Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية
Book of the day

የ “ባልበላውም ጭሬ ልበ.pdf


  • word cloud

የ “ባልበላውም ጭሬ ልበ.pdf
  • Extraction Summary

እንኳንስ በህዝቡ ውስጥ በገዥው ፓርቲና በማዕከላዊ መንግስት ውስጥ ያለው የኃይል ሚዛንም እንዳልነበረ ሆኖ ይፋለሳል አብዛኛው የአገሪቱ ህዝብ ከኦሮሞ ብሔርተኛው በተፃራሪ በጋራ በመቆም ህልውናውን ለማስከበር መታገሉ አይቀሬ ይሆናል እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ ለኦሮሞ ህዝብ ዘላቂ ጥቅምና የወደፊት ታሪክ ስለማይጠቅምም የኦሮሞ ብሔርተኞች አካሄዳቸውን ሰከን ብለው መፈተሽና ማስተካከል ይኖርባቸዋል መፍትሄውስ ወዴት ነው።

  • Cosine Similarity

ህጉመንግስቱና የአዲስ አበባ ህዝብ መብት አንድ ህገመንግስት በአንድ መንግስት የተለያዩ መዋቅሮች መካከል ከስልጣን ክፍፍልና ቁጥጥር አኳያ የተለያዩ ወይም ተበላላጭ መብትና ስልጣን ሊሰጥ ይችላል ነገር ግን በአንድ አገር ውስጥ በሚገኙ ዜጎችና ማህበረሰቦች መካከል ተበላላጭ የፖለቲካ መብት እንዲኖር ማድረግ ተገቢ አይደለም በኛ ህገመንግስት ይዘት ላይ በግልጽ እንደሚታዬው ግን የአዲስ አበባ ህዝብ የፖለቲካ መብት ከሌላው የአገሪቱ ህዝብ ጋር ሲነፃፀር በብዙ መጠን ያነሰና የተገደበ ነወ ይህም በዋናነት ሊሆን የቻለው በሌሎች ክልሎች ለሚኖረው ህዝብ የተሰጡ በርካታ መብቶች በሚሊዬን የሚቆጠር ህዝብ ለሚኖርባት አዲስ አበባ ሳይሰጥ በመቅረቱ ነው በዚህም ምክንያት የአዲስ አበባ ህዝብ በህገመንግስቱ መሰረት የሚከተሉትን መብቶች አጥቷል የክልልነት መብት ማጣት አዲስ አበባ የስልጣን ደረጃዋ ልል ሳይሆን አስተዳደር ነወ ሐረሪንና ቤኒሻንጉል ጉምዝን የመሳሰሉ ከአዲስ አበባ በብዙ ርቀት ያነሰ የህዝብ ቁጥር ያላቸው አካባቢዎች የክልልነት ደረጃ ሲሰጣቸው በሚሊዬን የሚቆጠር ህዝብ ያላት አዲስ አበባ ግን የክልልነት ደረጃ አልተሰጣትም ይህም በመሆኑ በውስጧ የሚኖረው ህዝብ ከሌላው የአገሪቱ ህዝብ ተለይቶ የሚከተሉትን መሰረታዊ መብቶች እንዲያጣ ተደርጓል የፌዴራል መንግስቱ አካል አለመሆን አዲስ አበባና ድሬዳዋ የክልልነት ደረጃ ስላልተሰጣቸው ህገመንግስቱ በፌዴራሉ መንግስት አካልነት አያውቃቸውም ምክንያቱም በሕገመንግሰቱ አንቀጽ ፖ መሰረት የፌዴራል መንግስቱ አካል ተብለው እውቅና የተሰጣቸው ዘጠኙ ክልሎች ብቻ ናቸው አዲስ አበባ የፌዴራሉ መንግስት አካል ባለመሆኗ ከተማዋም ሆነች በውስጧ የሚኖረው ህዝብ ከሌሎች ክልሎችና ህዝቦች ተለይቶ የሚከተሉትን መብቶች አጥቷል ሀ ወደፊት ክልል የመሆን መብት ማጣት አዲስ አበባ አሁን ላይ የክልልነት ደረጃ አለማግኘቷ አላንስ ብሎ ወደፊትም ክልል የመሆን ዕድል እንዳይኖራት መብቷ ተገድቧል። ምክንያቱም በህገ መንግስቱ አንቀጽ ቁጥር መሰረት ወደፊት ክልል የመሆን ጥያቄ የማቅረብ መብት ያላቸው በዘጠኙ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ብሔርብሔረሰቦችና ህዝቦች ብቻ ናቸው