ጽላትም ሲሉ ታቦትም ሲሉ ያኑ ጽላቱን ነው ብለዋል ትምህርተ ክርስትና ኛ መጽሐፍ ገጽ አንድ ጊዜ ታቦት በሌላ ጊዜ ጽላት መባሉ የሚያደናግር ቢመስልም በሁለቱም ስም የሚጠራው ያው አንዱ ዝርግ ሰሌዳ ነው የሚሠራውም ዐልፎ ዐልፎ ከዕብነ በረድ አብዛኛውን ጊዜ በተለይም ደግሞ በዘመናችን ከዕንጨት ነው የጽላቶቹን መጠን በተመለከተ አንድ ወጥ በሆነ መስፈርት ሳይሆን እንደ ሠሪው አለካክ በተለያየ መጠንና ውፍረት የተሠሩ ናቸው በሰሌዳው ላይ ዐሠርቱ ቃላት እንደተጻፈ አድርገው ብዙዎች በመናገራቸው ሕዝቡ ይህንኑ ተቀብሎ ይኖራል እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው በአገራችን ጽላቶች ላይ ዐሠርቱ ቃላት የማይጻፍባቸው መሆኑን ስለአሠራሩ የሚያስረዳውን መጽሐፍ የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ በመመልከት ለማረጋገጥ ይቻላል የሚጻፉትና የሚቀረጹት ሌሎቹ ነገሮችም ቢሆኑ ሰው እንጂ እግዚአብሔር ያልጻፋቸውና ያልቀረጻቸው ናቸው የቅዳሴ ማርያም አንድምታ በአገራችን ጽላቶች ላይ የሚጻፈውንና የሚቀረጸውን አስመልክቶ የሚከተለውን ያትታል የሚጻፈው ሀ ታቦቱ የማርያም የኢየሱስ የዮሐንስ ወንጌላዊ ከሆነ በመጀመሪያ አልፋ ወኦ የሚለው የጌታ ስም ቀጥሎ የዮሐንስ ወንጌላዊ በመጨረሻም ምስለ ፍቁር ወልዳ ማርያም ከተወዳጅ ልጂ ጋር ለ ታቦቱ የሰማዕት የጻድቅ ከሆነ በመጀመሪያ የጌታ ከአጠገቡ የዮሐንስ ወንጌላዊ ቀጥሎ የጽላቱን ባለቤት የሰማዕቱን ወይም የጻድቁን ስም በሦስተኛ ደረጃ ምስለ ፍቁር ወልዳ የሚቀረጸው የሚሣለው ከላይ የሥላሴ ዝቅ ብሎ የእመቤታችን ከዚያም ሰማዕትም ጻድቅም ቢሆን የጽላቱ ባለቤት ይቀረጻል ቅዲ ማርያም በኀበ ኩሉ መካን ርእስት አንቲ የሚለውን ሐተታ ተመልከት በዚህ ውስጥ በመላእክት ስም ስለሚቀረጸው ጽላት የተባለ ነገር የለም የአገራችን ጽላት እልፍ አእላፋት እንደመሆናቸው መጠን በጐራጥራቸው ልክ በዓለ ንግሥ ተሠርቶላቸዋል ባማሩና ባሸበረቁ መጐናጸፊያዎች አጊጠው በቀሳውስት ተሸካሚነትና በሕዝቡ አጃቢነት ከየመቅደሶቻቸው ወጥተው ሕንጻውን ሦስት ጊዜ በመዞር ይዘመርላቸዋል ይዘፈንላቸዋል ይሰገድላቸዋል መቼም በዚህ ሁኔታ እየተመለክ ያለውን ታቦት ከኦሪቱ ታቦት ጋር ማመሳሰል ብርፃንና ጨለማ አንድ ናቸው ከማለት በምንም አይለይም እነዚህ የአገራችንን ታቦታት ከሚሰጣቸው አምልኮና ስግደት አንጻር እናመሳስል ከተባለ ግን ሊመሳሰሉ የሚችሉት በኢሳ ኤር ላይ ከተገለጸው ጋር ነው በአምላክ ስም የተጠሩ ጥቂቶች ቢኖሩም አብዛኛዎቹ በሚታወቁና በማይታወቁ ቅዱሳን መላእክትና ሰዎች ስም የተሰየሙ ናቸው አገልግሎቱ የሥጋሁ ወደሙ መፈተቻና ማስቀመጫ ነው ይህንንም የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየመጽሐፎቻቸው አስረድተው ጽፈዋል ብፁዕ አቡነ መልከ ጹዴቅ «የጻሕሉና የጽዋው ማስቀመጫ የመሥዋዕቱ መክበሪያ ታቦት ወይም ጽላት ይባላል» ትምህርተ ክርስትና ኛ መጽሐፍ ገጽ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስም «የደብተራ ኦሪት ጽላት እግዚአብሔር ጅ በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጽበት ዙፋን ነበር ይህ ግን የአገራችንን ታቦት ማለታቸው ነው የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት የምሕረት ምሥዋዕ ነው» የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ እንግዲህ ስሙ ብቻ ታቦት ወይም ጽላት ይሰኝ እንጂ በአሠራር በይዘትና በአገልግሎት ከኦሪቱ ታቦትና ጽላት ጋር ፈጽሞ አይመሳሰልም ይህን ባለማስተዋል ግን አንዳንድ ወገኖቻችን በስሙ ከተጠራ አይቀር ብለው ስለ ኦሪቱ የእግዚአብሔር ታቦት በብሉይ ኪዳን የተጻፈውን ሁሉ ለዚህኛው ሰጥተው በመተርጐም ታቦታችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው በማለት ክርክር ያነሣሉ ያልተጻፈለትን እየጠቀሱ መከራከሩ ብዙ እንደማያዋጣ የተረዱት አልረታ ባዮች ደግሞ ለታቦቱ የምንሰግደው የአክብሮት ስግደት ነው ከማለት ዐልፈው ተርፈው በታቦቱ ላይ የተጻፈው የጌታ ስም በመሆኑ በፊልጵስዩስ መሠረት ታቦቱ ላይ ለተጻፈው ስሙ ነው የምንሰግደው ሲሉ ይደመጣሉ ይህን አባባል ገና ከእነርሱ ሰማን የእግዚአብሔር ቃል ግን እንዲህ አላስተማረንም ስሙን የሆነ ነገር ላይ ጽፈንና ከፊታችን አድርገን እንስገድ ከተባለ ለጌታ በአውነትና በመንፈስ መሰገዱ ዋጋ ሊያጣ ነው ዮሐ ፌ በፊል ላይ የምናነበው ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ በማድረግ እስከ መስቀል ሞት ድረስ ታዛዥ በመሆኑት እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ እንዳደረገውና ከስም ሁሉ በላይ ያለውን ስም እንደሰጠው በዚህም ምክንያት በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ፍጥረታት ሁሉ በኢየሱስ ስም እንዲንበረከኩና መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር የኢየሱስን ጌትነት እንደሚመሰክር የሚናገር ነው ቃሉን እነርሱ በሰጡት ትርጉም መሠረት እንቀበለው ቢባል እንኳ ስመ አምላክ ተጻፈበት የሚባለው ጽላት የሚገኘው በኢኦተቤክ ብቻ ስለሆነ በሰማይና ከኢትዮጵያ ምድር ውጪ ባለው ምድር ከምድርም በታች ያለው ፍጥረት በኢየሱስ ስም መንበርከኩ ፋይዳ ላይኖረው ነው ማለት ነው ይህንና የመሳሰለውን ስንመለከት ታቦት እየተባለ የሚጠራው ዛሬ በሕዝቡ ልብ ትልቅ ስፍራን ያገኘው እንዲህ በቀላሉ አለመሆኑን እንረዳለን የታቦቱ ፈጣሪዎች ተቀባይነትን እንዲያገኝላቸው የአግዚአብሔርን ቃል ትርጐም አስከ ማዛባት የደረሰ ሸፍጥ በመሥራት ብዙ ደክመውለታል ከድካማቸው ውስጥ የማይዘነጋው በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረው የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል በማለት የፈጠሩት ታሪክ ገው ለዚህ ታሪክ አንደ መነሻ የሚጠቀሰው ንግሥተ ሳባ ሰሉሞንን የመጐብኘቷ ታሪክ ነው ነገ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ካሰፈረው ታሪክ ውጪ ይህን ጫፍ ይዞ ክብረ ነገሥት የተባለው መጽሐፍ ንግሥቲቱ ወደ ምድሯ ስትመለስ ከሰሎሞን ፀንሳ አንደተመለሰችና ቀዳማዊ ምኒልክን እንደ ወለደች ቀዳማዊ ምኒልክም ሲያድግ አባቱን ሲተዋወቅ እንደ ፄደና በዚያ ቆይታ አድርጎ ሲመለስ ከአባቱ ከተሰጡት ካህናትና ሌዋውያን ጋር በመመሳጠር የእስራኤላውያንን ታቦት በስርቆት ወዉደ ኢትዮጵያ እንዳመጡት ይተርካል ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቃል የሚነገር ታሪክም አለ ይኸውም በኢየሩላሌም መቅደስ ሁለት ታቦታት እንደ ነበሩና አንደኛው ታቦተ ማርያም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ታቦተ ሚካኤል እንደ ሆነ ንጉሥ ሰሎሞንም ከሁለቱ መካከል ለልጁ ለቀዳማዊ ምኒልክ እንዲሰጥ የፈቀደው ታቦተ ሚካኤልን እንደነበር ነገር ግን ካህናቱ አለዋውጠው ታቦተ ማርያምን እንዳመጡ የሚተርክ ነው ባፍም በመጣፍም ሲነገር የመጣውን ይህን ትረካ አንዳንቀበል የሚያደርጉ ብዙ እውነታዎች አሉ ዋናው መሠረታዊ ምክንያት ግን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት የሚናገረው ነው በሰሎሞን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጣ የተባለው ታቦት ከሰሎሞን በኋላ ብዙ ዓመታት ቆይቶ በነገሠው በኢዮስያስ ዘመን በዚያው በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ እንደነበረ ዜና ያስነብበናል «ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት እንደሚታወቀው ሰሉሞን ከ ዓዓ የነገሠ የአስራኤል ንጉሥ ነው ኢዮስያስ ደግሞ ከ ዓዓ ድረስ የነገሠ የይሁዳ ንጉሥ ነው በሰሎሞንና በኢዮስያስ መካከል የ ዓመት ልዩነት አለ ማለት ነው ሰሎሞን ከሞተ ከ ዓመት በኋላ እንኳ ታቦቱ ከኢየሩሳሌም አልወጣም ነበር ስለዚህ ከ ዓመት በፊት በሰሎሞን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጣ የሚለው የክብረ ነገሥት ትረካና ሌላውም አፈ ታሪክ በቀጥታ ፈጠራ ነው ከሚሰኝ በቀር ሰሚም ተቀባይም የለውም በተለይም በቃል የሚነገረው ታሪክ ዐይን ያወጣ ውሸት ለመሆኑ ምስክር አያሻውም የታሪኩ አቀነባባሪዎች ግን ታሪኩን በዐላማ እንደ ፈጠሩት ፈጽሞ ልንዘነጋው አይገባም ምክንያቱም በፈቃዳቸው በተለያዩ ስሞች ታቦታትን አባዝተውና አራብተው ሕዝባችን እንዲቀበላቸው ለማድረግ የፈጠራው ታሪክ መንገድ ጠራጊ ሆኖ አገልግሏቸዋል በቤተ ክርስቲያናችን በኦሪት ዘመን በእግዚአብሔር ስም ብቻ የተጠራውን ታቦት «ታቦት ጽዮን» ብሎ መጥራት የተለመደ ነገር ሆኗል ታቦቱ በጽዮን ከተማ ያለ ታቦት መሆኑን ለመግለጽ ታስቦ የተሰጠው ስያሜ ከሆነ ከአውነታው ብዙም የሸሸን አንሆንም ጉዳዩ ግን ሌላ ነው አንዲህ ብሎ መጥራት ቀስ በቀስ ጽዮን ማርያም» ስለሆነች ታቦተ ጽዮን የማርያም ታቦት ነው ወደሚል ድምዳሜ አምጥቶናል መቼም ቅድስት ድንግል ማርያም ባልኖረችበት ዘመን ለአስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ስም የተሰጠውን ታቦት የማርያም ታቦት ነው በማለት ጤነኛ ሰው አይናገርም የሆነው ሆኖ ከእግዚአብሔር ላይ ተቀምቶ በማርያም ስም ታቦቱ መጠራት ከጀመረ በኋላ በዚሁ ብቻ ሳይወሰን ሌሎች ሰው ሠራሽ ታቦታት በሚታወቁና በማይታወቁ ስሞች መጠራታቸው ቀጥሏሷል እንግዲህ በታቦት ስም ምን እየተሠራና ወደ የት እያመራን እንደሆነ ልናስተውል ይገባናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያልሆኑትን ሌሎቹን አብያተ ክርስቲያናት ትተን ከአገራዊ ባህልና ልማድ ውጪ በአስተምህሮ ከኢኦተቤክ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትን ከተመለከትን እንደ አገራችን ያለ ታቦት የሌላቸው መሆኑ የታወቀ ነው ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ግን በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ታቦት ተለመዴ ነገር መሆኑን ጽፈዋል የኢቤክታሪክ ገጽ ይህ ምናልባት የአሁኑ ታቦት በሌሎቹ ሳይኖር በኢኦተቤክ ብቻ እንዴት ሊኖር ቻለ። የሚል ጥያቄ እንዳይነሣ ለማድረግ ሲባል የተነገረ ይመስላል አሳቸው «ታቦት» የሚል ስያሜ የሰጡትን ንዋየ ቅድሳት አብያተ ክርስቲያናቱ ታቦት ነው ብለው የተቀበሉበትን ማስረጃ አናገኝም ለምሳሌ ግብጻውያን «ሉሕ» ይሉታል አርሱም የጐርባኑን ኅብስት የሚይዘው ጻሕልና ወይኑ የሚጨመርበት ጽዋዕ የሚቀመጡበት በተለያዩ ቀለማትና በሐረግ ያጌጠ ጠረጴዛ ነው የተቀሩትም የግሪክ የሩስያ የሩማንያና የመሳሰሉት አብያተ ክርስቲያናትም የጌታ ስቅለት ወይም ግንዘት የተሣለበት የነጭ ሐር መጉጐናጸፊያ በጠረጴዛው ላይ ይዘረጋሉ አገልግሎቱ ከግብጾች ሉሕ ጋር ተመሳሳይነት አለው ይሁን እንጂ በኛ ዘንድ እንደሚደረገው ታቦት ብለው ቀሳውስት ተሸክመው የሚያከብሩትና ወድቀው የሚሰግዱለት አይደለም ምናልባት እንዲህ አድርገው ቢገኙ እነርሱም ስሕተተኞች ይባላሉ እንጂ ተመስግነው አድራጎታቸው እንደ ትክክለኛ ማስረጃ ሊቀርብ አይችልም እንግዲህ እስካሁን የአገራችን ታቦት በብዙ መንገድ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን ተመልክተናል ሰዎች ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊና ታሪካዊ ለማስመሰል ከተቻላቸውም ለማድረግ የተለየዩ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል ያም ቢሆን በመጽሐፍ ቅዱስ አውነት ፈራሽ ነው ሰዎች ለዐላማቸው መሳካት ሲሉ ያቀናበሩት ታሪክ ውሸት ነው ካልን ስለ አገራችን ታቦት አመጣጥና አጀማመር የሚናገር ሌላ ተአማኒነት ያለው ትውፊታዊ ታሪክ መፈለግ የግድ ሊኖርብን ነው ትውፊታዊው ታሪካችን እንደሚያስረዳን ታቦት ወይም ጽላት የሚባለው ሰሌዳ አንደ አምላክ ተቁጥሮ ስግሂትና አምልኮ ወደሚቀበልበት ደረጃ ከመሸጋገሩ በፊት አንድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን ለመትከል እንደ ፈቃድ መስጫ ሰነድ በመሆን ያገለግል ነበር ይኸውም አንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ሲታሰብ የአካባቢው ምእመናን ለመንበረ ጵጵስናው ጥያቄ ያቀርባሉ መንበረ ጵጵስናውም ቤተ ክርስቲያን ሊያሟላ የሚገባውን ማንኛውንም መስፈርት ማለትም የአገልጋዮችን ብዛትና ብቃት የምእመናኑን ብዛት ምእመናኑ ለቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ የሚሆኑ ወጪዎችን መሸፈን የሚችሉ መሆናቸውንና መሰል ጉዳዮችን ካጣራ በኋላ መስፈርቱን አሟልቶ ቢገኝ ፈቃድ ይሰጣል እንደ ፈቃድ ማስረጃ ይሰጥ የነበረውም ከዕንጨት ወይም ከድንጋይ የተሠራ ዛሬ ታቦት ወይም ጽላት ተብሉ የሚጠራው ሰሌዳ ነበር በሰሌዳው ላይ የሚጻፈውም በኛው ገጽ ላይ አህያ ሼር አህያ «አህያ» የሚለው ስም ላልቶ ይነበብ ኤልሻዳይ አዶናይ ጸባዖት የተባሉና በብሉይ ኪዳን የተገለጹት ሦስት መለኮታዊ ስሞችና በተጨማሪም አልፋ ኦሜጋ አልፋ ወዖ የተባሉ ሁለት የዐዲስ ኪዳን ስሞች እንዲሁም የውጣ ወይም የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ መጀመሪያ በግሪክ ፊደል ይጻፋል በኛው ገጽ ላይ ደግሞ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ ስም የፈቃጁ ጳጳስ ስም በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ስም አንዳንድ ጊዜም የዕጨጌውሩ የቤተ ክርስቲያኑ ገበዝና የክፍሉ ምስለኔም ታክሰው ይጻፍ ነበር ጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቀ ገጽ ምናልባት ቀደም ብለው በተተከሉት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በዚህ መልክ የተሠሩትን የቀድሞዎቹን ታቦታት እናገኝ ይሆናል እንጂሩ በአሁኑ ሰዓት የቀድሞውን የታቦት ይዘት አናገኝም አሠራሩ ሁሉ ተለውጧል ዛሬ እንዲያውም በሐረግና በመስቀል ቅርጽ ብቻ ያጌጠ ታቦት መቀረጽ መጀመሩን እንረዳለን የተከበሩ አቶ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ «የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ይኩኖ አምላክ እስከ ዐፄ ልብነ ድንግል» በተሰኘው መጽሐፋቸው ገጽ ላይ በዚህ ዘመን ያለውን የታቦት የላት አቀራረጽ ሁኔታ በተመለከተ በቅርቡ ከቱሉ ዲምቱ የተገኘውን ጽላት ፎቶ ግራፍ አውጥተውታል አንባቢ እንዲያገናዝበው በማሰብ በዚህ መጽሐፍ ላይ ያው ፎቶ ግራፍእንዲወጣ ተደርጓል ከዚህም በተጨማሪ የብሉይ ኪዳን ታቦት አሠራሩ ምን ዐይነት እንደነበረ የሚያሳየው ሥዕል ለንጽጽር ቀርቧል የአገራችን ታቦት በምን ዐላማ ተጀምሮ በዘመናት ጉዞ ውስጥ የአገልግሎቱን ዐላማና አቅጣጫ በመሳት ዛሬ እንደ ቀድሞው የእግዚአብሔር ታቦት መቁጠርና ወደ መመሰክ እንደ ተሸጋገረ እናስተውል። ስንክ መስ። ንፍቀ ታቦት ማቴጸሀ ወ ። ታቦት ዘመርጡል ፓታቦጉ ሕ ። ጸጵት እምቅድመ ያልብስ ታቦተ ወይኩን ታቦት ዘይፈልስአመካንው ከተመካገክመ። ስንክ መስ ። ስንክ ግንኔ ። ጽሌ ላንድ ጽላት ለኹለት ለብዙም ይ ጾኖል ።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

تعليقات:


memezon

خيارات التنزيل | تحويل إلى قوات الدفاع الشعبي | كتاب اليوم

© dirzon | شروط الخدمة | خصوصية | حول | خدمات | اتصال