Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ከቅኔ ቤት ወደ አስኳላ ባህር ማዶ መቻ ቀጥ ቢል እኛም ቀጥ ነው ይሉ ነበር። ለጓደኞቼ ባማክራቸው ቢስኪሌት እንድገዛና በየቀኑ እያከራየሁ ብጠቀም ይሻላል ብለው መከሩኝ። የራሴን ቢስክሌት ገዝቼ እያከራየሁ ገበያ እንዳልሻማቸው ፈርተው የዋሹ ነበር የመሰለን። ነበርና የተመኘሁት መቶ ሊሬዬን ከእናቴ ተቀብዬ ቢስክሌት ልገዛ መሄዴን በፉከራና በጉራ ከነገርኳቸው በኋላ ወደ ጣልያኑ ቤት አመራሁ። ሁል ጊዜ ጨርቃቸው ካፍንጫቸው አለመውረዱ ለምን እንደሆነ ይከነክነኝ ነበር። ሃርሳቸው ትልልቅ የበቆሎ ፍሬ ይመስል ነበር። አቀማመጡም በአንዳንድ የበቆሎ ራስ ላይ እንደሚታየው እዚያና እዚህ ተራርቆ ነበር። እንዲህ ነው ስለት የሚገርም ነው። ድገም አንድ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ያስወጡኛል። እዚህ የላኩኝ ቋንቋውን ብቻ እንድማር ነው። ከስድስት ወር በኋላ ሐዲስ መጀመሬ ነው። የጅምናስቲኩ መምህር እዚያው በዚያው ባለመቀጣቴ ወይም ከተማሪቤት ባለመውጣቴ በጣም ተበሳጭቶ ነበር። ጅምናስቲኩን ትተህ እዚህ ምን ታደርጋለህ። ይኸ ታላቅ ተአምር ነው። ይኸውም በዚያች መጽሐፍ ፊደል የቆጠረና ንባብ የተለማመደ ጀማሪ ልጅ እመጽሐፍ መጨረሻ ሲደርስ የሚያነበው ከሁለት ገጽ የማይበልጥ የስድ ንባብ ድርሰት እንዲሁም አብሮ የዚያኑ ያህል ያማርኛ ግጥም መፃፍ አለበት ማለታቸው ነው። እኔም በግዕዝ መግጠም ከቻልኩ በአማርኛ መግጠም ያውከኛል ብለው አልጠረጠሩም። ምናልባት ቪቢጠረጥሩም ከዚያ በፊት እንደቀረበላቸው ግጥም ያለመጠን እንዳይራቀቅና ውትብትብ ሆኖ እጅና እግሩን ለደቶ ለመፍታት የሚያስቸግር እንዳይሆንባቸው ነበር የፈሩት። ስለዚህ በዚያ ታሪክ ላይ ቆሞ እሱን መሠረት አድርጎ ቅኔ ይቆጠራል። የኸ ያማርኛው ግጥም ግራ የሚያጋባ ነው። ስለዚህ የታሪኩ አቀራረብ እንደሱ ያለ ሆኖ የታሪኩ ምሥጢር ግን ቁም ነገርነት ያለው ትምህርት ያለበት መሆን እንዳለበት ተገንዝቤ ነበር። ጣጣው እዚህ ላይ ነበር። የአማርኛ ድርሰት ሆ በት የመጀመሪያየ የሆነው ያማርኛ ግጥ ሉው ቀጥሎ የተመለከተው ነበር።
አሣታሚው ክፍል አንድ ግለ ታሪክ መንደርደሪያ በባህል ሚኒስትሩ አስተያየት ዕድሜዬ ለጡረታ የደረሰ መሆኑን ባለመዘንጋት ሰው ሃምሣ ዓመት ከሆነው በኋላ አንድ አይነት ግለ ታሪክን የያዘልህከሀከ የሆነ ፅሑፍ ለተከታዩ ትውልድ ማቆየት እንዳለበት በመገንዘብ አንድ ጥሩ ደብተር ገዛሁ። የአጋግ ባለቤት የሶስት ጊዜ ታላቅ ወንድሜ ጋሼ ልሳን ነው። ብዙ ሰው ሳያይ ባሳቻ ጊዜ ነው እሳቸው የሚሰጡት። አንድ ቀን እኔና ወንድሜ መርሐ እኛስ እንደሌሎቹ ከቅጥር ውጪ ብንኮለኮልና ቤሳና መሀለቅ ብንቀበል። እዚህ ላይ ታላቅ ወንድሜ ጋሼ መዓዛ ያን ጊዜ የጽህፈት ሚኒስቴር ጽሐፊ ሠራተኛ ነበርና ከውጭ አምሽቶ ለመኝታ እቤት ሲገባ በዚህ በሚያስገርም ሁናቴ ላይ ይደርሳል። አባታችን በበኩላቸው አንድ ብርሌ ጠላ አንድ ብርሌ ጠጅ ጠጥተው ሁለት ሞልተዋል። ስለዚህ እኔና ትልቁ ወንድሜ መርሐ ባሊሳ ትምህርት ቤት ባን። እሱም የጣልያን ፖስታና መኮሮኒ ጥሞት ኖሮ ከዚያ ላለመሳቀቅ ሲል አሁን ሥራ ስለያዘና እሳቸው አባቱ በቅስናቸው ከሚቀበሉት ደመወዝ የበለጠ ደህና ደሠወዝም ማግኘቱን እንዲያውም ቤት ውስጥ የሚቸግራቸው ከሆነ ሊረዳቸው ፈቃደኛ መሆኑን ይገልፅላቸዋል። አባታችን ለወይዘሮ ፍሥሐ ማረፊያ እንዲሆናቸው የሰጡዋቸው ቤት በዚያን ጊዜ በጣሊያኖች ላይ ሽፍቶ የፊታውራሪ በዕደ ወታደር ለሆነው ለታላቄ ታላቅ ወንድሜ ለጋሼ ልሳን ተሰርቶለት የነበረውን ሁለት ክፍል የቆርቆሮ ቤት ነበር። በዚህ ሁኔታ ጥቂት ጊዜ ቆይተው አንድ ቀን ለገበያ ወደ አደሬ ግንብ ሲወርዱ የገዛ አሽከራቸውን ትተው እኔን ተከተለኝ ብለው በእግራችን አብረን ወረድን። ለራሳቸው የሚገዙትን ከገዙ በኋላ ለኔ ሥዕል መሳያ ወረቀት ደረቅ እርሳስ ከዚህ ሁሉ የበለጠውን ደግሞ ከዚያ በፊት ከባሊላ ተማሪ ቤት ወዲህ እጄ ገብቶ የማያውቀውን አንድ ፓኬት አሥራ ሁለቱን ቀለማት የያዘ የቀለም እርሳስ ገዝተው ሰጡኝ። ጧት ከሰዓት ወደማታ አንድ አንድ ሰዓት። ጫማ ሳም አሉኝ ወይዘሮ ፍሥሐ። በፊት ጊዜ እኔና ወንድሜ የሀበሻና የጣልያን ጦር አዛች ሆነን ሠራዊታችንን አሰልፈን አንድ ሳምንት ሙሉ ከተዋጋን በኋላ ኔ የሀበሻው ወገን ድል መሆኑን በሰሙ ጊዜ አባታችን የተቆጡት አጓጉል ሟርት ነው ብለው ነበር። የሥነ ድርሰት ዝንባሌዬ ግን ለጊዜው ባላውቀውም አንድ ታላቅ እርምጃ ያደረገው ጣልያን ሊወጣ ሲቃረብ እቅኔ ትምህርት ቤት ስገባ ነው። አባታችን ቅኔ ተማሪ ቤት ግባ ሲሉት ግን ሊገባ አልፈለገም። ዜማ ቅኔ ዝማሬ ትርጓሜ ውዳሴ ማርያም ሁሉም ለአዲሱ ጊዜ አይረባም። በዚህ ጊዜ ነው አቦከር በየቀኑ እየተመላለስክ ቅኔ ተማር ተብዬ የታዘዝኩት። ከዚህ ሌሳ አባትና እናቴ ወንድሞቼም ሳያውቁብኝ አንድ የጣልያን የመንግሥት ሠራተኛ ቤት በቀን ተመላላሽ ሠራተኛነት ተቀጥሬ ቤት እጠርግና አልጋ አነጥፍ ውሀ በኮዳ እቀዳ ስለነበረ በወር አሥራ አምስት ሌሬ ይከፍለኝ ነበር። አንድ ቀን እንደለመድኩት ልቀዳ ሄጄ አንድ እኔ እማላውቃቸው ግን የሚያውቁኝ ሴት ወይዘሮ ውሀ ሊቀዱ መጥተው እዚያ ግጥም አልን። ብዙ ጊዜ ከዚያ ቀዳሁ። ቅኔ ተማር። እንዳሉትም በጧት ተነሥቼ ቅኔ ልማር አቦከር እየኔታ ማእምር ቤት ሄድኩ። ከዚህ የተነሣ አባቴ በቁጣ እብድ ሆነው በመጫኛ አንድ ቀን ጧት ጠበጠቡኝ። ወዲያው ግን የኔታ ጨርቃቸውን ክፍንጫቸው አወረዱና ተቀበል አሉኝ ወዲያው አንድ ጉባኤ ቃና ዘረፉ። ወይዘሮ ዓለሚቱ ቅኔ ለመማር ከአደሬ ጢቆ አቦከር በየቀኑ ዞሥላለሴን እናቴ በነገረቻቸው ጊዜ ያደሬ ጢቆ ቤታቸውን አፍርሰው አቦከር በሠሩት ቤታቸው አንዲት ትንሽ ክፍል በፈቃደኝነታቸው ስለሰጡኝ ነው እሳቸው ጋ ማረፌ። ምነው ዛሬ ቅኔ ትምህርት የለም እንዴ። እኔ ለራሴ አንዲት ጉባዔ ቃና መቁጠር አቅቶኝ ቀኑን ሁሱ አቦከር ጋራ ውዬ ባዶ እጄን የኔታ ፊት እንዴት እቀርባለሁ በማለት እንደ ደንቡ በአሥራ አንድ ሰዓት እሳቸው ጋ ሳልሄድ ቀርቻለሁ። ውጪ ነፍስ ግቢ ነፍስ ሆነ ያቺን ሁለት ቤት ቅኔ ከድንጋጤ ጋር ለማስታወስ ለመሞከር ዝም እንዳልኩ ብዙ ጊዜ ቆየሁ። ግን ፈንጠዝያው በዝቶ ደስታው ወደ ሐዘን እንዳይለወጥ በማሰብ ራሴን ገትቼ ወደማታ እንደተለመደው በአሥራ አንድ ሰዓት ገደማ ወደ የኔታ ቤት አመራሁ። ይሁን እንጂ የኔታ እንደማላሳፍራቸው በልባቸው ተማምነው ነበርና አንድ ቀን ከረፋዱ ተባዔ በኋላ ተማሪዎች ስንበታተን እኔን እንዳትሄድ የማናግርህ ነገር አለ አሉኝ። በደስታ እጅ ነስቼ ወደ ልጆች መኝታ ቤት ሄድኩና እዚያች እሶልዳቶ ሸራ አልጋዬ ላይ ጋደም ስል ያቦከር ብርድ ባዶ ገላዬን ለጊዜው ቢያንቀጠቅጠውም ደስታው ከራሴ ጠጉር እስከ እግሬ ጥፍር አጥለቅልቆኝ ይነዝረኝ ነበር አባቴ እሺ ካሉ የኔታ ማእምርማ አባቴን ፈርተው ነበር ያንገራገሩት አሁን ሁለቱም ተስማሙልኝ መቀኘቴ ነው። አንተ ገና ልጅ ነህ እንዲህ ያለው ነገር አይገባህም አሁን ቶሎ ሂድና ጫማ ሳም አሉኝ። ቅኔ ተቀኝቼፓ ደብተራ መንግሥቱ ተብዬ ጥቂት እንዳገለገልኩ አንድ ቀን ከታላቄ ታላቅ ከጋሼ ገብረ ክርስቶስ የተፃፈ ደብዳቤ ለአባታችን ከተፃፈው ጋር ለኔም መጥቶልኝ ኖሮ አባታችን ጠርተው ሰጡኝ። ይኸውም ቅኔ መቀኘትህ ለቋንቋ ትምህርት መንገድ ይጠርግልሃል ቅኔ የተቀኘ ሰው ማንኛውንም ቋንቋ ልማር ቢል አያስቸግረውም። በዚያን ጊዜ ሙሴ አንቶን ጆንሰን በኬንያ ያስተምሯቸው የነበሩትን የኢትዮጵያ ስደተኞች ልጆች ሰብስበው ወደ ሐረር ተመልሰው የስደተኞች ትምህርት ቤት የሚባለውን ተማሪቤት አቋቁመው ነበር። ታዲያ ነገሩ በዚህ ላይ ቆሞ ሳለ አንድ ቀን በድንገት የፈረንጅ ትምህርት ለመማር ቆርጨ ተነሣሁ። መሀል ቤት የለም። ዋናው ነገር እዚህ ተማሪ ቤት ያልተለመደ ነገር ጅምናስቲክ የተባለ ትምህርት ማስተማሩ ነው። አባቴ የፈረንጅ ትምህርት አይወዱም። ነገ በአሥር ሰዓት በጅምናስቲኩ ጊዜ እንዲሁ አንተ እዚህ ና። እንዲሁ አሉ ሙሴ አንቶን ጅምናስቲክ ሥራ እንቢ እቢሮ የጽሕፈትና የሥዕል እንቢ ካልክ እንዲሁ እዚህ ተማሪ ቤት ምን ታረጋለህ። ቢሆንም አንድ አጠር ያለ የግጥም ድርሰት በዚያች መጽሐፍ መጨረሻ ላይ መፃፍ እንዳለበት በብርቱ ይሰማቸው ነበርና ቢቸግራቸው ከቅኔ ተማሪ ቤት በቅርቡ ተመርቄ የወጣሁትን ወጣት ደብተራ የሊቁን ያለቃ ለማን ልጅ ግጥሙን ባንድ ሳምንት ውስጥ አሰናድቼ እንዳቀርብ አዘዙኝ። ይህን ሳወጣ ሳወርድ የታላቄ ታላቅ ጋሼ ገብረ ክርስቶስ በጣልያን ጊዜ አንድ የሚያስቅ አጭር ታሪክ በአማርኛ ግጥም ደርሶ ለጓደኞቹ እያነበበ በጣም ተደንቆበት ነበር።