Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ከ እንጨት አለዝቦ ጣዖት አድርጎ የሚያቆም ማንም የለም እናንተም በቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት ላይ ብትሰብኩ መልካም ነው። ሃይማኖት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ራሱን የገለጠበት መንገድ ነው። ራሱ አምላካችን እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከማለት ይልቅ ያከበራቸውን የቅዱሳኑን ስም ማስረሳት ምን ማለትህ ነው። ሳራ እውነት እህቴ በሠራሁት ሥራ በጣም ተፀፅቻለሁ ራሴን ለማስተካከል እየጣርኩ ነው። ይሄ የሚያሳየው እግርሽ ስንት ቦታ እንደረገጠ ነው። ጊዜው እኮ የሱባኤ ወቅት ነው። ሶስና እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ተማሩ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ሊጠራ አልመጣምና ነው። በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና እነሆ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው።
ምዕራፍ አንድ ሥነ ግጥም ሇዊ ግእዝ በል ሆ ግእዝ በል ይሻልሃል ቅድመ ዓለም የነበረ በፍጥረቱ ይታይሃል ሐመ ወሞተ በእንቲአነ ኃያል ወልድ ፍቅር በመስቀሉ ያጸናሃል ለክፉ ቀን ጥማት የሕይወት ውኃ ይሆናል ሁ ካዕብ በል ሰብሑ ለስመ እግዚአብሔር የሰማዩ መና በምድር ተገልጦል የመላእክት እንጀራ ለሰዎች ተሰጥቷል ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለህ የርሃብ ቀን ምግብ ድኅነት ይሆንሃል ሟ ሣልስ በል ዘልማዱ ጊሩት ችር ጠባቂ ነፍሱን ቤዛ አድርጎ ለበጎቹ የሰጠ ዘጠና ዘጠኙን ትቶ አንዱን በበረሃ የፈለገ ዛሬም ይጠራሃል ራብዕ በል ሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ ከአባቶችህ ሀገር ለመድረስ ተራራውን መወጣጫ እንዳትስት መንገድ ብርሃን ይሆንሃል የሚጠቁም አቅጣጫ ሄ ሀምስ በል ሔት ብሂል ሕያው እግዚአብሔር ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ለዘለዓለም የሚኖር ሕያው አምላክ መሆኑን ብትመሰክር ልበ ጠበብት ትሆናለህ አዋቂ የወንጌል ገበሬ የስንዴ ምርት መጋቢ ሳድስ በል ኅብስት ለርኀባን በመስቀል ላይ የተቆረሰ ጥማችንን ሊያረካ ደሙን ያፈሰሰ ማን አለ በወዳጆቹ ቤት የቆሰለ ሞትን ወስዶ ሕይወቱን የከፈለ ከመንገድህ ፈቀቅ ብለህ በርሀብ እንዳትሞት በጠባቧ በር ጠንክር የሲኦልን ባሕር እንድትሻገር በርታ እንዳትረታ አጥብቅ ምርኩዝህን በርታ ጥበቅ አጥብቅ ጉብዝናህን ሇ ሳብዕ በል ንሴብሖ ለእግዚአብሔር በል የቃሉን ትምህርት ሰምተህ የእጆቹን ተአምራ አይተህ ከዲያብሎስ ነጻ ወጥተህ በስሙ ተጠርተህ ሥጋውን በልተህ ደሙንም ጠጥተህ ንሴብሖ ካላልክ ተራራ ስትወጣ ድንጋይ ይፈነቀልና ይመታሃል አለት ሆ በል ቅኔ ዝረፍ የሰው ስትፈልግ እንዳታዘረፍ ጥበብ ሸማ ማግህን ግእዝ ሁ ካዕብ ማለት ሚስጢር ነው የሚነግርህ ማንነትህን ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም የዳዊት ልጅ መድኃኔዓለም በኪሩቤል ግርማ የሚቀመጥ አልፋና ኦሜጋ በቀስተ ደመና ላይ ዙፋኑን የዘረጋ በእሳት መድረክ ላይ የሚመላለስ በሱራፌል የሚቀደስ የሚወደስ ሰባት መቅረዝ በፊቱ የሚያበራ መንጦሳእትህ ብርሃን ማደሪያህ የሚያስፈራ በልዩ ልዩ ቅኔ በመለከት ድምዕ በመብረቅና በነጐድጓድ የምትገስዕ ዓይኖችህ እንደ እሳት የሚያበሩ እግሮችህ እንደ ነጠረ ነሀስ የመሰሉ የልብስህ ዘርፍ ቤተመቅደሱን የሞላ የኃያላን ኃያል ባለብዙ ሺህ ሠረገላ በማደሪያህ በጸባኦት ባይቻለን አንተን ማየት ልትባርከን በበረከት ልትፈውሰን በምህረት የአዳም ልጅ የአግዚአብሔር ልጅ ልትጨበጥ ልትዳሰስ በአህያ ላይ ተቀምጠህ አገኘንህ ቤተመቅደስ ሆሳዕና በአርያም በጌታ ስም የሚመጣ ከምርኮ አገር ከባርነት የሚያወጣ ብሩክ ቅዱስ የአበው ተስፋ የመርገም ጨርቅ ባንተ ጠፋ የነቢያት ትንቢት የጽድቃቸው ዜና የሕይወት እንጀራ የእስራኤል መና ቃል ከስጋ ጋራ በተዋሕዶ ጸና በሰማያት የተከለልክ የተጋረድክ በደመና በምድር ላይ ተመላለስክ ታየህ በጎዳና አላዋቂ በማስተዋሉ ተደገፈ በጥበቡ አመነ የዚህ ዓለም እውቀት ግን ከንቱ ሆነ በማኅበር በጉባኤ መካከል ተገለጠ የዋህ ሆኖ የጽዮን ልጅ በአህያ ላይ ተቀመጠ ከህፃናት ከሚጠቡ አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ከንፈሮቻችንን ለምስጋና አንደበታችንን ለዝማሬ ከፈትህ እኛም ልጆችህ ይዘን ዝንጣፊ ዘንባባ በሐሴት ተመልተን አሸብርቀን እንደ አበባ የሰላም ንጉስ መድኃኔዓለም ስለ ስምህ ተቀኝተናል ሆሳዕና በአርያም ዕግትዋ ለጽዮን ያዳውራል የጠላት ሰበቃው ኩናቱ እስራኤልኣዊነት ካዛብ መለየቱ በሺህ ቢደበደብ አይታክት እውነቱ ኢዝራኤል ቢወረር ጽዮን አምባይቱ። እርሱ እግዚአብሔር ሠራት አያት ሰፈራትም ጥበብ እናቴ ቤተክርስቲያን ድኅነቴ የሕይወት ቤት መሠረቴ እንደ እንቁ የሚያበሩ ከዋክብት ልጆችሽ ምስክሮች ሁነው ዘመን አሻገሩሽ ዛሬም በኛ ልብ ውስጥ ጸንተሽ ትኖሪያለሽ የአብራክሽ ክፋዮች ቢቆጠር ዘራቸው በገድል ትሩፋት ይህው በእኛ ዘንድ የታወቁ ናቸው ነገስታት ነበሩ ጠፍር የታጠቁ በጥበብ የላቁ ምስጢርን ያራቀቁ ወልድ ዋሕድ ብለው ኃይማኖት ያጸኑ ሰውን ሰው ያረጉ ሀገርን ያቀኑ በአጥንታቸው ድንበር ቅጥሩን የቀጠሩ በደማቸው ድርሳን ታሪክ የዘከሩ ገዳም የገደሙ ደብር የደበሩ መስቀል የተከሉ አለት የወቀሩ ፊደል በገበታ ቆጥረው የቀመሩ የሰማይ ስርዓት በምድር የሰሩ እኒያ ብርቱ ልጆች እንደ እንቁ የሚያበሩ የአምላክን ሰው መሆን የልደቱን ምስጢር የክርስቶስ ፍቅሩን የመስቀሉን ነገር ውለታውን ሰፍሮ ለመክፈል ብድሩን ቢተጉ ቢያስሱት ገፀ በረከቱን ስጦታው አንድ ሆኖ ምስጋናን አገኙት በቀንና ሌሉት ቢያዜሙ ቢቀኙት የምድር ብልፅግና የአፍላጋቶን እውቀት ቢበሉት ቢበሉት ቢጠጡት ቢጠጡት ልባቸው ባይረካ ቢቃጠል በፍቅር ከአርያም ደርሶ ከመላዕክት ሀገር ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊ ድምፀ መልካም ማህሌታዊ ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ እምሰማይ እያለ ሃሌ ሉያ ብሎ መላዕክት መሰለ ባኮስ ጃንደረባ ቀዳማዊ ሐዋርያ ሕጽዋ ለሕደኬ ንግስተ ኢትዮጵያ አፄ ካሊብ መናኝ ንግስናው በርሃ ቅዱሳን ነገስታት አብርሃ ወአጽብሃ ገብረ ማርያም ላሊበላ ነአኩቶለአብ ይምርሐ የጻድቅ ከተማ የጥበባት ማዕድ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘደብረ ነጐድጓድ የወንጌል ገበሬ አርበኛ ተጋዳይ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ የኃይማኖት ተክል ካህናተ ሰማይ የእውቀት ብርሃን የምስራቅ በር መውጫ ዓምደ ሃይማኖት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መሐርኩኪ በለኝ ፀሎት ትረፋቱ መጠለያ አንባ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ በግብጽ ንሂሳ ምስራች ተሰማ ገና በማህጸን ጌታው የመረጠው የወንጌል አውድማ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብሎ እንደ መላእክቱ ምስጋናን ወደደ ጸጉር የለበሰ ወተት የማይቀምስ ህፃን ተወለደ ለሰው ለጆች አምባ ተጋዳይ አርበኛ በበረሃ ኖረ አንበሳና ነብሩን አድርጎ ጓደኛ ገዳምን ገደመ ልጆቹን አጸና ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያን ባረከ ዝቋላን አቀና የሰው ልጅ እንዳይወድቅ በኃጢአት ጐዳና ዲያቢሎስ እንዲማር አምላኳን ተማፅና ሲኦልን ያንኳኳች የእርቅ ሐዋርያ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ኮከብ ዘአቅሊሲያ ጥበብ እናቴ ቤተክርስቲያን ድኅነቴ የሕይወት ቤት መሠረቴ እንደ እንቁ የሚያበሩ ከዋክብት ልጆችሽ ምስክሮች ሁነው ዘመን አሻገሩሽ ዛሬም በኛ ልብ ውስጥ ጸንተሽ ትኖሪያለሽ ያኔ ስትገለጥ በግርማ መንግሥትህ በቀኝም በግራም የምንቆም ልናይህ ልትከፍል ዋጋችንን ልትሰጥ በክህልናህ ሲገለጥ ችሎትህ የማይዛባ ሚዛንህ በወንድም እህቱ ላይ በክፋት የቆመ እሱ ነው እሷ ናት እያለ ጣቱን የጠቆመ ፍቅር እንዲጠፋ ጠዋት ማታ የለፋ እኔ ብቻ ብሎ ራሱን ያኮፈሰ ወንድሙን ለፍቅረ ንዋይ ሲል በግፍ የከሰሰ የእጅህን ሥራ ሁሉ በግፍ ያቃለለ ድሀውን በማንኳሰስ ጨርቃም ያለ ፍርድን ስታደርግ በመለኮትህ ኃይል በዓይኑ በብረቱ ያን ጊዜ ያይሃል እንግዲህ። የደስታ ምንጭ ሆና ኀዘንተኛዋ ናት እንደ ቀማ ወንበዴ ዱር እንዳለ ሽፍታ ሀገር እንዳጠፋ ተሰቀለ ጌታ እንደ ትንቢቱ ቃል እንደ ተነገረ ረዳት እንደ ሌለው ሆነ እንደተቸገረ ባየነውም ጊዜ አሳከበርነውም እንወደውም ዘንድ ደም ግባት የለውም እኛ ግን መታነው እሱ ታገሰልን እኛው አደማነው ደምን ለበሰልን ልብን የሚጠግን ልቡ ላይ ወጋነው በችንካር ቸንክረን በዋንጫ ቀዳነው አቤቱ አምላኬ ታማኙ መድኅኔ እሺ ብለህ የሞትክ ለሰቀልኩህ እኔ ስለ ኃይል ትርጉም በብርታት ስጠብቅ አንተ በትህትና መጣህ ልታሳውቅ ስህተት በሞላበት የኃይል ግንዛቤ ትዕቢት በገነባው እንዳይገኝ ልቤ አቤት የአንተ ፍቅር አቤት የአንተ ነገር በዚያች ጭንቅ ሰዓት ስለ ሰቃዮችህ መዳን ታስብ ነበር ያ ስደት የኔ ነው የኔ ነው ሰንበሩ ርጩኸትህም ዕሬጩኸቴ የኔ ነው ችንካሩ በደሌን ቻልክልኝ ሆነህ በኔ ቦታ ሞትህ ሞቴ ነበር መድኃኒቴ ጌታ ልኖር ተወልጄ ሞት ስላሸነፈኝ ልጄ በርታ እያልከኝ አንተ ልትሞት መጥተህ ማሸነፊያ ሆንከኝ ግን ያችን የኀዘን እናት ያችን ብላቴና ምን ብዬ ላጽናናት ድንግል ስለ ልጀ ዛሬ ኀዘን ላይ ናት በጸሎትህ ጠብቅ ከቅዱሳን አበው የሆነ ውልደትህ የጸሎታቸው መልስ ለእናት አባትህ ክብርህ እጅግ በዛ እንደራስ ጠጉርህ ፍጥረት ያስደሰተ የውልደትህ ዜና ገና ህፃን ሳለህ የጀመርክ ምሥጋና ጽድቅን ተጎናጽፈህ ወንጌል ተጫምተሐል በጉብዝናህ ወራት መስቀሉን ሽተሃል እንደጠዋት ጠዛ በምትረግፈው ዓለም ልብህ ሳይሸነፍ ለምቾት ሳትደክም ከትዳርህ ይልቅ ምንኩስናን መርጠህ ከጫጉላ ቤት ወጥተህ በረኸ ተገኘህ እንጦንስ አባትህን አርገህ አርአያ የመላእክት አስኬማን የለበስህ ሐዋርያ እልፍ አእላፍ ያፈራህ የጽድቅ ዘንባባ ቃል ኪዳንህ ጽኑ መጠለያ አንባ ከሰይጣን ተጋድለህ ያሸነፍክ አርበኛ ዐቃቤ ሃይማኖት የሥርዓት ዳኛ አራቱን ወንጌላት ዞረህ አስተምረሃል በመብረቅ ጸሎትህ አጋንንት ጠፍተዋል ትእግስት ጽንአትህ በአምላክህ ተደንቋል መምህረ ሰላም ፍቅር ወአንድነት ለአንተ ይገባሐል ስለ አምላክህ ክብር የተጋደልክ ጸንተህ እንደ ተወደደ የዘይት ዕንጨት ነህሀ የተጋድሎህ ፍሬ መዓዛው ያውዳል እልፍ አእላፍ አምነው ባንተ ተጠምቀዋል የብርሃን ደመና ጠቅሰህ ተጉዘሃል በጸሎትህ ኃይል ሙት አስነስተኻል ገድል ተአምርህን የወንጌሉን ሥራ አቡነ ዜና ማርቆስ ሆይ መካነ ጸሎትህ ደብረ ብሥራት ታውራ የሚታዘዙልህ ንስርና አሞራ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ብርሃንህ በራ በኪደተ እግርህ ኢትዮጵያን ቀደስካት ለእግዚአብሔር መንግስት ሙሽራ አረካት አጋንንት ከፊትህ እንደ ጢስ በነዋል ኃይል ጽንዐቱን ክርስቶስ ሰጥቶሃል ቅዱስ ቃል የዘራህ ትጉኹ ገበሬ ማደሪያህ የሆነች ኢትዮጵያ ሀገሬ ዛሬም በጸሎትህ ታፍራ መቶ ፍሬ የጸጋህ ብርሃን ጨለማዬን ትግፈፍ በረከት ጸሎትህ ለትውልዱ ትትረፍ ጣፋጩ መዓዛህ ዘወትር ይሽተተኝ ረደረኤት በረከትህ ሁሌም ትጠብቀኝ ሕግና ሥርዓትን ያስተማርክ ፃድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ የመንፈሴን ዝለት በጸሎትህ ጠብቅ ባለመንበር መንታ ኤልሻዳይ ንጉሥ ነው ልዕለ ጌታ ባለመንበር መንታ ካንድም ሁለት ቦታ ቀዳሚው በላይ ነው በላይ በሰማያት በአምሳለ አራዊት በግርማ ትስብእት በብርሃን ተከብቦ በሚጣፍጥ ዜማ በሚያምር ሽብሻቦ በስብሐት ተከብቦ ቅዱሳን መላእክት ስሙን ሲያወድሱት በዝማሬ እልልታ መለከት ሲነፋ ከበሮ ሲመታ ፈርተው ተንቀጥቅጠው ሕያው የማይሞተው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቢለው ሠለስቱን ጠቅልለው ጥቅልሉን ሠልሰው ዓይኖቻቸውን ተሸፍነው ባክናፋቸው ንጉሥን ሲያነግሥት ከፊቱ በመቆም ወድቀው ሲነሱለት አቤት። ፊታቸው ላይ ያለው ውሃ ቀለማቸው እስኪ አስተውሏቸው ካባ ደርበዋል የንጉስ ልጅ ናቸው ምነው በታች አምና መቶ ዓመት የሞላው አረጋዊው አባታቸው እንጀራው ደብር ላይ ደብረ መድኃኒት ላይ ቀጥቶ አሳደጋቸው ወልድ ዋህድ ብለው ጸኑ በእምነታቸው ማር ወተት ጠጥተው ጮማ እየቆረጡ ያደጉ ልጆቹ በወልድ ዋህድ መዳፍ ዛሬ ተገለጡ ስማቸው ይጠራ አባታቸው ይኩራ ኃይሉ ኃይሉ ኃይላቸው ነው በዓለም የሰፈነ በዓለም ውስጥ ሆኖ ከዓለም የመነነ ዓለም ስትጠራው ዓለምን ሲሸሻት ለካስ በዓለም ውስጥ የተለየ ዓለም ናት ጥሩ ዓለም አግኝቶ ኃይሉ ተዋሀዳት አንዱ አንዱዓለም አንድ ነው ለእናቱ ምርጥ ዘር በሐምሌ የሚዘራ የሐምሌው ምርጥ ዘር ሠላሳና ስልሳ መቶ እንዲያፈራ በወልድ ዋህድ ማሳ ቀድሞ በመስከረም በፀሐይ ቢዘራ የፀሐይ ሀሩሩ ዘሩን እንዳይበላው ውሃ እያጠጣች ፌቨን ብትከልለው በሮሜ መልዕክቱ ቅዱስ ጳውሎስን እንደተራዳችው ዛሬም የእኛ ፌቨን ሰምሮ አገልግሎቷ አንዱዓለም ቪ ሆኖ ይኖራል በቤቷ ኃይሌ ኃይሌ ኃይለ ማርያም የአምላክ ስጦታ ርህርሂት እናትህ መስቀል ስር ተገኝታ ተሽቀዳድመህ ወስደህ በልብህ አኖርካት በህሊናህ መዝገብ በወርቅ ቀለምህ ፅፈህ አስቀመጥካት በዝች ልዮ እናት በጐዳናው መሀል ጠብና ክርክር ሁከት ቢነሳባት ከእናት በላይ ፍቅር የለብህምና ምርኩዝህን ይዘህ በአባቶችህ ፋና በቀናችው መንገድ ወጥተህ በጐዳና ሰውን እንዳይወጋ እሾህ አሜኬላ አጋምና ቀጋ አሰናክሎ እንዳይጥል የእንቅፋቱ ዲንጋ ኩርንችቱን ስጠርግ መንገድ ስታቀና ዝለት እንዳይገጥምህ ጸናህ በህሊና ሙሽሮች ሁላችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ በቅዱሳን ፀሎት ይቅና ትዳራችሁ የአብርሃም የሣራ ይሁን ጋብቻችሁ የጽድቅ ብርሃን የወንጌላዊው ማርቆስ ብሥራት የካህኑ ዮሐንስ በረከት የደጋጎች የዘር ፍሬ የማርያም ዘመዳ ዝማሬ በብርሃናት ልብስ ተሸልሞ በብዙ ሀብታት ያጌጠ ሥጋን ከነምኞቱ ሰቅሎ ለምትበልጠው ጸጋ ያለመታከት የሮጠ አሸቀንጥሮ ጥሎ ምድራዊ ድሎቱን በገድል ትሩፋት እጅግ የደመቀ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት በምሥጢር ጥበባት የመጠቀ ወንጌል እየዘራ በሚያንፅ ስብከቱ አእልፍ ነፍሳትን ከበረቱ የጨመረ ከተፈጥሮ ሕግ አይለ በዋጀው ዘመኑ ለመንጋው የኖረ በትጋት ባፈራው በድንቅ ተአምራቱ በምሁር ሰማይ ላይ ፀሐይን ያቆመ ቃል ኪዳኑን አምነው አባት ሆይ ለሚለ ሌት ተቀን ሚማልድ ማርልኝ እያለ ይህ ነው ዜና ማርቆስ ትውልድ የሚያወሳው የጽድቅ ብርሃን ጧፍ ሆኖ የሚያበራው ያ አፈር ጠቢብ የጥበበኞች ጥበበኛ ከአፈር መርጦ ሸክላ ሰሪ ሙያተኛ በእጆቹ ቀርፆ አበጃጅቶ ልቅም አርጐ ሠርቶ ሰባቱን ባህርያት በአንድ ላይ ገምዶ ነፋሱን ከስጋው አቆራኝቶ አዋዶ በመልኩ በምሳሌው አስተካክሎ ከእርሱ ከራሱ ከእስትንፋሱ ከፍሎ እፍ ብሉ ቢለግሰውሕይወት ድንቅ ስራ ሆነ ግሩም ፍጥረት ያ አፈር አፈርነቱን ዘንግቶ ከከዋክብት ልቆ እንደ ፀሐይ አብርቶ ገነትን ዳረጐት ቢሰጠው መንግሥተ ሰማያት ጭቃ ማቡካት ቀላል መስሎት ሸክላ መስራት ጠቢብ ላይሆን ተጠብቦ ሞትን በላት ቀጥፎ ንብረቱን ያችን አንድ አጥንት ታቅፎ እርሷን ተማጽኖ በመሬት ላይ ዘርቶ ተስፋውን ከሩቅ አይቶ ተመልክቶ ሕይወቴ ነሸ እያለ ያ አፈር መልሶ አፈር ሆኖ በሰበሰ ወደ ጥንቱ ወደ አፈሩ ተመለሰ ያለ ዋጋ ሸጠው በተንጣለለው ምድር በተቀየጠ ዓለም ገበያ ዘርግቶ ሲሸቅጥ ህዝበ አዳም የንግዱ ስያሜ አይነቱ ብዛቱ የአንዱ ተመሣሣይ ቁጥሩ ማታከቱ ጥሬ ዕቃ አቅርቦቱ የፋብሪካው ምርቱ የገበሬው ሰብል የጓሮ አትክልቱ ደርሶ ለገበያ ሁሉም በየወቅቱ በጅምላ ችርቻሮ ወይም በጉልቱ የኑሮ ውጥንቅጥ የዋጋው ንረቱ አንዱ ሲከስርበት ሁለተኛው ሲያተርፍ ሶስተኛው ሲቀማ አራተኛው ሲዘርፍ የሰውን ልጅ ችግር ድኸነቱን አይቶ በገበያው መሐል ባለፀጋ ገብቶ የዘላለም መንግሥት እርስቱን ዘርግቶ ለህዝብ ቸረቸረው በርካሽ አውጥቶ በቁራሽ እንጀራ በሳንቲም ድቃቂ በአንዲት ጥሪኝ ውኃ በተለበሰ ልብስ በትንሽ እላቂ የዘላለም ሕይወት መተኪያ የሌለው የዚህ ዓለም እውቀት ወርቅ ዕንቁ ማይገዛው በቅዱሳኑ ስም ያለ ዋጋ ሸጠው ይብላኝ ላንቺ ቤተ ሳይዳ አንቺ የበጎች በር ቤተ ሳይዳ ምን አጠፋሁ ምን በደልኩኝ። በፊትህ ናት ልጄ ጐሽ ጐሽ እሰይ አደክልኝ ለወግ ለማዕረግ ይኸው በቃህልኝ አንተን አንድ ልጄን ከነፍሴ አጣብቄ እንደ አሽከር አገልጋይ ወገቤን ታጥቄ ልጄ ልጅ እንድትሆን ሕይወትን ገልጩ የጥንት አባቶቼን ታሪክ አስረግጩ ባቀኑት ሀገር ላይ ሌት ተቀን ተጉዢ የዘር ሐረግህን ከግንዱ መዝዢ ያልተበረዘ ያልደፈረሰ እንደምንጭ ውኃ የጠራ ይኸው ማንነትህ የጥንት አባቶችህ የጸናው አደራ በሳባ ተጸንሶ የጥበቡ ምሥጢር ምኒልክ ተወልዷል ከሩቅ ምሥራቅ ሀገር የቃል ኪዳን ታቦት ቀይ ባሕርን ከፍሏል በነቢያት ትንቢት ሱባኤ ተቆጥሯል በሐዲሱ ኪዳን ምድር ተቀድሷል የሰማይ መልአክ ወደ ምድር ወርዶ ደስ ይበልሽ አላት ታጥቆ አደግድጎ ቅድስተ ቅዱሳን ማደሪያ ታቦቱ ንጽሕተ ንጹሐን ለአምላክ እናቱ የቅዱስ ገብርኤል ትጸንሲ ሲላት ድንቅ ነው ብስራቱ ቅዱስ ላሊበላ ደብረ ሮሃ ገብተህ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ብለህ ሰላም ለፍጥረታት ብስራት እየሰማህ ሰውና መላእክት በኅብረት ሲያዜሙ አምላክ በበረት ውስጥ ተወልዶ ታያለህ ከውኃና መንፈስ ሁለተኛ ልደት የተወለድክበት ሰው መሆን ከገባህ የእግዚአብሔር ልጅ ሁነህ የተቆጠርክበት ባሕረ ዮርዳኖስ ቆመህ ትገኛለህ ሥላሴ በገሐድ ከተገለጡበት ቡሄ ቡሄ ብለው ልጆች የሚያዜሙት