የአዲስ አበባ ህዝብ በዘጠኙ ክልሎች ውስጥ የማይገኝ በመሆኑ ምክንያት የክልልነት ደረጃ የመጠየቅና የማግኘት መብት ህገመንግስቱ አልሰጠውም ለምሳሌ በክልሎች ውስጥ የሚገኙ በቁጥር አናሳ የሆኑ ሙርሲንና አርጎባን የመሰሉ ህዝቦች ከፈለጉ ክልል የመሆን ፈለጉ የመገንጠልም ጭምርን ጥያቄ የማቅረብና ክልል የመሆን መብት ህገመንግስቱ የሰጣቸው ሲሆን በሚሊዬን የሚቆጠረው የአዲስ አበባ ህዝብ ግን የአንድ ብሔር ወይም ብሔረሰብነትን መስፈርት አያሟላም ተብሎ ስለታመነ ያለአግባብ የክልልነት ጥያቄ የማቅረብ መብት ተነፍጎታል ለሊ በፌዴሬሺኑ ምክር ቤት አለመወከል በህገመንግስቱ አንቀጽ ፅገ ቁጥር ገ መሰረት የአዲስ አበባ ህዝብ በፌዴሬሺኑ ምክር ቤት ውስጥ ከሌላው የአገሪቱ ህዝብ ተለይቶ ወክልና ተነፍጎታል ማለትም አንድ ወረዳ ወይም ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ ቢያቀርብ ወይም አንድ ክልል ከአገሪቱ የመገንጠል ጥያቄ ቢያቀርብ ወይም የፌዴራል መንግስቱ አንድ ቀን ላይ ድንገት ብድግ ብሎ አገሪቱን ለማፍረስ ቢወስን ከሌላው የአገሪቱ ህዝብ ተለይቶ የአዲስ አበባ ህዝብ የእነዚህ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ተጋሪ የመሆን መብት የለወም በጥቂት ሺዎች ብቻ የሚቆጠር የህዝብ ብዛት ያላቸው ብሔርብሔረሰቦች በሙሉ በፌዴሬሺኑ ምክር ቤት ውስጥ ውክልና ያላቸው ሲሆን ከስድስት ሚሊዬን በላይ እንደሚሆን የሚገመተው የአዲስ አበባ ህዝብ ግን በፌዴሬሺንምክር ቤት ውክልና እንዳይኖረውና ህገመንግስቱን የመተርጎም መብት ተጋሪ እንዳይሆን ተደርጓል ሐ የሉዓላዊነትና የአገር ባለቤትነት መብት አለመኖር በወቅቱ የአገሪቱ ህገመንግስት መሰረት ሉዓላዊነት ያላቸው ዜጎችና አገሪቱ ሳይሆኑ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚባሉ ማንነቶችና ቡድኖች ብቻ ናቸው በዚህ ምክንያት እነዚህ ቡድኖች የፈጠሯቸው ዘጠኙ ክልሎች አአሁን ላይ ጊገ ሁነዋልን ያለምንም የፌዴራሉ መንግስት ጣልቃ ገብነት የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን ሉዓላዊ ስልጣን አላቸወ እነዚህ ክልሎች አገሪቱን በስምምነት ያቋቋሙና የአገሪቱ ባለቤት ስለመሆናቸውም በህገመንግስቱ ውስጥ የተደነገገላቸው በመሆኑ ከስልጣን እርከን አኳያ የፌዴራል መንግስቱ የበላይ አለቆችና ባለቤቶች ናቸው አዲስ አበባ ግን የአገር ባለቤትነትና ሉዓላዊነት መብት ተጋሪ ስላልሆነች ከሌሎች ክልሎች በተለዬ ተጠሪነቷ ለፌዴራል መንግስቱ እንዲሆንና የአገሪቱ ሉዓላዊነትና ባለቤትነት ተጋሪ እንዳትሆን ተደርጓል መ የልዩ ጥቅም አለመከበር ህገመንግስቱ በአንቀጽ ቁጥር መሰረት የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኝ ክልል መሆኑን በመጥቀስ ከተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ከመሰረተልማት መስፋፋትና ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ ከተማ ላይ እንዲኖረው ደንግጓል ያለአግባብ አከራካሪ ሲሆን ቢታይም በእኔ አመለካከት ግን ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ዙሪያ ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ጥቅም እንዲኖረው መደረጉ የሚጠበቅና የሚገባ ነው ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ተከባ ወይም መሃል ላይ የምትገኝ ከተማ በመሆኗ በኦሮሚያ ክልል ሊኖራት ስለሚገባው ልዩ ጥቅም ህገ መንግስቱ የደነገገው ነገር የለም አንዳንድ የኦሮሞ ጽንፈኛ ብሔርተኞች የአዲስ አበባን የመጠጥ ውሃ መስመር እንቆርጣለን በማለት ህዝብን ሲያስፈራሩ ቆሻሻችሁን ልትጥሉብን አትችሉም በማለት በህዝብ ላይ ሲዝቱ የሚታየው ህጉመንግስቱ የአዲስ አበባንና የኗሪዎቿን ልዩ ጥቅሞች የሚያስከብር ግልጽ ድንጋጌ ስለሌለው ነው እነዚህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ጉዳዮች አዲስ አበባና ኑዋሪዎቿ በህገመንግስቱ መሰረት ያጧቸው መብቶች ሲሆኑ ከዚህም በተጨማሪ ከህግ ውጭ በሆነ መንገድ አዲስ አበባ በርካታ ጥቅሞች እያጣችና መብቷ እየተገፈፈ ይገኛል የሚከተሉትን አራት ጉዳዮች በምሳሌነት ማዬት ይቻላል። አንደኛ አዲስ አበባ በአገሪቱ ህገመንግስት ድንጋጌ መሰረት የምትጠራበት ስም አዲስ አበባ ሆኖ እያለ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሞ ልሂቃን የሚጠሯት ግን ፊንፊኔ ብለው ነው አዲስ አበባ ከተቆረቆረችበት ዕለት ጀምሮ ይዛው የኖረችውን ስም ያለአግባብ ቀይሮ በአንድ ትንሸ መንደር ወይም አካባቢ ስም ፊንፊኔ ተብላ እንድትጠራ መደረጉ ህገ ወጥነት ነወ ሁለተኛ የአዲስ አበባ ህዝብ ራሱን በራሱ ማስተዳድር እንዳለበት በህግ ተደንግጎ እያለ ይህ መብቱ ግን በተደጋጋሚ ሲጣስ ታይቷል ከአቶ ተፈራ ዋልዋ ጀምሮ አስከ የአሁኗ ወሮ አዳነች አበቤ ድረስ ለአዲስ አበባ የተሾሙላት ከንቲባዎች በሙሉ ከክልል የመጡና እንኳንስ የከተማ አስተዳደርን የከተማ ኑሮንም በቅጡ የማያውቁ ናቸው ካላቸው ልዩ ባህሪ አኳያ ከተሞች በከተማ አስተዳደር ጉዳይ ላይ በቂ ልምድና ዕውቀት ባላቸው ባለሙያዎች መተዳደር ሲገባቸው አዲስ አበባ ግን ለአለፉት ዓመታት የተመራችው አዲስ አበባን ሲያዩ ኒውዮርክንና ፓሪስን እንዳዩ በደስታ በሚደመሙ የገጠር ካድሬዎች ነወ አንዳንዴም የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ያልሆኑ ሰዎች ለአዲስ አበባ ከተማ ከህግ ውጭ ከንቲባ ሆነው ሲሾምላት ታይቷል ባልተጻፈ ህግ መሰረትም ለአለፉት ተከታታይ ዓመታት በቋሚነት የአዲስ አበባ ከንቲባዎች ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ብቻ እንዲሆኑ ተደርጓል ሦስተኛ የኦሮሚያ ክልል ያለምንም ህጋዊ መሰረት ከሌሎች ክልሎች ተለይቶ የክልሉን ዋና ከተማ አዲስ አበባን አድርጓል አንድ ክልል የራሱ ክልል አካል ያልሆነን ሌላ ከተማ ዋና ከተማ አድርጎ መጠቀሙ በየትም ዓለም ያልተለመደና በኛም አገር ምንም ዓይነት