ወግ ባሕል ትውፊቱ ጸንቶ የቆየበት ተረት እንዳይመስልህ ወንጌል ነው ስብከቱ በደብረ ታቦር ላይ ብርሃነ መለኮት የተገለጠበት ዐብይ ምክንያቱ የአዳም ልጅ የእግዚአብሔር ሆኖ መገኘቱ ሆሳዕና ሆሳዕና ሆሳዕና በአርያም የዳዊት ልጅ መድኃኔዓለም ነጋዴ ሸቃጩ ቤተመቅደስ ገብቶ ቤትህ የጸሎት ቤት መሆኑን ዘንግቶ ለዚህ ዓለም ተድላ አውጥቶ ቢሸጥህ የተገመደውን ጅራፍክን አነሳህ አዳም ከአይሁድ ጋር በአንድነት አብሮ በርባንን ፍታልን ክርስቶስ ይሰቀል አለ በታላቅ ቃል ድምጽን ከፍ አድርጎ የዓለም መድኃኒት የሰው ልጆች ቤዛ የአዳም ድኅነቱ በመስቀል ላይ ታዬ ኃያል ብርቱ የፍቅር ጽናቱ ምድር ተደሰተች ሐሴት አደረገች በደመ ክርስቶስ ታጥባ ስለነጻች የአዳም እዳ በደል ቀንበሩ ተሠብሯል በትንሳኤው ብርሃን ጨለማው ተሽሯል በፍቅረ ንዋይ ልቡ ለነደደው ለሠላሳ ዲናር ጌታውን ለሸጠው ለዛ ለይሁዳ ሞት እንዲቆርጥለት ጥሩና ንገሩት ጌታ በእልልታ አምላክ በስብሐት አረገልህ በሉት በኀኅምሳኛው ዕለት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ በእሳት ቢያጠምቃቸው በሦስተኛው ሰዓት ጉሽ የወይን ጠጅ ሐዋርያት ጠግበው ጠጥተው ታዩአቸው ሰምተው ተገረሙ የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉም በቋንቋቸው ለካስ የወይኑ ጠጅ የሕይወት ቃል ሆኖ ልባቸው ተነካ እጅግ ተደነቁ ሦስት ሺህ ነፍሳት ንስሐ እየገቡ አምነው ተጠመቁ እምነት ማለት ልጅ ተራራ ያፈልሳል ባሕርን ይከፍላል በእሳቱ መሀል በሰይፍ ስለት ላይ መንገድ ይመራሀል ይኸው የአንተ አባት ሃይማኖት ያጸናው ለከተማው መብራት ሆኖ እየነደደ እንደ ጧፍ ቀልጦ ነው መስቀል ተሸክሞ በነገሥታት መሀል ማንንም ሳይፈራ በደብረ ይድራስ ላይ እንደ እህል ተፈጭቶ በነፋስ ተዘራ በዱር በገደሉ በበረሃ ወድቆ ንባቡን ተርጉሞ ምሥጢርን አራቆ ድምጸ አራዊቱን የሌሊቱን ግርማ በጽናት ታግሶ ሀገርን ጠበቀ ትውልድን አቀና አፈር ጤዛ ልሶ ልጄ ልጅ ሆጄፔ በአባቴ ስም እንደተጠራሁ እኔም በተራዬ አንተን ወልጃለሁ ያ እዝራኤላዊው ናቡቴ በሰማርያ የወይኑ ፍሬ ናት የማንነቱ መለያ ቅጥር ቀጥሮ ጠብቆ ከተኩላ ተግቶ ይጠብቃል በኤልዛቤል እንዳትበላ አክአብ ድንበርተኛው በወይኗ ጐምጅቶ ነቃቅሎ ሊጥላት በጐመን ተክቶ ያችን መልካም እርሻ ባድማ ሊያደርጋት ሊገዛት ወደደ በጥፍ ሊለውጣት ሕይወቱ ናትና ገንዘብ የማይገዛት አባቶቹ ደጅ ጠንተው የወረሷት ናቡቴ ልጅ ባይኖረው ወይኑን የሚወርሳት ስለ መልካም እርሻው ደሙን አፈሰሳት ምስኪኑ ናቡቴ ደሙ እንደፈሰሰው እኔ ግን አልደማም። ይህ ነው ደጅ የጠናሁበት የልፋቴ ዋጋ አባት በልጅ ጦር ልቡ ከተወጋ የወይኑ ዘለላ አጋም እና ቀጋ ዘሩ አመንዝሮ ዲቃላ ካፈራ ለአክአብ ከሸጠው የውርሱን አደራ ልጁም ልጅ አልሆነ ወይኑም አላፈራ ዔሳው ብኩርናውን ንቆ ክብሩን ካቃለለው ያዕቆብ ይነሳል የምድር በረከቱን በሰማይ ሊወርሰው በመከራ ወራት መስቀል የሚሸከም እግዚአብሔር ሰው አለው ልጄ አንተ ልጅ ከሆንከኝ ዔሳውን ተክተህ ብኩርና ይሄ ነው ማተቤን ላውርስህ በዓለም አሸንክታብ ጉልበትህ ካልዛለ በጊዜ ሠንሠለት ልብህ ካልታሰረ በምድር ተድላ ደስታ ዓይንህ ካልባከነ የእውነት ልጅ ከሆንክ የተወለድክባት የናቡቴ እርሻ ያንተም ርስትህ ናት ከትውልድህ ጋራ በልተህ ጠጥተሃት ዘመንህን ሁሉ እያገለገልካት ደግሞም በሰማያት የምትከብርባት ቅድስት ቤተክርስቲያን ይኸው በፊትህ ናት መንግሥተ ሰማያት ይኸው በፊትህ ናት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አንቺ ምድር እማማ የግዮን እመቤት ነሽ የበረከት ማማ የመስቀሉ ሥር ኮረብታ የቅዱሳን ከተማ ብርሃን ያረፈብሽ በደም የከበርሽ አውድማ የአምላክ ልዩ ገፀ በረከት ስጦታ ነሽ የእናቱ ርስት የንግሥት ሳባ ቤት የሰው ዘር መፍለቂያ የሰሎሞን ዘር ክፋይ የጥበብ ማደጊያ የሙሴ ምሥጢር ነሽ የድንኳኑ ቤዛ የምኒልክ ዘውዱ የዛጉዌ መዓዛ የብሉይ ኪዳን ሠንሠለት የጽዮን ማደሪያ የአዛርያስ ግንቡ የኦሪት መሠዊያ የሐዲስ ኪዳን መሠረት እማማ ኢትዮጵያ የጃንደረባው ቅኔ የፍቹ ምሥጢር መገኛ የአባ ሰላማ አክሊል የፊሊጳስ መልእክተኛ ተዋሕዶ ያፈራብሽ የምስጢራት አውራ የሰላም ምንጭ ነሽ የእምነት ተራራ የተክለ ሃይማኖት ገድል የተዘከርሽ በአርያም የተሰዓቱ ቅዱሳን ማረፊያ የገብረ መንፈቅ ቅዱስ ገዳም የሐዋርያት አዝመራ የክርስቲያኖች ደብር የመነኮሳት በዓት የቀሳውስት ሀገር የምስጋና ጅረት ነሽ ሀገረ እግዚአብሔር የያሬድ ማህደር የድጓው መፍለቂያ እማማ አንቺ ምድር ኢትዮጵያ ምነው። ዴማስ እግዚአብሔር ይመስገን እንዴ አሮን አንተ ነህ እንዴ። ዴማስ ጥሩ ጥያቄ ነው ተመልከች ማርቲየ ይህ ስዕል የአሳሳል ጥበቡ ውስብስብ ስለሆነ ሰዎች እንደ አዩት ቶሎ አይረዱትም ስለዚህ ቀለል ባለ መንገድ እንደ ገና ተስሎ መቅረብ አለበት አሮን እናታችንን ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ የሳላት አባታችን ነው አባታችን ለእኛ ለልጆቹ እናታችንን በምንረዳበት መጠን ውብ አድርጎ ስሎ ሰጥቶናል እኛ ግን ከእናታችን ይልቅ ወደ እንጀራ እናታችን ስናደላ ትናንት የምናውቀው ምስል ዛሬ ውስብስብ ሆነብን ማርታ እውነት ነው እናታችንን ሁሉም ሰው ያውቃታል እንደውም ከመታወቋ የተነሣ ብዙ ሰዎች እኔን በእርሷ ስም ነው የሚጠሩኝ ዴማስ ማርቲ እንደ ዱሮው አይምሰልሽ እናታችን ታዋቂ የሆነችው በእኛ ሀገር እና በአንዳንድ አካባቢዎች ነው ይህ ደግሞ በቂ አይደለም በዓለም ሁሉ ታዋቂ መሆን አለባት ለዚህ ደግሞ ዓለምን በሚማርክ መልኩ ስዕሏ እንደገና ተከልሶ መቅረብ አለበት ማርታ ጥሩ ሀሳብ ነው የእናታችን ስዕል እንደ ገና በመከለሱ ዓለም ሁሉ የሚከተላት እና የሚያደንቃት ከሆነ እኔ በግሌ በጣም ነው ደስ የማሚለኝ አሮን አስተውሉ። ማርታ የእናንተን ጭቅጭቅ ከመስማት ዘወር ማለትን እመርጣለሁ ወጥታ ትሄዳለች ዴማስ እጅግ በጣም አዝናለሁ አንድ ቀለም ከሚስተካከል ይልቅ አንድ ሺህ ሰው ቢጠፋ የምትመርጥ ሰው ነህ አሮን እውነት አንተ አሁን አንዲት ቃል ከሚያልፍ ሰማይ እና ምድር ቢያልፍ ይቀላል በሚለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ሰዎችን ማጽናት አቅቶህ ነው። አንተ ሰው። ተው ተው ተው አንተ ሰው እንዳትሳሳት እያለ መጥቶ መሀል ገብቶ ይገሳግላል ከሳሽ መንገደኛውን እየተማጸነ እባክህ ወንድሜ ይህንን ሰው በሕግ አስረህ ከዳኛ አድርሰን መንገደኛ ፊቱን ወደ ተከሳሽ መልሶ ና ቅረብ ወዲህ በሕግ ታስረሀል ተከሳሽ መንገድ እየጀመረ በቁጣ አልታሰርም መንገደኛ ወደ የት ልትሄድ ነው ቁም እንጂ በል በሕግ ሲሉት እንኳን ሰው ውኃ ይቆማል ተከሳሽ ከሕግ በላይ መሆኑ አስፈርቶት መለስ ሲል መንገደኛ እንፍታው ከሳሽ ያለ ሰማይ ደመና ያለ ቅቤ ጉተና ዱላ ያለ ጁና እውነት የያዘ ይወጣል ሐሰት የያዘ ይሰምጣል አባይ ሲናገር ያስታውቃል እሱ ሲበላ ይታነቃል በሉ እስቲ ምድን ነው ችግራችሁ እዚሁ ዳኛ ሳለ ተናገር ውኃ ሲጠራ ተሻገር ለዳኛ አመልክት እንዲሆን መሠረት ነውና ጉዳያችን እንደ ቋጥኝ ድንጋይ የከበደ ስለሆነ አቆራኝተህ ከዳኛ አድርሰን እላለሁ። ዳኛ የክስህን መልስ አሰማ ተከሳሽ እጅ እየነሳ በልሀ ልበልሀ ያጤ ሥርዓቱን የመሠረቱን አልናገርም ሐሰት ሐሰቱን ሁሌ እናገራለሁ እውነት እውነቱን በሀገራችን የውኃ ችግር ቢፈጠር ጠቢብ ከባሕር ማዶ መጥቶ ቢመረምር ጠቅላይ ግዛቱን የሚያጠጣ ተማሳው ላይ ውኃ እንዳለ በምርመራ ወጣ የሀገራችን ሰው እንዳያልቅ በችግር እንዳይቀጣ ማሳውን ከልለን ቁፋሮ ይዘናል ውኃ ልናወጣ ታያ ይህ መልካም ሥራ ከሳሸ ተቆጥሮ እንደ ክፉ ሴራ ከዳኛ ፊት ቀረብኩ ወንጀሉ ሊጣራ ገዳሙስ እያለው ስንት ጋሻ መሬት ምን ይጎልበታል ማሳው ቢነሳበት አንተም ስለ ሰጠህ ለገዳሙ መብት ከዳኛ ፊት ቆመህ አትችልም መሟገት በልሀ ልበልሀ ያጤ ሥርዓቱን የመሠረቱን አልናገርም ሐሰት ሐሰቱን ሁሌ እናገራለሁ እውነት እውነቱን ምድር እና ሰማዩን ጌታ ሲወስነው በአራቱም መዓዝን ምድር እንድትጠጣ አፍላጋት ሰጥቶ ነው ውኃ ከአፈር ሳይሆን ውኃ ከእግዚሀር ነው ውኃው ለአፈሩ የተፈጠረ ነው ጠቢባን ያልካቸው የፍልፈል ዝርዮች አፈር የሚገፉ ድሮም የተነሠሠ ሀገርን ሊወርሱ ሃይማኖት ሊያጠፉ ዛሬም በጠቢብ ስም የበግ ለምድ ለብሰው የቤተስኪያን ጓሮ የገዳም በር አልፈው ሥርዓት ሊያጠፉ ቁፋሮ ይዘዋል ይኸው በልማት ስም ግብራቸው ደም ሆኗል ዓይን ወግቶ ማይዘልቀው ጠፍ መሬት እያለ በጠቅላይ ግዛቱ እንኳንስ ለውኃ ከምድር ይፈልቃል ማር እና ወተቱ ይህ ሁሉ ስጦታ ሞልቶ በሀገሩ ከገዳሙ መሬት ምነው መተኮሩ ይቺን የቅርስ ግምጃ ቤት የታሪክ ማህደር ተከሳሽ ከሳሽ ሊያጠፋ ሲመጣ ሊዘርፍ ሊመዘብር ምንድን ነህ አትበሉኝ እንደ ልጅነቴ ዘብ እቆማለሁኝ ከማህጠነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ተወልጃለሁኝ ወዳጄ ጠቢብ ሰው ደልሎህ ሀገርህን ሽጠሃል አንተም ለጥፋቱ አንድ አካል ሆነሃል ላጠፋኸው ጥፋት ቅጣት ይገበሃል ጌታየ እግዜር ያሳይዎ መላኩ ያመልክትዎ ተውሻ አርክሶ ከጤፍ አሳንሶ ሀገሩን እንደ ሸጠ መናኛ ቆጥሮኝ ክዳታም ብሎኛልና ልብ በሉልኝ እንደ ምናምኔቴ ተቆጥሬ ተከስሼ ቀርቤአለሁና በአደባባይ ተነውሬ በልቶ መጠጥ ያጣ ተበድሎ ፍርድ ያጣ እንዲሉ ሀገሬን ለማቅናት ብወርድ ብወጣ በሐሰት ተወንጅያለሁና ከሳሽ ይቀጣ አይቡ ዳኛ ቅቤው መልከኛ ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል ሐሰት ከሆነ የኔ ነገር ተመርምሬ ልጠየቅ አንተም ተጠየቅ ተጠየቅ ተከሳሽ አልጠየቅም ሰማይ አይታረስ መሬት አይተኮስ ብረት አይርስ ውኃ አይታፈስ በሀገር ጉዳይ አንተም እኔን አትከስ ከሳሽ ሰማይ በመብረቅ ይታረሳል መሬት በማረሻ ይተኮሳል ብረት በከሰል ይርሳል ውኃ በእንሥራ ይታፈሳል ሀገሩን የበደለ ይከሰሳል ክዶ ከመሞገት አምኖ መረታት ነውና እንግዲህ የኔም ሙግት እውነቱን ካላዘለ በቁልቀለት እንደ ቀበሮ በዳገት እንደ ዝንጀሮ አፈ ባና እግረ ደቆና አራት እግሯ ከብርሌ አፍ የሚገባ ስትሄድ የምታፈናጥጥ ሰጋር በቅሎዬን እሰጥ ተከሳሽ ለሰጠሁ አገባ ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይመስክር የነበረ የኔም ሙግት እውነቱን ካላዘለ ሲጭኗት የምታረበርብ የምትንሳፈፍ እንደ መርከብ የምትገባ ለራስ አመለ ወርቅ ኩንስንስ በቅሎ እሰጥ ከነሸማ የምታነሣት ከሆነማ ከሳሽ ለሰጠሁ አገባ ዳኛ ይብቃችሁ ይብቃችሁ እይህ ላይ ይብቃችሁ ዳኛ ቢያጋድል በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ በሞኝ ቢፈርዱ ሞኝ ይወልዱ የበላ ዳኛ የወጋ መጋኛ እንዲሉ እነሆ ፍትሕ ካዛባሁ ይፍረድብኝ ጌታዬ ሰይፈ ሞት ይላክብኝ ብቀርብም በሰይፍ ብርቅም በመድፍ አርዶ ፈርዶ ይጣለኝ እንግዲህ የተጠሙ ወደ ጅረቶች የተበደሉ ወደ ዳኞች ውኃ ቢያንቅ በምን ይውጡ ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡ እግር ቢሳሳት በአንጋዳ አፍ ቢሳሳት እዳ ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ ነገር ቢሳሳት ከእውነቱ ድሀ ቢጠቃ በፍርድ ይካሣል በቃ እንዲህ ነውና ነገሩ የችሎታችን ምሥጢሩ እኛን የሚመለከት ነው ክሱ በምግባሩ። ዲን ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን። ሰላም እንዴ። እንዴ። በረከት አንተ ትልቅ ሰው ሆነህ የለ እንዴ። በረከት ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን። ድንቅ ነው ስራው ሁሉ በእርሱ ሆነ ተመስገን ነው ሰው ከመሞት ከኃጢአት ዳነ የክህደት ግልጥ ሚሥጢር ማኅደሩ ተከደነ እኔስ እሄዳለሁ ወደ አስደናቂው የዓለም ሲሳይ የአምላክን ስራ ላደንቅ ማዳኑንም በአይኖቼ ላይ አዎ መንገደኛ ነኝ የጌታን ምሕረት ናፋቂ ከደጁ ካለው በረከት ከፀጋው ክብር ጠባቂ ቤተልሔም በከብቶች በረት ትመሰላለች በረቱ ውስጥ የቤተክርስቲያንን አሳሳል የጠበቀ የልደት ስዕል ይታያል ነገስታቱ ወደ በረቱ እየጠቆሙ ኛ ንጉስ የዓመታት ልፋት ጽዋው ተሰፍሮልን የእግዚአብሔር ቸርነት ምሕረት በዝቶልን ይኸው ዛሬ ደረስን ከልደቱ ቦታ እጅግ ደስ ይበለን እናቅርብ እልልታ አጃግሬ ወዲህ ና ስጦታውን ስጠኝ እጅ መንሻ አቅርቤ በረከትን ላግኝ ኛ ንጉስ ከአጃግሬ ስጦታ ተቀብሎ ወደ በረቱ ተጠግቶ እየተበረከከ እጅ ይነሳል ስጦታውን አስቀምጦ ሲመለስ ኛ ንጉስ ወደ በረት ይገባል ኛ ንጉስ ከበረት ሲመለስ እንዴት ብዬ ልመነው አሁን ቤተልሔም መንደር መጥቼ አንተን ላይ መታደሌ እንደ ልጅ እጅ ነስቼ በጽናት እቆም ይሆን ከብርሃን አምድ ገብቼ ሰማያት የሚርዱለት እሳት የሆነ መንበሩ ሱራፌል ቅዱስ የሚሉት ሊገለጽ የማይቻል ክብሩ በበረት ሊገኝ ቢወስን እረቂቅ ሆነብኝ ፍቅሩ እምነቴ እንደ አለት ጸና አይቸህ በበረት ጌታ ልቤ በሐሴት ሞላ በታምራትህ ኃይል ተረታ ኛ ንጉስ ስጦታን ሰጥቶ ከበረት ሲመለስ ኛ ንጉስ ወደ በረት ይገባል ኛ ንጉስ አውግስጦስ ቄሣር የሮም ንጉሥ ለህዝቡ ሁሉ መልዕክት ሲያደርስ በሀገሪቱ በሮም ከተማ ቆጠራ ሆነ ይህ ሊሆን ፍርድ አሳለፈ ንጉስ በኃይል ወሰነ በዚያ ውርጅብኝ ወራት ግርግር በተመላበት እናትህ መንከራተቷን ከሜዳ ወደ አንድ አቀበት ወደድከው ደሀ መባሉን ለድሆች የድል ነፃነት የፍጥረትን ብዛት የወሰንክ ድንቁ የዓለም ገናና እናትህ ጋር ቤተልሔም ልትቆጠር ብታቀና ልክ አንደ ምስኪን ዘር አጋር እንዳጣ እንግዳ በበረት ተገኘህ አዳምን ልትረዳ ኛ ንጉስ ከበረት ሰግዶ ስጦታ ሰጥቶ ሲመለስ ኛ ንጉስ አንተ ግን አንተ ነህ ቃልህ የማይታበይ ለእንስሳት መኖ በተዘጋጀ በከብቶች ግርግም ልትታይ ስጋን ተዋሐድክ ከድንግል ማርያም ልትሆን ወደድክ የዓለም ሲሳይ ምን አይነት ፅናት ሰጠሀት በምንስ ኃይል ቃኘሃት መሸከም ያለም ፈጣሪን መታቀፍ መለኮት እሳት ይደረግልኝ ባሪያው ነኝ ሆነ ለገብኤል ብስራት ለእኔስ እፁብ ድንቅ ነው አዕምሮዬን ጠበባት ለምድርስ ምን ኃይል ሰጠሀት እንደ አምላክ ስታይህ አንተን እንደ ልጅ አለቀስክባት እኔንም ለክብር ጠራኸኝ አምላክን በእጄ ልዳስስ በኮከብ እየተመራሁ በመወለድህ ላገኝ ሞገስ ከእንግዲህ እግሮቼ የሞትንና የሕይወትን መንገድ ለዩ አይኖቼ ማዳኑን አዩ አይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና የሚለውን የተስፋየ ኢዶን መዝሙር በሕብረት ይዘመራሉ ተፈጸመ ቅድስት አቅሌስያ ሴት ተራኪ አለባበሶ ነጭ በነጭ እነሆ በአንዖኪያ አቅሊሲያ የተባለች ንጽህት ቅድስት እናት ነበረች ይህች እናት ደግነቷና ፍቅሯ ወሰን የለውም የህይወትን ምግብ የህይወትን መጠጥ ያለ ስስት በለጋስነት ለአዳም ዘር ሁሉ ትመግባለች ከርህራሄዋም የነተሳ ተስፋ ላጡ ለድኩማን ሁሉ መጽናኛ ናት የጥበቧ ጥልቀት የእውቀቷ ስፋት እንዲህ ነው ተብሎ አይነገርም እንዲሁ ባህረ ጥበባት ብንላት ይሻላል በሞት ጥላ ውስጥ በድንግዝግዝ ያሉትን በእውነት መንገድ መርታ ወደ ብርሃን ታደርሳለች ሁሉን በተዕግስት ተሸክማ የተጣመመውን እያቀናች ወደ ሰላም ሀገር የምታሸገግር ድልድይ ናት ከእርሷ ቤት ገብቶ ማንም ሰው የፈለገውን ስለማያጣ ስንዱ እመቤት እያሉ ይጠሯታል ይህችን እናት ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በሰላሳ አራተኛው ዓመተ ምህረት ፊሊጳስ ከተባለ ቅዱስ ሰው ዘንድ ስላገኛት ዳግም ከእርሷ ተወልዶ ልጅ ሆኗት እርሷም እናት ሆናው እርሱም እጅግ ስለወደዳት በሰረገላው ጭኖ ወደ ኢትዮጵያ ይዚት ገባ ኢትዮጵያውያንም በታላቅ ደስታ ተቀበሏት እንግዲህ ከዛን ግዜ ጀምሮ ይህች እናት በከፍተኛ ቦታ ላይ ቤቷን ሠራች ሰባት ምሰሶዎችን አቆመች ፍሪዳዋን አረደች የወይን ጠጅዋንም በማድጋ ጨመረች ድምጂጺንም ከፍ አድርጋ ተጣራች ኑ እንጀራዬን ብሉ የጠመኩላችሁንም የወይን ጠጅም ጠጡ ስንፍናንም ትታችሁ በህይወት ኑሩ ልጄ ሆይ ህጐቼን አትርሳ በፍፁም ልብህም በእግዚአብሔር ታምነህ ኑር የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው የቅዱሳንም ምክር እውነት ነው ሕግንም ማወቅ ለልብ ደግ ነው በዚህ ስርዐት ብዙ ዘመን ትኖራለህ የህይወት ዓመታት ይጨመሩልሃል እያለች ከጥበብ ማዕድ እየመገበች ከእውቀት ማድጋዋ እያጠጣች በሃይማኖት በምግባር እያጸናች እንደ ዕንቁ የሚያበ እንደ እሳት የሚፋጁ እንደ ሰይፍ ስለት የሚቆርጡ እንደ ሰማይ ጠል የደረቀውን የሚያለመልሙ እልፍ አዕላፋት ከዋክብትን ያፈራች እናት የዮዲትን መከራ ታግሳ የግራኝን ሰይፍ ችላ በቀንና በሌሊት እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ አምላኳን ተማፅና ያሳደገችው ልጅ ዳር ድንበሯን የማያስነካ ህልውናዋን የማያስደፍር በእናቱ የማይደራደር ጀግና ልጅ ባለበት ሱስንዮስ ቢነሳ ከቤተ መንግስቱ ገብቶ አንገቱን ለሰይፍ ሰጠ የፋሺስት መድፍ ቢያጓራ ልጂ እንደ ቅጠል ረግፎ እናቱን በህይወት አቆመ ያች እናት ንጽህት ንጽህት ቅድስት አቅሊሲያ ንጽህት ቅድስት ኦርቶዶክስ አዋህዶ ቤተክርስቲያን ኢትዮጵያ ወላድ ሆና ማህፀኗ ሳይመክን ምነው ልጅ መፈለጓ እናት ወደ መድረክ እየገባች ተራኪ ወደ እናቲቱ ጠቁማ ከመድረክ ትወርዳለች አለባበሷ እናትነትን የሚገልጽ ነው ነጭ በነጭ ቀሚስ የነጠላ ጥለት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ወይም መስቀል እናት እንደምን ዋላችሁ እባካችሁ ልጆች ጠፉብኝ ። ኢዮብ እንዴ። ቤቲ ሰው እየፈለገች ሰው ሰው ሰው ሰው የታለ የአባቶቹን ድንበር የሚያጸና በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚጠብቅ ለመንጋው ምሳሌ የሚሆን ማኅበሩን በሰላም በፍቅር የሚመራ ሰው የታለ። ወይ ሰው። እንዴ። ሳራ ለምን። ሳራ ድሪሜ የት እንደጠፋ ታውቃለህ። ሳራ ምን። ተስፋ ኦ። ተስፋ ለምን። ሳራ ተው እንጂ። ተስፋ። እንዴ ምንድን ነው ቤቱ። ሳራ አይ። ተስፋ እንዴ። ሶስና ሳራ የት ነው የጣልሽው። ሳራ አዎ። ሶስና እውነት ነው አንድ ጊዜ የክርስቶስን ፍቅር ቀምሶ እንደ አንተ ወደ ዓለም የኮበለለን ሰው መመለስ ጭንቅ ነው። ተስፋ አስተውይ ሳራ።