ህጋዊ ድጋፍ የሌለው ውሳኔ ነው ከዚህ ጋር ተያይዞም የአዲስ አበባ ህዝብ ልጆቹ ያለፍላጎታቸው የኦሮሚያን ክልላዊ መዝሙር እንዲዘመሩ የኦሮሚያን ሰንደቅ ዓላማ እንዲሰቅሉና ያለፍላጎታቸው በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሲገደዱ አይተናል የኦሮሚያ ፖሊሶችም ያለ ክልላቸው በአዲስ አበባ ፀጥታ የማስከበር ህገወጥ ኃላፊነት እንዲኖራቸውም ሲደረግ ታይቷል ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ግን ያለምንም ህጋዊ መሰረት ነውወ አራተኛ ከሁሉም በላይ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት በሚል እየቀረበ ያለው ጥያቄ ቀስ በቀስ እንድንላማመደው እየተደረገ ያለና የከተማዋንም ሆነ የአገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ የጣለ ጥያቄ ነወ ህገ መንግስቱ አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌዴራሉ መንግስት መሆኑንና የፌዴራሉ ርዕሰ ከተማ መሆኗን በግልጽ መደንገጉ እንደተጠበቀ ሆኖ ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ልዩ ጥቅም እንዲኖረው በግልጽ መደንገጉ በራሱ አዲስ አበባ የኦሮሚያ አለመሆኗን በማያሻማ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ነው ምክንያቱም ኦሮሚያ የአዲስ አበባ ባለቤት ቢሆን ኖሮ ሙሉ ጥቅም እንጅ ልዩ ጥቅም እንዲኖረው አያስፈልግም ነበር በአጠቃላይ የኦሮሞ ብሔርተኞች አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ለሚለው አቋማቸው በመከራከሪያነት ሊያቀርቡ የሚሞክሩትም ተገቢ የሆነ ህጋዊ ድንጋጌን ሳይሆን አዲስ አበባ ጥንት የኦሮሞዎች መኖሪያ ነበረች የሚል ከባለቤትነት መብት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው አገሩ የተካለለው በታሪክ ሳይሆን በማንነትና በቋንቋ መስፈርት መሆኑን የረሳ ውሃ የማይቋጥር መከራከሪያ ነው የሚገርመው ይህ ሁሉ ህገወጥ ጥያቄ በአዲስ አበባ ላይ ሲቀርብ በስልጣን ላይም ሆነ በተቃዋሚነት ከሚገኙት የኦሮሞ ተዋቂ የፖለቲካ ሰዎች መካከል አንዳቸውም የህግና የመርህ ተገዥ በመሆን ለመቃዎም ሲሞክሩ ታይቶ አያውቅም ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ለምንድን ነውን ይህንን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ህጉመንግስቱን ባረቀቁና ባጸደቁ የፖለቲካ ኃይሎች በኩል የነበረውን ፍላጎት አሁን ላይ ካለው የኦሮሞ ብሔርተኞች ፍላጎትና ዓላማ ለይቶ ማዬት ጠቃሚ ይሆናል ዓ ም ላይ ወደ ስልጣን የመጡትና የህገ መንግስቱ አርቃቂዎችና አጽዳቂዎች የነበሩት የፖለቲካ ኃይሎች መሰረታዊ ፍላጎት አገሪቱን ከነሱ የፖለቲካ አደረጃጀት ጋር በሚያጣጥም ሁኔታ በቋንቋና በብሔር ማንነት መስፈርት ከፋፍሎ ማደራጁት ነበር ምክንያቱም በወቅቱ ህገመንግስቱን ያረቀቁት የፖለቲካ ኃይሎች ህገመንግስቱን ያወጡት የአንድ አገር አካል ሆነው አስከወዲያኛው ለመኖር በመወሰን ሳይሆን ሲቻልየበላይነትን አስጠብቆ አብሮ ለመኖር ሳይቻል ግን ተገንጥለው በመውጣት የራስን አገር የማቋቋም መንታ ፍላጎት ይዘው ስለነበር ነው በአጭሩ እነዚህ ኃይሎች ህገመንግስቱን ያረቀቁት አገሪቱን አንድነቷ ምልዑ ሆኖ እንደሚቀጥል ቋሚ አገራቸው በማዬት ሳይሆን እንደ ጊዜያዊ የኪራይ ቤት በመቁጠር ነበር በዚህም ምክንያት ከተፈጥሯዊ ማንነቷ ጋር በተያያዘ አንድ የብሔር ባለቤት ሊኖራት የማይችለውና ቅይጥማንነት ያላት አዲስ አበባ የክልልነት መብት እንዳይኖራት ተደርጓል በተጨማሪም በህገመንግስቱ አርቃቂዎች ዘንድ አዲስ አበባ በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ውድቀት የተገነባች የነፍጠኛና የትምክህተኞች ምሽግ ነች የሚል አቋም ስለ ነበራቸው መብቷን የመገደብ ፍላጎታቸው ከዚህ የተዛባ አስተሳሰባቸው የመነጨ ነበር ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የወቅቱ የኦሮሞ ብሔርተኛ ኃይሎች ግን አዲስ አበባን በሚመለከት እያራመዱት ያለው አቋም ከቀድሞዎቹ የህገመንግስት አርቃቂዎች ጋር የሚገናኝበት የራሱ አንጓ ቢኖረውም ሙሉ በሙሉ አንድ ዓይነት ነው ማለት ግን አይቻልም ። የወቅቱ የኦሮሞ ብሔርተኞች የአዲስ አበባ ከተማ ብቸኛ ባለቤት የመሆን ፍላጎት ጎልቶ እየመጣ ያለው እገረኦሮሚያን ለመመስረት ተቃርበናል ይህንን ዓላማ በብቃት ለማሳካትም አዲስ አበባን አስቀድሞ አለመቆጣጠር እንቅፋት ይሆንብናል እንቅፋት ከመሆንም በላይ የመጨረሻ ነፃ አገር የመመስረት ስኬታችንን ጎደሎ ያደርገዋል የሚል ስጋት ስለአደረባቸው ነው አዲስ አበባ ከሌላ ከማንኛውም ክልል ጋር ሳትዋሰን ሙሉ በሙሉ በኦሮሚያ ክልል ተከባ የምትገኝ ስለሆነች እሷ የኦሮሚያ ክልል አካል ባልሆነችበት ሁኔታ ኦሮሚያ የሚባል ወጥ የሆነ አገር መፍጠር አይቻልም አዲስ አበባ በኦሮሚያ አካልነት ካልተካተተች እንደ ሳንማሪኖ በበበዕ ወይም ሌሴቶርከ በአንድ አገር ወስጥ ተከባ የምትገኝ ሌላ ደሴት አገር ትሆናለች ማለት ነው ይህ እውነታ ነው የአምልኮ ያህል እናምንበታለን የሚሉትን ህገመንግስት በመቃረን ጭምር አዲስ አበባ የሁላችን ነች ሳይሆን በተለየ ሁኔታ የኦሮሞ ናት እንዲሉ ያስገደዳቸው የኦሮሞ ብሔርተኞች ከመቸውም ጊዜ በላይ በአሁኑ ወቀት ከፍተኛ የታጠቀ ኃይል አለን በፌዴራሉ መንግስትም የበላይነት ይዘናል ሊቀናቀነን የሚችለው የአቢሲኒያ ኃይልም እርስ በርሱ እየተዋጋ ተዳክሟል ብለው ስለአሰቡ አገረኦሮሚያን ለመመስረት ከመቸውም ጊዜ በላይ የተመቸው ጊዜ ዛሬ ነው የሚል እምነት ያሳደሩ ይመስላሉ በአጠቃላይ በህጉመንግስቱ የቀድሞ አርቃቂዎችና አጽዳቂዎች ዘንድ አዲስ አበባ የጥቃት ዒላማ የሆነችው እንደማንኛውም የአገሪቱ ከተሞች ከብሔር አደረጃጀት ጋር የማትጣጣምና የኢትዮጵያዊነት የፖለቲካ አመለካከት ምሽግ ተደርጋ የምትታይ በመሆኑ ነውወ በአሁኖቹ የኦሮሞ ብሔርተኞች ዘንድ የጥቃት ዒላማ የሆነችው ደግሞ ለሚመኙት የአዲስ አገር ምስረታ ፊታቸው ላይ ቆማ እንቅፋት ስለሆነችና የመጨረሻ የድል ሪቫናቸውን ሊቆርጡባት የወሰኑ የመጨረሻ ቋጠሮ በመሆኗ ነወ የኦሮሞ ብሔርተኞችና የመገንጠል ጥያቄ በአዲስ አበባ ዙሪያ የገጠመን ችግር መፍትሄው ቀላልም ከባድም ነወ ኢትዮጵያውያን በአንድ አገር ህዝብነትና በእኩልነት አብረን ለመቀጠል ከወሰን መፍትሄው በእርግጥም ቀላል ነው መነጣጠልን ግባችን አድርገን ከወሰድን ግን የአዲስ አበባ ጉዳይ ጭራሹንም መፍትሄ የለሽ ነው የብሔርተኝነት ፖለቲካ አንድ ጊዜ የሆነ የጥንካሬ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ግፃ አገር ከመመስረት ያነሰ ማንኛውም ዓይነት ውጤት ሊያረካው አይችልም ብሔርተኝነት እደርስበታለሁ የሚለው የመጨረሻ ወጤት ላይ ደርሶ እስከ መጨረሻው ከቅራኔ አዙሪት እንደማይዎጣ ካላዎቀ ወይም ራሱን በልቶ ካልጨረሰ በስተቀር ነጭናጫና አልቃሻ ከመሆን ሊላቀቅ አይችልም የወቅቱ የኦሮሞ ብሔርተኞች ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳዬንም ይህንኑ እውነታ ነው የኦሮሞ ብሔርተኞች በቅድሚያ ትልቅ ክልል መፍጠርና አንፃራዊ የሆነ ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል አገኙ ከዚያም ጥያቄያችን አልተመለሰም ብለው በመታገልም በፌዴራሉ መንግስት የመሪነት ድርሻ አገኙ ይህም ሁሉ ሆኖ ግን አሁንም ከሌላው ህዝብ በበለጠ እኛ ተበዳይ ነን ብለው ሲጮሁና ከዚያም አልፈው የመገንጠል ዓላማን ለማሳካት ሲጥሩ እያዬን ነወ በአዲስ አበባ ዙሪያ እየታዬ ያለው የወቅቱ ችግርም እኩል ወይም የበላይ ከመሆንም ባለፈ ትልቅ አገርን አፍርሶና የህዝብን ህልውና አደጋ ላይ ጥሎ የራስን ነፃ አገር የመመስረት ፕሮጀክት አካል ነወ ምክንያቱ ይህ ባይሆን ኖሮ አዲስ አበባ የእኛ ብቻ ነች ለማለት የሚያስደፍር ምንም ዓይነት አመክንዮ ሊኖር አይችልም የኦሮሞ ብሔርተኞች ግፃ አገር የመመስረት ጥያቄ ለእነሱ በርግጥም አንድ ግፃ አገር የመመስረት ፍላጎት ነው ጥያቄው የህዝብ ነው ወይንስ የጥቂቶችን። መደምደሚያ በአጠቃላይ ከአራቱም የአገሪቱ ማዕዘናት የመጣ ህዝብ ከገዐ በላይ ለሆኑ ዓመታት ጥሪቱን አፍስሶ በጋራ የገነባትን ከአምስት በላይ የሆኑ ተከታታይ ትውልዶች ተወልደው ያደጉባትን የሚሊዬኖች አገር የሆነች ከተማ የእኛ ብቻ ናት ብሎ መጠየቅ ከሞራል ከታሪክ ከህግም ሆነ ከፖለቲካ አኳያ ተቀባይነት የሌለው አጀንዳ ነወ እንኳንስ አዲስ አበባ ራሱ ኦሮሚያ ክልልም የሁሉም የክልሉ ኗሪዎች እንጂ የኦሮሞዎች ብቻ ክልል ሊሆን አይችልም በአለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ ጋሞዎች በማንነታቸው ተለይተው ሲገደሉ የትግራይ ተወላጆች በጅምላ ከስራ ሲባረሩና ሲታሰሩ አማራዎች ተለይተው ቤታቸው ሲፈርስና ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ሲታገዱ በአጠቃላይም ኦሮምኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ዜጎች ቤት ሰርተው የማይኖሩበት ሸገር የሚባል የከተማ ቀለበት እንዲመሰረትና የአዲስ አበባ ህዝብ በከበባ ውስጥ እንዲገባ ሲደረግ በገሃድ እያየን ነው ይህ ሁሉ የሚያሳየን በአዲስ አበባም ሆነ በአገር ደረጃ የኦሮሞ ብሄርተኞች እየፈጠሩት ያለው አደጋ አንድን ብሄር ለይቶ የሚጎዳ ሳይሆን የኦሮሞን ህዝብ ጨምሮ መላውን የአገሪቱን ህዝብ የሚጎዳ መሆኑን ነው አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ትስስርና አብሮነት ዋና ቋጠሮ ነች ይህ የህልውና የመጨረሻ ቋጠሮ ተፈቶ አገሩ እንዲበተንና በዚያም ምክንያት አገርና ዜግነት የለሽ መሆንን ማንም ህሊና ያለውዜጋና ህዝብ በፀጋ ሊቀበለው አይችልም አይገባምም ከስድስት ሚሊዬን በላይ የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ በአግባቡ ከነቃና ከተደራጀ ዛሬ ላይ ጥቅሙንና ህልውናውን ሊያስከብር እንደሚችል ጥርጥር የለውም የአዲስ አበባ ህዝብ ራሱን ችሎ ከፖዐ በላይ ከሚሆኑት የአለም አገራት የተናጠል ቁጥር የበለጠ የህዝብ ብዛት ያለው በመሆኑ በአግባቡ ከነቃና ከተደራጀ ራሱን በብቃት መከላከል የሚችል ህዝብ ነው ይህ አቅምና ብቃት ግን በጊዜ ሂደት ሊቀየር እንደሚችል መገንዘብ ይገባል ትግሉ ዓላማዬን በዲሞግራፊ ለውጥ ጭምር ማሳካት አለብኝ ብሎ ከሚያምን አጅግ አደገኛና ፅንፈኛ የሆነ ብሄርተኛ ኃይል ጋር ስለሆነ በእንዲህ ዓይነቱ ትግል ጊዜን ቀድሞ መገኘት እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ መሆኑን በአግባቡ መገንዘብ ያስፈልጋል ይህ ትውልድ በታሪኩ ከዚህ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ በጋራ ተባብሮ ሊቆምለትና በጋራም ሊሞትለት የሚገባው ሌላ አጀንዳ ሊኖረው አይችልም መንግስትና የህግ የበላይነት በአገራችን ቢኖር ኖሮ ሌላውን ሁሉ ትተነው የአዲስ አበባን ህዝብ የውሃ አቅርቦት እናቋርጣለን ብሎ መዛት በአንድ ህዝብ ላይ የዘርማጥፋት ለመፈጸም እንደቀረበ ዛቻና የጦርነት አዋጅ ተደርጎ ሊታይ የሚገባው ወንጀል ነው ስለሆነም ጉዳዩ የመላው አገሪቱ ህዝብ የህልውና አደጋ መሆኑን በመገንዘብ ብጊዜ የለንም ፍጥነት ሁላችንም በጋራ ቁመን በአስቸኳይ ልንታገለው የሚገባ ነወ ይሁንና እንዲህ ዓይነቱ ትግል የወረቀት መግለጫ በመስጠት ቁጭ ብሎ በማማረርና የጥቂቶችን ትግል ዳር ቆሞ በመታዘብ ለውጤት ሊበቃ አይችልም ተከታታይነት ያለው የተቀናጀና የተደራጀ ሠላማዊ የህዝብ ትግል ማካሄድን ይጠይቃል ስለሆነም በስራ ላይ ባሉትም ሆነ አዲስ በሚፈጠሩ ፓርቲዎች ዙሪያ መደራጀትና ከፖ ዓ ም በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች የፖለቲካ ማዕከልነቷን ያጣችው አዲስ አበባ እንደገና ወደ ቀደመ ቦታዋ እንድትመለስ ማድረግ ያስፈልጋል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Comments:


memezon

Download options | Convert to Pdf | Book of the day

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact